Лента постов канала ከፍልስፍና ዓለም ™ (@Philosophy_Thoughts1) https://t.me/Philosophy_Thoughts1 አዋቂ ሰው ማለት ፍላጎቱን የመግታት እውቀቱ ከፍተኛ የሆነ ማለት ነው በሕይወት ዝቅተኛው ደረጃ ራስን በፍላጎት አጥር ውስጥ ማስቀመጥ ነው አብዛኛው የሰው ልጅ በብዙ ፍላጎትና በጥቂት እውቀት የተሞላ ነው ፤ አዋቂነት ግን ብዙ እውቀትና ጥቂት ፍላጎት ብቻ ይበቃታል አርተር ሾፐንሀወር ru https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Tue, 19 Aug 2025 14:42:25 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Tue, 19 Aug 2025 14:40:19 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Mon, 18 Aug 2025 21:43:32 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:48 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 17 Aug 2025 13:46:48 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 16 Aug 2025 19:50:52 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 16 Aug 2025 13:53:11 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Fri, 15 Aug 2025 12:48:34 +0300
I think therefore I'm!
እያሰብኩ ነው አለሁ!

የበፊት ፈላስፋዎች ዋነኛ መከራከርያ የነበረው የፈጠረን አለ ወይ የሚል ነበር፣ ቀጥሎ ደግሞ የህልውነት ፍልስፍና አቀንቃኞች አይ! አይ! መመርመር ያለብን ከእራሳችን ማንነት በመነሳት ነው አሉን! እሺ አልን! የዴካርትን አባባል ተቀብለን ፎከርንበት! የዴካርትን ሀሳብ ከዘመኑ አንጻር ልንረዳው ብንችልም ማሰባችን ብቻውን ግን ለመኖራችን ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም። የማያስቡ ጀለሶቻችንም፣ አብረውን እየኖሩ ነው። 🙂

የሰው ልጅ ከዚህ ቀደም በምናውቀው ትርጉም ስናየው የለም። እኔ የለሁም፣ እናንተም የላችሁም። የሌለ ነገር ድምር ውጤቶች ነን። «የሌሉ» ክዋርክ የሚባሉ ነገሮች ኒውትሮን እና ፕሩቶንን፤ ኤሌክትሮንን ደግሞ ሌፕተን የምንለው «የሌለ ነገር» ተጣምሮ ሰርቶታል።

የለም ስል ክብደት የለውም፣ ቦታ አይዝም፣ አካል የለውም የሚለውን traditional definition እየተጠቀምኩ ነው። [ያው የለም ሲባል የምናስበውን ነገር፣ የየለም ሳይንሳዊ ፍቺ ማለቴ ነው። ]

እና እነዚህ የሌሉ ነገሮች ድምር ሶስቱን መሰረታዊ ፓርቲክሎች መሰረቱ። እነዚህ ቅንጣቶች ደግሞ 99.99 ክፍሉ የሌለ አተም የሚባል ነገር መሰረቱ! እነዚህ አተሞች ደግሞ ተሰበሰቡና ህዋስ የሚባል ነገር ፈጠሩ። [ አተሞች ይሄ ሁሉ ህብር ሲፈጥሩ፣ መሰረቱ ምናምን ሲባል እየተጠጋጉ እንጂ እርስበእርስ እንደማይነካኩ እንዳይረሳ! ] ለማንኛውም ይሄ ህዋስ አብዛኛው ክፍሉ ውሃ ነው። ህዋሶች ደግሞ የሰውነት ክፍሎቻችንን ፈጠሩ [ህዋሶችም ቢሆን በተለመደው የመነካካት መንገድ አይነካኩም] የሰውነት ክፍሎቻችን ደግሞ የምናደርገውን ነገር ያደርጋሉ።

አይምሮዋችን ልክ እንደቲቪ ነው። አራት በአራት የተዘጋበት ጨለማ ክፍል ዓይነት አድርጋችሁ ውሰዱት። ቲቪ መረጃ ለመሰብሰብ ሲግናሎችን፣ ቫይብሬሽኖችን እንደሚጠቀም አይምሮዋችንም መረጃ ለመሰብሰብ ሲግናሎችን፣ ቫይብሬሽኖችን ይጠቀማል። የአይምሮዋችን አንቴናዎች የስሜት ህዋሳቶቻችን( ማየት፣ መስማት መዳሰስ፣ መቅመስ፣ ማሽተት) ናቸው። ቲቪ የቀረበለትን ሲግናል በእራሱ እንደሚተረጉመው ፣ የእራሱ ምስል እንደሚሰጠው ሁሉ አይምሮዋችንም መረጃዎችን ተቀብሎ ያንኑ ያደርጋል። አይምሮዋችን መረጃዎችን እንደወረዱ መመልከት አይችልም፣ በእራሱ መንገድ ነው የሚተረጉመው። እናላችሁ ምን እና አለው😃😃 የላችሁም ግን ኑሩ🤯

መልካም ውሎ🙏
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 14 Aug 2025 20:56:54 +0300
አሁን ወደቤት ስገባ

«ባዳ ባዳ ነው
ሰውነትማ ባዳ ነው»


የሚል ዘፈን ሰማሁ። ባዳ ሲሄድ ይሄዳል ከሚል አግባብ ነው መሰለኝ ቃሉን የተጠቀመው፣ ቆንጆ ዘፈን ነው። እና ከዘፈኑም ከፍልስፍናውም ጋር ጥብቅ ቁርኝት ባይኖረውም ከህይወታችን ጋር የተሳሰረ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! የደም ትስስር\ዝምድና የተለየ ቦታ የምትሰጡት ጉዳይ ነው? በብሄር አይደለም በዝምድና እና በባዳነት መሀል የምታሰምሩት መስመር አለ? ዘመዶቻችሁን በተለየ ታያላችሁ? ዘመዶቻችሁን ዘመዶቻችሁ ስለሆኑ ብቻ ትወዷቸዋላችሁ? ዝምድና ለምታሰምሩት ግንኙነት matter ያደርጋል?...

Just asking!
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 14 Aug 2025 18:08:28 +0300
ኃይለሥላሴ እና ሁለቱ ሉሉዎች በቤተ መንግስት

ጄኔራል ሉሉ እንግሪዳ የሚባሉ የአፋር ተወላጅ ከወፍራሙ ግራዝማች ዑመር ዲንጎ ቀጥሎ የኃይለስላሴ ሾፌር የነበሩት በቤተመንግስት የታወቁና የተከበሩ ሰዉ ነበሩ ። ጃንሆይን በሾፌርነት ሲያገለግሉ ኑረዉ በ1996 ዓ ም ከህይወት መዝገብ ተሰናብተዋል ።

ጃንሆይ በእስር ሲወሰዱ ቤተ መንግስቱ ዉስጥ ቆማ የነበረችዉ የጄኔራል ሉሉ የግል ቮልክስዋገን ቢትልስ መኪና ጃንሆይ እንዲሳፈሩባት ተደርጎ ከሄዱባት በኋላ መኪነዋም ታስራ ለረጅም ዓመት ቆይታ ለቤተሰቡ ተመልሳ እየተገለገሉባት እንደሆነ ተገልጿል ።

ሌላዋ ሉሉ የታወቀችዉ የጃንሆይ ድንክ ዉሻ ነበረች ። ይህች ድንክ ዉሻ አቶ ጀማነህ አላብሰዉ ተማሪ በነበረበት ጊዜ በ1942 ዓ.ም ለጃንሆይ በስጦታ ያበረከቷት ነች ። በተበረከተችበት ጊዜ ጃንሆይ " ስሟ ማነዉ " ብለዉ ቢጠይቁ ግለሰቡ ያልተዘጋጀበት ጉዳይ ስለነበር አፉ ላይ እንደመጣ " ሉሉ ነዉ " ብሎ መለሰላቸዉ ። ከዚህ ወቀት አንስቶ የዉሻዋ ስም ሉሉ ሆኖ ቀረ ።

ይህች ድንክ ዉሻ የተለየችና አቶ ጀማነህ ከየት አምጥቶ እንዳሳደጋት በእርግጥ የሚያዉቅ ሰዉ አልተገኘም ። ይሁንና የነቃችና ብልህ ዉሻ ስለነበረች ለብዙ ጊዜ ሉሉን በዉጭ ሀገር ጉብኝታቸዉ ጭምር ሳያስቀድሙ ንጉሠ ነገሥቱ አይሄዱም ነበር ። ጃንሆይ ሉሉን ሳያስከትሉ የሚሄዱበት ቦታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነበር ። ( አሁን ላይ ቢኖሩ ግን ዘዋት እንደሚሄዱ አልጠራጠርም ) ጃንሆይ አዉስትራሊያን ለመጎብኘት ሲሄዱ የሀገሩ ህግ እንስሳ እንዲገባ ስለማይፈቅድ ሉሉ ልትገባ ባለመቻሏ አንድ የቤተመንግሥት ባለስልጣን ሉሉን ይዞ ወደ ሚቀጥለዉ የጉብኝት ሀገር ደቡብ ኮርያ ሄዶ ጃንሆይ እዚያ ሲደርሱ አስረክቧል ።

