Лента постов канала Ministry of Education Ethiopia (@ethio_moe) https://t.me/ethio_moe This is Ministry of Education's Official Telegram Channel. For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe ru https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Sat, 23 Aug 2025 11:56:26 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Fri, 22 Aug 2025 17:15:59 +0300
በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገራዊ ምክክር መድረክ የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት ውጤት አመላካች መለኪያዎች ላይ የጋራ ስምምነት በመፈራረም ተጠናቋል።

----------------------------------------------

(ነሐሴ 16/2017 ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ሲያካሄድ የነበረው የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገራዊ የምክክር ከሁሉም የክልልና ከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት ውጤት አመላካቾችን የስምምነት ሰነድ በመፈራረም አጠናቋል።

መድረኩ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የተመከረበትና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከመግባባት የተደረሰበት መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የትምህርት ተሳትፎ፣ ጥራትና ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ረገድ በ2017 የትምህርት ዘመን የተገኙ ስኬቶችን በማስፋትና በማስቀጠል በመጭው አመት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መድረኩ በመምከር አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በዘርፉ የአፈጻጸም ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶች በመሻገር በ2018 የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረትም እንዲሁ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የተመከረበት እንደሆነም ክብርት ሚንስትር ዴኤታዋ አያይዘው ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1UQesBy5es/
Подробнее
12.75 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Fri, 22 Aug 2025 11:30:09 +0300
እንደ ሀገር ፕሮጀክቶች ጀምሮ በፍጥነት ማጠናቀቅ በትምህርት ቤቶችም ባህል እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ።
------------------------------------------

(ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በሲዳማ ክልል ያለውን የትምህርት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚሁ ጊዜ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በትምህርት ቤቶቹ ተገኝተው ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።

በተለይም በወንዶ ገነት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው የመማሪያ ህንፃ በ8 ወር ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን ተመልክተዋል።

ይህም እንደ ሀገር ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የሚለው ባህል እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ያሉ ሲሆን ሌሎች ክልሎችም ከዚህ ልምድ ሊወስዱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የሲዳማ ተሃድሶ በሚል የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተሠሩ ሥራዎችን አብራርተዋል።

በተለይም እንደ ክልል ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት ተመሳሳይ ስታንዳርድ ያላቸው 78 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአዲስ መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።

የጉብኝቱ ዓላማም በክልሎች መካከል ልምድ መለዋወጥ መሆኑም ተገልጿል።
Подробнее
12.79 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Fri, 22 Aug 2025 09:40:38 +0300
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በውጭ ሀገር ካሉ አቻ ተቋማት ጋር የሚያደርጓቸውን ስምምነቶች አፈጻጸም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ፤
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ አስተባባሪነት ኢንሃ ከተሰኘ የኮሪያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

==================================

(ነሃሴ 16/2017 ዓ.ም) በስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትብብር ስምምነቱ በአቬሽን ሳይንስ፣ ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ እና ስማርት ሲቲ ትምህርት ፕሮግራሞችን በማጠናከር እንደሆነም ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን የአቬሽን ሳይንስ እና ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለማጠናከር ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመ ሲሆን ኢንሃ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ፕሮፌሰር ሂቸንግ ኮህ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ደግሞ አቶ ኤፍሬም ዋቅጅራ ተፈራርመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን የስማርት ሲቲ ትምህርት ፕሮግራምን ለማጠናከር ከአዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመ ሲሆን አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን በመወከል የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ከማል ኢብራሂም ተፈራርመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1G7Sv7ydtY/
Подробнее
13.07 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Thu, 21 Aug 2025 13:50:33 +0300
Подробнее
15.63 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Thu, 21 Aug 2025 11:40:09 +0300
Подробнее
17.69 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Thu, 21 Aug 2025 08:38:28 +0300
Подробнее
24.74 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 19 Aug 2025 11:49:11 +0300
ቻይና በኢትዬጵያ የሠው ሀብት ልማት ውስጥ ያላትን አበርክቶ ለማጠናከር እንደሚሠራ ተጠቆመ።

(ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ አመራሮች በቻይና የሻንሺ ግዛት ውጪ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኋንግ ዬንግ የተመራ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ጊዜ ቻይና በኢትዬጵያ የሠው ሀብት ልማት ውስጥ ያላትን አበርክቶ ለማጠናከር እንደሚሠራ በቻይና የሻንሺ ግዛት ውጪ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኋንግ ዬንግ ገልጸዋል።

