Лента постов канала ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit (@ortodoxmezmur) https://t.me/ortodoxmezmur የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR ru https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 17 Aug 2025 12:18:03 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 17 Aug 2025 08:55:09 +0300
Подробнее
11.74 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 16 Aug 2025 12:44:19 +0300
#ቡሄ_በሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
15.47 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 16 Aug 2025 12:44:19 +0300
#ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (2) ልጆች ሁሉ የኛማ ጌታ
የዓለም ፈጣሪ የሰላም አምላክ
ትሁት መሀሪ በደብረ ታቦር የተገለጠው
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየው
ልብሱ እንደብርሃን ያንፀባረቀው

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(2)

ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ
አባቱም አለ ልጄን ስሙት
ቃሌ ነውና የወለድኩት

ታቦር አርሞንኤም ብርሃን ታየባቸው
ከቅዱስ ተራራ ስምህ ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሀነ መለኮት ባንቺ ላይ አበራ

በተዋህዶ ወልድ የከበረው
የእግዚአብሔር አብ ልጅ
ወልደማርያም ነው
ቡሄ በሉ/2/ የአዳም ልጆች
ብርሃንን ተቀበሉ

አባቴ ቤት አለኝ ለከት
እናቴ ቤት አለኝ ለከት
አጎቴም ቤት አለኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት

የዓመት ልምዳችን ከጥንት የመጣው
ከተከመረው ከመሶቡ ይውጣ
ከደብረ ታቦር ጌታ ሰለመጣ
የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ

ኢትዮጵያውያን ታሪክ ያላችሁ
ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ
ችቦውን አብሩት እንዳባቶቻችሁ
ምስጢር ስላለው ደስ ይበላችሁ

አባቶቻችን ያወረሱን
የቡሄን ትርጉም ያሳወቁን
እንድንጠብቀው ለእኛ የሰጡን
ይህን ነውና ያስረከቡን

ለድንግል ማርያም አሥራት የሆንሽ
ቅዱሳን ጻድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ
ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ነሽ

ለሐዋርያት የላከ መንፈስ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ጸጋውን ያፍስስ
በበጎ ምግባር እንድንታነጽ
በቅን ልቦና በጥሩ መንፈስ
በረከተ ቡሄ ለሁላችን ይድረስ

ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና

በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና


እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ
ላመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሳችሁ
ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ
እንዲሁ እንዳለን በፍቅር አይለየን
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሰን
አማኑኤል በቀኙ በፍቅር ያቁመን
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርገን


የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(2) ይግባ በረከት(2)

እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (3)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 16 Aug 2025 06:57:15 +0300
ነሐሴ ፲ /10/


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥር በዚች ቀን በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ ዲሜጥሮስ ዘመንና በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመነ መንግሥት ቅዱስ መጥራ በሰማዕትነት ሞተ።

ይህም ቅዱስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖት መስገድን የሚያዝ የንጉሡን ደብዳቤ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ ወዲያውኑ ሒዶ ከወርቅ የተሠራ የአጵሎንን ክንድ ሰረቀ በየጥቂቱም ሰባብሮና ቆራርጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው።

የጣዖቱም አገልጋዮች ክንዱ ተቆርጦ አጵሎንን በአገኙት ጊዜ ስለርሱ ብዙዎችን ሰዎች ያዟቸው ። በዚያንም ጊዜ ወደ መኰንኑ ቀርቦ ክርስቲያን እንደሆነ በፊቱ ታመነ ሁለተኛም የአጵሎንን የወርቅ ክንድ የወሰድኩ እኔ ነኝ ለድኆችና ለችግረኞችም ሰጠኃኋቸው አለው።

መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ አስጨናቂ የሆነ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤና አወጣው። ከዚህም በኋላ እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ ብዙ ደም ከአፍንጫው ወደ ምድር እስከ ሚወርድ ዘቅዝቀው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት።

በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ቅዱስ መጥራንን ፈታው ከተሰቀለበትም አውርዶ በመዳሠሥ አዳነው ። አንድ ዕውር ሰውም መጣ ከአፍንጫው ከወረደውም ደም ወስዶ ዐይኖቹን ቀባ ወዲያውኑ አየ። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጀ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
15.12 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 15 Aug 2025 15:53:35 +0300
Подробнее
16.54 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 15 Aug 2025 06:59:30 +0300
Подробнее
18.72 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 15 Aug 2025 06:40:02 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 14 Aug 2025 09:12:49 +0300
​ነሐሴ 8/12/2017 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ ሮሜ 9÷24-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦1 ጴጥ 4፥12-ፍ.ም
ንፍቅ ካህን፦ ግ ሐዋ፦ 16÷35-ፍ.ም

ምስባክ ፦ መዝ 57፥8-10

ወድቀት እሳት ወአርኢክዋ ለፀሐይ
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውህጠክሙ

ትርጉም
እሳት ወደቀች ፀሐይንም አላዩአትም
እሾኳችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችዋል

ወንጌል ፦ ማቴ 7÷12-26
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
18.85 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 14 Aug 2025 06:59:50 +0300
ነሐሴ ፰ /8/


በዚች ቀን አልዓዛርና ሚስቱ ሰሎሜ አንኤም አንጦኒኃስ ዖዝያ አልዓዛር አስዮና ስሙና መርካሎስ የሚባሉ ልጆቻቸውም ሰባቱ በሰማዕትነት አረፉ።

ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት።

የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው።

ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት ። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኮል እንዲገባ አደረጉት።

በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው ። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የእሊህ ቅዱሳንም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑርለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
18.56 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 14 Aug 2025 05:52:14 +0300
ፅላት ዘሙሴ

ፅላት ዘሙሴ እፀጳጦስ ሰሲና/2/
ፅናፅል/5/ ለአሮን ካህን
አዝ     

አልፌአለውና እመቤቴ ያን ሁሉ መከራ
ከኔጋር ስለሆንሽ እመቤቴ ስምሽን ስጠራ/2/
በዚያ በጭንቅ ቀን ድንግል
እጅግ በሚያስፈራው ድንግል
ማን ያድነኝ ነበር ድንግል
ስምሽን ባልጠራው ድንግል
በሞትና በህይወት ድንግል
መካከል ብሆንም ድንግል
ተዐምርሽ አነሳኝ ድንግል
ማርያም አልተውሽኝም ድንግል  አልተውሽኝም
አዝ

እጅግ የከበደ ነበር ያገኘኝ ፈተና
ታሪክ ሆኖ ቀረ እመቤቴ ባንቺ ዳንኩኝና /2/
ዙሪያው የሚያስፈራ ድንግል
ፅኑ ነው ገደሉ ድንግል
በዚያ የወደቁ ድንግል
እንዴት ይተርፋሉ ድንግል
ስምሽ ድጋፍ ሆኖ ድንግል
ከስር ተነጠፈ ድንግል
በሚያስደንቅ ምስጢር ድንግል
ህይወቴ ተረፈ /2/

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
17.11 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 13 Aug 2025 12:01:48 +0300
Подробнее
19.26 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 13 Aug 2025 09:45:22 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 13 Aug 2025 09:29:54 +0300
Подробнее
20.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 13 Aug 2025 08:04:19 +0300
Подробнее
19.17 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 13 Aug 2025 06:58:00 +0300
Подробнее
16.24 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 13 Aug 2025 06:00:32 +0300
Подробнее
16.22 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 12 Aug 2025 22:02:36 +0300
​​ነሃሴ_7
ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት

ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ። በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ።

የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር። የዋሃን (ገና ምሥጢርን ያልተረዱ) ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ። ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን። ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት።

አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው። "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው። ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ።

ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ። "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው። እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ።

ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ። ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና። በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው። (ማቴ. 16:16)

ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት (መሠረት) ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ። ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ (ሥልጣን)" ተሰጠው።

ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ። ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ ማርያም: አካላዊ ቃል: ሥግው ቃል: ገባሬ ኩሉ: የሁሉ ፈጣሪ" ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
20.18 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 12 Aug 2025 18:40:09 +0300
👉 የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
19.56 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 12 Aug 2025 13:14:28 +0300
የሲሎንዲስ ጥበብ

የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለው
የናሆም መድኃኒት እወድሻለው
ማርያም አከብርሻለው
ማርያም እወድሻለው
አዝ

ተጨንቄአለሁ ልንገርሽ
ምስጢረኛዬ እናቴ ነሽ
ሰው ያልሰማውን ብርቱ ምስጢር
ድንግል ሆይ ላንቺ ላማክር
የቁስለኛው መድኃኒቱ
የአዳም ዘር ሁሉ ነሽ ህይወቱ
መፍትሄ አለ በእጅሽ
ተንበርክኬ ልማጸንሽ
አዝ

ሳልናገረው ይገባሻል
የውስጤ ሁሉ ይታይሻል
ድረሽ እናቴ ተራጅኝ
ያላንቺ ለኔ ማን አለኝ
ደስታዬ ደሰታ የሚሆነው
በሀዘኔ የምጽናናው
አንቺ ከእኔ ጋር ስለሆንሽ
ተጽናንቻለው በስምሽ
አዝ