ጃንሆይ አዉሮፕላን ከመዉረዳቸዉ በፊት ሉሉ ትወርድና የራሷን ጉብኝት ታደርጋለች ። የስፖርት ዉድድር ለመመልከት ወደ ስታዲየም ሲመጡ ቀጥ ብላ ኳሱ ሜዳ መካከሉ ድረስ ትሄድና ተመልሳ እስራቸዉ ትተኛለች ። በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል በ1954 ዓ.ም በተደረገዉ የሶስተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ዕለት ሜዳዉ ዉስጥ ገብታ እንዲያዉም ጎል መግቢያዉ መረቡ ድረስ ሄዳ መመለሷን እንደ ትልቅ ነገር የሚያወሱ ሰዎች አሉ ። ይኽን ሁሉ የሚመለከት ሰዉ ይህች ዉሻ ነገር ያላት ናት እያለ ይናገራል ።

ሉሉን የሚወዷት ሰዎች የመኖራቸዉን ያህል የሚጠሏትም ብዙዎች ነበሩ ። በተለይ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጃንሆይ ለምርቃት በዓል ሲመጡ የእሷ አብሮ መምጣት አይጥማቸዉም ነበር ። እሷም መካከላቸዉ እየገባች ታነፈንፍ ስለ ነበር አንድ አመት ላይ አንድ ምሩቅ ሰዉ ሳያየዉ ረገጣትና ጮኽች ። በዚህን ጊዜ አጃቢዎች ረጋጩን ተማሪ ለመለየት ብዙ ቢሞክሩም ሌሎቹ ተማሪዎች ስለሸፈኑት ተማሪዉ ሳይለይ ነገሩ እንዲሁ በቅሬታ ታለፈ ።

ባለቤቱን ካልናቁ ዉሻዋን አይነኩም እንደሚባለዉ ጃንሆይን ካልናቁ ወይም ካልጠሉ ዉሻዋን አይነኩም በሚል ዉሻዋን ሁሉ ሰዉ ያከብር ነበር ። አንድ ጊዜ ኮለኔል ተክሉ ገብሩ ሻምበል በነበሩበት ወቅት ተግባር ዕድ ትምሕርት ቤት የ radio communication ትምህርት ሲማሩ ጃንሆይ ትምህርት ቤቱን ለመጎብኘት ሲመጡ መኮንኑ እግር ስር ሉሉ መጥታ ስላስቸገረቻቸዉና ጃንሆይም በቅርብ ስለነበሩ ዉሻዋን ወይጅ! ማለት ስለፈሩ " ወይዱ " ስላሉ ጓድኞቻቸዉ ወይዱ! የሚል የቅፅል ስም ሰጥተዋቸዉ እንደ ነበር ይነገራል ።

ሉሉ የወር ደመወዝ ተቆርጦላት በወር የአንድ ሻምበል ደመወዝ 175 ብር ታገኝ እንደ ነበር የታወቀዉ ጄኔራል መንግስቱ ንዋይ ለገሃር በሚገኘዉ የጦር ካምፕ እስር ላይ በነበሩበት ወቅት ለአንድ ሻንበል " እኔ እዚህ ችግር ዉስጥ የገባሁት ያንተን ደመወዝ ከአንድ ዉሻ ደሞዝ እንዲሻል ለማድረግ ብዬ ነበር " ብለዉ በመናገራቸዉ ነዉ ።

ሞት አይቀርምና ሉሉ ስትሞት ቤተ መንግስት ዉስጥ ተቀብራ መቃብሯም በዕብነ በረድ ስለተሰራ ጃንሆይ ከተወቀሱበት ነገር አንዱ ሆኗል ። በሀገራችን ለእንስሳት ክብር ሐዉልት መስራት ያልተለመደ ሆኖ ነዉ እንጅ አገልግሎት ለሰጠ እንስሳ ማስታወሻ ማድረጉ አይከፋም ነበር ። በኢሕአዴግ ዘመነ መንግስትም በትግል ዘመን ታሪክ ለሰራች አንድ የሃምሳ አለቃ ደሳለኝ ለምትባል አህያ ሓዉልት ተሰርቷል ። ስለህነም ሉሉ በኢትዮጵያ ዉስጥ ሓዉልት ከተሰራላቸዉ እንስሶች በታሪክ የመጀመሪያዋ መሆኗ ነዉ ።

ጥላሁን ብርሃነ ስላሴ በፃፈዉ
የ20ኛዉ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ በ1996 ዓ.ም ከፃፈዉ መፅሐፍ የተገኘ
መጠነኛ መነካካትም ከሌሎች መፅሀፎች ተደርጎበታል ።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 14 Aug 2025 18:08:26 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 13 Aug 2025 21:42:09 +0300
ሰለሞን ደሬሳ የፃፋቸው ወይም በco-writerንት የተሳተፈባቸው አርቲክሎች ያሉዋችሁ ወይም ልታገኙ የምትችሉ ወዳጆች @Jerus_allem ላይ ብትልኩልኝ......
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 13 Aug 2025 21:34:26 +0300
Shifting Gears

I who swim
In the stealth of a dream
Listening to the minds of insane silence scream,
Because of the colour lack
I shall paint your loving face
In the colourless breath,
With grapnel-fingers in an empty colour rack,
Beneath the quiet curve of your lashes
Two simple awesome dots in black,
You whose love never wavered
Towards whom I forever crack
On the tip of my parched tongue.


Solomon Deressa
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 13 Aug 2025 15:54:28 +0300
ስልጡን አካላት እኛ ብቻ ነን ወይ? ዩኒቨርስ ውስጥ ብቻንን ነን ወይ?
ኤልየን (ባዕዳን) የሚባሉ ነገሮች አሉ ወይ?
ካሉስ ምን ዓይነት ነገሮች ናቸው?

የውይይት ፍላጎታችሁን አይቼ ልመለስበት እችላለሁ።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 13 Aug 2025 10:31:33 +0300
ለዓመታት በቀና አይኔ ያየሁት በብዙ ያነበብኩበት ጉዳይ እንዲህ ደምድሜዋለሁ።

ፌምኒዝም የለዝቢያን፣ ከወንዶች ለማትረፍ የሚፈልጉ ሰዎች እንቅስቃሴ ነው!



በኢትዮጵያ አውድ ካየነው ደሞ በስህተት(በቅንነት) የተከተሉት ካልሆነ የሚያደርጉትን የሚያውቁ ሴቶች «ፌምኒስት ነን» ካሏችሁ ለዝቢያንነት፣ የወንድ ጥላቻ፣ ጸረ የወንድ እና የሴት ግንኙነት አቋም እንዳላቸው እወቁ።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Tue, 12 Aug 2025 19:13:49 +0300
On the homosexuals

ክፍል ሁለት!

በክፍል አንድ ተቃራኒ ሀሳብ ሊኖር ይችላል በሚል ዘርዘር ያሉ ሀሳቦችን ለመዳሰስ አስቤ ነበር። አልነበረም። ስለዚህ በፍጥነት ርዕሰ ጉዳዩን ልጨርሰው። LGBTQ+ ተፈጥሮአዊ ነው ወይ? በሳይንስ ይደገፋል ወይ? መልሱ አዎ ነው። በተመሳሳይም አንድን ውሻ አይቼ ለውሻዋ ብማረክ በተመሳሳይ ተፈጥሮአዊ ነገር ነው። አንድ ሴት አንድ አህያ ሲያናፋ አይታ በአህያው አናፋፍ ብትማረክ ተፈጥሮአዊ ነው። አንድ ትልቅ ሰውዬ የሁለት አመት ሴት ልጅ አይቶ የፍቅር ግንኙነት መጀመር ቢፈልግም ተፈጥሮአዊ ነው። «የፍቅር ፍላጎትን» የሚገፋው ነገር በአጭሩ በውል አይታወቅም። [Gay gene የሚሉት ውሸት ነው] ነገር ግን ሌሎቹ ድርጊቶች የሚበየኑት ከማህበራዊ Ethics አኳያ ስለሆነ ሌሎቹ ክልክል ናቸው። አንዱ የLGBTQ+ ነጥብ «ለአካለመጠን የደረሱ ሰዎች ከተፈቃቀዱ ሌላ አካል dictate ማድረግ የለበትም» ከሚል የምዕራባውያን የነጻነት principle አካል ነው። ስለነጻነት የበየኑበትን አካሄድ በመጀመርያው ክፍል አስቀምጫለሁ]

በርከት ያሉ ሴቶች ከግንኙነት ይልቅ በመነካካት የስሜታቸው ጫፍን ማየት ይችላሉ። ለዝቢያን ሴቶች የሚያነሱት ነጥብም ይሄው ነው። የወንዶች G-spot የሚገኘው prostate gland ጋር ነው። እናም ይሄንን አካል በመነካካት የሚገኝ ነገር «ማፈኛው(rectum)» ላይ ይዋል ይደር እንጂ ጉዳት ማምጣቱ አይቀርም። ማፈኛው ለዚህ አገልግሎት የሚውል ተፈጥሮአዊ ስሪት የለውም! በቀላሉ የሚበጠሱ ቬኖች ያለው ነው። ተፈጥሮአዊ ማለስለሻም የለውም! ብዙ ጊዜ በዚህ ሕይወት ውስጥ የቆዩ ወንዶች በዳይፐር የሚንቀሳቀሱት ለዛ ነው! በሳይንሱ ዓለም «ኤቲክስ ቢኖር፣ ፍላጎቱ ቢኖር» ተፈጥሮ ከውልደት አንስቶ ሴታሴት ያደረገቻቸው ወንዶችን(ስድብ አይደለም)፣ ወንዳወንድ ያደረገቻቸው ሴቶችን የሆርሞን ማስተካከያ መስጠት ይቻል ነበር። ቁጥራቸውም ትንሽ ነው።

በግሌ የማስበው «ከአንዳንድ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሰዎች በቀር» የሌሎቹ ልቅ ወሲባዊ ፍላጎት ነው ብዬ ነው። ሀሳቤ ከመሬት የተነሳ እንዳልሆነ ላሳይ....! በዛውም «ፍቅር ጾታ የለውም» የሚለው claim ብዙም አሳማኝ እንዳልሆነ ለማስረዳት ልሞክር! ...

