Лента постов канала Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል (@ahmedin99) https://t.me/ahmedin99 ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው! ru https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Mon, 18 Aug 2025 15:50:54 +0300
Подробнее
10.08 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Mon, 18 Aug 2025 15:50:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Tue, 12 Aug 2025 05:32:27 +0300
#አፋልጉን
🔴🔴🔴

ከላይ የምታዩት ወጣት የ 10 አመት ልጃችን ሙስአብ ከማል
ይባላል። በቀን 30/11/2017 ዓ.ም, ሃይሌ ጋርመንት አከባቢ ከሚገኘው መኖረያ በቤት ወደ ትምህርት ቤት አንደ ሄደ አልተምለሰም። ልጃችንን ያገኘ ወይ ያለበተን የሚጠቁመን ወረታዉን አንከፍላለን ፤ ወላጆቹ።
ስልክ :-  0911909327, 0912255990,  0917126278
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Tue, 05 Aug 2025 22:09:09 +0300
Подробнее
21.57 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Mon, 04 Aug 2025 21:09:06 +0300
ኦዲት እንዲደረግ ሲጠየቁም «አታምኑኝምን? » በማለት ኦዲት መደረግን እንደ አለመታመን መቁጠር ይኖራል። በሌሎች ጉዳዮች ላይም ሲሆን «እኔ እገሌን አምነዋለሁ። እናንተም እመኑት» የሚል ምላሽ ሊሰጥ ይችላል።

2. መጅሊስ ሂደትና አሰራር ተኮር ከመሆን ግለሰብ ተኮር ይሆናል።

3. በተቋሙ ዉስጥ የበለጠ ስልጣንና ስፍራ የሚኖራቸው የተሻለ አቅም ያላቸው ሠራተኞች ሳይሆኑ ሸኽየውን ከሌሎቹ ይበልጥ የሚያከብሩ፥ የሚተናነሱና የሚታዘዙ ይሆናሉ።

4. መጅሊስ የአስተዳደርና የአገልግሎት ተቋም መሆኑ ቀርቶ ኡለሞችን ብቻ የሚመለከት የዑለማ ምክር ቤት ይሆናል።

5. «አጅነቢ» በሚል ሴቶች በመጅሊስ ተገቢውን ሚና እንዳይኖራቸው በር የመዝጋት ሁኔታም ሊፈጠር ይችላል። በሂደትም መጅሊስ የወንድ ዓሊሞች ብቻ መድረክ ይሆናል። የሴቶች ዘርፍ መሪን በሥራ አስፈጻሚ ዉስጥ ላለማካተት ሲባል የሴቶች ጉዳይ ዘርፍም በወንድ እስከ መመራት ሊደርስ ይችላል።

6. በነርሱ ስልጣንና አካሄድ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ወጣቶችን ይቸኩላሉ፥ ፊትና ሊፈጥሩ ይችላሉ፥ አካሄዳቸው ከመንግስት ጋር ያጋጫናል፥ ወዘተ በሚሉ ምክንያቶች የመግፋት ሁኔታ ይፈጠራል።

7. በሥራ ሂደትና አሰራር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ትችቶችን ዑለማን እንደመናቅና ማዋረድ በመቁጠር ተቃውሞን ዝም ለማሰኘት ሊሞክሩ ይችላሉ።

8. ከተቆናጠጡት የመጅሊስ የአመራርነት ወንበር ላለመልቀቅ ወደ መንግስት ከለላ የመግባት ሁኔታ ሊፈጠርም ይችላል።

የዑለሞች የኃይል ልምምድ ይገደብ!
🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የሙስሊም ኢትዮጵያውን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች የሚስተናገድበት ሀገር ዓቀፍ መሪ ተቋም ነው። የመፍትሄ እርምጃውም የሚነጨው ከዚሁ እይታ ነው። ይህ ማለት መጅሊስ የዑለሞች ብቻ ሳይሆን የወጣቶች፥ የሴቶች፥ የምሁራን፥ የተርታው ሙስሊም፥ በአመራር ላይ ያሉ አካላት ደጋፊም ተቃዋሚም ሙስሊም ሁሉ ተቋም መሆኑን አምኖ መቀበል ማለት ነው። ቀጥሎ ደግሞ ሁሉም ሙስሊም ተቋሙ ምን ዓይነት ሚናና ቅርጽ እንዲይዝ ይፈልጋል? የሚለውን በጋራ ምክክር መወሰን ይገባል።

ይህ ከሆነ በኋላ ሕዝበ ሙስሊሙ መሪዎቹን የመምረጥ፥ የማውረድ፥ የመተቸትና የማረምና የማስተካካል ሙሉ ስልጣን እንዳለው ማረጋገጥ ይገባል። ቀጥሎ ደግሞ ተቋሙ ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር የሚሄዱ ብቃት ያላቸውን መሪዎች የሚመረጡበትን ስርዓት መዘርጋት። በመተዳደሪያ ደንቡ የአመራሮች ሚናና ስልጣን የተገደበና ቁጥጥር ያለበት (Chek and balance) ጠንካራ ስርዓትን መዘርጋት። አሰራራቸው ግልጸኝነትና ከአድሎ የጸዳ እንዲሆን በማድረግ ጉድለትና ሥህተት ሲኖር እነርሱን የመቃወም መብትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የኡለማኦች መከበርም ሆነ ካላቸው ደረጃ ከፍ ዝቅ የማለት ጉዳይ የሚማያሳስበውም ሆነ የሚመለከተው በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል ባለ ግንኙነት እንጂ ከሌሎች ጋር በሚኖር ግንኙነት አይደለም።ለምሳሌ መጅሊሱን የሚመራው ኡለማእም ሆነ የአካዳሚ ምሁር ወይም ተክኖክራትም ሆነ ጃሂል በሌሎች ወገናች በኩል የሚያመጣው ለውጥ የለም።ይለቁንም ካለፉት ጊዜያት መረዳት እንደሚቻለው የማህበረሰባችንን ማንነት ማህበረሰመባችንንየሚመጥን ከሆነ ተደማጭነት ያገኛል አለበለዚያ በየትኛውም ደረጃ ቢሆን እይታው ተመሳሳይ ነው።