በምክትል ቢሮ ሀላፊው የተመራው የግዛቲቲ ልዑክ ከትምህርት ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በሠው ሀብት ልማት ዙርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሠው ሀይል ግንባታ ትብብር ለማሳደግ ፍላጎቶ ያለ መሆኑን በሁለቱ ወገኖች ተገልጿል።

በቀጣይ በሚደረግ ግንኙነት በተማሪዎችና መምህራን ልውውጥ፣የትምህርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትና በመደገፍ እንዲሁም ነጻ የትምህርትና ስልጠና እድሎችን በማመቻቸት ረገድ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዬች ላይ ውይይት ተደርጎል።

የሻንሺ ግዛት አስተዳዳሪ በቅርቡ በኢትዬጵያ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ወቅት ቀጣይ በዉይይቱ እንደሚደረጉም ገልጿል።
Подробнее
19.25 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 19 Aug 2025 11:29:31 +0300
የተማሪዎችን የንባብ ክህሎት ለማዳበር በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
==================
(ነሃሴ 13/2017 ዓ,ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከወርልድ ቪዥን ኢትዮኦጵያ ጋር በመተባበር የመጀመሪያውን ብሄራዊ የንባብ ጥምረት ጉባኤን አካሄዷል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ ጉባኤውን በከፈቱበት ወቅት የንባብ ክህሎት የመማር የመጀመሪያውና መሠረታዊ ክህሎት እንደመሆኑ መጠን የተማሪዎችን የንባብ ክህሎት እንዲዳብር በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ከታችኛው የትምህርት ክፍሎች ጀምረው ሊኖራቸው የሚገባቸውን የንባብ ክህሎት እያዳበሩ እንዲመጡ ወላጆችን ጨምሮ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዶ/ር ሙሉቀን አክለውም ጥምረቱ ውጤታማ ሥራ እንዲሰራና ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን የጥምረቱ አባል ድርጅቶችና በተለይ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ለበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነው በቀጣይም የጀመሩዋቸውን ሥራዎች አጠናክረው እንዲሚቀጥሉበት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የትምህርት ፕሮግራም ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ታደሰ በበኩላቸው ብሄራዊ የንባብ ጥምረት ከተቋቋመ አንድ አመት መሆኑን ጠቅሰው ከሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ጎን ለጎን በአሁን ወቅት በሀገር ደረጃ የተማሪዎች የንባብ ክህሎት ያለበትን ሁኔታ ለመገምገምና ክህሎቱን በተሻለ መንገድ ለማዳበር ሊወሰዱ ስለሚገቡ መትሄዎችና እርምጃዎች ላይ ያተኩሩ ጥናቶችን የማካሄድና የሀገራትን ተሞክሮና ልምድ የመቀመር ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/1FwDtt8TUo/
Подробнее
18.29 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Mon, 18 Aug 2025 09:10:02 +0300
ሁሉንም የአካል ጉዳት እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።
የአካቶ ትምህርት አተገባበር ነባራዊ ሁኔታና ውስንነቶች ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ተካሄደ።
------------------------------------------
(ነሐሴ 12/2017ዓ.ም) በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፉት የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት መሻሻል መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዩሐንስ ወጋሶ የአካል ጉዳትና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች ወደ ትምህርት ቤት በማምጣትና ውጤታማ በማድረግ ረገድ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም በሚጠበቀው ልክ አለመሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ሁሉም የአካል ጉዳት እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣትና በትምህርት ቤት ለማቆየት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀው በአውደ ጥናቱ የቀረቡ ክፍተቶችንም መፍታት እንደሚገባ አመላክተዋል።