ላለመዋሸት ፊልም ከነጭራሹ አላይም[my fault] ፣ ግን የNetflix ፊልሞች ላይ አየን ከሚሉ ሰዎች እንደምሰማው ideal homosexuals ሁለት ወንዶች፣ ወይ ሁለት ሴቶች ተፋቅረው ብዙ ችግር አሳልፈው ለዘላለም ኖሩ...ምናምን በእውነታው ዓለም አይሰራም። homosexuals በብዛት የሚታወቁት አጭር ትዳር፣ አጭር ግንኙነት...በመስረት ነው።

ከአጭሩ ግንኙነትም ባሻገር ጥናቶች እንደሚያሳዩት 83% የሚሆኑት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ከግንኙነታቸው ውጪ ቢያንስ ከ 50 ወንዶች ጋር ግንኙነት አድርገዋል። 43%ቱ እስከ 500 የሚደርሱ ወንዶች ጋር፣ 28% ውስጥ ደግሞ ከ1000 ወንዶች በላይ ግንኙነት አድርገዋል። እንደማስረጃ የፌምኒስት ጎርደን እና ጌኒ ስኮፕን leak ተመልከቱ...በተጨማሪም 79% Homosexual ወንዶች የወሲብ ጓደኞቻቸው አይተዋቸው እንኳ የማያውቁዋቸው ሰዎች እንደሆኑ በጥናቶች ተመላክቷል። [ HIVን ጨምሮ የአባላዘር በሽታ ስርጭቶች የትየለሌ ናቸው፣ ]

[አንድ ሰው ከ1000 የማያውቃቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ አስቡት😢]

ለማንኛውም ይሄ ከመሬት የተነሳ bold claim ሳይሆን ከ LGBTQ+ ጋር የተገናኘ ባህርይ ነው። ከሀገራዊ context አንጻር ለመመልከት በሚል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እንዲህ ዓይነት ሰዎች የመሰረቱትን የማህበራዊ ሚድያ[FB] ግሩፖችን ስመለከት ካገኘሁት ዓለምአቀፍ መረጃ ጋር ተስማምቶ አግኝቼዋለሁ።

እዚህ ቦታ ነኝ፣ በውስጥ ሜሴጅ ላክልኝ..
ሀዋሳ ቦተም ካለ ስልኬ ይኸው...
ሳሪስ ቶፕ ለሶስት አግኙኝ...
እዚህ ፔንስየን አልጋ ይዣለሁ የቀደመ ይምጣ


ቃላቶቹ ባይገቡኝም[እንዲገቡኝ ባልፈልግም] homosexuality የልቅ ወሲባዊ(pervert) ስሜት እንጂ የእውነት «ሁለታችን ተዋደድን፣ፍቅር ጾታ የለውም አትግደሉን» የሚል አይነት እንዳልሆነ ማሳያ ናቸው። እናም ...

ምን እና አለው.😃

ትውልድ ያመክናሉ፣ ልጆቻችን ይደፈራሉ ብለው የሚሰጉ ሰዎች ከእውነታው ጋር ያልተጣሉ ትክክለኛ አቋም የያዙ ሰዎች ናቸው!! የጅምላ እሳቤ ትክክል ሆኖም ባያውቅ በዚህ ጉዳይ ግን ብዙ ስህተቱ አልታየኝም።


ግን...

ስለሚጠሉዋቸው ብቻ የሰዎችን ስም «በዚህ» ማጥፋት፣ ከሌላ ያልተረጋገጠ መረጃ ተቀብሎ ለሌሎች ማስተላለፍ፣ የትኛውንም ንግግር በእዛ ማዕቀፍ አይቶ መበየን፣ የሰዎችን የንግግር ነጻነት መንፈግ...ባልተረጋገጠ ጉዳይ ላይ (በተረጋገጠም) የደቦ ፍርድ ለማድረግ መንቀሳቀስ...አግባብ ያልሆኑ ነገሮች ናቸው። መደረግ ካለባቸው ነገሮች ውስጥ:- ለፍርድ ማቅረብ፣ ሰዎች ድርጊቱን እንዲሸሹት ማድረግ፣ እዛ ውስጥ ያሉ የቅርብ ሰዎች ካወቅንም እንዲወጡ ማገዝ፣ ድርጊቱን ለሁሉም... አንተም ነህ፣ አንቺም ነሽ፣ እናንተም ናችሁ በሚል በባዶ ከኪስ እያወጡ በማላከክ አለማላመድ!

በዚህ ልጥፍ ብዙ ልል ነበር፣ የተቃወመኝ ስለሌለ በአጭሩ ልቋጭ።

ለትኩረታችሁ🙏🙏

አበቃሁ...

ይሄ በቃ ተፈጥሮዬ ነው ብላችሁ የምታምኑ፣ ድርጊቱን ያደረጋችሁ\የምታደርጉ፣ አሁን በፍርሀት ይህንን የምታነቡ ካላችሁ፣ በዚህ ወጀብ መሀል አብሬ እናንተ ላይ ድንጋይ ለማንሳት ሳይሆን፣ ከጥላቻ በመነሳት ሳይሆን፣ መሬት ላይ ያለውን እውነት ከማሳወቅ አንጻር ነው። .. «ብሮ..ለመተው ሞክር.. ሲስ ለመተው ሞክሪ...» አስተዋዋቂዎቹ ጤናማ ነው ይበሉ እንጂ ድርጊቶቹ ከጤና ጋር የሚሄዱ ነገሮች አይደሉም። መፈክሮችን፣ ማባበያዎችን ሳይሆን የሚወጡ ሪሰርቸቾችን ተመልከቱ...ለእናትህ ወንድ ሁን! ለአባትሽ ሴት ሁኚ!!!
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Tue, 12 Aug 2025 15:52:28 +0300
On the homosexuals

ክፍል አንድ!

ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ከእኔ በተቃራኒ ያለውን ሀሳብ አጣምሜ ላለማቅረብ በብዙ ማገላበጥ አስፈልጎኛል። ብዙ ከዚህ ቀደም የማላውቃቸውን ነገሮችም አውቄያለሁ። አንድ ፍልስፍና፣ነጻነት፣ የሰዎች ባህርይ ጥናት እንደሚመቸው ሰው ከዚህ ቀደም ሀሳቡን በተደጋጋሚ አውጥቻለሁ አውርጃለሁ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ እንቅስቃሴ እንዳለ በዚህ ልክ ያወኩት ገና ሰሞኑን ነው።

የዛሬው ወጋችን የሚሆነው፣ ቻነሉም የፍልስፍና እስከሆነ አንጻር LGBTQ+ «እግዚአብሔር የማይወደው ኃጢአት ነው» የሚልን ሀሳብ ለማስመር ሳይሆን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ እንደ አንድ አፍሪቃዊ፣ እንደ አንድ ነጻ አሳቢ «በማኅበር ኑሮዋችን ውስጥ» ምን አቋም መያዝ እንዳለብን ለመማከር ነው። ይህንን ጽሑፍ የጻፍኩት ከእራሴ፣ ከአብዛኛው ማኅበረሰብ አንጻር ስለሆነ በእዚሁ አንጻር ብትመለከቱልኝ ደስ ይለኛል። የትኛውንም አይነት አቋም ለመከላከል እቅዱ የለኝም።

በ 2007 ፒው የተሰኘ የጥናት ተቋም ኢትዮጵያውያንን በLGBTQ+ ላይ ያላቸውን ምልከታ ባጠናው መሰረት 97+% የጥናቱ ተሳታፊ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱ አስጸያፊ፣ መወገዝ ያለበት፣ ፈጽሞ መፈቀድ የሌለበት ነው ብለው ያስባሉ። [1] እንደመረጃው ከሆነ(ነው) ሀሳቡ ማኅበራዊ «የሀሳብ ተቃርኖ» አይደለም ማለት ነው። «አብዛኛው ማኅበረሰብ የመረጠው ይሁን» በሚል ሀሳብ ስር የሚካተት ከሆነ መልሱ አጠያያቂ አይደለም። ብዙሀኑ የሚኖርበትን መንገድ የመምረጥ ሙሉ መብት አለው!! ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ «ፍቅር ጾታ የለውም፣ ሰዎች በሰውነታቸው ማዘዝ ይችላሉ፣ LGBTQ+ ተፈጥሮ እንጂ ምርጫ አይደለም» የሚሉ የሰብአዊ መብት[የነጻነት] መሰል ጥያቄዎች ናቸው።[በቀጣይ ክፍል እናያቸዋለን] ለማንኛውም እዚህ ላይ በጥንቃቄ እንዲታዩ የሚያስፈልጉ ሀሳቦች አሉ። ሁለቱን አስምረን ጥናቶችን ተደግፈን እንመልከታቸው!!!