በሌላ መልኩ ኡለማኦች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና መቀነስ ትልቅ ማህበረሰባዊ ኪሳራን ያስከትላል።ይሄ ደግሞ በተለይ እእደ መጅሊስ አይነቱን ህዝባዊ ቋም በመምራት በህዝብና በመንግስት መሀል የሚመራ አካል ተቀባይነት ማጣትን በማስከተል ለህዝብም ለሀገርም ለመንግስትም ጥሩ አለመሆኑና ካለፉት ልምዶች መቅሰም ያስፈልጋል።

በተለይ በዘንድሮ ምርጫ ዑለሞች ከሌላው ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በመጅሊስ በሁሉም እርከን አመራርነትን ካልያዝን እያሉ ስለሆነ ተቋሙ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል፥ እነርሱንም ከዉድቀት በመታደግ፥ ተቋማዊ አሰራርን ለማረጋገጥና ተጠያቂነትን ለማስፈን ይቻል ዘንድ በተቋም አሰራር በበላይነት ገዢ መሆን ያለበት ሕግና ደንብ እንጂ ግለሰብ መሆን ስለሌበት በተቋም ዉስጥ ዑለሞች መሪም ሆነ አባል ሆነው እስከ ገቡ ድረስ የዑለሞች የኃይል ልምምድን እንደሚገደብ ማስረዳትና በተግባርም መገደብ ግዴታ ይሆናል።

ይህ ደግሞ እውን የሚሆነው «ሼካችን» ፥«ዓሊማችን» እና «የሃይማኖት አባት» በሚል ሲያጠፉ ለመገሰጽ በማፈር በዝምታ በማየት አልያም እስኪሳሳቱ ጠብቆ በማውገዝ ሳይሆን ከወዲሁ የግለሰባዊ አካሄድንና የተቋማዊ አሰራርን እንዲለዩ፣ስለተቋም ባህሪያት እንዲገነዘቡና እንዲለምዱ ተጠግቶ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ነው። የዚህ ጽሁፍ ተልዕኮም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ይህኑ በማሳካት ላይ ማገዝ ነው።ይህ ሲሆን ብቻ ነው መጅሊስ ዘመኑን የዋጀ የሙስሊሞች ተቋም ሆኖም መቀጠል የሚችለው። አላህ ቸር ያሰንብተን!
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Mon, 04 Aug 2025 21:09:06 +0300
ዓሊሙ እንደ ዶክትሬት፥ ማስተርስ፥ ዲግሪና ኢጃዛ ያሉ ከፍ ያለ የእውቀት መመዘኛ ማዕረጎችን ይዞ በተግባር እንደሚጠበቅበት ሚናውን ባለመወጣቱ በማህበረሰቡ ቅሬታ በርሱ ላይ ሊፈጠርበት ይችላል።

መ) የሸሪዓ ፍርድ ቤት ቃዲ(ዳኛ) ሲሆን
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲

ዓሊም በሸሪዓ ፍርድ ቤት ውስጥ ዳኛ ሲሆን የኃይል ምንጩ ከዳኝነት ስልጣን የሚመነጭ ነው። በዚህ ሂደት የዳኛው ስልጣን ክልል ችሎቱ ሲሆን በችሎት «የተከበሩ ዳኛ» ተብሎ ይጠራሉ። ለችሎቱ ክብር ሲባል አቤቶታ ሲቀርብና ለመናገር ሲፈለግ ጭምር ከነርሱ ፈቃድ ይፈልጋል። በግራ ቀኙ ከቀረቡላቸው ማስረጃዎች በመነሳትም ተገቢ ነው ያሉትን ዉሳኔ ያሳልፋሉ። በዚህም በችሎቱ ዉስጥ የመጨረሻው ዉሳኔ ሰጪና ፈራጅ ናቸው።

የዳኞች ሚና በሚያዩት መዝገብ ላይ ዉሳኔ መስጠት ነው። የሚወስኑትም በፍርድ ቤቱ አሰራርና የዳኝነት ሥነስርዓት መሠረት በመሆኑ እንዲሁም የፍርድ ቤቱ አመራሮችና የፍትህ ሰርዐት ከነርሱ በላይ በመሆናቸው ስልጣናቸው ዉስን ነው። ዉሳኔያቸውም በሚቀርብአቤቶታ የበላይ በሆነው የይግባኝ ሰሚ ችሎት ሊቀለበስ ይችላል።

ከፍርድ ሂደቱ ዉሳኔ ጋር ባልተያያዘ ሁኔታ አግባብነት የሌለው የጥቅም፥ የአድሎና የሙስና አካሄድ ከተጓዘም በአስተዳደርም ሆነ ወንጀል ሊጠየቅ ይችላል። በየወሩ በሥራ ገበታው ተገኝቶ ለሚሰራው ሥራ ደሞዙን ከተቋሙ የሚቀበል በመሆኑ በአስተዳደር ቁጥጥር ይደረግበታል። ሰለዚህ ፍጹማዊ ኃይል (absolute power) የመለማመድ እድሉ ዉስን ነው።

የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆነ ዓሊም ወደ መጅሊስ መሪነት ሲመጣ የሚከተሉት ሊከሰቱ ይችላሉ፦

