Лента постов канала ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy (@Zephilosophy) https://t.me/Zephilosophy ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ልማዳዊ እምነቶችን በመሞገት እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል። በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ። ru https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Thu, 14 Aug 2025 22:00:03 +0300
ስለ ፍትህ

1."ህግ ታናናሽ ሰዎችን ሲገዛ ፣ ስነ-ምግባር ደግሞ ታላላቅ ሰዎችን ይገዛል።"
አቡነ ሺኖዳ

2."ግማሽ እውነት ሙሉ በሙሉ ሀሰት ነው።"
እስራኤሌያውን

3."የብልህ ሰው ህግ የህይወት ምንጭ ናት። ማስተዋል የሌለው ግን በኀጢአት ይሞታል ።"
ምሳሌ 13:14

4."ብዙዎቹ ሀይማኖቶች ያስቀመጧቸው መመሪያዎችና ደንቦች ገነት ለመግባት ጉቦ የመክፈል ያህል ነው።"
ጲላጦስ

5."የሁሉም መብቱ በፍርድ ቀን ይመለስለታል ፣ ቀንድ የሌለው በግ እንኳን ከወጋው ቀንዳም ወጠጤ ላይ ካሳውን ይቀበላል።"
ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

6."ወንድሜ ሆይ ሳይፈረድብህ በራስህ ላይ ፍረድ"
መርቆርዮስ

7."መልካም መስራትን ተማሩ ፣ፍርድን ፈልጉ ፣ የተገፋውን አድኑ ፣ ለተበዳዩ ፍረዱለት ፣ ለመበለቲቱ ተሟገቱ "
ኢሳ ፤ 1፣17

8."ትክክለኛ ፍትህ የሌለበት የመንግስት አስተዳደር ፣ የራስ ወዳድ ግለሰቦችና የአድርባዮች መሰብሰቢያ ካንምኘ ይሆናሉ።"
በላይ ደስታ

9."በጎረቤት ላይ ፍትህ ሲጓደል እያየህ ዝም ካልክ ፣ ቀጣዩ ተረኛ አንተ መሆንህን አትዘንጋ።"

ሞገስ በላቸው

10."በስንፍና ከሚፈርዱ ፈራጆች ጩኸት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።"
መክ፤ 9:17

@zephilosophy
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Wed, 13 Aug 2025 18:43:00 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Wed, 13 Aug 2025 18:42:12 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Wed, 13 Aug 2025 18:41:30 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Wed, 13 Aug 2025 18:40:19 +0300
📚Thus Spoke Zarathustra
Friedrich Nietzsche (Author),
Adrian Del Caro (Translator)

ዘስ ስፔክ ዛራቱስትራ የተሰኘው በጥልቅ የኤግዚስተንሺያል ፍልስፍና ይዘቱ በዓለም በመጀመሪያዎቹ ተርታ የሚጠቀስ ድንቅ መፅሐፍ ነው። እንደሚታወቀው ይህ መፅሀፍ በዝነኛው ደራሲና ፈላስፋ - በፍሬደሪክ ዊልሄልም ኒቼ በጎርጎሮሳውያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1880ዎቹ መጀመሪያ የተፃፈና የታተመ ነው።

ከተፃፋበት ጀርመንኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው ኮፒ - "ዘስ ስፖክ ዛራቱስትራ" - በዓለም በስፋት ከተሠራጩ የፍልስፍና ነክ መፅሐፎች ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Mon, 11 Aug 2025 20:50:32 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Thu, 07 Aug 2025 18:26:42 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Wed, 06 Aug 2025 19:39:23 +0300
አቶ ወሬ

ወሬኞችና ወሬያቸው ሰልችተውኛል፤ ነፍሴ ተፀይፋቸዋለች፡፡ …የማየው ነገር ሁሉ በግብዝነት የተሞላ ትርጉም አልባ የወሬ ቋት ነው፡፡

ከአንድ ጓደኛዮ ጋር ቁጭ ብል አቶ ወሬ ሳይጋበዙ ይቀላቀላሉ፡፡ በዘዴ ላታልላቸው ብሞክር እንደምንም ይቀርቡኝና በድምፃቸው ማሚቱ ዕረፍት ይነሱኛል፣ እንደ በሰበሰ ስጋ ጨጓራየን ያውኩታል፡፡ …ወፍራም ከናፍራቸውን እየከፈቱ ሲለፈልፉ አገኛቸዋለሁ፡፡ አጃቢዎቻቸውም ለእሳቸው ያጨበጭቡላቸዋል፣ በእኔ ይሳለቁብኛል፡፡

በባዶ ወሬ ውስጥ ግርግር የማይኖርበት ስፍራ ይኖር ይሆን?