ስለ ነጻነት ሲነሳ ስማቸውን የምናነሳው አሜሪካ እና ምዕራባውያንን ነው። የፖለቲካ አመራሮቻችን ሳይቀር እስቲ አሜሪካንን እዩ! ሂዱ አውሮጳን እዩ! ነው የሚሉን። ምሳሌዎቻችን፣ ፍልስፍናዎቻችን ከእነሱ የመጡ ናቸው። ስለነጻነት ካወራን በምዕራባውያን ዐይን ነጻነትን የምንፈታው ከሆነ ያለምንም ጥርጥር LGBTQ+ መብታቸው መከበር፣ በሰውነታቸው ከእነሱ ውጪ ማዘዝ የለበትም። በምዕራባውያን የነጻነት ብያኔ አንድ ሰው ነጻ የሚሆነው የፈለገውን ነገር ማድረግ ሲችል ነው። ህገ መንግስታችንም ቢሆን ከእነሱው የነጻነት ፍቺ ወስዶ የበየናቸው የመናገር፣ የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት መብቶች አሉ።

ምዕራባውያን የነጻነት ትርጉማቸው የሚበየነው ከታሪካቸው ነው። ምዕራባውያን ነጻነታቸውን የሚበይኑት ከአምባገነኖቻቸው ነጻ መውጣትን ነው። ወደ አሜሪካ የተሰደዱት ሰፋሪዎች የአምባገነን መንግስታትን ሽሽት ነበር፣ አውሮጳ ውስጥም ቢሆን የማኅበራዊ ብያኔያቸውን የቀረጹት አምባገነን መሪዎቻቸውን በመጣል ውስጥ ነበር። ስለዚህ የምዕራባውያን የነጻነት ብያኔ መንግስት ላይ ያለው [ወይንም ሌላ ሀይል ያለው] አካል የግለሰባዊ የእንደፈለጉ መሆን (መብት) አለመጋፋት ላይ ነው። ይሄ የእራሱ ጉዳቶች እንዳሉት [ አውሮጳ በሚፈሩት እስልምና ስትዋጥ፣ ኢአማኒነት ሲነግስ፣ የህዝብ ቁጥር ሲቀንስ፣ ቢልየነሮች በዝተው ድህነትም ሲበዛ፣ የንግግር ነጻነቶች ሌሎች አካላትን ሲጎዱ፣ 101 + ጾታዎች ሲፈጠሩ ..] ብቻ ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶቻቸውን መገምገም የእራሳቸው የቤት ስራ ነው።

አሁን ቻይኖችን ወይ ሌሎች ሀያላን ሀገራትን እንውሰድ! የነጻነት ብያኔያቸው የሚነሳው ህብረተሰቡን ከጥፋት፣ ከፍትህ አልባ ክፍፍል «ነጻ ማድረግ» ላይ ነው። ቻይናም ሆነ መሰሎቿ ጠንካራ ሀገረመንግስት አጥተው በኬዎስ ውስጥ በመገዳደል፣ በመዘራረፍ ውስጥ ለብዙ ዘመን አልፈዋል። ስለዚህ ነጻነት ለእነሱ ሳይዘረፉ ወጥቶ መግባት፣ የሚተማመኑበት፣ አቤት የሚሉት ሀገረ መንግስት መኖር ነው። ለምሳሌ እኔ ቻይና ሄጄ እንደፈለኩ ማድረግ፣ የፈለኩትን መናገር ነጻነቴ ነው አልልም! ማንም እንደፈለገ አድርጎ፣ የፈለገውን አውርቶ የእኔን ነጻነት መገደብ አይችልም ነው ማለት የምችለው። ሌላ ደግሞ...ሳውዲ እና በርከት ያሉ እስላማዊ ሀገራትን እንውሰድ! ነጻነታቸው የሚበየነው እስልምና ሀይማኖትን ከሌሎች ሀይማኖቶች ተጽዕኖ ውጪ ሆኖ መለማመድን ነው። ስለዚህ ነጻነትን በምዕራባውያን ታሪክ አኳያ ብቻ መመልከት ሁሉን አቀፍ ምልከታ አይደለም። ወደሀገራችን እንመለስ...!

ሀገራችን ነጻነት የምንለው ከውጪ የሚመጣ አካል እኛ ላይ ከሚያደርሰው ተጽዕኖ ውጪ መሆን ነው። እኛ «የሌላን ሀገር የነጻነት ምልከታ» ወስደን ካልሆነ ነጻነት የምንለው የሌላ የውጪ ከምንለው አካል ግልጽ ተጽዕኖ ነጻ መውጣትን ነው። የ#nomore ፣ አትችሉም ሲሉን፣ ዐባይ ግድብ በራሳችን፣ የአድዋ መዘክር» ወዘተ የሚሉ መፈክሮቻችን ምስክሮች ናቸው። እንደ ሀገር «ነጻ ነን» ስንል ጣልያን ኢትዮጵያ ከቆየባቸው ጊዜ በላይ ህዝቡን የበደለ መሪ ጠፍቶ ሳይሆን ነጻነታችን ለነጻነት የምንሰጠው ፍቺ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው።

ወደ ሀሳባችን ስንመለስ ለአብዛኛው ህዝብ ነጻነት ከውጪ በጫና የሚመጣ ነገርን አለመቀበል ነው። ጽሁፉን ስለረዘመብኝ ወደሚቀጥለው ክፍል ላስተላልፈው...


በጽሑፉ ውስጥ Philosophical claim የምትፈልጉ ከሆነ:- በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ሁለት ሀሳቦችን አንስቻለሁ:-

« የመጀመርያው ነጻነት context እንዳለው፣
ሁለተኛው ደግሞ የአብዛኛው ማኅበረሰብ ፍላጎት ድርጊቱን ማውገዝ፣ አለማየት እንደሆነ»


[1] Pew global attitude, 2007, page 35,81& 117
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Mon, 11 Aug 2025 19:47:43 +0300
ሴትና ወንድ የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር ብቻ ነው ሁለቱም ሴትን አያምኑም!!


መቼም የፍልስፍና ተግባር ሕይወትን መዳሰስ ሲሆን የሕይወት አንዱ ክፍል ደግሞ ሴቶች ናቸውና ፍልስፍና እነሱንም በሚገባ ዳሷል

፦ ወንድን ጓደኛህ ልታደርገው ስትችል ከሴት ጋር ግን ከትውውቅ በላይ (Acquaintance) ልታልፍ አትችልም ያለው ማን ነበር?? ታውቁት ይሆን

Aristotle ስለ ሴት ሲናገር "ተፈጥሮ መጀመርያ ወንድን ፈጠረች..ለሁለተኛ ግዜ ደግሞ ወንድን መስራት ስትጀምር የሁለተኛዋ ስራው ከሸፋባትና ሴት ተፈጠረች" አለ😂😂 እንግዲህ ሴት የተፈጥሮ ክሽፈት ናት ማለቱ ነው..። ፕሌቶ ይህን ሀሳብ በእጅጉ ኮንኖት" እንደውም ወንዶች የሚከፈትላቸው ማንኛውም ዕድል ለሴት የተከፈቱና አልፎም የተመቻቸ ሊሆኑ ይገባል" ብሏል።
ፕሌቶ ይህን ይበል እንጂ የእሱ ደቀ-መዛሙርት የነበሩትም ሲናገሩ..የፕሌቶ ፀሌት እንዲህ ብቻ ነበረች..ፀሎቱም😂😂ወንድ አድርገህ ስለፈጠርከኝ አመሰግናለሁ ማለት ብቻ ነበር ይሉናል..(ዊል ዱራንትም..ፕሌቶ "ወንድ ስለሆንኩ ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ" ብሎ መፀለዩን በአንድ መፅሐፉ ላይ ጠቅሶት እናገኛለን)

አስቀድመን ባነሳነው የአርስቶትል ሀሳብ አብዛኛዎቹ ፈላስፎች ሲስማሙ "ይህን ጉዳይ ራሱ እግዛብሔርም አምኖበታል..አድርጎታልም በማለት ነው። በብሉይ ኪዳን ጂሆቫ (እግዚአብሔር) ለሙሴ በመጨረሻ በሰጠው ትዕዛዝ..የእስራኤል ወንድ ልጆች ሴቶችና እናቶችም ከብቶሽም እንዲሁም የቤታቸው ንብረት ሰብስበው እንዲወጡና እሱም እንዲመራቸው ማዘዙን ይጠቅሱና " እንግዲህ ሴት ለወንዱ አንደ የንብረቱ ክፍል አድርጎ እግዚአብሔርም ቆጥሯታል"ይሉናል🤭🤭

ይህ የፈላስፎቹ እይታ ነው አደራ ይሰመርበት😂😂
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Mon, 11 Aug 2025 18:33:47 +0300
ተፈጥሯዊ ከሆነው የወንድ እና የሴት ግንኙነት ውጪ ያለ ሌላ ግንኙነት የተወገዘ መሆኑን ለትውልድ እንሰብካለን!