1. ከባልደረቦች ጋር በትብብር ከመስራት የፍርድ ቤትን ከላይ ወደ ታች የማዘዝ ስነልቦናን ወደ መጅሊስ አሰራር ለማምጣት ሊሞክሩ ይችላሉ።
2. ተቃውሞን ልክ እንደችሎት መድፈር፥ ፍርድን አለመቀበል አድርገው ሊያዩ ይችላሉ።

ሠ) ዓሊም የመጅሊስ መሪ ሲሆን
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ዓሊሞች የመጅሊስ መሪ ሲሆኑ የኃይላቸው መሠረት በተቋሙ ዉስጥ በመዋቅሩ የተሰጣቸው ስልጣን ይሆናል። የሚጠበቅባቸው የማህበረሰቡን ጥቅምና ፍላጎት ማስከበር ነው። ስልጣናቸው ወሰንና ቁጥጥር አልባ አይደለም። ያሻቸውን የመወሰን፥ ባሻቸው ጊዜ ወደ ሥራ የመግባትና ያለመግባት ፥ ደስ ሲላቸው ያሻቸውን የመሥራት እና ከተሰጣቸው ስልጣን ዉጭ መሆን አይችሉም። ሰለዚህ በተቋሙ ዉስጥ ያለው የተጠያቂነትና የግምገማ ሂደት ከለመዱት ተቃራኒ ይሆንባቸዋል። ቃላቸውና ሀሳባቸው የሚገመገም፥ የሚተችና ተቀባይነት አለማግኘት እድል መኖሩ አያስደስታቸውም።

ለመደመጥ መናገር ብቻ ይጠበቅበት የነበረ ዓሊም ሀሳቡ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ማሳመንና የጋራ ሰምምነት የሚባል አሰራር መኖሩ የሚያስደስተው አይሆንም። በዚህ የተነሳ በቂርዓት ጊዜ በደረሶች ላይ ያለው ኃይል፥ ተደማጭነትና ተጽዕኖን በተቋሙ ዉስጥ መልሶ ለማግኘት ሲሉ በተለያዩ መንገዶች ይጠቀማሉ፡፡ በተደጋጋሚ ዓሊም መሆናቸውን መጠቀስ፥ ሰለ ተቋማዊ አሰራር የሚያሰታውሷቸውን አካላትን «ዓሊም አታከብሩም» በሚል መውቀሰ፥ «እናንተ የተማራችሁ ሰዎች ዑለሞችን ትንቃላችሁ» የሚሉ ቃላቶችን በመሰንዘር ፍጹማዊ ተደማጭነት ለማግኘት ይጥራሉ።

በተለይ የተቋሙ ዋና መሪ ሲሆኑ ከዚህ የኃይል እየቀነሰ መሄድ ስሜትና «ዑለማ ከተቋም ደንብና ሕግ በላይ ነው» ከሚል ግላዊ ፍላጎት የተነሳ የሌሎች የሥራ አስፈጻሚዎችን ሀሳብን እየተጋፉ በመሄድ በሹራ(ምክክር) የመምራትን ተቋማዊ አሰራርን የማክሰም እድል ይፈጠራል። በሂደትም ከሕግና አሰራር ውጪ የሆነ ተጠያቂነት የሌለበት ስልጣንን መለማመድ ይፈጠራል። በዚህ ሁኔታ ትችት ሲቀርብባቸውም «ዑለማ ተደፈረ» የሚል ቅስቀሳ ይጀምራሉ ። ሰሞኑን በግልጽና በይፋ በመጅሊስ ጉዳይ ከምጽፋቸው ጽሑፎች ጋር በተያያዘ ይህ ሁኔታ ተስተውሏል።

የኔ ሀሳብ ዑለሞችን ከመናቅና ማሳነስ የራቀ ቢሆንም «የተነሳው ሀሳብ የኛን የተደማጭነትና ተቀባይነት ኃይልን ይቀንስብናል» በሚል በጁምዓ ኹጥባና በተገኘው የመድረክ አጋጣሚ «የዑለሞች ክብር» በሚል ርዕስ ለሕዝቡ ትምህርት ለመስጠት ተምክሯል።

በመጅሊስም ሆነ በየትኛውም ተቋም ላይ ተጠያቂነትና ተቀናቃኝ የሌለበትን ፍጹም ኃይል(absolute power) የመፈለግ አዝማሚያ እጅግ አደገኛ ነው።

ከተማሪዎቻቸው ፍጹም ታዛኝነትን የተለማመዱ ዓሊሞች በመጅሊስ ዉስጥ ኃይላቸውን ከፍ ለማድረግ አንድም እንደ ተማሪዎቻቸው የማይሆኑላቸው የተማሩ ሰዎችና በከተማ ያደጉ ወጣቶችን ከመጅሊስ የአመራርነት ስፍራ ለማራቅና በምርጫም የራሳቸው ዓይነት የሆኑ ዓሊሞችና ተማሪዎቻቸው መጅሊሱን እንዲሞሉ የማድረግ ስልትን እየተከተሉ እንዳሉ ይሰተዋላል።

ይህ አካሄዳቸውም ከተቋማዊ በሕግ የተገደበ ስልጣንና ተጠያቂነት አሰራር ጋር የገጠማቸውን ተግዳሮት (Challege) በማሸነፍ ለፍጹማዊ ኃይል (absolute power) እንዲታገሉ አድርጓቸዋል። ለዚህም ነው የመጅሊስ የጠቅላላ ጉባኤም፥ የሥራ አስፈጻሚውና አመራርነት በዓሊሞች ሊያዝ ይገባል የሚል ትግል ውስጥ የተገባው። ትግሉን ለማሸነፍ ደግሞ ለራሳቸው የሚመቹ የምርጫ አካሄዶችና መስፈርቶችን እስከ ማውጣት ደረሱ። ከዚህ ምርጫም በኋላም ሕዝቡ የሚሳተፍበት የመጅሊስ ምርጫ እንዲቀርና ምርጫው በዑለሞች መካካል እንዲካሄድ ፈትዋ በመስጠት የምርጫን ፋይል እንዘጋለን የሚል አዝማሚያም ተሰተውሏል።