ወንድሞቼ እንኳን ቢሸጡኝ
ሰው ሁሉ ጠላት ቢሆነኝ
በእመ አምላክ ኃይል ከብሬአለሁ
በጠላቴ ላይ ሰልጥኛለሁ
የረሰኙ ሁሉ ያስቡኛል
የተጣሉኝም ያከብሩኛል
አንቺ አንግሰሽኝ አልወድቅም
እቆማለሁኝ ዘለዓለም
አዝ

መንገዴ እረዝሞ ደክሜብሽ
መከራው በዝቶ ታምሜብሽ
ወድቄ ሳዝን ድረሽልኝ
ለባሪያሽ ሃይሉን እንድትሰጭኝ
ፍቅርሽ በውስጤ ተንሰራፋ
በእናትነትሽ ልቤ ሰፋ
የሚለያየን ማንም የለም
ማርያም ልበልሽ ለዘለዓለም

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
21.61 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 12 Aug 2025 09:10:35 +0300
​ነሐሴ 6/12/2017 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 1ኛ ቆሮ 3÷10-22
ንፍቅ ዲያቆን፦1 ጴጥ 3፥1-7
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 13÷16-19

ምስባክ ፦ መዝ 44፥12-14

ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነምድር
ኩሉ ክብረ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን

ትርጉም
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻ ይዘው ይሰግዱለታል
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ
ለሐሴቦን ንጉስ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው

ወንጌል ፦ ማር 16÷9-19
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
19.71 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 12 Aug 2025 06:59:15 +0300
ነሐሴ ፮ /6/


በዚችም ቀን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች መግደላዊት ማርያም አረፈች። ከዘህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ አገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ አለች እስከ ቀበሩትም ድረስ አልተለየችም።

በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች ። መልአኩም እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል አላቸው።

ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው አላት ። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው።

ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋርተቀበለችው።

ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው ። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት።

ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም በፍቅር አረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
19.99 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 12 Aug 2025 06:00:54 +0300
ማርያም አርጋለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት/2/
የሰማይ መላእክት እያረጋጒዋት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች
አዝ

የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አዝ

ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አዝ

የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አዝ

ሐዋርያት አበው እንኩዋን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሐኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
18.61 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 11 Aug 2025 14:22:48 +0300
Подробнее
20.46 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 11 Aug 2025 13:08:02 +0300
Подробнее
21.31 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 11 Aug 2025 10:53:20 +0300
Подробнее
19.62 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 11 Aug 2025 07:00:39 +0300
Подробнее
20.66 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 11 Aug 2025 06:00:57 +0300
Подробнее
20.34 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 10 Aug 2025 18:05:02 +0300
ምስጉን ነው 

ምስጉን ነው የተመሰገነ
ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
ይመስገን ይመስገንልኝ
ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ
አዝ

እጅህ ሰፊ እንደሆነ አውቃለሁ ጌታዬ
የጎደለው ሞልቷል ይድረስ ምስጋናዬ
ያጣሁትን ከአንተ አግኝቻለሁ
ሁሉን ነገር ለበጎ ብያለሁ/2/
አዝ

ማቄን የቀደደው ደስታ አስታጠቀኝ
ባዶ የነበርኩት ሁሉ ተሰጠኝ
ሰጭም ነሽም እግዚአብሔር ብቻ ነው
የሰው ድርሻ በር ማንኳኳት ነው/2/
አዝ

እገፋለሁ እንጂ እኔ አልጨነቅም
መሰረቴ አንተ ነህ ከቶ አልናወጥም
ስትሰጠኝ የሚታየውን
እንዳትነሳኝ የዘለዓለሙን/2
አዝ

ቢሰጥ አያልቅበት ለጋስ ክቡር ጌታ
ሁሉን ከወነልኝ በልዩ ችሮታ
ድሆች ስንሆን ሁሉ አለንና
አምላካችን ይድረሰው ምስጋና/2/

ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
23.23 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 10 Aug 2025 12:47:51 +0300
ታትመሻል

ታትመሻል በሰው ልቦና
የደካሞች ምርኩዝ ነሽ እና
ላመስግንሽ በአዲስ ዝማሬ
እመቤቴ ገናነው ፍቅሬ
አዝ

የተጽናናንብሽ የድሆች ማረፊያ
ንፋስ ውቂያኖሱን ወጀቡን መቅዘፊያ
ወርሰናል ስምሽን ከወርቁ መዝገብ ላይ
ወለድሽልን ድንግል የሕይወትን ፀሐይ
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን
(2)
አዝ

ቀስተ ደመናዬ ሆነሽ ምልክቴ
አለሁ እስከ ዛሬ በአንቺው በእመቤቴ
ልጅሽን አምኜ ምን ይጎድልብኛል
ያስጨነቀኝ ሁሉ ይታዘዝልኛል
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን
(2)
አዝ

ተከቧል ተራራው በብሩህ ደመና
የአብ ልጅ ክርስቶስ በአንቺ ወርዷል እና
ይባቤ ምስጋና አፋችን ይሞላ
መቅደስ አላየንም ድንግል ከአንቺ ሌላ
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን
(2)
አዝ

የከሳሼን ጉልበት ፅናቱን ሰብረሻል
የአዳም ልጅ ከሲኦል ከሞት ወቶብሻል
ጣፈጣት ለነፍሴ የማህፀንሽ ፍሬ
ስጠራሽ እኖራለሁ በያሬድ ዝማሬ
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን
(2)

ዘማሪ ዕዝራ ኃ/ሚካኤል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
22.26 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 10 Aug 2025 09:57:09 +0300
ነሐሴ ፬ /4/


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ አራት በዚችም ቀን እንደ በግ የጸጒር ልብስ ለብሶ በበረሃ የሚኖር አባ ማቴዎስ አረፈ። እርሱም መርምኀናምን ያሳመነው ሣራንም ከለምፅዋ ያነፃት ነው። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
23.36 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 10 Aug 2025 08:23:04 +0300
👉 የእሁድ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
23.75 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 09 Aug 2025 21:27:59 +0300
Подробнее
25.18 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 09 Aug 2025 13:26:50 +0300
Подробнее
27.31 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 09 Aug 2025 06:58:21 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 09 Aug 2025 06:00:46 +0300
Подробнее
22.62 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 08 Aug 2025 12:59:05 +0300
ሞትማ ለመዋቲ ይገባል

ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል/2/
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል/2/
አዝ

ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ/2/
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ/2/
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት/2/
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያ መልአከ ሞት/2/
አዝ

ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ/2/
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ/2/
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ/2/
አዝ

ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት/2/
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት/2/
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው/2/
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው/2/
                   
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
25.35 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 08 Aug 2025 11:47:07 +0300
👉 የአርብ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
24.05 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 08 Aug 2025 06:57:35 +0300
ነሐሴ ፪ /2/


በዚች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር ቅድስት አትናስያ አረፈች። የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ባለጸጎች ነበሩ እነርሱም በሞቱ ጊዜ እንግዶችን እና የገዳም አባቶችን ሁሉ ትቀበላቸው ነበር።

ከዚህም በኋላ ክፉ ሰዎች ወደ ኃጢአት መለሷትና ኃጢአት መስራት ጀመረች። ስለዚህም ነገር የገዳም አባቶች ሰምተው ዮሐንስ ሐጺርን በንስሐ እንዲመልሳት ላኩት። እርሱም ወደርሷ በገባ ጊዜ በዝሙት ልትጥለው አልጋዋ ላይ ሆና ጠበቀችው። እርሱም እንዲህ እያለ ይዘምር ነበር በሞት ጥላ ውስጥ ብሔድም እንኳ ክፉን አልፈራውም አንተ ከእኔ ጋራ ነህና።

ከእርሷ ጋራም በአስቀመጠችው ጊዜ ራሱን ዘንበል አድርጎ አለቀሰ መነው ብትለው እግዚአብሔርን እንዳሳዘነችው ነገራት። በመጨረሻም ቃሉንም ሰምታ ደነገጠችና ተንቀጠቀጠች ምን ይሻለኛል አለችው ንስሐ ግቢ አላት እርሷም እግዚአብሔር ይቀበለኛልን አለችው እርሱም አዎን አላት እርሷም ወደምትሔድበት ከአንተ ጋራ ውሰደኝ አለችው እርሱም ነዪ ተከተይኝ አላቴና ተከተለችው።

በመሸ ጊዜም እርሷን አስተኝቶ እርሱ ግን በጸሎት ይተጋ ነበር። ሌሊትም በጸሎት ላይ ሳለ የብርሃን ምሰሶ አየ መላዕክትም የአንዲትን ነፍስ ሲያሳርጉ አየ። በነጋም ጊዜ ወደ አትናስያ ሲደርስ ሞታ አገኛት። ስለ ርሷም ያስረዳው ዘንድ እየሰገደ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም ገና ቤቷን ትታ ስትወጣ ይቅር እንዳላት ነገረው።

ከዚህም በኋላ ሒዶ ለአረጋውያን የሆነውን ሁሉ ነገራቸው እነርሱም እርሱ እንዳያት ማየታቸውን ነገሩት የኃጢአተኛን ወደ ንስሐ መመለሱን እንጂ ሞቱን የማይሻ እግዚአብሔርን አመሰገኑት።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
28.49 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 08 Aug 2025 06:01:36 +0300
ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ

ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ
መጣሁ ከደጅሽ ሱባዔ ገባሁ
ማን አፍሮ ያውቃል ባንቺ ለምኖ
በኪዳንኪ ተማህጽኖ
አዝ

የነፍሴ እረፍቷ ታዛ መጠጊያ
ካንቺ  ተገኝቷል የሞቴ መውጊያ
በሰላምታሽ ድምጽ ተባርኳል ቤቴ
የጌታዬ እናት ለኔም እናቴ
ማርያም ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ
እስመ ተማኅፀንኩ አንሰ ተማኅፅኖ
ለሥዕልኪ ስዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
አዝ

ቀንን ስናፍቅ በለሊት ሆኜ
አላተረፍኩም በሰው ታምኜ
ቁልፉ ልጅሽ ነው ለቋጠሮዬ
አሳስበሽልኝ አልፏል ስቃዬ
ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለልቡናየ ብርሃኖ
እስመ ተማኅፀንኩ አንሰ ተማኅጽኖ
ለሥዕልኪ ስዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
አዝ

ጉልበቴ ዝሎ ቀልዬ ሳለሁ
በኪዳን ጥላሽ ተስፋ አግኝቻለሁ
ደጅሽ መጥቼ ኃይሌ ታደሰ
ያሳዳጆቼ ምክር ፈረሰ
ወላዲተ አምላክ ኩኒ ለእርቃንየ ክዳኖ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማህጽኖ
ለሥዕልኪ ስዕለ አድህኖ ንሰግድ ለኪ
አዝ

የዝናቡ ምንጭ ፈጣን ደመና                    
ከሴቶች ሁሉ ክብርሽ ገናና
አንድያ ልጅሽ ወይን አድርጎኛል
ከትናንት ይልቅ ዛሬ ባርኮኛል

በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
24.45 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 07 Aug 2025 21:40:49 +0300
Подробнее
24.52 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 07 Aug 2025 13:11:36 +0300
Подробнее
28.78 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 07 Aug 2025 06:57:21 +0300
Подробнее
30.35 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 06 Aug 2025 20:07:37 +0300
​​​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው?

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ 

‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› 

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ 

ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
33.59 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 06 Aug 2025 13:00:58 +0300
ፍስለታ የሕፃናት ደስታ

የፍቅር የሰላም የደስታ ፆማችን
ከጌታችን እናት በረከት ማግኛችን
ፍልሰታ መታለች እጅግ ደስ ይበለን
ለቅዳሴ እንሂድ ልጆች ተሰብስበን
ፍስለታ /2/ የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ /2/
አዝ

ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ
ከእመቤታችን እጅ ሰበኗን አግኝቶ
የተደሰተባት የበረከት ፆም ወቅት
ፍልሰታ መታለች እንሂድ ለፀሎት
ፍስለታ /2/ የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ /2/
አዝ

መንፈሳዊ ቅናት ሐዋርያት ቀንተው
እነሱም ለማየት ትንሣኤዋን ሽተው
በህብረት በመሆን ጠይቀው በእምነት
ትንሣኤዋን አዩ በፆምና ፀሎት
ፍስለታ /2/ የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ /2/
አዝ

ሁል ግዜ በዓመት የምንናፍቃት
በፍቅር ምንፆማት ለማግኘት በረከት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንማርባት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንቁረብባት
ፍልሰታ /2/የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ/2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
26.99 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 06 Aug 2025 06:55:32 +0300
ሐምሌ ፴ /30/


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሠላሳ በዚች ቀን ቅዱሳን የገሊላ ሰዎች መርቆሬዎስና ኤፍሬም በሰማዕትነት አረፉ።

እሊህም ከአክሚም ከተማ የመጡ የሚዋደዱ በመንፈስ ቅዱስ ወንደማሞች በሥጋም ዘመዳሞች ነበሩ መንፈሳዊ ስምምነትንም ተስማምተው በላይኛው ግብጽ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም መነኰሱ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደሉ በገዳሙ ውስጥ ሃያ ዓመት ያህል ኖሩ።

ከዚህም በኋላ ጠላት ሰይጣን በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ከአርዮሳውያን ችግርን በአመጣ ጊዜ አርዮሳውያኑ በአርዮሳዊ ንጉሥ ትእዛዝ መሥዋዕትን ሊሠው ወደ ኦርቶዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገቡ ቀንተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡና አርዮሳውያን ያኖሩትን መሥዋዕት በተኑት።

እንዲህም አሏቸው በሥሉስ ቅዱስ ስም ያልተጠመቀ መሥዋዕትን ያሳርግ ዘንድ አይገባውም ። ያን ጊዜም አርዮሳውያን ይዘው ደበደቧቸው ታላቅ ግርፋትንም ገረፏቸው ዐጥንቶቻቸውም እስኪሰበሩ ድረስ በምድር ላይ ጥለው ረገጧቸው ነፍሶቻቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ ምእመናንም መጥተው ሥጋቸውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖርዋቸው ከእነሱም ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስ ሆነ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእኒህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
28.89 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 06 Aug 2025 06:00:46 +0300
​​ድንግል ወላዲተ ቃል

ድንግል ወላዲተ ቃል/2/

አሟሟዋትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር - - ድንግል
ያንቺ ለብቻ ነው ትንሳኤሽ ሲነገር - - ድንግል
ስጋሽ በምድር ላይ የታለ እንደፍጡር - - ድንግል
አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር - - ድንግል
አዝ

ስጋሽን ሲያሳርጉ መላክት ከሰማይ - - ድንግል
ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ - - ድንግል
መግነዝ ተረከበ ለሐዋርያት ሊያሳይ - - ድንግል
አዝ

ትንሳኤሽን ሽተው ግራ ሲገባቸው - - ድንግል
ሐዋርያት ጾመው ተገልጥሽላቸው - - ድንግል
ተቀብራ አልቀረችም በምድር ከደጅዋ - - ድንግል
ወደላይ አረገች እርሷም እንደልጅዋ - - ድንግል
አዝ

ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሳኤ - - ድንግል
እርገቷን አወቁ በልዩ ሱባኤ - - ድንግል
እኛም እንጸልይ በራችንን እንዝጋ - - ድንግል
ከወላዲተ አምላክ እንድናገኝ ዋጋ - - ድንግል

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
27.65 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 05 Aug 2025 13:01:32 +0300
Подробнее
29.34 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 05 Aug 2025 07:00:12 +0300
Подробнее
28.21 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 05 Aug 2025 06:38:25 +0300
Подробнее
24.92 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 04 Aug 2025 20:31:14 +0300
​​​​​​የጾም ዓይነቶች

ጾም የግል ,የዐዋጅ (የሕግ) እና የፈቃድ ጾም በመባል በሦስት ይከፈላል፡፡ ወይም የግል ጾምን የንስሐና የፈቃድ ጾም ብለን በሁለት እንከፍለዋለን፡፡ የዐዋጅ (የሕግ) አጽዋማት ሰባት ናቸው፡፡ እነዚህም :-

1⃣ ዐቢይ ጾም
2⃣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)
3⃣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
4⃣ ጾመ ገሃድ
5⃣ ጾመ ነነዌ
6⃣ ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ) እና
7⃣ ጾመ ፍልሰታ ናቸው፡፡

የዚህ ጽሑፍ መነሻም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነው ጾመ ፍልሰታ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ወቅቱ የፍልሰታ ጾም ስለኾነ፡፡

የፍልሰታ ጾም

ከዚህ በመቀጠል ጾመ ፍልሰታን ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምን እንደ ኾነ እንመለከታለን፡፡ የፍልሰታን ጾም ሕፃን አዋቂው ሳይቀር በልዩ ሥነ ሥርዓትና በደመቀ ኹኔታ ይጾማል፡፡

አብዛኞቹ ምእመናን የዕረፍት ጊዜ በመውሰድ በገዳማትና በየአብያተ ክርስቲያናት ሱባዔ በመግባት ከነሐሴ አንድ ጀምሮ እስከ አሥራ አምስት ቀን ድረስ ጾም፣ ጸሎት በማድረግ ይቆያሉ፡፡ ጾም ጸሎት ሲያደርጉ ደግሞ በድሎት ሳይኾን በየዋሻው፣ በየመቃብር ቤቱና አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ እንጨት ረብርበውና ሳር ጎዝጉዘው ጥሬ እየበሉ ነው፡፡

በቀጣይ 👉 ፍልሰታ ምን ማለት ነው? የሚለውን እናያለን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
26.56 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 04 Aug 2025 15:28:08 +0300
ጌታ እኮ ነው