ሰዶምን እንዲፀየፉ እንመክራለን!

#ሰውነት
#ሁለት_ፆታ_ብቻ
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Mon, 11 Aug 2025 16:16:27 +0300
ማኅበራዊ ጥያቄ

👉ወንድ እና ሴት ቤስት ፍሬንድ መሆን ይችላሉ?
👉ከትዳር በኋላስ ጓደኝነታቸው መዝለቅ ይችላል?
👉አጋራችሁ የተቃራኒ ጾታ best friend እንዲኖረው ትፈቅዳላችሁ?

👉Even ሴት እና ሴት ወንድ እና ወንድ ወደ እየ-ትዳራቸው ከዘለቁ በኋላ የቀደመ ጓደኝነታቸው ሳይነካ መቀጠል ይችላል?

👉አጋራችሁ በጣም የሚያቀርበው\ባት ጓደኛ እንዲኖረው\ዋት እንዲኖረው ትፈቅዳላችሁ? እናንተስ ይኖራችሁዋል?

መልሱ የየእራሳችን ስለሆነ ያለ ከልካይ ሀሳብ እንካፈልበት! ለሌሎች እናስተምር እኛም እንማር...
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 10 Aug 2025 19:59:12 +0300
ጥያቄ ስለ ደስታ....

ሰዎች የተወሰነ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! ከእራሳችሁ መማከርም እዚህ ለሌሎቻችንም ማካፈል ትችላላችሁ! ደስ እንዳላችሁ?

ደስ ማለት፣ ደስታ ምን ማለት ነው? የደስታ ስሜት እንዴት ያለ ነው? ደስታ የሚመጣበት ቀመርስ አለው?

ደስታ ምርጫ ነው? ወይንስ በእራሱ የሚመጣ ነገር ነው? ደስታ በገንዘብ ይገኛል ወይንስ አይገኝም?

የግለሰቦች ደስታ ልክ ሄዶኒስቶች እንደሚሉት የህይወት ግብ ሊሆን ይችላል? ከነጻነት ጋር የሚያያዝ ነገር አለው? ነጻነት ሳይኖር ደስታ ሊኖር ይችላል? ደስተኛ ጅል መሆን ይሻላል ወይንስ ደስታ የራቀው ብልህ አሳቢ??

ከሰዎች ተሽሎ መገኘት፣ ስኬትን ማሳካት ለደስታ ቁልፍ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ያለ ጓደኞች ለብቻ ደስተኛ መሆን ይችላል? ደስታ ይሰለቻል? ደስታ እንዲኖር ስቃይ ማለፍ አስፈላጊ ነው?


እስቲ ከእራሳችሁም ከእኛም ጋር ተማከሩ.. ሀሳባችሁ ለሚያነበው ሰው ትልቅ ግብዓት ሊሆን ስለሚችል ..ሀሳባችሁን አትሰስቱ...
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 09 Aug 2025 22:25:28 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 09 Aug 2025 14:01:41 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Fri, 08 Aug 2025 19:11:15 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Fri, 08 Aug 2025 16:45:32 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 07 Aug 2025 20:30:32 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 07 Aug 2025 20:30:23 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 06 Aug 2025 12:42:39 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 06 Aug 2025 12:42:15 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Mon, 04 Aug 2025 15:06:16 +0300
Honest ምልከታችሁን እፈልጋለሁ። «ዝግመተ-ለውጥ እውነት ይከሰታል ብላችሁ ታምናላችሁ ወይንስ ዳርዊን ተሳስቶ ያሳሳተው ተረት ነው ትላላችሁ?

ታድያ መልሱን ስትመልሱ honest ሆናችሁ!! መልሳችሁን የምታስቀምጡበት ከጀርባው ያለን ሀሳብ አስወግዱ!! እና neutral ቦታ የያዘ ምክንያታችሁን እንወያይበት..

ምላሾቻችሁን አይቼ Is evolution a fact or just a myth? የሚል ጥሑፍ አዘጋጃለሁ...
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 03 Aug 2025 19:03:05 +0300
የሰለሞን ደሬሳ "ልጅነት" ከተሰኘችዋ የስነ ግጥም መድብል ዉስጥ "በቋፍ" የምትለዋን አርስት ተመሰጡባት ፦

በቋፍ
አልቦዘንሁም አበባዬ
ባሰላስል ቁጢጥ ብዬ
ላስፈተልክ ምርጡን
ላዉጣዉ አባብዬ

አልፌም ጠጣለሁ
ሰክሬ ላገሳ
ዳዊትም ገልጣለሁ
ቢሆን ብየ ካሳ
በምንባብ ዉቅያኖስ
በብዛት ጠበቃ
ሃሳብን ባሳብ መርዝበመርዝ ላጠቃ

ፍልሰታን ጦሜአለሁ ነነዌን ጠርጥሬ
ትንግርቱን ትርንጎ ልመና በቁሜ

መናፍቅ ጥሞና ማንን ለማታለል
ባረቄ በድግምት ምታት አይባበል

ወዴት ሽሽት አለ ከኔዉ ሲሆን
ብዳከም ቢበቃኝ እያፈነኝ ያለእንቅልፍ እያዛለኝ

ጠሎት ስሜት ሲሆን
ሃሳብ ከሰል ረመጥ
እኔዉ ዉጥር ሽቦ ግሎ ሲንቀጠቀጥ

ይታበድ እንጂ እንግዲያማ
ይነደድ ይቀለጥ እንደሻባት ሻማ
ዝርዝር ብጥስጥስ እንደለማኝ ሸማ

ፍሬኑ ሲበጠስ
ከፍሮቻ ሌላ ማርሹ ሲቀላቀል
ሹክሹክታቸዉን በስላቅ አምልጬ
ባበሻ ልጓም ጥርስ-ድዱን አድምቼ
አጓርቼም ካልተፋሁት አማስዬ
ትክ ብዬ አንዴም አባብዬ
ዜሮ መሸሻ ቀልቡን ስቶ መግቢያዬ ።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 03 Aug 2025 18:02:43 +0300
❤️
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 02 Aug 2025 20:59:03 +0300
* _\\___ *

እኛው ምዕ
መናን አዋተን ባሰራነው ቦታ ላይ «ስንሞት የመቃብር ስፍራ የሚቸበችቡልን» ቤተክርስቲያን እና መስጅዶች እውነት ዘላለማዊ የማረፍያ መንገዱን ቢያውቁት በነጻ ይነግሩን ነበር?

ዝም ብዬ ሳያቸው አይመስለኝም።

* _/\___*


መገናኛ ጋር ሰከም ሰ
ከም እያልኩ ስሄድ አንዱ እየሱስ ያድናል ብሎ ይጮሀል፣ አጠገቡ ደሞ እኔ ነኝ ደራሽ ለወገኔ የሚል ዘፈን ተለቆ ለህክምና ገንዘብ ይሰበሰባል። ሳይተያዩ ቀርተው ነው ወይንስ ያልታመመ መንገደኛ ነው የሚፈውሰው?

* \\ *

የቲቪ ቻነሌን ስ
ቀያይር የጼንጤ ፈውስ በዛብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማውቀው ፈውስ ለማያምኑ ሰዎች ምልክት ለመስጠት እና እነዛን ደቀመዝሙር ለማድረግ ነበር። አንድ ሰው ቸርች ውስጥ ከተፈወሰ ምን ይገርማል? ቸርች ኢየሱስ ያድናል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ አይደል እንዴ? እውነት ከልባቸው ካመኑት ሰው መፈወሱ ለምን ይገርማቸዋል? ወይንስ እዛ ያለውን ሰውዬ ከፍ ከፍ ለማድረግ ነው?

* \\__ *


አቡነ እንትና አሜሪካ ሀገር ህክምናቸውን ተከታትለው ተመለሱ፣ አቡነ እንትና እንግሊዝ ሀገር ታክመው አገገሙ...እኛ እኛ ስንሆን ቃጥላ ማርያም እነሱ ሲሆኑ ግን...ሆስፒታል.. የሆነ ነገርማ ስቻለሁ...

* /\__*

እንትን ቤተክርስትያን
እየፈረሰ ነውና የእግዚአብሔርን ቤት እንገንባ የሚል ማስተዋወቅያ በየቦታው ነው። እኔ የምለው ሲኖዶሱ እራሱን ችሎ ቤተክርስቲያን አናጸ የሚባል የምንሰማው መቼ ነው?