ለዚህ ደግሞ አሁን ያለው የዑለማ ምክር ቤት ምርጫው እርሱን የማይመለከት ቋሚ ሆኖ ማን ወደ መጅሊስ የአስተዳደር መሪነት መምጣት እንዳለበት መስፈርት የማውጣትና የመወሰን በዚህም ለራሳቸው የአንጋሽነት ስልጣን (King maker) ሚናን ወሰዱ።

ይህ የሕዝበ ሙስሊሙን ጥቅምና ፍላጎትን ሳይሆን የራስንና የጀመዓን ኃይል የማስጠበቅ አካሄድ ወደ መጅሊስ ሲገባ ተቋሙን ሽባ በማድረግ በሕዝበ ሙስሊሙና በተቋሙ መካከል ክፍተት ይፈጥራል። በሂደትም ሁሉንም ወገን ለአላስፈላጊ መሰዋትነት ይዳርጋል። «ዑለሞች እንደ አፍሪካ መሪዎች ስልጣን ናፋቂ ናቸው» የሚል እይታ በሕብረተሰቡ ዘንድ ከተፈጠረ እይታው በመጅሊስ ስልጣን ላይ ያሉትን ብቻ ሳይሆን ከመጅሊስ ዉጭ ያሉትን ዓሊሞችን ጭምር ክብርና ተቀባይነትን በመሸርሸር ሚናቸውን በቀላሉ እንዳይወጡ እንቅፋት ይሆናል።

ከላይ በጠቀስናቸው አሰራሮች የተነሳ በተቋሙ ዉስጥ ግልጸኝነትን ያጠፋል። ጤናማ ተቋማዊ ሪፎርም ይሞታል። ተቋሙ በግለሰቦች ፍላጎትና አካሄድ ሥር ይወድቃል።በተቋሙ ዉስጥ የራሳቸውን ደረሶች፥ተማሪዎችንና የነርሱን ፍጹማዊ ኃይል እውቅና የሚሰጡ ሰዎች ኔትወርክ ይፈጠራል። በሂደትም የነርሱ ኔትወርክ የሆነና ያልሆነ በሚል ለሁለት ጎራ ተከፍሎ የውስጥ ሽኩቻ እንዲጠመድ ያደርጋል።

ቀጥሎም ተቀናቃኞች እየተገፉ ተቋሙ በታማኞቻቸው እንዲሞላ በማደረግ መጅሊስ የመከነ ይሆናል። ተቋሙ በሕግና መመሪያ፥ በፖሊሲና ፕሮሲጀር የማይመራ በማድረግ የግለሰቦች እስረኛ ያደርገዋል።

ዉስጣዊ ሽኩቻ በመፍጠር ተቋሙን ለሕዝቡ አንዳች የማይፈይድ ያደርገዋል። በዝምታ መመልከት የለብንም በሚል ተቋማዊ ለውጥ እንዲኖር ድምጻቸውን የሚያሰሙትንና በግልጽ የሚቃወሟቸውን አካላትን ሊያጋልጡን ነው በሚል የተለያዩ ስያሜ እየሰጡ የመፈረጅና የመግፋት ሁኔታ ይፈጥራል።

ቢሮከራሲውን የማያውቁ ዓሊሞች ወደ መሪነት ሲመጡ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

ቢሮክራሲያዊ ልምድ የሌላቸው ዓሊሞች ወደ የተቋም መሪነት ሲመጡ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፦

1.
Подробнее
13.57 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Mon, 04 Aug 2025 21:09:05 +0300
በሸኽነት ያገኙትን ቁጥጥር የሌለበት ኃይል ወደ መጅሊስ የዉሳኔ አሰጣጥ ሂደት ለማምጣትና በደረሳዎቻቸው ዘንድ ያላቸውን ታዛኝነትንና ተሰሚነት ከመጅሊስ አባላት የመጠበቅ አዝማሚያ ዉስጥ ይገባሉ።

2. በነርሱ ደረጃ ያሉትን የሥራ አስፈጻሚዎችን እኩል መብት እንዳላቸው ባልደረቦች ሳይሆን በፍጹም ታዛኝነት ሊያድሩ የሚገባቸው አካላት አድርገው ይመለከቷቸዋል።

3. በውሳኔ አሰጣጥና በተቋማዊ አሰራር ውስጥ ቁልፍ የሆነውን የማማከር ሂደትን በመተው ልክ እንደ ፈትዋ ዓይነት ትዕዛዛትን ወደ መስጠት ሊያመሩ ይችላሉ።ተቃውሞ ሲገጥማቸውም ለአድራጎታቸው የተቋሙን ደንቦችንና መመሪያዎችን ከመጥቀስ ይልቅ ለድርጊታቸው ማፅኛ የሚመስሉ ሃይማኖታዊ ማስረጃዎች በማምጣት በማሸማቀቅ ትችትን ሊከላለኩ ይችላሉ።

4. በተቋም ውሰጥ ኃይል የሚተገበረው ቁጥጥር ባለበት (Check and Balance) ሰርዓት ውሰጥ በመተዳደሪያ ደንብ፣ በመመሪያና በአሰራር ማንዋሎች ተገድቦ በመሆኑ ከለመዱት የኃይል አተገባበር አንፃር ለተቋማዊ አሰራር እንግዳ የሚሆኑበትና ለመልመድ የሚቸገሩበት እድሎች ይኖራሉ፡፡