ጌታ እኮ ነው ይህን ያደረገው
አምላኬ ነው ለኔ የታመነው
በዘመኔ ሁሉ ድንቅን የፈፀመው
ጌታ እኮ ነው ይህን ያደረገው
አዝ

የጠላቴን ሴራ ያፈራረሰልኝ
ከድንጋይ መወገር እኔን የታደገኝ
የሞት አዋጅ ሽሮ ጽድቅን ያለበሰኝ
አምላኬ ብቻ ነው እኔን ያባበለኝ
ጌታ እኮ ነው ሃጥያቴን የሻረው
  ''   ''   ''   ''   በሰላም ሂድ ያለኝ
  ''   ''   ''   ''   ልቤንን ያረጋጋው
  ''   ''   ''   ''   ስተክዝ የረዳኝ
አዝ

ከወንበዴዎች እጅ የታደገኝ ፈጥኖ
ቁስሌን በዘይቱ ያበሰልኝ አዝኖ
ወዳጅ ሆኖ ቀርቦ ሀዘኔን ያስረሳኝ
ጌታዬ እርሱ ነው መጽናኛ የሆነኝ
ጌታ እኮ ነው በምህረቱ ያየኝ
  ''   ''   ''   ''   ቁስሌን የፈወሰው
  ''   ''   ''   ''   ከጠላት ያስጣለኝ
  ''   ''   ''   ''   ሰላሜን ያወጀው
አዝ

ባህሩን ተሻግሮ ወደኔ የመጣው
የሙታንን ኑሮ በህይወት የቀየረው
ያሰረኝ ጠላት በስሙ ገጽሶት
ነጻ አወጣኝ ጌታ ታሪኬን ለውጦት
ጌታ እኮ ነው ልቤን የመለሰው
  ''   ''   ''   ''   ልጁ ያደረገኝ
  ''   ''   ''   ''   ጠላቴን የጣለው
  ''   ''   ''   ''   በቤቱ ያኖረኝ
አዝ

በምስኪኑ ድንኳን ገብቶ የሚቀመጥ
በሀዘን ለተዋጠው መጽናናት የሚሰጥ
እጅግ ቸር ጌታ ነው ማዳኑን አይተናል
ስሙን አወድሱት እልልታ ይገባዋል
ጌታ እኮ ነው ከእስራት የፈታኝ
  ''   ''   ''   ''   ጥልቁን ያሻገረኝ
  ''   ''   ''   ''   በሰልፍ ያበረታኝ
  ''   ''   ''   ''   ያከናወነልኝ

ሙሐዘ ስብኃት ዳግማዊ ደርቤ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
25.32 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 04 Aug 2025 06:58:03 +0300
ሐምሌ ፳፰ /28/


በዚች ቀን የእንድራኒቆስና የሚስቱ የአትናስያ መታሰቢያቸው ነው ። እነርሱም ከአንጾኪያ ከተማ ነበሩ ። በወርቅና በብርም የከበሩ ባለጸጎች ነበሩ ከገንዘባቸውም ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር።

ከዚህም በኋላ አንድ ወንድ ልጅና አንዲት ሴት ልጅን ወለዱ አስራ ሁለት አመት በሆናቸው ጊዜ ታመው ሞቱ። በዚህም እንድራኒቆስ እንደ ጻድቁ እዮብ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ ብሎ አምላኩን አመሰገነ።

አንድ ቀንም እናታቸው ከመቃብር ቦታቸው ሔዳ ስታለቅስ በሰማይ ያገኙትን ማዕረግ አየችና ለባሏ ነገረችው። ከዚህም በኋላ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን መጽውተው ሁለቱም በወንዶችና በሴቶች ገዳም ገዳመ አስቄጥስ ሔደው በአባ ዳንኤል እጅ መነኮሱ።

በዚያም አስራ ሁለት አመት ከቆዮ በኋላ እንድራኒቆስ አባ ዳንኤልን አስፈቅዶ ከቅዱሳት መካናት ይባረክ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ጀመረ። በጉዞ ላይም ሚስቱን አትናስያን አገኛት ነገር ግን እንደ ወንድ መነኩሴ ስለለበሰች እርሱ አላወቃትም ነበር እርሷ ግን አወቀችው ነገር ግን ሚስቱ እንደሆነች አልገለጠችለትም።

ወደ እስክንድርያ በተመለሱ ጊዜ አባ ዳንኤልም ሚስቱ እንደሆነች በመንፈስ ቅዱስ አውቆ እንድራኒቆስን ባልንጀራ ካደረግኸው ከዚህ መነኰስ ጋራ በአንድ ቦታ ኑሩ እርሱ ቅዱስ ነውና አለው ። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በአንድነት ኖሩ ማንም የአወቀ አልነበረም።

ከዚህ በኋላ አትናስያ በታመመች ጊዜ አባ ዳንኤል አቁርቧት ሞተች ሲገንዟትም እንድራኒቆስ ሚስቱ እንደሆነች አወቀ። በዚህም ጽኑ ሐዘን አዘነ። ከጥቂት ቀንም በኋላ እርሱም ታሞ አረ። መነኮሳትም በረከቱን ተቀበሉ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 04 Aug 2025 06:00:36 +0300
አኑሮኛል ቸርነትህ

አኑሮኛል ቸርነትህ ልክ የሌለው ደግነትህ
እንዳንተ አይነት ከየት ይገኛል
ሁሉም ነገር ትዝ ይለኛል/2/
እዝ

ያቺ ፈዋሽ አዳኝ እጅህ
ዛሬም ለኔ ተዘርግታ
በሐጢያት ርቄ እንዳልጓዝ
አስረኸኛል በውለታ
ደግሞስ ህይወት ምርጫ ቢሆን
ካንተ ወደማን ይኬዳል
አባቴ ፍቅርህ እኮ
ጌታዬ ፍቅርህ እኮ
አለምን ያስክዳል
እዝ

ሞቼ ነበር ተቀብሬ
ጌታ ወደ እኔ ባትመጣ
አንተ ሞቴን ባትሞትልኝ
ወዴት ነበር የእኔ እጣ
ከንቱ ነበር ማንነቴ
ተሽናፊ ለዚች ዓለም
ግን አንተ የያዝከው
አባቴ የያዝከው
ይኖራል ዘላለም
እዝ

መቅደስህን ተጠግቼ
አይቻለሁ ብዙ ነገር
በልቤ ውስጥ ያስቀመጥኩት
እንዲህ ለሰው ማይነገር
ግን የሆነው ሁሉም ሆኖ
የለም ዛሬ ያላረፈ
የመከራው እሳት
የፈተናው እሳት
ባንተ እየታለፈ
እዝ

አይጠፋኝም ያ ፈገግታ
ልጄ ብለህ ያሳየህኝ
አመፀኛ መጥፎም ሆኜ
በትክሻህ ላይ ያኖርከኝ
እንዲህም አይነት ወዳጅ አለ
እየጠሉት የሚያፈቅር
ስሙም ኢየሱስ ነው/2/
የፅድቃችን ሚስጥር
እዝ

ስነፈርቅ ሳለቅስብህ
እሺ እያልከኝ ሁሉም ሆነ
ማይሆንለት ነገር የለም
ለካስ ባንተ የታመነ
መቸኮሌ መጣደፌ
አምላኬ ሆይ በከንቱ ነው
መፈፀሙ ላይቀር/2/
ጌታዬ አንተ ያልከው

ዘማሪት ምርትነሽ  ጥላሁን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
24.39 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 03 Aug 2025 18:04:14 +0300
Подробнее
25.45 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 03 Aug 2025 13:01:48 +0300
Подробнее
25.68 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 03 Aug 2025 09:57:33 +0300
Подробнее
26.89 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 02 Aug 2025 13:16:31 +0300
እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው

እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው
ለእኔ ያደረገው ብዙ ነው
እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው
ለእኔ ያደረገልኝ ብዙ ነው
አዝ

እረዳት እርሱ ነው ከሰማያት
እግዚአብሔር ጠባቂ የኔን ሕይወት
ብርሃኑን በፊቴ የሚያበራ
አምላኬ ድንቅ ነው የእርሱ ስራ
አዝ

በመንገዴ ሁሉ የሚመራኝ
ስነሳ ስወድቅም የሚያስበኝ
ማንም አልመጣልኝ ከወገኔ
ከሁሉም ይበልጣል እርሱ ለኔ
አዝ

የእዳዬን ደብዳቤ ውድቅ አድርጎ
ሕይወቴን መራልኝ ወደ በጎ
ኧረ እንደእግዚአብሔር ማን ይሆናል
እሱን ለሚፈሩት ይታመናል
አዝ

እንድ ቀን አስቤ ተጨንቄ
ለመኖር አልቻልኩም ተጠንቅቄ
ሁሉን ነገር ለእርሱ ትቼዋለሁ
በምሕረቱ ጥላ እኖራለሁ

ዘማሪ እንዳልካቸው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
27.58 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 02 Aug 2025 07:08:07 +0300
ሐምሌ ፳፮ /26/


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ስድስት በዚች ቀን መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ጻድቁ ዮሴፍ አረፈ

እርሱም እምቤታችንን በርሱ ዘንድ ካስጠበቋት ጀምሮ በሁሉ ነገር ያገለግላት ነበር ። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም ። በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ ። ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት ። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን ተሰናበታቸው እጆቹንም ጠርቶዘርግቶ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ። የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ ።

በአረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃበር አኖሩት ። ዕረፍቱም ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዊ በዐሥራ ስድስት ዓመት ነው ። በረከቱ ከእኛ ጋር ትሁን ለዘላለሙ አሜን ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 02 Aug 2025 06:09:19 +0300
የተወደደ ቀን

የተወደደ ቀን የተወደደ ዓመት
ወደ አባቴ መቅደስ የተመለስኩበት
አንባር ቀለበትን የተሸለምኩበት
የተወደደ ዓመት
አዝ

አምሽቶ የመጣ አይገባም አትበሉ(2)
አባክኖ የመጣ አይገባም አትበሉ(2)
ፍቅር ስለሆነ እግዚአብሔር ለሁሉ(2)
ልጅ ቤቱን ይወርሳል እንደተስፋ ቃሉ(2)
አዝ

ከናዝሬት መልካም ሰው አይወጣም እያሉ(2)
ፊልጶስ ናትናኤል ይነጋገራሉ(2)
አድርጎታልና ውሀውን ወይን(2)
ዛሬም ለውጦኛል ወስዶታል ልቤን(2)
አዝ

እኔ ነኝ አላማው እኔ ነኝ ሀሳቡ(2)
አባቴ ደግ ነው የሚራራ ልቡ(2)
ዘጠና ዘጠኙ ታምነውት እያለ(2)
አንዱን ይፈልጋል ወዴት ነህ እያለ(2)
አዝ

ሁሉን አይቻለሁ ሁሉን መርምሬአለሁ(2)
አለም ካንተ ሌላ እንደሌለ አውቃለሁ(2)
እንደማይለወጥ አባትነትህ ወዳጅነትህ
ጠፍቼ ስመጣ አየሁት ልጅህ(2)

ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
25.38 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 01 Aug 2025 13:47:57 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 01 Aug 2025 06:57:26 +0300
Подробнее
28.88 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 31 Jul 2025 12:58:39 +0300
ዮሀንስ ፍቁረ እግዚእ

ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
ታኦሎጎስ ቅዱስ አቡቀለምሲስ
የሚወድህ በፍቅር ጌታክርስቶስ
አዝ

የልሳናት አባት የሚስጥራት መዝገብ
ከትበህ የያዝከው ረቂቁን ጥበብ
የኤፌሶን ኮከብ ደምቀህ ምታበራ
የወንጌል ዘር ዘርተህ ፍሬ ምታፈራ
አዝ

ብፁዕ ነህ ዮሐንስ ፅኑ ሐዋርያ
ከቶ ያልበገረኸ የአይሁድ ማስፈራሪያ
ከሀዋርያት መካከል መስቀል ስር አየንህ
አምርረህ ስታለቅስ በእድሜ በዘመንህ
አዝ

ነገርህ የጣፈጠ እጅጉን ያማረ
ዮሐንስ ልዑል ነህ ስምህ የከበረ
ካህን እና ነብይ የፍቅር መምህር
ድንግል ማርያምን የተሸለምክ በክብር
አዝ

እንደ ሄኖክ እና ነቢዩ ኤልያስ
ሞትን አልቀመስክም ሐዋርያዉ ዮሐንስ
ወልደ ነጎድጓድ ነህ የዓለም ፀሀይ
ለይቶ ያከበረህ አምላክ አዶናይ
አዝ

እንደ ሄኖክ እና ነቢዩ ኤልያስ
ሞትን አልቀመስክም ሐዋርያዉ ዮሐንስ
ወልደ ነጎድጓድ ነህ የዓለም ፀሀይ
ለይቶ ያከበረህ አምላክ አዶናይ

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
28.38 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 31 Jul 2025 07:01:16 +0300
ሐምሌ ፳፬ /24/


በዚች ቀን ከደቡባዊ ግብጽ ከታችኛው ምድር አውራጃ ከንሒሳ ከተማ ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት ሆኖ ሞተ ።

የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ቅዱሳን ንጹሐንና የሚራሩ ነበሩ ። ይህንንም ቅዱስ ኖብን በወለዱት ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት እስኪሆነው ፈሪሀ እግዚአብሔርን እያስተማሩ አሳደጉት ።

አንድ ቀን ቄሱንም ምእመናንን እንዲህ እያለ ሲያስተምራቸውና ሲያበረታቸው “ጣዖታትን ከምታመልኩ ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ስለ ክርስቶስ ነፍሳችሁን ለሞት አሳልፋችሁ ብትሰጡ ለእናንተ መልካም ነው” ሲላቸው ሰማው። ከዚህ በኋላ ያለውን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ ።

ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ገምኑዲ ሔደ በዚያም ላለው መኮንን ስለ ጌታችን አምላክነት መሰከረ። በዚህም ብዙ አሰቃየው የእግዚአብሔርመልአክተገልጦ አጽናናው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ ሰሜን አገር ሲጓዝ የከበረ ኖብን ከእርሱ ጋራ በመርከብ ወሰደው በመርከቡም ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው የእግዚአብሔር መልአክም አዳነው። በዚህም ወታደሮቹ አምነው ሰማዕትነትን ተቀበሉ። መኮንኑ ግን በብዙ አሰቃየው አቅፋሐስ ከሚባል አገርም ዮልዮስ መጣ ከእርሱም እንደ ተረዳ ገድሉን ጻፈ ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። እንዲሁም አደረጉበትና ሰማዕትነትን ተቀበለ። ጌታችንም ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት።
ሥጋውንም ቅዱስ ዮልዮሰ አንሥቶ ከሁለት አገልጋዮቹ ጋራ ንሒሳ ወደ ሚባል አገሩ ላከው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
29.61 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 31 Jul 2025 06:00:29 +0300
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ 

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/2/
አዝ

በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር
ተክለሃይማኖት ወዳጄ       
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ

አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና
ተክለሃይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
አዝ

ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ       
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ

ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና    
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
26.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 30 Jul 2025 12:58:32 +0300
Подробнее
28.42 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 30 Jul 2025 06:57:37 +0300
Подробнее
29.49 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 30 Jul 2025 06:42:03 +0300
Подробнее
26.05 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 29 Jul 2025 18:31:46 +0300
ዑራኤል ብርሃና

ዑራኤል ብርሃና/4/
ለኢትዮጵያ/2/ ብርሃና ለኢትዮጵያ /2/
አዝ

እንለምንሃለን ወድቀን ከፊትህ
እየተማጸንን በስነ - ሥዕልህ
ስለሚገልጽብህ እግዚአብሔር ኃይሉን
በቅድመ እግዚአብሔር ቆመህ አማልደን
ለኢትዮጵያ/2/ ብርሃና ለኢትዮጵያ
አዝ

መራኄ ብርሃናት ከሣቴ ምስጢር
ከሞት ወደ ሕይወት የምታሻግር
ከመላእክት ሁሉ አንተ ተመረጥክ
በብርሃን ጽዋ ደሙን ተቀበልክ
ለኢትዮጵያ/2/ ብርሃና ለኢትዮጵያ
አዝ

ለጥበብም ሰዎች መሪ ኮከባቸው
እስከ ቤተልሔም መርተህ ያደረስካቸው
ዛሬም ልጆችህን አስገባን ከርስቱ
አጽናን አረጋጋን እንዳንቀር በከንቱ
ለኢትዮጵያ/2/ ብርሃና ለኢትዮጵያ
አዝ

የክርስቶስን ደም ስትረጭ በምድር ላይ
ቃለ ማዕነቅህ ተሰማ እስከ ሰማይ
እንደ ቅዱስ ሄኖክ እንደ ዕዝራ ሱቱኤል
ሰማያዊው ካህን ባርከን ዑራኤል
ለኢትዮጵያ/2/ ብርሃና ለኢትዮጵያ
አዝ

ለድንግል ማርያም መንገድ የመራሃት
በስደቷም ወራት ቀርበህ የረዳሃት
ኢትዮጵያም ስትደርስ ነበርክ ከሷ ጋራ
የረገጥካትን ምድር ኢትዮጵያን አደራ
ለኢትዮጵያ/2/ ብርሃና ለኢትዮጵያ

ዘማሪ ዲ/ን ሳይዛና ጌታቸው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
27.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 29 Jul 2025 13:07:56 +0300
ቅዱስ ዑራኤል

ቅዱስ ዑራኤል አባቴ
ስጠራህ ግባ ከቤቴ
ቅዱስ ዑራኤል ብለን
ምን ጎድሎብናል በዓለም
ቅዱስ ዑራኤል/2/ ዑራኤል/2/ቅዱስ ዑራኤል
አዝ

በዓለም ማዕበል ተዉጠን
መግቢያ መዉጪያዉ ለጠበበን
አንተ በተሰጠህ ስልጣን
ከዚህ ከመዓቱ አዉጣን
አዝ

ዓለም እንክርዳድ ሆናለች
ጥሩ ፍሬዋን የጣለች
ከክፉ ሃሳብ ጠብቀህ
አኑረን ቤቱ አጽንተህ
አዝ

ቅዱስ ዑራኤል ብለናል
ፈጣን እርዳታህ ደርሶናል
ቅዱስ ዑራኤል መልአክ
አማላጃችን ከአምላክ
አዝ

በደስታ ዕንባ ተመልተን
ስላንተ እንመሰክራለን
ሰላምታ ለአንተ ይገባል
ከስዕልህ ፊት ወድቀናል

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
27.87 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 29 Jul 2025 06:58:14 +0300
ሐምሌ ፳፪ /22/