በዚህ ምድር ራሱ ቢያወራ የማይወድ ሰው ይኖር ይሆን?

ከዚህ ሁሉ ሕዝብ መሃል አፉ ለወስላታው አቶ ወሬ መሸሸጊያ ያልሆነ ይገኝ ይሆን?

አንድ አይነት ወሬኞች ብቻ የሚገኙ ከሆነ እኔ እረታለሁ፡፡ ነገር ግን ወሬኞች በቁጥር የሚያዳግቱ ናቸው፡፡ በጎሳና በቡድን ሊከፈሉም ይችላሉ፡፡ … አንዳንድ ጊዜ ራቁታቸውን ከነፈሰው ጋር የሚነፍሱ ወሬኞች የተሰበሰቡበት ቡድን እናገኛለን፡፡ ብዙውን ጊዜ አንድ የተለየ መዋቅር ያለው ቡድን እናገኛለን፡፡ የዚህ ቡድን ወኪሎች ልክ እንደ ወፎች ቢሆኑም በቃላቶቻቸው ሞገድ ውስጥ ሲፈስሱ ግን ራሳቸውን እንደ ንስሮች ይቆጥራሉ፡፡

ሌሎችም ወሬኞች አሉ፤ በደወል ድምፅ የሚመሰሉ፡፡ ሰዎችን ወደ አምልኮ ሥፍራ የሚጠሩ ቢሆንም ራሳቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ዝር ብለው አያውቁም፡፡

…ከእነዚህ ሁሉ ግን በእኔ አስተሳሰብ አስገራሚዎች የሚመስሉኝ በሚያንኮራፋ ድምፃቸው ዓለምን የሚያውኩና ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሳቸውን እያነቁ "እንደ እኛ ሊቅ የት ይገኛል!” የሚሉ እንቅልፋሞች ናቸው፡፡

ለአቶ ወሬና ለጓደኞቻቸው ጥላቻዮን ከገለፅኩ በኋላ ራሴን ልክ ራሱን ማዳን እንደማይችል ሐኪም ወይም ለእስር ቤት ጓደኞቹ እንደሚጸልይ እስረኛ ሆኘ አገኘዋለሁ፡፡ አቶ ወሬንና ወሬኛ ጓደኞቻቸውን በራሴ የወሬ መንገድ በምፀት ተችቻቸዋለሁ፡፡ ከወሬኞች የተነጠልኩ ብሆንም እኔ ራሴ ወሬኛ ነኝ፡፡ እግዚአብሔር እኔን ባርኮ ወሬኞች በማይኖሩበት የዕውቀት፣ የእውነትና የፍቅር ዓለም ከማስቀመጡ በፊት ሃጢአቴን ይቅር ይለኝ ይሆን?

ካህሊል ጅብራን
📖የጠቢባን መንገድ
@Zephilosophy
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Wed, 30 Jul 2025 20:00:18 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Tue, 29 Jul 2025 20:54:33 +0300
አንድ ሰው ማሃቪራን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡-

እውነተኛ ቅዱስ ማን ነው?
እና ማን ነው ጥፋተኛ?

ምናልባት ጠያቂው በሃይማኖታዊ ጽሑፎች ውስጥ የሚሰጠውን ዝግጁ የሆነ መልስ ፈልጎ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን እንደ ማሃቪራ ያሉ ሰዎች ከራሳቸው ነባራዊ ግንዛቤ ነው የሚናገሩት። የተናገረው ነገር በጣም ያምራል። የሰጠው ፍቺ ልዩ ነው። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ምንም ተመሳሳይነት የለውም።

ማሃቪራ እንዲህ ብሏል፦
የነቃ ቅዱስ ነው።
የሚተኛው ኃጢአተኛ ነው።

ቀላል ፣ ግን በጣም አስፈላጊ…
"ንቃት" ያለው ብቸኛው ቅድስና ነው።እና ፤ንቃተ-ህሊና ማጣት ብቸኛው ኃጢአት ነው. ሌሎች ኃጢአቶች የሚመነጩት ከዚህ ካለማወቅ ነው። ሥሩን ይቁረጡ፤ ሥሩን ራሱ ይምቱ! ቅጠሉን አይቁረጡ።