5. በሸኽና በተማሪው መካከል ባለው ግንኙነት የእቅድና የስራ ሪፖርቶች ግዴታዊ ባለመሆናቸው ለተቋም አሰራር ቁልፍ ለሆኑት የእቅድና የስራ ሪፖርቶች እንዲሁም ተዋረዳዊና የጎንዬሽ ግምገማዎችን አላሰፈላጊ አድርገው ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡

ለ) የመስጂድ ኢማም የኃይል ልምምድና ገደብ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

የመስጂድ ኢማሞች ስልጣንና ኃይል የሚመነጨው በመስጂዱ ዉስጥ ካላቸው ሚና ነው። ኢማሞች ሰላትን ያሰግዳሉ። ዳዕዋና ኹጥባ ያደርጋሉ። ኪታብ ያቀራሉ። በመስጂዳቸው ዉስጥ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን የመተርጉም፥ እንዲሁም ዳዕዋ ማድረግ ያለበትንና የሌለበትን (በኮሚቴው ዉሳኔም ሆነ በራሳቸው) የመበየን ሚና አላቸው። ከዚህ በተጨማሪም ከመስጂዱ ጀመዓ አባላት ጋር በየእለቱ ከሚያደርጉት ግንኙነት፥ መስተጋብር፥ ቅርርብና መልካም ምግባራቸው የተነሳ ከግርማ ሞገስ የሚመነጭ ኃይልን (Power Originated from Charisma) በተጨማሪነት ይጎናጸፋሉ።

ዓሊሞች የመስጂድ ኢማም በመሆን ገደብ አልባ ኃይልን(absolute power) በመስጂዱ ዉስጥ ለመተግባር ይቸገራሉ። ምክንያቱም ሕብረተሰቡ በዚያ መስጂድ ለመስገድ፥ የነርሱን ዳዕዋና ቂርኣትን ለመከታተል የሚያስገድደው ነገር የለም።

በተጨማሪም የነርሱ የኢማምነት አፈጻጸም በመጅሊስም ሆነ በመስጊዱ ኮሚቴ ክትትል ስር ስላለ ስልጣናቸውን ያለገደብ የመተግበር እድላቸው የመነመነ ነው። በተጨማሪም በምክትል ወይም በሌላ ኢማም የመተካት እድላቸው ሰፊ ስለሆነ ሚናቸውን በጥንቃቄ እንዲወጡ ይጠበቅባቸዋል። የኃይላቸውን መሠረት ለማሳደግ ከፈለጉ ከመስጂዱ ጀመዓዎች፥ ከመስጂዱ አስተዳደርና ከመጅሊስ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ከመፍጠር ባሻገር በመስጂዱ ዉስጥ በሚሰጡት ዲናዊ አገልግሎት ልቀው መገኘት ግድ ይላቸዋል።

የመስጂድ ኢማም የሆነ ዓሊም ወደ መጅሊስ መሪነት ሲመጣ የሚከተሉት ሊከሰቱ ይችላሉ። ይችላሉ ነው እንጂ እርግጠኛ በመሆን አይደለም።ለማንኛውም እነሆ፦

1. መጅሊስን የኹጥባ ማድረጊያ ሚንበሩ ቅጥያ አድርጎ የማየት አዝማሚያን በመፍጠር ልምድ በሌላቸው ጉዳይ ጭምር ምክርና ትምህርት የመስጠት ሁኔታን ይፈጥራል።

2. በነርሱ ላይ የሚቀርብን ትችትና ወቀሳን ዓሊምን ወይንም ሃይማኖቱን እንዳለማክበር ወደ መቁጠር ያመራሉ።

3. የመጅሊስን አስተዳደር ማህበረሰባዊ መድረክ አድርጎ በማየት ችግሮችን በዳዕዋ ብቻ ለመፍታት ሊሞክሩ ይችላሉ።

4. በራሳቸው መስጂድ ለረጅም ጊዜ ኢማም ሆነው ያገለገሉ ኢማሞች ወደ መጅሊስ መሪነት ሲመጡ መጅሊስን የነርሱ የዳዕዋ ማዐከልና ቀጣይ ቅርንጫፍ የማድረግ አዝማሚያ ሊኖር ይችላል።

5. የመስጂድ ኢማም የኢማምነት የጊዜ ገደብ (ወሰን) ስለሌለው በመጅሊስም የሚኖራቸው ሹመት ያለገደብ መቆየት ከመፈለግ ምርጫ እንዳይኖር የማድረግ ፍላጎታቸውን ሊያንጸባርቁ ይችላሉ።

ሐ) ዓሊም የዩኒቨርሲቲ መምህር ሲሆን
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ዓሊም የዩኒቨርሲቲ መምህር ሲሆን የኃይል ምንጩን የሚያገኘው የተመደበበት ዘርፍ ላይ ብቁ መምህር ከመሆን፥ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ካለው የእውቀት ጥልቀት፥ እንዲያስተምር የሚጠበቅበትን በአግባቡ ከማስተማር፥ ካለው መልካም ስነምግባር፥ ከተማሪዎቹና ከአስተዳደሮች ጋር ካለው መልካም ግንኙነት ነው።

እነዚህ ሁሉ የተደማጭነት (የኃይል) መሠረቶቹ የተነሳ ተቀባይነቱ ከፍ ወይም ዝቅ ሊል ይችላል። በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የዩኒቨርሲቲ መምህር ገደብና ቁጥጥር የሌለበት ፍጹም ኃይል ሊለማመድ አይችልም። ላድርግ ብሎ ቢሞክር እንኳ ከተማሪዎች፥ ከሌሎች መምህራንና ከአስተዳደሮች ቅሬታ ይቀርብበታል። በዚህ የተነሳም የተቋሙን ሕግና መመሪያ ተከትሎ የመምህርነቱን ሚና በሥርዓት እንዲወጣ ይገደዳል። ካልሆነ እርምጃ ሊወሰድበት ብሎም ሊባረር ይችላል። ይህን በመረዳት ሕግና ስርዓት አክብሮ መገኘት ግዴታው ይሆናል።

የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ዓሊም ወደ መጅሊስ ሲመጣ ከዚህ በፊት የማስተዳደር ልምድና ተሞክሮ ከሌለው አንድም ልክ በዩነቨርሲቲ ቆይታው የራሱ የትምህርት ዘርፍ ብቻ ላይ አተኩሮ ሚናውን ይወጣ እንደነበረው በመጅሊስም ሌሎችን ከፍሎችንና ሠራተኞችን አስተባበሮ ለመምራት ይቸገር ይሆናል።

የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ዓሊም ወደ መጅሊስ መሪነት ሲመጣ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፦

1. የዩኒቨርሲቲ መምህርነትና የመጅሊስ አስተዳደርነት ይጋጩበታል። በዩኒቨርሲቲው በነበረው ቆይታ በዘርፉ ላይ ለተማሪዎች እውቀትን መስጠት ስለነበር ሚናው ወደ መጅሊስ ሲመጣ በፖሊሲ፥ በማስፈጸም፥ ተቋማዊ ቅንጅት ላይ ልምድና ተሞክሮ ስለሌለው የርሱ ትኩረት ሀሳቦችን በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ለተማሪዎች ማቀበል ላይ እንጂ ስርዓት በመገንባትና ስርዓትን በመቆጣጠር ላይ ባለመሆኑ በሥራው ክፍተት ይንጸባረቅበታል።

2. ዓሊሙን ልማዱ ስለሚጎትተው ከመጅሊስ የሥራ ባልደረቦቹና ሠራተኞች መካካል የሚኖረው ግንኙነት በተማሪና መምህር መካካል እንዳለው የማየት አዝማሚያ ሊያመራ ይችላል። ነገሮችንም ከመማርና ማስተማር ሁኔታ አንጻር ብቻ ሊያይ ይችላል።ይህም በርሱ የተግባቦት ሂደት ላይ እንቅፋት ሊፈጥርበት ይችላል።

3. በመጅሊስ ዉስጥ እንደ ዩኒቨርሲተው ደረጃው የሚመዘነው ባለው እውቀት ማረጋጋጨ የምስክር ወረቀቱ ሳይሆን በሥራው ላይ ባለው ብቃት፥ አገልግሎትና ዉጤት በመሆኑ በእውቀቱ ብቻ እንዲከበር ወደ መፈለግ ሊያዘነብል ይችላል። ነገሮችን ከእውቀት፥ ከመማርና ማስተማር እይታ ብቻ ወደ ማየት በማዘንብል በተግባራዊ የአመራር ሚዛን አንጻር ስኬታማ ያለመሆን ሁኔታ ይፈጠራል።

4. የዓሊሙን የትምህርት ማስረጃን አጋንኖ በመመልከት ሌሎችም በዚያ እንዲመለከቱ ሊገፋፋና እንዳሰበው ሳይሆን ሲቀር በመከፋት ያለመጣጣም ምንጭ ሊሆን ይችላል። በሥራው ላይ ባለው አፈጻጸም ሲገመገምም ከእኔ ያነሱ ሰዎች እኔን ሊገመግሙኝ አይችሉም የሚል ያለመቀበል አዝማሚያ ሊፈጥር ይችላል። ይህም የተቋማዊ አካሄድን ሊጎዳው ይችላል።

5. ሌሎች የሥራ አስፈጻሚዎች በተግባርና በአገልግሎት ቢበልጡት እንኳ የርሱ መለኪያ እውቀት እየሆነ እነርሱን በእውቀት ከርሱ ያነሱና እውቀት የሌላቸው አድርጎ በማየት የመናናቅ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። የዲናዊ እውቀት ብቃት መመዘኛ በቀጥታ ከአስተዳደርና የማስፈጸም ብቃት ጋር ስለማይያዝ ስኬታማ ላይሆን ይችላል።

6.
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Mon, 04 Aug 2025 21:09:05 +0300
የዑለሞች የኃይል ልምምድና ገደቦች
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
በአሕመዲን ጀበል
💥💥💥💥💥💥

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) እና የኡለማእ ምክር ቤት (ጉባኤ ) የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው አስተዳደራዊ ባህሪይ ስላለው መጅሊስ እንጂ ፍፁም በኡለሞች ብቻ መመራት ስላለበት የኡለማእ ምክር ቤት አይደለም።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) ዘመኑን የዋጀ ጠንካራ ተቋም እንዲሆን አንዱ ሥርዓት መያዝ የሚገባው የመሪዎች ስልጣንና ኃይል ልምምድ ሁኔታ ነው። በተለይ በዚህ ወቅት የዑለሞች የኃይል ምንጭ ግንዛቤና ተግባራዊ ልምምድ በሚገባ መረዳትና መነጋገር የሚያሻ ጉዳይ ነው።

በተለይ በዚህ ምርጫ በመጅሊስም ሆነ በዑለማ ምክር ቤት ያሉ አመራሮች «መጅሊስን መምራት ያለብን እኛ ዑለሞቹ ነን» በማለት ለዚያ የሚሆኑ መደላድሎችን እየፈጠሩ ባሉበት ጊዜ ይህን በሚገባ መረዳት እጅግ ጠቃሚ ይሆናል። ይህን ነጥብ ደፍሬ የማነሳው ዑለሞቻችንን ማሳነስ ከመፈለግ ሳይሆን እነርሱን፥ ተቋማችንንና ዲናችንን ሊከሰቱ ከሚችሉ አደጋዎች ለመጠበቅ ያግዛል ከሚል መነሻ ነው።