በዚችም ቀን ቅዱስ ለውንትዮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ክርስቲያን ከሀድያን ከሆኑ ሠራዊት ጋር ይኖር ነበር ሀገሩም ጠራብሎስ ነው መልኩም ያማረ በገድሉም ፍጹም የሆነ ነበር። አምላክ ያስጻፋቸው መጻሕፍትንም ያነብ ነበር። ይልቁንም የዳዊትን መዝሙር ሁልጊዜ ያነብ ነበር። ባልንጀሮቹ ለሆኑ ወታደሮችም ያስተምራቸው ይመክራቸውም ነበር። እግዚአብሔርንም እንዲፈሩ ያስገነዝባቸው ነበር።

የማይጠቅሙ የረከሱ የአማልክትንም ሸክም ከትከሻችሁ ጣሉ ይላቸው ነበር። ከስሕተትም ተመልሰው ክብር ይግባውና በጌታችን ያመኑ አሉ። ከእነርሱም ወደ መኰንኑ ሒደው የከሰሱት አሉ።መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀርቦ ጠየቀው እርሱ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስን እንደሚያመልከው በመኰንኑ ፊት ታመነ።

መኰንኑም ጭካኔውን አይቶ ሥጋው እስከ ሚቆራረጥ ደሙም እንደ ውኃ በምድር ላይእስኪፈስ ድረስ ሥቃዩን እጥፍ ድርብ አደረገበት ። ከዚህም በኋላ በውኃ እንዲዘፍቁት በእግሩም እንዲጐትቱትና በወህኒ ቤት እንዲጥሉት አዘዘ በዚያም ነፍሱን አሳለፈ ገድሉንም ፈጸመ።

የምታምን ሀብታም ሴት መጥታ ለወታደሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥታ የቅዱሱን ሥጋ ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው የወርቅ ሣጥንም አሠርታ በውስጡ አኖረችው ። ሥዕሉንም አሣለች በፊቱም ሁልጊዜ የሚያበራ ፋና አኖረች ። ለዚችም ሴት ቅዱሱ ያደረገላት የድካም ዋጋዋ ሰኔ አንድ ቀን ተጽፎ አለ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 29 Jul 2025 06:01:02 +0300
ዑራኤል

ክብሩ የተለየ የአምላክ ባለሟል ነው
የስሙ ትርጓሜ እግዚአብሔር ብርሃን ነው
የመላዕክት አለቃ ስሙ ዑራኤል ነው
አዝ

የሄኖክ መምህር ምስጢር የምትገልፅ
መልአከ ሰላም ነህ ወመልአከ ህይወት
እንደ አባ ጊዮርጊስ እንደ ቅዱስ ዕዝራ
ጥበብን አጠጣህ በፅዋ ልቦና
ዑራኤል ብርሀኔ ሆነህ ለዘመኔ
አንደበቴን ሞላው በምስጋና ቅኔ
አዝ

መልአኩ ዑራኤል አንተ ነህ ወዳጄ
በመከራ ሠአት የጭንቅ አማላጄ
በጨለማው ዓለም ብርሀን የሆንክልኝ
አብሪ ኮከቤ ነህ መንገድ የምትመራኝ
ዑራኤል ብርሀኔ ሆነህ ለዘመኔ
አንደበቴን ሞላው በምስጋና ቅኔ
አዝ

የምታረጋጋኝ ሆነኸኝ ሰላሜ
ለህይወቴ መሪ ማስተዋል ጥበቤ
በባህሩ ሞገድ ልቤ እንዳይታወክ
ሀይልን እንዲሰጠኝ አማልደኝ ከአምላክ
ዑራኤል ብርሀኔ ሆነህ ለዘመኔ
አንደበቴን ሞላው በምስጋና ቅኔ
አዝ

ማስተዋል በማጣት ነፍሴ እንዳትጎዳ
ፍሬን ሳላፈራ እንዳልቀር ከሜዳ
የብርሀን ፅዋህ ልቦናዬን ያብራ
በእምነት ፀንቼ ፅድቅን እንዳፈራ
ዑራኤል ብርሀኔ ሆነህ ለዘመኔ
አንደበቴን ሞላው በምስጋና ቅኔ

ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
26.55 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 28 Jul 2025 12:54:19 +0300
Подробнее
28.85 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 28 Jul 2025 07:33:03 +0300
Подробнее
28.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 28 Jul 2025 06:00:48 +0300
Подробнее
26.64 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 27 Jul 2025 18:07:02 +0300
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ

ያለሽ ልዩ ፀጋ ያለሽ ልዩ ክብር
የሁሉ እመቤት በሠማይ በምድር
አቁራሪተ መዓት ምዕራፈ ፀሎት
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት
አዝ

በመከራ ላለ ሁኚለት መፅናኛ
ዕንባውን አብሺው አይዘን ዳግመኛ
ጉድለቱን ሙይለት በፈረሰው ቆመሽ
ስለምታስምሪው በልዩ ኪዳንሽ
ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው
አዝ

ይበጠስ ከእጁ የወህኒው ሰንሰለት
የሞቱ ደብዳቤ ይቀየር በህይወት
አዲስ ተስፋ ሞልተሽ አዲስ ሰው አድርጊው
መቅበዝበዙን ይርሳ ድንግል አረጋጊው
ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው
አዝ

በእንባ የመጣው ይመለስ በደስታ
መጠማቱ ይቅር ይሞላ በእርካታ
ስዕለቱ ሰምሮለት ይቁም ለምስጋና
የአብራኩን ክፋይ አሳቅፊዉና
ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው
አዝ

ተይዞ ለሚኖር በአልጋ ቁራኛ
እርቺው እመቤቴ የደዌውን ዳኛ
መንገርስ ላንቺው ነው መማፀን ወደ አንቺ
ተስፋን ለምትቀጥይ እልምን ለምትሰ
ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
28.86 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 27 Jul 2025 13:06:05 +0300
የመላእክት አለቃ

የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ላከው
ኃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህሪይ ልጄ ወዳንቺ  ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል
አዝ      

ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳል
በተለየ አካሉ ወዳንቺ ይመጣል
ከሥጋሽም ሥጋን ከነፍስሽም ነፍስ
ነስቶ ይዋሃዳል በግዕዘ ሕፃናት ካንቺ ይወለዳል
አዝ

ደንቆሮ ሊሰማ ዲዶች ሊናገሩ
በጌታ ተአምራት እውራን ሊበሩ
ሙታን ይነሱ ዘንድ በማሕፀንሽ ፍሬ
ከእግዚአብሔር ወዳንቺ ተልኬአለው ዛሬ
አዝ

ደስ አሰኛት አለው በልዩ ሰላምታ
ሐሴት እንድታደርግ ምስራቹን ሰምታ
ድዳ እንዳደረከው ካህን ዘካርያስን
እንዳታሳዝናት ከእርሷጋር ስትደርስ
አዝ

ገብርኤል በደስታ ምስራቹን ይዞ
ከሰማይ ወረደ በአምላኩ ታዞ
በሊባኖስ መንደር እስኪሰማ ድረስ
ክንፉን እያማታ መጣ ሲገሰግስ
አዝ

ደስ ይበልሽ አላት እየተሳለማት
ሐርን ከወርቅ ጋር ስትፈትል አግኝቷት
እውነተኛው ንጉሥ ካንቺ ይወለዳል
ላንቺ ፍቅርና አንድነት ይገባል

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
28.06 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sun, 27 Jul 2025 10:15:01 +0300
ሐምሌ ፳ /20/

በዚህች ቀን ለስም አጠራሯ ክብር ይሁንና እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብታለች። በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ የእመቤታችን በዓላት እንደ አንዱ አይቆጠርም። ምክንያቱም ቅዱሳን ሊቃውንት በዓታ ከበዓታ ጋር ይስማማል ብለው የታኅሣሥ ሦስትን በዓል ከሰላሳ ሦስቱ ደምረውታል።

እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው ሁለት ጊዜ ሲሆን አንደኛው ዛሬ የምናከብረውና በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የገባችበት ነው። (ከግንቦት 1 ጀምረን እናስላው 80 ቀን ይመጣል::) ኦሪት እንዳዘዘው ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ንጽሕት ሕፃን ድንግል ማርያምን ታቅፈው የርግብ ልጆች (ግልገሎች) ዋኖስም ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሒደዋል። ካህናቱ ዘካርያስና ስምዖን ወጥተው በደስታ ተቀብለዋቸዋል። እመቤታችን ለወላጆቿ ማኅጸን የከፈተች በኩር ናትና በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋታል::

ሁለተኛው ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደ ስዕለታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ወስደው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋት ተመልሰዋል።