* /\__*

እስልምና ሰላም ነው ብሎ የሰበከኝ ሰው ነብያችን ተሰደቡ ብሎ የጂሀድ እሪታውን ሲያቀልጠው ሰማሁኝ። ሰላም ነኝ ካልክ እኮ መስመሮችህን ማላላት፣ ከአንተ ውጪ ካሉት ጋር አብረህ ለመኖር የምትከፍለው ዋጋ ሊኖርህ ይገባል። ነብዩ (ሰዐወ) ለዓለም ተላኩ ካልክ ከአንተ እኩል ለዛ ላልተቀበላቸው ሰውም ተልከዋል እያልክ ነው። ይህ ማለት ያንተ ብቻ property አይደሉም ማለት ነው። ለምን ሁሉን ነገር አንተ ላይ ብቻ የተቃጣ ታስመስለዋለህ??
* _/\__*
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 02 Aug 2025 18:02:37 +0300
ሴቶች እና ደራሲ- ስብሐት ገ/እግዚአብሔር


ጋሽ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር መፅሐፍና ሴት እንደሚወድ በግልጽ ተናግሯል  ስለሴት በተለያዩ መፅሐፎቹ ብዙ ብሏል፡፡ በሕይወቱም ከብዙ ሴቶች ጋር እንዳሳለፈና በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ፍቅር እንደያዘውም ራሱ ተናግሯል፡፡

ፍቅር የአፍቃሪው ሕይወት ላይ ተፅዕኖ እንደሚያደርስ ለማወቅ ጠንቋይ መቀለብ አይጠበቅብንም፡፡ ስብሐትም ከመጀመሪያ ፍቅረኛው ከነበረችው ከሀና ይልማ ጋር ከተለያየ በኋላ ለ40 ዓመታት ያህል ጋዜጣ ላይ ለእንጀራ ብሎ ከሚፅፋቸው ሰብርባሪ ሃሳቦች በስተቀር የረባ መፅሐፍ እንዳልፃፈ ደራሲ ያዕቆብ ህርሃኑ በ‹‹ከባዶ ላይ መዝገን›› በሚል መፅሐፉ ይገልጣል...

ለምሳሌ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በሚወጣው ፅሁፎቹ ቅር የተሰኘ ሰው አለ እዚህ??

ለነገሩ ቅር ብትሰኙም ጋሼ እንደው መልሱ ይታወቃል ምን አለፋን።

እስቲ ማለፊያ ይሆነን ዘንድ ስለ ጋሽ ስብሀት እድሉን ካገኛቹ አይቀር ተንፍሱ ወሲብ ላይ ባለውም አቋሙም ቢሆን 

React አይረሳ 🫶
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Fri, 01 Aug 2025 18:36:27 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Fri, 01 Aug 2025 09:00:06 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 31 Jul 2025 20:56:06 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 31 Jul 2025 20:46:52 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 30 Jul 2025 22:35:10 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Wed, 30 Jul 2025 17:40:23 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Tue, 29 Jul 2025 21:07:16 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Tue, 29 Jul 2025 21:07:16 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Tue, 29 Jul 2025 21:07:12 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Mon, 28 Jul 2025 13:29:41 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sun, 27 Jul 2025 17:19:36 +0300
ድህነትን ማን ይወዳል?  ገንዘብንስ ማ ነው የሚጠላ?  አይ ድህነት!! ከወዳጅ ከጓደኛ የምትለዪ ፥ ንፉግ ሳይሆኑ ንፉግ የምታሰኚ። ለምን ተፈጠርሽ? የሌለብንን በሽታ ልትፈጥሪ! በአንቺ ምክንያት የገዛ ወንድማችንን እንድንገድል ነው ወይስ የማንወደውን እንድናገባ! ወይስ ሌባና ቀማኛ እንድንሆን! ምነው እንደማስቸግርሽ መልስ ለመስጠት ብትቸኩይ


ገንዘብን የሚጠላ ይኖር ይሆን?😁
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 26 Jul 2025 17:24:59 +0300
አልበርት ካሙ

የሲሲፈስ እጣ ፈንታ..(The myth of sysiphus)
(የቀጠለ...)

ከላይ ባለው ክፍል ካሙ የተጠቀማቸውን ምሳሌዎች ማየት ጀምረን ነበር። በዚህኛው ክፍል «መጽሐፉን ያላነበባችሁት ካላችሁ» ካሙ ለማስረዳት የተጠቀማቸውን ምሳሌዎች፣ ምዕራፎቹን በስሱ ገርደፍደፍ እያደረግን ለመዳሰስ እንሞክር! ከዚያም በሚቀጥለው ክፍል «አጠቃላይ ስለ መጽሐፉ ...ይዘት» እንመለከታለን። ይህንን ሁሉ ለማድረግ ያለኝ ውሱን ቃላት ስለሆኑ በተፍታታ ግን አጭር በሆነ መልኩ ለመረዳት የአንድ መጽሐፍ ቁራጭ እለጥፋለሁ። ይህ የምለጥፍላችሁ «የካሙ ስራዎች ስብስብ አጠር.. አጠር.. ባለ መልኩ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ ከቀረበ መጽሐፍ» ላይ ተቆርጦ የወጣ 24 ገጽ [ብቻ] ጽሑፍ ሲሆን እሱን እንድታነቡት እየጋበዝኩ እኔ ግን እንደፌንጣ መዛለሌን ልቀጥል😁 እዚህ ላይ ስትነኩት ወደሱ ይወስዳችሁዋል

በላይኛው ክፍል ካሙ ለማስረዳት የተጠቀመበትን «የዶን ሁዋንን» ገጸባህሪ አይተናል። ከእሱ ስንቀጥል.. ቅኝ አድራጊ በሚል ምሳሌው የሚያነሳው ድል አድራጊ ሰው... እናገኛለን። ካሙ በዚህ ምሳሌው ሌላን አካባቢ ቅኝ ከማድረግ ይልቅ አመጻ ላይ ትኩረት ያደርጋል። እራስን ነጻ ማድረግ ሌላን አካባቢ ከመቆጣጠር የተሻለ እንደሆነ ማሳያ አድርጎ ያቀርበዋል። ለካሙ ሁሉም ትግሎች፣ ቅኝ አገዛዞች እርባና ቢስ ናቸው።

አንድ ከንቱነትን ለተረዳ ሰው(Absurd man) ሁሉም ትግል ከንቱ ነው፤ ድልም ዘለቄታዊ አይደለም። ግን ደግሞ ይሄ ተስፋ የሌለው ትግል ህይወቱን ይደነግጋል። ካሙ «ብዙ ነገር ካስከተለ አናውጤ ትግል ይልቅ የከሸፈውን ትግል እና የምስኪኖች ትግልን» ይመርጣል።

ሶስተኛው ደግሞ «አርቲስትን» እንደምሳሌ ያቀርባል። አንድ አርቲስት በተሰጠው ሰዓት የተሰጠውን ተውኖ ያልፋል፤ በተመሳሳይም የእኛም ኑረት እንዲህ ነው ይላል... ሌላው... አንድ የመድረክ ተዋናይ በአንድ መድረክ ላይ ድንቅ ጥበብ ቢያሳይ ተደራሾቹ እዛው መድረኩ ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው።😁 ዓለማየሁ ታደሰ «ባቢሎን በሳሎን» የተሰኘ ቲያትር ላይ በአንድ ቀን ያሳየነው ትዕይንት ተአምር ሆኖ ከዘላለም ዘላለም አይነገርም። እዚያው አዳራሹ ተጨብጭቦለት ያልፋል።

ወይ ድሮ ለታ...ኢቴቪ ላይ «ስንቅ የሚል ድራማ» ላይ በሆነ ቀን አለልኝ መኳንንት ጽጌ ያደረገው ትዕይንት ፣ሰውየው እራሱ፣ ድራማው እራሱ ከወቅቱ ጋር አብሮ ከስሟል። አሁን ያ ድራማ masterpiece አይደለም። አክተሮች\ተዋናዮች እዛው መድረክ ላይ ያለው ትዕይንት፣ ክፍያቸው ላይ፣ በህይወት እስካሉ እንጂ «ዘላለማዊ አሻራ» ለማስቀመጥ አይሹም ባይ ነው ካሙ! ካሙ ኑረትን ከአክተሮች ጋር አመሳስሎ ሲያስረዳ «ታላላቅ የመጽሐፍት ጸሐፊዎች» ደግሞ ግፋ ቢል 500 አመት ያህል ቢታወሱም [ ለምሳሌ ጎት የተሰኘው ደራሲ እንደአብነት ጠቅሶ] 10,000 አመት በኋላ ስራውቸም እነሱም ይረሳሉ ይላል።

ወደ ካሙ ዘመን አርቲስቶች ስንመለስ አርቲስትነትን ካቶሊክ በቀና የማታይበት ዘመን ስለነበር ብዙ አክተሮች አልነበሩም። እና ያሉት ውስን አክተሮች ብዙ ቦታዎች(ተውኔቶችን) ለማዳረስ ሲሉ ትንሽ እና ጥንቅቅ ያለ ስራ [ዘመን አይሽሬ ስራ] ከመስራት ይልቅ፣ በሙያቸው ወቅት ተደራሽ በመሆን ለረጅም ጊዜ ተፈላጊ መሆንን ያስቀድማሉ።

«Absurd man» በሚለው የመጽሐፉ ክፍል ላይ በእነዚህ ሶስት ምሳሌዎች እያስረዳ ብዙ ሀሳቦችን አስተላልፏል። በዚህ [አሁን በምታነቡት] ጽሑፍ በቃ ስለ «ሲሲፈስ ዕጣ ፈንታ» መጽሐፍ ተብራርቷል፤ መጽሐፉን ሙሉ በሙሉ አወቅን ማለት ሳይሆን መጽሐፉን ለማንበብ እንዲያበረታታን የተጻፈ ነው። ካሙ ውስብስብ ቃላትን፣ ውስብስብ ሀሳቦችን የሚያስተላልፍ ለመረዳት ተንታኝ የሚያስፈልገው ዓይኑት ፈላስፋ ሳይሆን በሃሳብ ፍሰቱ በማብራራት ክህሎቱ የምትደነቁበት ፈላስፋ ነው። እንደውም ውስብስብ ሀሳቦቹን የገለጸበት ቀላል መንገድ እያዩ ብዙ ሰዎች more novelist ይሉታል።