የማነሳውም አጀንዳና ነጥቦች በምናብ ዉስጥ የፈጠርኳቸው ሳይሆኑ በመጅሊስና ኢስላማዊ ድርጅቶች ላይ አመራር የሆኑና የነበሩ ዑለሞችን ሁኔታ በአንክሮ ከመገምገማ የመነጨ ነው። ኒያዬም የተባለው እንዲሆን ሳይሆን እንዳይሆን ቀድሞ መከላከል ነው። ሌላው በግልጽ ማሳሰብ የምሻው ነጥብ ሁሉም ዑለማ በዚህ ጽሑፍ ዉስጥ የሚነሳው ጉዳይ ሰለባ ናቸው ወይም ይሆናል እያልኩ አይደለም። ፈጽሞ!

ሳይጨርሱ ከሚያቋርጡት ነህ? አንቺስ?
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

በመጅሊስ ጉዳይ ላይ በተከታታይ ጽሑፎችን እያስነበብኩ ያለሁት ሳንፈራራ የመወያያ አጀንዳ በመፍጠርና በግልጽ በመወያየት የተሻለ ተቋም እንዲኖረን ለማገዝ ነው። በወረቀት ላይ 3-5 ገጽ ጽሑፍን ስለጥፍ እኔ ጸሐፊው እያለሁ ብዙዎች ለማንበብ ሲደክሙ አያለሁ። ታዲያ 5 ገጽ ለማንበብ ወኔ የሌለውና ቶሎ የሚሰለች ሰው እንዴት የተሻለ ተቋም ስለ መመሥረት ሚና ሊኖረው ይችላል? በተለይ ይህ ጽሑፍ ርዕስ አንብበው አስተያየት ለሚሰጡ ወይም ጀምረው ለሚያቋርጡ ወገኖች አይደለም! ለመሆኑ አንተ ጀምረው ሳይጨርሱ ከሚያቋርጡት ነህ? አንቺስ? ለምንኛውም የዛሬው ሀሳብ እጅግ ወሳኝና በግልጽ መነጋገር የሚሻ ጉዳይ በመሆኑ ሳይጨርሱ እንዳያቋርጡ እየጠየኩ መልካም ንባብ እንዲሆንልዎ እጋብዛለሁ!

የዑለሞች የኃይል ምንጭ ከየት ነው?
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

ጉዳዩን ለመረዳት እንዲቀለን የኃይል ጽንሰ ሀሳብን ጥቂት እናፍታታው። ኃይል (Power) ማለት በሌሎች አስተሳሰብ ፣ድርጊት፣ እምነትና ፣ ባህሪ ላይ ተጽዕኖ በማሳደር እኛ እንደ ምንፈልገው እንዲሆኑ ወይም የምንፈልገውን እንዲያደርጉ የማድረግ ወይም የመቆጣጠር አቅም ነው፡፡ በዚህ ረገድ የዑለሞች የተደማጭነታቸውና የተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ኃይል ምንጭ ከየት ነው?

ይህን መረዳት በመጅሊስ መሪነት የተቀመጠ ዓሊም በሕግ ማዕቀፍ ከተሰጣቸው ስልጣንና ደረጃ በላይ በመያዝ ስህተት እየፈጸሙ እንኳ ራሳቸውን ከተጠያቂነት፥ በስርዓቱ ከመተቸትና እርምት እንዲያደርጉ ከሚጠየቁበት አሰራር አጥር ዉጭ እንዳያስቀምጡ እንዲሁም ሌሎችም እነርሱ የማይጠየቁ፥ እነርሱን መጠየቅና መተቸት ዲኑን መገዳደር አድርገው እንዳይመለከቷቸው ለማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው።

የዑለሞች የኃይል ምንጮች (sources of Power) ምንድናቸው? ዑለሞች ሌላ ስልጣንና ካባ (ማዕረግ) ባልደረቡበት ጊዜ የኃይል ምንጫቸው በሃይማኖቱ ረገድ ካላቸው እውቀት፥ «ዑለሞች የነቢያት ወራሽ ናቸው» በሚለው አሰተምህሮ በማህበረሰቡ ዉስጥ በተሰጣቸው ደረጃ (Power originated from Status) እና እንደ የሃይማኖት አስተማሪነት ከሚኖራቸው ግርማ ሞገስ የሚመነጩ ናቸው።

የመጅሊስ ወይም የሌላ ተቋም መሪ ሲሆኑ ደግሞ በዚያ ተቋም ዉስጥ ለመሪው በሕግ(በደንቡ) ከተሰጠው የተለካ ስልጣን የሚመነጭ ኃይል (Power originated from position) ይኖራቸዋል ማለት ነው።

ዑለሞች እንደ መጅሊስ ባሉ ተቋሞች ላይ መሪ ሲሆኑ ቀደም ሲል በሃይማኖታዊ እውቀት፥ ግርማ ሞገስና ማህበረሰባዊ የቅቡልነት ደረጃ ባገኙዋቸው ኃይሎች የተነሳ በተቋሙ ዉስጥ በመተዳደሪያ ደንቡ ከተሰጣቸው የተለካ ስልጣን ገደብ በላይ አልፈው ሲሄዱ እንዴት ማረም እንደሚገባ አለማወቅ ይሰተዋላል፡፡ዑለሞችም ከተጠያቂነት ዉጭ እንዳልሆኑ ባለመረዳት በዝምታ መመልከት የመጅሊስን አቅም እያዳከሙና ወደፊትም ሊያዳክሙ ከሚችሉ አንኳር ነጥቦች መካከል ናቸው።