እግዚአብሔር ዛሬ ያልቃል: ነገ ይደቃል የማይባለውን የድንግል እናቱን ፍቅር አብዝቶ ያድለን። በረከቷም በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 26 Jul 2025 18:00:31 +0300
Подробнее
30.74 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 26 Jul 2025 12:59:08 +0300
Подробнее
29.25 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 26 Jul 2025 07:09:30 +0300
Подробнее
32.77 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Sat, 26 Jul 2025 06:51:26 +0300
Подробнее
28.05 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 25 Jul 2025 21:31:45 +0300
ገብርኤል - Gebreal 🛑 አዲስ ዝማሬ

https://youtu.be/wRLUWznP-QE?si=OmpOrkO8PJQEqHYy
Подробнее
28.73 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 25 Jul 2025 20:34:56 +0300
​​​​👆የቀጠለ

እኒኽም ቅዱሳን ይኽንን በሚነጋገሩበት ጊዜ በውስጡ አንገትን የሚቆለምም ልብንም የሚያቀልጥ ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርን የሚበጣጥስ መሳሪያ ካለበት የብረት ጋን ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረቱን ጋን እሳት አጠፋው፡፡ ከቅዱሳኑም አንዳቸውንም ሳያቃጥላቸው የብረቱ ጋር ማቃጠሉና መፍላቱ ጸጥ አለ፡፡

ወንድሞቻችን ሆይ እንግዲህ በጭንቃቸው ጊዜ ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ይህ መልአክ ከሰማእታትና ከጻድቃን ጐን እንደማይለይ እወቁ ለኃጥአንም ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላቸዋል፡፡ እኛም የዚህ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓሉን እያከበርን አማላጅና ወዳጅ እናድርገው። በዚህም በሚመጣውም ዓለም ሊረዳን ይችላልና፡፡

ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡

አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል።

የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን። ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› መዝ. ፻፴ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡

በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ፈራች፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው፡፡ ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን ‹‹እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ›› አላት፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም ‹‹ልጄ የነፍስ አባት ሁነኝ›› አለችው፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ከዘመናቸው ሳይደርስ፣ ታሪካቸውን ሳይማር የሠለስቱ ደቂቅን ታሪክ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ‹‹አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል›› ቢላት ፍርሃቱ ሊለቃት ባለመቻሉ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡፡

‹‹ጌታ ሆይ! የወይኑን ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን? እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን ታጠፋታለህን?›› ብሎ በጸለየጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና መንግሥተ ሰማያትን በዓይነ ሥጋ እንድታይ አደረጋት፡፡ ከዚህ በኋላ ፍርሃቱ ለቀቃትና ‹‹ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፣ አባቴ፣ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም›› ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው የብረት ጋን ገባችበት፡፡

በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል ያለውን ቃል ለመፈጻም እግዚአብሔር አምላክ መልአኩ
ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዝቅዞላቸዋል፡፡ በመልካቸውም እንደ ፀሐይ አበራ፡፡ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠሩራቸው አንድም ሳይጎዳቸው በደህና ወጡ፡፡

በመጨረሻም ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ እንዲህ አለ፡፡ ይህን ያህል ገድል ተጋድዬ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ ቢለው፣ ጌታ በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው፡፡ ዳግመኛም ሥጋህ በምድር ላይ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርሃለሁ አለው፡፡

ስለሆነም በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያናችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእናታችን ለቅድስት ኢየሉጣ እና ለሕፃኑ ለቅዱስ ቂርቆስ ያደረገውን ይህን ታላቅ ተአምር ድንቅ ሥራ በማሰብ ከዋዜማው ጀምራ እግዚአብሔርን ስታመሰግን ትውላለች ታድራለች፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን፡፡
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
32.95 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 25 Jul 2025 20:33:33 +0300
​​ሐምሌ 19
ቅዱስ ገብርኤል


እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡

በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡

ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡

መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡

መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡

በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡

እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡

ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡

አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
29.63 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 25 Jul 2025 12:56:08 +0300
እግዚአብሔር ጽዮንን

እግዚአብሔር ጽዮንን  መርጧታል ለክብሩ
ማደሪያው እንድትሆን መኖሪያ ሀገሩ
እንዲህ ካደረገ ከወደዳ እርሱ
ምን ያደርጋል ማመጽ አምላክን መክሰሱ
አዝ

ይህች ለዘላለም ማደርያ ናትና
መረጥኳት  እያለ አምላክ እንደገና
በእርሷ  አዛውንቱ ሲባረኩ እያየህ
እንዴት ማማለዷን ክብሯን ትክዳለህ
አዝ

ድሆችን እንጀራ ያጠግባል በእርሷ
ምድርም ታበራለች በጸጋ ታድሳ
የካህናት ሞገስ የደህንነት ልብስ
በእመቤታችን ነው  ሁሉ የሚታደስ
አዝ

ቅዱሳን በድንግል ደስተኛ ናቸው
ድንቅ ስለሆነ የእግዚአብሔር ምርጫው
የዳዊት ቀንድ ሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ከድንግል ተወልዶ ወገኑን ሊቀድስ
አዝ

እግዚአብሔር ጽዮንን  መርጧታል ለክብሩ
ማደሪያው እንድትሆን መኖሪያ ሀገሩ
እንዲህ ካደረገ ከወደዳ እርሱ
ምን ያደርጋል ማመጽ አምላክን መክሰሱ

በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
29.59 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 25 Jul 2025 11:12:26 +0300
ገብርኤል


ዛሬ ምሽት በዝማሬ ዳዊት ቲዩብ ይጠብቁን።
Подробнее
28.39 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 25 Jul 2025 07:06:23 +0300
ሐምሌ ፲፰ /18/


በዚችም ቀን ከቍልዝም ከተማ ቅዱስ አትናቴዎስ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ከነገሥታት ወገን ነበረ በሃይማኖቱም የጸና ነበረ። እኒህ ከሐዲያን ነገሥታት ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ የጣዖታትን አምልኮ በዓወጁ ጊዜ ይህን አትናቴዎስን ለግብጽ አገር ገዥ አድርገው ሾሙት አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲአፈርስ አዘዙት።

እርሱ ግን ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ሒዶ በረከትን ተቀበለ እርሱም ክርስቲያን እንደሆነ ነገረው በእርሱም ደስ አለው። ንጉሡም በሰማ ጊዜ ይዞ ይመረምረው ዘንድ ሌላ መኰንን ላከ መኰንኑም በደረሰ ጊዜ ተገናኘውና የአማልክትን ፍቅር ለምን ተውክ አለው። አትናቴዎስም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ ከታናሽነቴ ጀምሬ ክብር ይግባውና የክርስቶስ ነኝ የቀናች ሃይማኖቴንም አልተውም።

መኰንኑም የንጉሥን ትዕዛዝ የሚለውጥ ሁሉ ቅጣት እንዲአገኘውና በጽኑ ሥቃይእንዲሠቃይ እታውቅምን አለው። ቅዱስ አትናቴዎስም እንዲህ አለው አንተ ሰነፍ በአንተ ላይና በንጉሥህ ላይ ቸር ሕይወት ሰጭ እግዚአብሔርን በሚጠላ በአባትህ ሠይጣን ላይ የሚመጣው የዘላለም ሥቃይን እስከምታይ ጥቂት ታገሥ አለው።

መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ቅዱስ አትናቴዎስም ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጋራ እንዲያሳርፍ ከቤተ ክርስቲያንም መከራን እንዲያርቅ የሮምንና የአኲስምን የክርስቲያን መንግሥት እንዲአጸና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ጸሎቱም በፈጸመ ጊዜ በርከክ ብሎ ሰገደ ጭፍሮችም ራሱን በሰይፍ ቆረጡ። ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ቀበሩት። ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ተአምራት ተገለጡ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
33.25 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Fri, 25 Jul 2025 06:01:12 +0300
ሳለምን

ሳለምን የሚያስፈልገኝን ታውቃለህ
ሳልጠይቅ የሚያስፈልገኝ ታውቃለህ
ብቻ ጤናን ስጠኝ አልጥፋ ከቤትህ እንዳመሰግንህ
አዝ

በሰላም የኖርኩት በጤና ያረፍኩት
ሞልቶ የተረፈው የቤቴ በረከት
አይደለም ጥበቤ የጸሎቴ ብዛት
ስለምታውቀው ነው የልቤን ፍላጎት
አዝ

ጠግቤም ተርቤም ምስጋናህ በአፌ ነው
ባይሞላልኝም እንኳ ግብሬ ዝማሬ ነው
አላስብም ነገን ምን ይሆናል ብዬ
በህይወቴም በሞቴም አንተ ነህ ጌታዬ
አዝ

ደጅህን ሳልመታው ምንም ሳልጠይቅህ
ጓዳዬ ሙሉ ነው መጉደልን ሳያውቅ
በነገሮች ሁሉ ነብሴን አስተምረህ
በሰጠኸኝ ጸጋ አንተን እንዳከብርህ
አዝ

መሻቴን ፈጽመህ በጸጋ ሞላኸኝ
በመልካሟ ስፍራ በቤትህ ተከልከኝ
ይኸው አበዛኸኝ ባረከኝ በብዙ
አይደለም በስጋ ከላይ ነው ትዕዛዙ

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
28.76 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 24 Jul 2025 13:17:47 +0300
Подробнее
30.49 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 24 Jul 2025 06:54:17 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Thu, 24 Jul 2025 06:00:38 +0300
Подробнее
26.46 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 23 Jul 2025 13:00:33 +0300
ምስጢረኛዬ ነሽ