አካታችና ጥራት ያለው የመምህራን ስልጠና" (Teacher Education for Inclusion and Quality (TEFIQ) ፕሮጀክት በኢትዮጵያ አስተባባሪ የሆኑት ማሪያ ማቲር በበኩላቸው መሠል አውደ ጥናቶች በአተገባበር ሂደት ውስጥ የጋራ መግባባትና ትብብር ለመፍጠር የሚያግዙ በመሆናቸው ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Cc1TAMes9/
Подробнее
23.34 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Thu, 14 Aug 2025 08:49:02 +0300
ማሳሰቢያ
በ2017 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍልን አጠናቃችሁ ወደ 9ኛ ክፍል የተዛወራችሁና መስፈርቱን በማሟላት ትምህርት ሚኒስቴር ባስገነባቸው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች በ https://sbs.moe.gov.et ላይ በመግባት ማመልከት የምትችሉ ሲሆን፣ በ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ በክልላችሁ ያልተጀመረባችሁ አካባቢዎች የ6ኛ ክፍል ውጤታችሁን ከፊትም ከጀርባም ስካን አድርጋችሁ እንዲሁም ስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ያልደረሰላችሁ ተማሪዎች ደግሞ የኦን ላይን ውጤታችሁን ስካን አድርጋችሁ ማያያዝ የመትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
በእነዚህ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተቀጥራችሁ ለማስተማር ፍላጎቱ ያላችሁ መምህራን ደግሞ በ https://sbs.moe.gov.et/carrier/teacher ላይ በመግባት ማመለከት የምትችሉ መሆኑን በድጋሚ ለመግለጽ እንወዳለን ።
ትምህርት ሚኒስቴር
Подробнее
51.43 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Wed, 13 Aug 2025 08:50:02 +0300
Подробнее
49.39 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Fri, 08 Aug 2025 17:32:29 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Fri, 08 Aug 2025 12:27:43 +0300
Подробнее
29.94 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Wed, 06 Aug 2025 17:28:12 +0300
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሁሉም ክልሎች የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን እንደ አንድ የሀገር ልጆች የሚቀበልበት የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮግራም ለጎንደር ብቻ ሳይሆን ለሀገሩም ምሳሌ የሚሆን መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ፤

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ እና ማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷ።

-------------------------------------------------------

(ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም) በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህ ክብረ በዓል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለጎንደርና ለአካባቢው ህዝብ ያለውን ፋይዳ እንዲሁም ህዝቡ ለተቋሙ ያለውን አክብሮት ያየንበት ነው ብለዋል።

በዓሉ ከዩኒቨርሲቲውና ከሆስፒታሉ ምስረታ በላይ በተለይ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የጎንደርን ህዝብ ጥልቅ የሆነ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያንፀባረቀበትም እንደነበር አንስተዋል።

በተለይም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሁሉም ክልሎች የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን እንደ አንድ የሀገር ልጆች የሚቀበልበት “የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮግራም” ለጎንደር ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

ዩኒቨርስቲዎች አንዱ እንዲያደርጉ የምንፈልገው የመንደር ሳይሆኑ የሀገር ሀብት እንዲሆኑ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፤

በተለይ አሁን ዋና ሪፎርም ዩኒቨርሲቲዎች ራሳቸውን እንዲችሉ በነፃነት የሚሰሩ፣ በነፃነት የሚያስቡ እውነትንና እውቀትን የሚፈልጉ ሰዎች የተሰባሰቡባቸው ሰላማዊ ቦታ እንዲሆኑ መሆኑን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1D3gaudqWn/
Подробнее
27.56 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Wed, 06 Aug 2025 17:10:30 +0300
Подробнее
25.16 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 05 Aug 2025 19:25:48 +0300
Подробнее
30.44 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 05 Aug 2025 17:52:12 +0300
የኢትዮ-ኮሪያ የትምህርት ዘርፍ የትብብር ግንኙነት ተጠናከሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፤

================================

(ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም) በኮሪያ የግዮንግሰንግቡክ ትምህርት ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ኪም ዳል ያንግ የተመራ ልዑካን ቡድን በትምህርት ሚኒስቴር በመገኘት ከትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ከዶ/ር ዮሃንስ ወጋሶ ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱም ዶ/ር ዮሃንስ ኮሪያ ከሁለት አመታት ወዲህ ለሀገራችን “ክሊክ” KLIC (Korean Digital-Learning Improvement Cooperation) በተሰኘ የትብብር ፕሮግራም የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሊጂ መሰረተ-ልማት ግብዓቶች ድጋፍና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ድጋፍ እየሰጠች መቆየቷን ጠቅሰው ፕሮግራሙ “በፓይለት” ደረጃ ሲታይ ውጤታማ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የልኡካን ቡድኑ መሪ ሚስ ኪም ዳል ያንግ ቡድናቸው ከሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለመምህራን የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ለማስጀመር እና እስካሁን የተደረጉ ድጋፎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ መሆኑን ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1AmuGS37mS/
Подробнее
21.38 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 05 Aug 2025 17:03:07 +0300
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ሥራ መስራት እንዳለባቸው የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ገለፁ።