ኦሾ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Fri, 25 Jul 2025 21:29:02 +0300
ዕውቀትና አዋቂ

ያ ሁሉ የዕውቀት ፍሬ- የልጅነት ዓለም
                                 ዝቆ የሰፈረው
ያ ሁሉ የዕውቀት ፍሬ -የልጅነት ጉጉት
                         አጣፍጦ የፈጠረው፡፡

ይኑር ምንም አይደል!
ምኞቶች ያፋፋል፣
በብርሃን ጽንፉ ጨለማን ይገፋል፣
ግን ልንገርህ አይደል?
እንደኔ የሆንክ ለት - ላይበቅል ይደፋል፤
                             ላይበላ ይረግፋል።

አዎ! እንደ እኔ የሆንክ ለት፣
ሁሉን ወደማወቅ የተቃረብክ ለት፤
ይሸረክትሃል፣
ይቆራርጥሃል -የእኩዮችህ ስለት፡፡

እውነቴን ነው የምልህ!
የዚህች ዓለም ቅኔ ግራ ነው ፣ ግራ ነው
                      'ሲፈቱት ይጠብቃል'፤
እያንዳንዱ እውነት በውሸት ይጠበቃል።

📖የመንፈስ ከፍታ
ገጣሚ -ሀፊዝ
@zephilosophy
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Fri, 25 Jul 2025 21:08:35 +0300
ትዕዛዝ እንዳንጥስ

ብዙ ተባዙ፣
ምድርንም ሙሏት
ከሆነ ትዕዛዙ፣
ምድሪቱ ሞልታለች፣
ከገደብ እንዳናልፍ፣
ትዕዛዝ እንዳንጥስ፣
ጎበዝ ፍሬን ያዙ፡፡

📖መደድ
ገጣሚ-ኑረዲን ዒሳ
@zephilosophy
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Tue, 22 Jul 2025 20:54:54 +0300
Подробнее
11.14 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001163708603 Sun, 20 Jul 2025 18:19:08 +0300
የህላዌ ትርጉም ምንድን ነው?

ዓለምና የሰው ልጅ በኁልቈ  መሳፍርት ሕዋ ውስጥ እንደ ጤዛ ነቊጥ ናቸው። ኢምንትነታቸው ያስደነግጣል። ሰዎች ሕይወት በሚሉት ነገር እስከ ሞት ድረስ ታመዋል። መተንፈስ፣ መናገር፣ መራመድ ስቃይ ኾኖባቸዋል። የፀሓይን መውጣት ለማየት አይሻሙም። ጀምበርን ተጋፍተው አይሸኙም። ጉጉታቸው ነጥፏል። ሕዋሳቸው አንቀላፍቷል። አእምሯቸው ዝሏል። አብሮነትን ፈርተዋል። በብቸኝነትም ተጎድተዋል። በተቃርኖ ፍላጎት ተወጥረዋል። ከሌላ ሰው ጋር በተቀራረቡ ቊጥር ከራሳቸው ይርቃሉ። ይበረዛሉ፣ ይከለሳሉ። ከአንድ ራሳቸው ጋር በተዛመዱበት መጠን ከቀሪው ዓለም ይርቃሉ። ይነጠላሉ፣ ይገለላሉ። እዚህ ከተማ ውስጥ ጸጉሩን ያላጎፈረ፣ ባለአንካሴ ብረት መስቀል ያልያዘ፣ ጢሙን ያላንዠረገገ፣ ዳባ ያልለበሰ ስንት ቆብ አልባ ባህታዊ ይኖራል?

ይህ ዓለም ፈጣሪና መጋቢ አለውን? ወይስ የሰው ልጅ የመለኮት እጅ ሥራ ሳይሆን ከአጽናፈ ዓለሙ ጋር ወደ መኾን የመጣ የዐቢይ ፍንዳታ ክስተት ውጤት ነው? በኹለት እግሮቹ ቆሞ ከመራመድ ተነሥቶ ታላላቅ ሥልጣኔዎችን እስከ መፍጠር የደረሰው በዝግመተ ለውጥ ክንዋኔ በኩል አልፎ ነው? አምላክ የሰውን ልጅ ፈጠረ ወይስ የሰው ልጅ አምላክን? በጋርዮሽ ሥርዐት የነበሩ ጥንታውያን የሰው ልጆች ሳይቀሩ ለፍቅር ለወላድነት፣ ለፀሓይ፣ ለዝናብ፣ ለጦር ድል መንሣት የሚወዱዋቸው ሕብረ አማልክትና ጣዖታት ለምን አስፈለጓቸው በኑባሬያቸው የተጋፈጡትን መከራና ስቃይ፣ በመስተልይ (mind) አልታረቅ ያላቸውን የሕይወት እንቆቅልሽ በአማልክት ለማንበር?