በዚህ ረገድ መጅሊስ የተሻለ ቁመና እንዲኖረው እየጻፍኳቸው ካሉ ጽሁፎች ጋር ተያይዞ ለመጅሊስ ቅርብ የሆኑት ጭምር «የምታነሳቸው ሀሳቦች ትክክል ናቸው። ነገር ግን እኛ ብንናገር ዑለሞችን መተቸት ይሆናል ብለን የፈራናቸውን ነጥቦች ነው አንተ ያነሳኸው።» የሚሉ መልዕክቶች ሰለ ሚደርሱኝ ይህን ጉዳይ አንስቶ መወያየቱ ጠቃሚነቱ ታየኝ። ምክንያቱም በየትኛው ሥፍራና ደረጃ ኃላፊነት ላይ የተቀመጠ አካል በዙሪያው ባሉት ሰዎች ፍራቻም እና ዝምታ የተነሳ ከሕግ በላይ፥ የማይጠየቁ፥ ያሻቸውን የማድረግ ስልጣን ያላቸው፥ ሁሌም ትክክል እንደሆኑ እንዲሰማቸው በማድረግ ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን እንዲጎዱ ሊያደርጋቸው ይችላልና።

ከዚህ በማስከተል ዑለሞች ደረሶችን የሚያስተምር ሼኽ፥ የመስጂድ ኢማም፥ የዩኒቨርሲቲ መምህር፥ የሸሪዓ ፍ/ቤት ዳኛ እና የመጅሊስ መሪ ሲሆኑ የሚኖራቸውን የኃይል ልምምድን ሁኔታን እንዳስሳለን።

ሀ) ዑለማ ደረሳ የሚያስተምር ሼኽ ሲሆን
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦

የነርሱ ኃይል የሚመነጨው በተማሪ(ደረሶች) አዕምሮ ላይ ከሚፈጥሩት ተጽዕኖ ነው። በተለይ ለተማሪዎቻቸው ስለቁርኣን፥ ሐዲስና ኢስላማዊ ስነምግባር ትምህርት የመጀመሪያው መምህርና ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን በመቻላቸው ነው። በዚህም የስነምግባር፥ የስነልቦናና ዓለምንና ዲንን በመረዳት ሂደት ተማሪዎቻቸው ላይ ተጽዕኖ ያሳርፋሉ።

በገጠር የሚያቀሩ ዓሊም በደረሶቻቸው ላይ ፍጹም ስልጣን፥ ተሰሚነትና ወሳኝነት ሚና አላቸው። የስልጣን ምንጫቸው ዓሊም መሆናቸው (Expert Power) ነው። ደረሶችም ያለምንም ገደብ የመታዘዝና ለነርሱ ትዕዛዛት ማደር ይጠበቅባቸዋል ። ዓሊሞቹ በፈለጉት ጊዜ፥ በፈለጉበት መንገድና ሁኔታ የመወሰን የማይጠየቅ ስልጣን አላቸው። የነርሱ ቃልና የሚያስተምሩት ትምህርት ድንበርና ወሰን ስለሌለው ቃላቸው ራሱ እንደመለኮታዊ ትዕዛዝ ይደመጣል።

እነርሱን መቃወም አላህንና ነቢዩን(ሰዐወ) እንደመቃወም ይፈራል። ትዕዛዛቸውን አለመቀበል ዑለማን አንደማዋረድ ተደርጎም ይታያል። በኢልም ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችም ቢሆኑ የደረሳ እና አሊምን ተዋረዳዊ ግንኙነትን መሰረት ያደረገና በመተናነስ የተሞላ ነው፡፡

በተጨማሪም ዓሊሞቹን ከማክበር፥ ከመውደድና ከመታዘዝ የተነሳ ተማሪዎቻቸውና የአከባቢው ማህበረሰብ የነርሱን እርሻ ያርስላቸዋል፤ ዉሃ ይቀዳላቸዋል፤ አቅም በፈቀደ መጠን የነርሱን ፍላጎት ለመሟላት ይተጋል። አክብሮትን ለመግለጽ ጉልበታቸውን ይስማል፤ ለነርሱ ይተናነሳል። ይህ ሁኔታ ዓሊሞቹ የአካቢያቸው የትኩረት ማዕክል ያደርጋቸዋል። ከፍ ሲልም የማህበረሰብ መንፈሳዊ መሪ ሚናም ይይዛሉ፡፡

ደረሳን የሚያቀሩ የነበሩ ዓሊሞች ወደ መጅሊስ ሲመጡ የሚከተሉት ይሆናሉ፦

1.
Подробнее
11.42 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Sat, 02 Aug 2025 22:20:06 +0300
የዑለማ ምክር ቤት ዛሬ ለዑለማ ምክር ቤት ይሁን ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች አመራር ምርጫ በግልጽ ያልለየ የተመራጭ መስፈርት አውጥቷል።

ለማንኛውም ይህን መስፈርት በማውጣት ዉስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃችሁ ያለበት ሁሉ መስፈርቱን ለራሳችሁ ያወጣችሁ ስለሚያስመስልባችሁ በዚህ ምርጫ በየትኛውም እርከንና ደረጃ በተመራጭነት ባለመሳተፍ ለሕዝቡ ጥቅም እንጂ ለራሳችሁ እንዳልቆማች የማስመስከር ታሪካዊ ሚናችሁን እንድትወጡ በአደራ ጭምር ጥሪ አደርጋለሁ።
Подробнее
17.72 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001376441762 Mon, 28 Jul 2025 09:55:24 +0300
«ሐጅ ሙሐመድ ሳኒን ማን ይተካቸው? » ትግልና ምርጫው

@ahmedin99
Подробнее
26.71 k
]]>