አውቀዋለሁ ደጅሽን የእረፍት ቦታዬን
ጽኑ ሰላም ጸጥታ ማግኛዬን
የት እሄዳለሁ አልልም ሲከፋኝ
ኪዳነምሕረት አንቺ እያለሽልኝ/2/
አዝ

ከአጸደ መቅደስሽ ከስዕልሽ ስር
እረፍቴ በዚያ ነው በቅዱሱ ደብር
ከተራራው አናት ከደጅሽ መጥቼ
ሰምሮልኛል ስምሽን ጠርቼ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

የሮማን አበባ መዓዛሽ ተወዳጅ
በረከትን ልቅሰም ሳልለይ ካንቺ ደጅ
አስራትሽ አድርጊኝ ጠቅልይኝ እናቴ
ታብብልኝ ትፍካልኝ ሕይወቴ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

አጠገቤ ጎኔ በዙሪያዬ እንዳለሽ
እንደርሱ ነው ልቤ እማ የሚያወራሽ
አልቅሼ ሲቀለኝ ነግሬሽ የውስጤን
አትዘገይም ስትሠሪልኝ ቤቴን
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

የእንጦጦዋ እናቴ እምዬ የምልሽ
ኪዳንኪ ደጓ የልብን ሰሚ ነሽ
በሄድኩበት አለሽ ተከትለሽኛል
ስላለሽኝ ሰላም ይሰማኛል
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
29.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Wed, 23 Jul 2025 07:05:09 +0300
ሐምሌ ፲፮ /16/


በዚች ቀን ቅዱስ አባት ወንጌሉ ዘወርቅ የተባለ ዮሐንስ አረፈ ። ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገርነበር አባቱም አጥራብዮስ የሚባል ባለጠጋ ነው ። የእናቱም ስም ብዱራ ይባላል ። እንዲማርም ለመምህር ሰጡት ቅዱሳት መጻሕፍትንም ተማረ ።

ከዚህም በኋላ አባቱ ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን አሰርቶ ሰጠው ከእርሱም አትለይም ነበር። በዚያም ወራት ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዝ መነኵሴ ወደ እነርሱ መጣ በእነርሱም ዘንድ አደረ ለቅዱስ ዮሐንስም ስለምንኩስና ነገር በዚህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ወደ ገዳም ሔዶ መነኮሰ። በብዙ ተጋድሎም ተጋደለ።

በዚህ ተጋድሎም ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከእነርሱ በረከትን ትቀበል ዘንድ ከመሞትህ በፊት ወደ አባትህና እናትህ ሒድ የሚል ራእይ አየ ።

ወደ አባቱ ቤትም በደረሰ ጊዜ በትንሽ ጎጆ ውስጥ በአባቱ ደጅ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደለ ባሮች ከአባቱ ማዕድ የሚጥሉለትን ፍርፋሪ እየተመገበ ሰባት ዓመት ኖረ። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰባት ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ትወጣለህ ብሎ ነገረው። ከዚህም በኋላ እናቱን አስጠርቶ ማንነቱን ሳይነግራት የመሞቻው ቀን ስለደረሰ በለበሰው ጨርቅ እና በሚኖርበት መጠለያ እንዲቀብሩት አምሏት የወርቅ ወንጌሉን ሰጣት። ለባሏ ባሳየችውም ጊዜ የልጃቸው እንደሆነ አወቁ።
ቢጠይቁትም ነገራቸው። ሰባቱ ቀንም ሲፈጸም ቅዱስ ዮሐንስ አረፈ።

ከዚህም በኋላ በስሙ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ። ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
Подробнее
30.27 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 22 Jul 2025 13:00:52 +0300
Подробнее
30.73 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 22 Jul 2025 07:25:05 +0300
Подробнее
29.91 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Tue, 22 Jul 2025 05:58:46 +0300
Подробнее
25.45 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 21 Jul 2025 20:50:48 +0300
​​ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ

እንድርያስ ማለት ጽኑዕ፣ በኩር ማለት ሲሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ነው።  የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ሳለ ዮሐንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳይቶት ከእርሱ ጋር ዋለ። (“በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ። እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ። ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ። ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው።እርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ ትርጓሜው መምህር ሆይ ማለት ነው።መጥታችሁ እዩ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ። ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ።እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና። መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው።ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ። አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ጴጥሮስ ማለት ነው።” ዮሐ.1፡36-43) ጴጥሮስንም ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ያመጣው እርሱ ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድርያስ ከወንድሙ ስምዖን ጋር አሳ በሚያጠምዱበት ጊዜ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” ተብሎ ተጠርቷል። (ማር.1፡16-17) ጌታችንን ስለኢየሩሳሌም መፍረስ ከጠየቁት አንዱ ነበር። (ማር.13፡3-4)

ቅዱስ እንድርያስ የሚጠራባቸው ቅጽል ስሞች

ኘሮቶክሌቶስ፦/ የተጠራ ማለት ነው፡፡/ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በዚህ ስም ይጠሩበት ነበር፡፡ አስቀድሞ ለሐዋርያነት ስለተጠራ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ዮሐ1

አስተባባሪ ሐዋርያ፦ ከሰው ጋር የመግባባት ችሎታ ስለነበረው በሐዋርያት ዘንድ እንደ አስተባባሪ ሐዋርያ ይቆጠር ነበር፡፡

የወጣቶች ሐዋርያ፡- ጥብርያዶስ ባሕር ሲማር ለቆየው ሕዝብ ቅዱስ እንድርያስ አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘውን ወጣት አቅርቦ አስባርኮታል ጌታም የአምስት ገበያ ሕዝብን በበረከት አጥግቧል፡፡ ዮሐ 6÷6 -7

የአሕዛብ ወዳጅ ሐዋርያ፡- ጌታችንን ለማየት የፈለጉትን ከአሕዛብ ወገን የነበሩትን ግሪኮች ተቀብሎ ከጌታ ጋር በማቀራረቡ በማገናኘቱ፡፡ ዮሐ 12÷20

የቤተሰብ ሐዋርያ፡- የጌታችንን ማደሪያ ካየ በኋላ ተመልሶ ለወንድሙ ለቅዱስ ጴጥሮስ በመናገሩ እና የወንጌልን ምሥራች ለቤተሰቡ በማብሠሩ የቤተሰብ ሐዋርያ ይባላል፡፡

ቅዱስ እንድርያስ መጀመሪያ የስብከት ሥራውን በፍልስጥኤም ጀመረ፡፡ የቤተክርስቲያን ፀሐፊ የነበረው አወሳብዮስ እንደገለጠው እንድርያስ በሩስያ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ቀጥሎም በቢታንያ፣ በገላትያ፣ በሩማንያ፣ በመቄዶንያ፣ በታናሽ እስያ፣ በግሪክ አገር አስተምሯል፡፡ የቁስጥንጥንያን ቤተክርስቲያን የመሠረተና የቁስጥንጥንያ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ መሆኑ ይነገራል፡፡ በመጨረሻም ግሪክ ውስጥ ምትራ/ ጳጥሪስ በምትባለዋ ሀገር ሲያስተምር በጣኦት አምላኪዎች እጅ / X / የሚመስል ቅርጽ ባለው መስቀል ተሰቅሎ በድንጋይ ተወግሮ ታኅሣሥ 4 ቀን በ60 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የ/መ/ገ/ጽ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤ እና ነገረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
27.62 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 21 Jul 2025 17:39:50 +0300
አሐዱ ብያለው - Ahadu Beyalew ​⁠ ዘማሪት ወገን ድንቁ

https://youtu.be/acFsuIK9JGs?si=LIyRapAHY6Rn3FUS
Подробнее
26.39 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001250471820 Mon, 21 Jul 2025 13:10:54 +0300
ባክኛለሁና

ባክኛለሁና በስጋ ፈተና
የዚህ አለም ሀዘን ጫፍ የለውምና
ፈጥነሽ ወደኔ ነይ ከትንሿ ቤቴ
አፅናኚኝ እመአምላክ ድንግል እመቤቴ
አዝ

ባህሩ ትልቅ ነው ድንግል እመቤቴ
ትንሽ ናት መርከቤ       "     /2/
የመንገዴ መሪ            "
አንቺ ነሽ ወደቤ           "     /2/
አዝ

በመንገዴ ብዝል          ድንግል እመቤቴ
አለም ትስቃለች           "      /2/
መመኪያ እመቤቱ        "
ወዴት ነች እያለች         "     /2/
አዝ

በቀቢፀ ተስፋ           ድንግል እመቤቴ
እንዳልሞትብሽ          "      /2/
በቀንም በሌሊት         "
ተስፋዬ አንቺ ነሽ         "      /2/
አዝ

የለም ያተረፍኩት         ድንግል እመቤቴ
ወጥቼ ወርጄ               "    /2/
ትርፌ አንቺ ብቻ ነሽ       "
ፅዩን አማላጄ                "    /2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Подробнее
30.98 k
]]>