----------------------------------------------------
(ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ መካሄዱን ቀጥሏል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራትን በማሳደግ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን በርካታ ስራዎች መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በገቡት የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም ውል መሰረት እስካሁን የሰሯቸውን ሥራዎች በቡድን ተከፍለው ሲገመግሙ ውለዋል።
Подробнее
22.82 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 05 Aug 2025 11:39:14 +0300
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና በጥናት የተለዩ ክፍተቶችን በመሙላት አቅም የሚገነባበት መሆኑ ተጠቆመ፤
ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡

-----------------------------------------------

(ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም) የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ የህይወት ዘመን ትምህርት ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር እዮኤል አባተ (ዶ/ር) ስልጠናው መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ይቸገሩበታል ተብሎ በጥናት የተለዩ ክፍተቶችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአገራችን ትምህርትን ከተማሪዎች ሀይወት ጋር አገናኝቶና ተግባር ተኮር አድርጎ በመስጠት ተማሪዎች ትምህርቱን ወደውትና ለህይወታቸውም የሚጠቀሙበትን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ ከማድረግ አንጻር ክፍተት መኖሩን ዶ/ር እዮኤል አመልክተዋል፡፡

ስልጠናው ተማሪዎች እውቀት ወይም ሀሳብ (concept) ወደ መሬት አውርደው ከራሳቸው ህይወት እና ተግባራዊ ሊሆን ከሚችል የማስተማር ስነ ዘዴ ወይም ፍልስፍና ጋር አቆራኝተው መስጠት እንዲችሉ አቅማቸውን የሚገነቡበት መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠናው በትምህርት ስርዓታችን ላይ አለ የሚባለውን ዋና እና መሰረታዊ ችግር ሊፈታ የሚችል የአቅም ማጎልበቻ ፕሮግራም በመሆኑ በአግባቡ መከታተልና ተገቢውን እወቀትና ክህሎት መጨበጥ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ማየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1YBEbroskD/
Подробнее
24.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Mon, 04 Aug 2025 15:01:59 +0300
በአገሪቱ በተመረጡ 30 ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና መሰጠት ጀመረ።
በስልጠናው ከ84 ሺ የሚበልጡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ይሳተፋሉ፡፡

-------------------------------------------

(ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም) ስልጠናውን መስጠት ከጀመሩ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዲን የቆየዓለም ደሴ (ዶ/ር) ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን በጥሩ ሁኔታ ለማሰልጠን የአሰልጣኝ መምህራን ፣ የስልጠና ክፍሎች፣ የተማሪዎች ማደሪያ ፣ የካፍቴሪያ እና የማሰልጠኛ ሞጁልና ምዝገባ አጠናቆ ስልጠና መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው መምህራን በሚያስተምሩበት ትምህርት ዓይነት ፣ በማስተማር ስነ ዘዴ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም በስነ ልቦናዊ ፣ ማህበራዊና የጤና ጉዳዮችን አካቶ የያዘና ሰፊ ክፍተትን የሚሞላ በመሆኑ ሰልጣኞች ተረጋግተው መሰልጠንና የመጡበትን አላማ ሳይረሱ ክፍል ውስጥም ሆነ ከሌሎች ጓደኞቻቸውና ከአሰልጣኝ መምህራን ጋር መነጋገር እና መማር እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤
https://www.facebook.com/share/p/1B56YnWyGA/
Подробнее
23.78 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Mon, 04 Aug 2025 13:58:47 +0300
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ።

የኢትዮጵያ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት "የከፍተኛ ትምህርት ለላቀ ተፅዕኖ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።

-----------------------------------------------------

(ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም) በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ ይህ ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም ተግባራት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምን ያህል ለውጥ ተመዘገበ ተብሎ የሚገመገምበትና የወደፊት አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን ገልፀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወዳዳሪ፣ የበለፀገች፣ ሉዓላዊት፣ ዴሞክራሲያዊት እና ፍትሃዊ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሚናቸው የጎላ መሆኑንም አንስተዋል።

በዚህም "የትምህርት ጥራት የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በገቡት የቁልፍ ተግባራት መለኪያ ውል መሠረት ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩና ባልተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ለመመካከር እድል ይፈጥራል ብለዋል።

በተጨማሪም መድረኩ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ልምድ ለመለዋወጥ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1HqM5HKsed/
Подробнее
24.25 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Mon, 04 Aug 2025 09:39:01 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Sun, 03 Aug 2025 16:07:05 +0300
Подробнее
37.53 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Sun, 03 Aug 2025 10:23:39 +0300
Подробнее
39.98 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Sat, 02 Aug 2025 15:42:18 +0300
ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ መምራት እንደሚባ ተመላከተ፤
‎በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ቦርድ የአሰራር ማኑዋልና የአፈጻጸም ግምገማ ዙሪያ ከተቋማቱ የስራ አመራር ቦርድ አመራሮች ጋር ምክክር ተደርጓል ፡፡