“ዓለም ኹሉ እርሱ ራሱ በፈጠረው ያምናል፣ ይገዛልም
ብዙዎች በፊቱ እየተገዙ ይሰግዱለት ዘንድ፣
ይኽንን ነገር ለመመልከት እሥራኤላውያን እንዲፈሩ
ሙሴ ፈጣሪውን ፈጠረ፣
ፈጣሪም እርሱን ፈጠረ”

ያ ፈጣሪ ዓለማት “ሰማያት ሳይዘረጉ፤ የየብሱ ፊት ሳይታይ ተራሮች ሳይቆሙ፤ የአየር ርዝመት ሳይከፈት፤ ቀላያት ጥልቅ ሳይሆኑ፤ የወንዙም ጎርፎች ሳይፈሱ፤ ነፋሳት ሳይነፍሱ፤ መባርቅት ሳይመዘዙ፤ ሳይመላለስ፤ ብልጭልጭታውም ነጎድጓድም ሳይሰማ፤ የደመናትም ግዘፍ ሳይሳብ፤ ብርሃናት ሳያበሩ፤ ጨለማ ሳይጋረድ፤ የመዓልትም ብርሃን ሳይበራ፤ ሌሊትም ሳይፈጠር” አስቀድሞም በባሕርይው ይኖር ሳለ ምን ያደርግ ነበር? አነዋወሩን የሚያውቅ ማን ነው? “ኢየሱስ ክርስቶስ ኑ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን ውረሱ ይላል። ዓለም ሳይፈጠር ምን ኖሮታል? ጥበቡ አይታወቅ።”

ይህ ዓለም ለሰው ልጅ ምንድር ነው? ሰውስ ለዚህ ዓለም? እውን የሰው ልጅ ይኮነንበት ዘንድ ነጻ ፍቃድ አለውን? በልቡ የጸጸት አለንጋ እንዲገረፍ፣ በሲዖል እሳት እንዲቃጠል ምርጫው በእጁ ነውን? ሕያውነትን ፈቅዶ፣ ቤተሰቦቹን እገሌና እገሊት ይኹኑ ብሎ፣ የቆዳ ቀለሙን፣ ዕትብቱ ተቆርጦ የሚወድቅበትን መልክአ ምድር፣ የሚቀላቀለውን ማኅበረሰብ ማንነት፣ ባሕል፣ እምነቱን፣ ሃይማኖቱን መርጦ የተፀነሰ እና የተወለደስ ማነው? የድርጊቶቹስ ምንጭ ከንቁ የአእምሮው ክፍል ብቻ የኾኑለት ማነውን? ምናልባት ሰው በረዥም ሰንሰለት እንደ ታሰረ ውሻ ቢኾንስ? ነጻነቱ በታሰረበት ሰንሰለት ርዝማኔ ቢወሰንስ? አለመምረጥ ይችላል? ሕይወት ያን ሳይጥሉ፣ ይሄን ደግሞ ሳያንጠለጥሉ ይቀጥላልን?

እኮ በሕይወት ፈተና ክንዱ የማይደክምበት፤ ነፍሱስ የማይዝልበት ማን ነው? ሞት ባይኖር የህላዌ ወለፈንድነት ይቀራል? የእድሜ ሐረግ እንደ ማቱሳላ ቢንዠረገግ፣ የሰው ልጅ ኢመዋቲነትን ቢጎናጸፍ፣ እስከ ዘላለም በፍስሓ ቢጥለቀለቅ ሕይወት ከመራራ ኩሸትነቱ ዝንፍ ይላልን? ያማከረ ባይኖርም ከዚህ ኹሉ ስቃይ አስቀድሞ አለመፈጠር ነበር። ከተወለዱ ወዲያ ግን ወደ ኋላ አይባል ነገር! የቸገረ ነገር። ደግሞስ የአለመኖርን ጣዕም የሚያውቅ ማነው? እኮ ምን ምን ይላል? ለእነዚህ ኹሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘትስ ትርጕም ይሰጣል??

መፅሀፍ-ፀሀይ ከጨላማዬ ምን አለሽ
ደራሲ-እሱባለው አበራ ንጉሴ

@zephilosophy
Подробнее
10.29 k
]]>