ይህ መጽሐፉ አራት ዋና ዋና ክፍሎች ሲኖሩት:-

Absurd reasoning /የህይወት ከንቱነት የተረዳ ሰው(የዘበትነት ምክንያት )

በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር
👇👇
የጋረደው መጋረጃ / absurd wall (ማለትም ስሜቶች በቃላት መገለጽ እንደማይችሉ፤ ዘበትነት፣ ከንቱነት ሙሉ በሙሉ በቃላት ሊሰፍር አይችልም። እንዲህ ያሉ ሀሳቦችን ያነሳል..)

philosophical suicide \ ምሁራዊ እራስን-ማክሰም

በዚህ ክፍሉ ሌሎች ፈላስፋዎች ምሁራዊ እራስን ማክሰም እንደፈጸሙ የሚያስረዳበት ነው። እነ ኪርክጋርድ፣ እነ ኸስርል እነ ጃስፐር እነ ኪርክጋርድ እነ ሀይዲገርን ይሞግታል። (በክፍል አንድ ነካክቼዋለሁ)

absurd freedom\ የዘበትነት ነጻነት

ካሙ ከንቱነትን (absurd) የሚገልጸው «የሰዎች ምክንያት እና የምንኖርባት አለም ምክንያት አልባነት የሚፈጠር ግጭት» ብሎ ነው። ያው በካሙ ገለጻ ምክንያታዊ ሰዎች ምክንያታዊ ባልሆነ አለም ላይ ለተወሰነ [አጭር] ጊዜ እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል። ይህንን እውነት መቀበል ህይወትን በምልአት መኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ነው። አንደኛ አንድ ሰው ከዘበትነት ታግሎ ለእራሱ በሚሰጠው ግብ እራሱን ያለማንም ጣልቃ ገብነት መወሰን ይችላል። ማለት :- አሁን አንድ ሰው መሆን የፈለገውን መሆን፣ ማሰብ የፈለገውን ማሰብ፣ መወሰን የፈለገውን መወሰን ...የመቻል ነጻነት አለው። ያ በውስጡ ያለው ሀሳብን ደግሞ ወደ ተግባር ገልብጦ መገለጫው ማድረግ ይችላል። አሁን የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆን ብፈልግ እና ብወስን...«የቤተሰብ አስተዳዳሪ» የሚባል የህይወት ትርጉም እሰጣለሁ። ያንን ለመሆን ደግሞ የሚያስፈልጉ ነገሮች ለማሟላት action መውሰድም እጀምራለሁ። ከሰማይ፣ ከመንፈስ፣ እርግጠኛ ካልሆንበት ነገር ጋር የተገናኘ ነጻነትና/ባርነት ለ ዘበታዊ ሰው ምንም አይደሉም። ለካሙ ይበልጥ ትርጉም ያላቸው የምናስበው፤ ያ ከምናስበው ነገር ወደ ድርጊት መርጠን የምንለውጥበት ነው።

ሁለተኛው Absurd man የሚል:- የዶን ሁዋን ምሳሌ፣ የአርቲስት\ድራማ ምሳሌ ፣ ድል ማድረግ የሚሉ ክፍሎችን ውስጡ ይዟል። ሶስተኛው ክፍል absurd creation\ የዘበትነት ስነፈጠራ ማለትም ስነጽሑፍ፣ አርት፣ ልብወለድ ፍልስፍና ምናምንን ይዳስሳል። ከስሩ philosophy and fiction በሚል ስር ስለ ፍልስፍና እና ስለ ልብወለድ ሲያብራራ ቀጥሎም በephemeral creation ክፍሉ ላይ የዲዮስቶቭን ስራ እና የሜሊቪል ሞቢዲክ ስራ ጠቃቅሶ ያልፋል። በመቀጠል ከዲዮስቶቭ ስራ ሳይወጣ "The possessed" የተሰኘ መጽሐፉ ላይ የፈጠረው kirlov የተሰኘ ገጸባህሪ ስም የሰየመው ምዕራፉን ይቀጥላል...(በውስጡ ብዙ ሀሳቦች አሉ)

አራተኛው "the myth of sysiphus የሚል ሲሆን በክፍል ሶስት እመለስበታለሁ፤ ካሙ አምስተኛው ክፍል ማለትም የመጽሐፉ ማከያ (appendix) ላይ ፣ ካፍካን ይጠቅሳል። ...


ይቀጥላል...
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 26 Jul 2025 17:23:53 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Sat, 26 Jul 2025 16:19:19 +0300
አንድም የሚጣል ፊልም የሌለው ዳይሬክተር ጥራ ብባል Christopher Nolan ነው። ከፊልም ወደ ፊልም እየተመነደገ፣ እየገዘፈ የሚሄድ ዳይሬክተር ነው። ግን አንድ ማስተርፒስ ብቻ ጥራ ብባል ሳላመነታ INCEPTION እላለሁ። የብዙዎች ምርጫ The Dark Knight እንደሆነ ይገባኛል። ለኔ ግን ኢንሰፕሽን አንድ ሌላ ጥሩ ፊልም ብቻ አይደለም። ኢንሰፕሽን ፍልስፍና ነው።

በነገራችን ላይ ክሪስ የኢንሰፕሽንን ሃሳብ ለራሱ ይዞት ለ10 አመታት ተቀምጧል። የሃሳቡ ትልቅነት ለራሱ ታይቶት መጀመሪያ በሌሎች ብሎክበስተር ፊልሞች ችሎታዬን ላጎልብት፣ መጥረቢያዬን ልሳል፣ እጆቼን ላፍታታ ብሎ ብዙ አመታትን ወስዷል። The Dark Knight ራሱ ኢንሰፕሽንን ለመስራት መንደርደሪያ፣ መለማመጃ ነበር።

አያችሁ የኢንሰፕሽን ማእከላዊ ሃሳብ ህልም ነው። በህልም አለም ደግሞ የማይቻል ነገር የለም። ክሪስቶፈር ኖላን ፍሩይድን በደንብ ያነበበው ይመስለኛል። ክሪስን የምታደንቀው ይሄኔ ነው። የፍሩይድ መፃህፍት በአሰልቺ ስነልቡናዊ ፅንሰሃሳቦች የተሞላ ነው። ክሪስ የሲኒማ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እነዚህን ቲዎሪዎች ወደ አዝናኝ የሶስት ሰአት የአቡጀዲ ላይ ጥበብ ይቀይራቸዋል።

ክሪስቶፈር ኖላን ሁሌም የምተማመንበት ነገር ቢኖር ሁሌም አዲስ ነገር ይዞ ይመጣል። ሃሳብ፣ ጭብጥ አይደጋግምም። ከራሱም ሆነ ከሌላ ዳይሬክተር አይኮርጅም። ቦታው ከታላላቆቹ ዳይሬክተሮች ጋር ነው—ሂችኮክ፣ ኩብሪክ፣ ስፒልበርግ፣ ስኮርሲስ፣ ኮፖላ ወዘተ[Tewdros]
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Fri, 25 Jul 2025 09:18:51 +0300
አልበርት ካሙ

ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ባልተለመደ መልኩ ብዙ ተቸግሬያለሁ፤ ከጀመርኩት ቆየሁ ግን ስለካሙ የቱን ብዬ የቱን ላድበስብሰው..መጽሐፍቱን እየመረጥኩ ዳሰሳ ላቅርብ ወይንስ ሙሉ ፍልስፍናውን በደምሳሳው ላቅርብ...?

የካሙ ፍልስፍና ለሁሉም የቻነላችን አባላት አስፈላጊ ነው? ወይንስ ለተወሰኑት? ለማያውቀው ሰው ሳይወሳሰብበት፣ ለሚያውቀው ደሞ በጣም ኤለመንተሪ ሳይሆንበት እንዴት «ካሙን» ላስቀምጥ ? ..የካሙ ፍልስፍና «ስለ ህልውና» በመሆኑ የእሱን ፍልስፍና አፍታቶ መናገር..የሚረብሻቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን? ብዙ ሀሳቦች በውስጤ ሲመላለሱ.. መጨረሻም አንድ የገነነ መጽሐፉን መርጬ ለማቅረብ ወስኛለሁ። የሲሲፈስ ዕጣ ፈንታ[ the myth of sysiphus] ....