-----------------------------------------------------

‎(ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በምክክሩ ወቅት እንደገለጹት ለፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች በውጤታማነት እንዲፈጸሙ በተደራጀና በተቀባጀ አግባብ መምራት እንደሚባ አመላክተዋል፡፡

የዩኒቨርስቲ የስራ አመራር ቦርድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተግባርና ኃላፊነቶቻቸውን ብሎም የሚተገብሯቸውን የሪፎርም ስራዎች በውጤታማነት መፈጸምና ማከናወን እንዲችሉ የስራ አመራር ቦርድ የአሰራር ማኑዋለል መዘጋጀቱን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ተቋማቱ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጡ እንደሚያስችላቸውና ተጨማሪ አቅምና አደረጃጀት የሚፈጥርላቸው መሆኑንም ክቡር አቶ ኮራ አስረድተዋል፡፡


‎የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) በበኩላቸው የስራ አመራር ማኑዋሉም ሆነ የአፈጻጸም ግምገማ መስፈርቶቹ የተፈጻሚነት ወሰን ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ቦርድ የሚያገለግል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/16jKH5oQJs/
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Sat, 02 Aug 2025 12:50:44 +0300
ተማሪዎችም በነጻነት ተምረው ውጤታማ እንዲሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢያቸው ከማንኛውም ጾታዊ ጥቃት ነጻ እንዲሆኑ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።

================================

(ሀምሌ 26/2017 ዓ.ም) ህብረተሰቡና የባለድርሻ አካላት በትምህርት ቤት ውስጥና አካባቢው የሚፈጽሙ ጾታዊ ጥቃቶችን ተረድተው እንዲከላከሉና ምላሽ መስጠት እንዲችሉ የሚረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና ከክሌሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሰቷል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በስልጠና መድረኩ ማስጀማሪያ መርሃ-ግብር ላይ እንደተናገሩት ወላጆች ያለስጋት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩና ተማሪዎችም በነጻነት ተምረው ውጤታማ እንዲሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢያቸው ከማንኛውም ጾታዊ ጥቃት ነጻ እንዲሆኑ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ቤትና አካባቢው ማህበረሰብ ጾታዊ ጥቃቶችን ከነመንስኤዎቻቸውና አይነታቸው ለይተው እንዲከላከሉና ከዚህም አልፈው ሲከሰቱ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ አቅም መፍጠር የሥልጠናው ዋነኛ አላማ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/p/19dN8uosE4/
Подробнее
22.03 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Sat, 02 Aug 2025 12:49:41 +0300
ተማሪዎችም በነጻነት ተምረው ውጤታማ እንዲሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢያቸው ከማንኛውም ጾታዊ ጥቃት ነጻ እንዲሆኑ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።

================================

(ሀምሌ 26/2017 ዓ.ም) ህብረተሰቡና የባለድርሻ አካላት በትምህርት ቤት ውስጥና አካባቢው የሚፈጽሙ ጾታዊ ጥቃቶችን ተረድተው እንዲከላከሉና ምላሽ መስጠት እንዲችሉ የሚረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና ከክሌሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሰቷል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በስልጠና መድረኩ ማስጀማሪያ መርሃ-ግብር ላይ እንደተናገሩት ወላጆች ያለስጋት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩና ተማሪዎችም በነጻነት ተምረው ውጤታማ እንዲሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢያቸው ከማንኛውም ጾታዊ ጥቃት ነጻ እንዲሆኑ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ቤትና አካባቢው ማህበረሰብ ጾታዊ ጥቃቶችን ከነመንስኤዎቻቸውና አይነታቸው ለይተው እንዲከላከሉና ከዚህም አልፈው ሲከሰቱ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ አቅም መፍጠር የሥልጠናው ዋነኛ አላማ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/p/19dN8uosE4/
Подробнее
24.27 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Fri, 01 Aug 2025 17:19:34 +0300
Подробнее
24.29 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Fri, 01 Aug 2025 09:16:56 +0300
Подробнее
24.02 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Thu, 31 Jul 2025 17:20:19 +0300
ተባብረን በመትከል ለልጆቻችን አረንጓዴ ሀገር እናስረክባለን፤ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

------------------------------------------

(ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች 700 ሚሊየን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ የግንፍሌ ወንዝ ዳር ፕሮጀክት አስቀምጠዋል።