የካሙ ፍልስፍና የሚነሳው «ህይወት ከንቱ ነች ከሚል ነው» ስለዚህ ህይወት ከንቱ አይደለችም፣ የአምላክ እጅ ስራ ነን፣ ሁሉ በኹሉሄ የሆነው ፈጣሪ በእኛ ያስቀመጠው ዓላማ አለ ብለው በጥብቅ ለሚያምኑ ሰዎች ካሙም ሆነ የህልውና ፈላስፋዎች relatable አደሉም። ካሙ:- ለኢአማኞች፣ ወይ እንዲሁ ዝም ብለው absurdism ምን እንደሆነ ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች፣ የተለያዩ ዓይነት ፍልስፍናዊ ምልከታዎችን ማየት ደስ ለሚላቸው ሰዎች፣ የህልውና(የመኖር) ጥያቄዎች በህይወታቸው ላሉባቸው፣ ሲኖሩ ለምን? እንዴት? እያሉ ለሚጠይቁ ሰዎች ካሙ «ምርጥ ፈውስ» ነው።

(በአንድ እጅ እየሱስ= በአንድ እጅ ካሙስ፤ በአንድ እጅ አልበርት = በአንድ እጅ አላህ አይሰራም)

ወደ ካሙ..እንመለስ...

ሰዎች ለህይወት መልክና ቅርጽ በመስጠት ከቶውኑ የማይመለሱ፣መልስ አልቦ የኾኑ ማለትም:- « ለምን እኖራለሁኝ፣ እኔ ማነኝ፣ ሰው ምንድን ነው?» ምናምን የሚሉ የህልውና ጥያቄዎች ቢጠይቁም «መኖራችን በዋነኛነት እራሱን የቻለ ትርጉም የለውም» ባይ ነው ካሙ። እኛ ምድር በምንላት አንድ ጠጠር የምታክል ጸሐይን እንደትቢያ በዙርያዋ ውር ውር ከሚሉ ዘጠኝ ክትለቶች አንዷ ብናኝ ላይ ኩስ ኩስ የምንል፣ ጊዜያችም ብልጭ ብላ የምትጠፋ ደቂቃን ፍጥረቶች!!!

ካሙ «ኑረት በእራሱ እኮ ሲቃ፣መከራ ነው» ከሚሉት እነ ሾፐንኣወር.. በህይወት ትርጉም አልባነት ሲስማማ ዋነኛ የህይወትን ትርጉም ባናገኘውም፤ ትርጉም ለመስጠት በውስጣችን ያለውን ትርጉም አልባነት ላይ አምጸን ድል ማድረግ እንዳለብን ያስረዳል። ይህንን ደግሞ እንዴት መደረግ እንዳለበት revolt(አመፃ) በሚለው ይበልጥ መጽሐፉ አብራርቷል። [በውስጣችን እንዲሁ በተፈጥሮ አለ ያለውን የህይወት ከንቱነት ከካቶሊክ original sin ጋር አነጻጽሮት ሊሆን ይችላል]

(ለዛሬ በግሪክ አፈ-ታሪክ የሰየመውን መጽሐፉን በተወሰነ መልኩ እየተመለከትንም አይደል? እንቀጥል...)

ህይወት በዋነኝነት ትርጉም አልባ ነች፣ መሰረታዊ ትርጉም የላትም ካልን እራሳችንን ብናጠፋስ? አደል?😁 ለምን እንደምንኖር አናውቀውም፣ ደሞ ግን ነገ የተሻለ እንደው ቢሆን ብለን ደቼ እንበላለን፤ ግን ደግሞ ነገ ከዛሬ ይልቅ ወደማይሞተው ሞት እየቀረብን ነው። ካሙ በህይወት ትርጉም አልባነት ከሌሎች የህልውና ፈላስፋዎች (ሀይዲገር፣ ኪርክጋርድ ምናምንን..) ጋር ተስማምቶ የተነሱበት ሀሳብ እና የደመደሙበት ወይ በእንጥልጥል ያስቀሩበትን መንገድን «ምሁራዊ ራስን ማጥፋት» ይለዋል። በካሙ ምልከታ «ግማሹ የህልውና ፈላስፋ ህይወት በመሰረታዊነት ትርጉም የላትም ይል...ይልና ፍልስፍናውን ካጧጧፈው በኃላ ወደ ጌታ እንሰብሰብ ይላል😁 ግማሹ ደግሞ ትርጉም አልባ ናት ካለ በኋላ የተነሳበትን ሀሳብ በሚያፈርስ ሌላ ሀሳብ ይደመድማል። » [በካሙ ምልከታ..ግነት ታክሎበት😄]

ካሙ በመቀጠል የሚያነሳው ጥያቄ « ህይወት ትርጉም አልባ ከሆነች ሰዎች የሚገ'ዙት የሞራል ህግጋት አይኖራቸውም የሚል ነው» የሆነ ሁሉን ማድረግ እችላለሁና አደርጋለሁ....ዓይነት። ለምሳሌ ሰዎች ካላዩኝ ወይንም በጉልበቴ ያንን ነገር ማድረግ ከቻልኩ፤ ያንን ግፍ፣ ያንን መጥፎ ነገር፣ ከማድረግ የሚያግደኝ ኃይል የለም ዓይነት ነገር!! ካሙ ለዚህ ዕውቅና ይሰጥና ይሄ ግን የደስታ ምንጭ ሳይሆን «መራራ እውነትን ከመቀበል አኳያ» እንደሆነ ያስረዳል። እንደ ማሳያም ሶስት ምሳሌዎችን ይጠቀማል። አንድ:- ዶን ሁዋን የተሰኘ [ነፍሰ ገዳይ]የሴት አውል ገጸ ባህሪ ያቀርባል። [ ይህ ገጸባህሪ ንስሀ እንዲገባ እድል ቢሰጠውም በድርጊቱ ቀጥሎበት የማይማር ኃጥዕ ሆኗል። ] ካሙ ያየበት መንገድ ግን ይህ ሰው የሰማይ ቤቱን ተስፋ ሳያደርግ..እዚሁ ምድር ላይ ያለውን ኑሮ መሰረት አድርጎ እንደኖረ ነው።

ዶን ሁዋን የተሰኘው ገጸባህሪ ብዙ ሴቶችን በተመሳሳይ መንገድ አማልሎ ያወጣል። ግን ከሴቶቹ ጋር አብሮ የሚቆየው ለትንሽ ጊዜ ነው። ያ ጊዜ ሲያልቅ ወደሌላ ሴት ይሄዳል። 😁 ካሙ ሲያስረዳ:- ህይወት ልክ ሁዋን «ሴቶቹን አማልሎ መተኛቱን» ወደ ትዳር የመሄጃ መንገድ ሳይሆን «ማማለሉን ~ ለማማለሉ ጥቅም ብቻ እንዳዋለው» ሰዎችም ከህይወት ባሻገር ስላለው ሳይሆን እዚሁ ኖረን አጠገባችን ያለውን ማጣጣም እንዳለብን ማሳያ አድርጎታል።

ካሙ «አብሰርዲስት(የህይወት ዘበትነትን የተቀበለ)ሰው የእራሱ ውስጣዊ ጽድቅ እንጂ ከውጪ አድርግ አታድርግ እያለ የሚመራው ሌላ የሞራል ኮድ እንደሌለ ያስረዳል። በወቅቱ [ከነበረው] ከፈጣሪ ህግጋት... የራቁ ሰዎች ሰይጣናዊ ናቸው ከሚለው ሀሳብ በተቃራኒ ለካሙ አብሰርዲስቶች ንጹሐን ያለምንም ማስፈራርያና ሽልማት ወደው እና አስበው ጥሩ የሚሆኑ ንጹህ እንደሆኑ ያትታል።

ገና ከመግቢያው ብዙ ...ፈቀቅ አላልንም። አብራችሁኝ እንዳላችሁ ምልክት ስጡኝ እቀጥለዋለሁ.....

እየቃኘኝ ያለነው የግሪክ ሚት ላይ ተመስርቶ ርዕሱ የተሰየመው The myth of sysphus የሚለው መጽሐፉን ነው።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Fri, 25 Jul 2025 09:16:46 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 24 Jul 2025 14:27:09 +0300
The strong do what they will,and the weak suffer what they must.

Thucydides(dialogue b/n Athenian and melians)
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001583550092 Thu, 24 Jul 2025 13:27:19 +0300
Today በዚህች Theory እስቲ እንፈሳፈስ አንዳንድ የዳርዊን ደጋፊ ስላላቹ በእናተ በኩል ያለውን ሀሳብ ታስቀምጡልኛላቹ እኔ የራሴን ልግለፅ👇👇


"Survival of the Fittest" የሚለው የዳርዊን theory "ቲዎሪ" ተብሎ ሊጠራ የማይገባ utterly absurd እና tautological fallacy ነው ምክንያቱም ይህ gross oversimplification የሕይወትን ተፈጥሯዊ ውስብስብነት፣ ብዝሃነትና ትብብርን ችላ በማለት በቃ "the fittest are simply those who survive" የሚል ባዶ ድግግሞሽ (a mere truism) ብቻ ያቀርባል..የሚገርመው በዳርዊን ዘመን እንኳን እንደ ሄንሪች ስፔንሰር (በሎጂካዊ ስህተቱ) እና ፍሌሚንግ ጄንኪን (በዝግመተ ለውጥ አሠራሩ) ያሉ በርካታ ሳይንቲስቶች ለዚህ fundamentally flawed concept አጥብቀው ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል ታድያ ዳርዊን ምንም ቢል አዋቂ ነውን😁😁 በዚህች ላይ ልቋጨውና መቀጠል ካለብኝ እቀጥላለሁ


React አድርጉ መቀጠል ካለብኝ እንዳልደክም
Подробнее
]]>