በምርሃ ግብሩ ተገኝተው አሻራቸውን ያስቀመጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተባብረን በመትከል ለልጆቻችን አረንጓዴ ሀገር እናስረክባለን ያሉ ሲሆን የጎዳናትን ፕላኔት ጥሩ ስራ ሰርተን ምቹ የሰው ልጆች መኖሪያ ለማድረግ መትጋት አለብን ብለዋል።

የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮች ችግኝ በአንድ ጀንበር የሚለው መርሃ ግብር ተሳታፊ መሆናቸው ደስታ እንደፈጠረባቸው ጠቁመው የሚተከሉት ችግኞች ጸድቀው ጥቅም እንዲሰጡ አስፈላጊው እንክብካቤ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የተተከሉት ችግኞች የአየር ሚዛንን በመጠበቅ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆንም አክለዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የሚተከሉት ችግኞች ለአካባቢውን ውበት እንደሚጨምሩ ገልጸው በዚህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳታፊ መሆናቸው ደስ እንዳሰኛቸው ተናግረዋል።
Подробнее
24.63 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Thu, 31 Jul 2025 17:19:02 +0300
ትምህርት ለሀገር እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ያበረክት ዘንድ የዘርፍ ባለሙያዎች ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ፣ የተቋሙን ተልዕኮ በሚገባ የሚፈጽሙና የሚያስፈጽሙ ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳሰቡ።

============================

(ሀምሌ 24/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በሚኒስቴሩ እና በሀገራችን የ2017 እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም የልማት ዕቅድ እንዲሁም በተቋሙ እየተካሄዱ ባሉ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ትምህርት ለሁለንተናዊ እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ያበረክት ዘንድ የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ፣ዘመናዊና የተቋሙን ተልዕኮ በሚገባ የሚፈጽሙ አርኣያነት ያላቸው ሠራተኞች ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ በቅንነትና በብቃት እንዲወጡ ምቹ የሥራ አካባቢ መኖር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም ለማሳካት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/173hcvtJbe/
Подробнее
22.62 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 29 Jul 2025 17:17:16 +0300
ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ያላትን ልምድ አካፈለች።
---------------------------------------------------
(ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም አተገባበር ያላትን ልምድና የመንግስትን ቁርጠኝነት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቅርበዋል።


የሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ፖሊሲ ፍሬም ዎርክ በማውጣት ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተግባራዊ በማድረግ የአካባቢ ልማትና ግብርናን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን አብራርተዋል።

በዚህ የሀገር በቀል የት/ቤት ምገባ ፕሮግራም መንግስት 6.3 ቢሊየን ብር መመደቡንና የማህበረሰቡ ድጋፍ ደግሞ 9.8 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጸው የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ ደግሞ 1.3 ቢሊየን መሆኑን አብራርተዋል።

ይህም በኢትዮጵያ ለት/ቤት ምገባ 90 በመቶ የሚደርሰው በጀት በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የሚሸፈን መሆኑን ገልጸው ተግባሩ የመንግስትንና የማህበረሰቡን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

የምገባ ፕሮግራሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አድረገው እንዲማሩ ከማድረጉ ባለፈ፤ ጤንነታቸው ተጠብቆ ትምህርታቸው ሳይቋረጥ እንዲማሩ ማድረግ ያስቻለ ተግባር ስለመሆኑም ገልጸዋል።


ክቡር ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከአለም የትምህርት ቤት ምግብ ጥምረት (School Meal Coalition) እና ከአለም የምግብ ፕሮግራም ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
Подробнее
32.69 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001444149166 Tue, 29 Jul 2025 15:59:14 +0300
የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ የበጎ ተግባራት መገለጫ በተለይም መተጋገዝን፣ መደጋገፍን፣ መረዳዳትንና መከባበር የበለጠ ለማላቅ እድል የሚሰጥ ነው፤ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ፤ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በጋምቤላ ክልል ተገኝተው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን አስጀምረዋል።
-----------------------------------------------------
(ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ፣ ተጠሪ ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በጋምቤላ ክልል ተገኝተው አስጀምረዋል።


በክረምት የበጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ በሀገራችን ከለውጡ ወዲህ የሀገርን ገጽታ የቀየሩ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን በተለይም የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቅሰው ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተጋች ባለች ሀገር እርስ በርስ መተጋገዝና መደጋገፍ ይገባናል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/19AsKQLJco/
Подробнее
27.59 k
]]>