Лента постов канала "፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel (@AndEmnet) https://t.me/AndEmnet ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ አስተምሮ ያላቸውን መርሃግብሮች የሚቀርቡበት ቻናል ነው። ከነዚህም መካከል ➯ዝክረ ቅዱሳን (የየቀኑን ስንክሳር)፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ መዝሙር፣ የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ PDF፣ ወቅታዊ የኦርቶዶክሳዊ መረጃዎች እና ወ.ዘ.ተ @AndEmnet Channel @AndEmnetZeeOrtodoxTewahdo Group @JONHABESHA Contact 🙏 ru https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 21 Aug 2025 20:48:05 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 21 Aug 2025 20:48:05 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 21 Aug 2025 20:48:05 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 21 Aug 2025 20:48:05 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 21 Aug 2025 20:48:05 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 21 Aug 2025 20:48:05 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Wed, 20 Aug 2025 11:05:00 +0300
#ነሐሴ_14_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇


"ዘአዘዝከ መድኃኒቶ ለያዕቆብ። ብከ ንወግዖሙ ለኵሎሙ ፀርነ። ወበስምከ ናኃሥሮሙ ለእለ እቆሙ ላዕሌነ"። መዝ.43÷4-5

#ትርጉም፦ "አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያዕቆብ መድኃኒትንህ እዘዝ። በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን"። መዝ.43÷4-5


#የእለቱን_ወንጌል

ማቴዎስ 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ወደ ሕዝቡም ሲደርሱ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ፦ ጌታ ሆይ፥ ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበት ክፉኛ ይሣቀያልና፤
¹⁵ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውኃ ይወድቃልና።
¹⁶ ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው አለው።
¹⁷ ኢየሱስም መልሶ፦ የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ።
¹⁸ ኢየሱስም ገሠጸው ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፥ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።
¹⁹ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ኢየሱስ ቀረቡና፦ እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው? አሉት።
²⁰ ኢየሱስም፦ ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።
²¹ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።
²² በገሊላም ሲመላለሱ ኢየሱስ፦ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፥ ይገድሉትማል፥
²³ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው። እጅግም አዘኑ።

#የሚቀደሰው_ቅዳሴ

#የእመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የፆም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ጾሙን የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነት፣ የበረከት፣ የድኅነት....ጾም ያድርግልን።
#የእናታችን_የእመቤታችን_የቅድስትመ_ድንግል_ማርያም_ወላዲተ_አምላክ ፍቅሯ በልባችን ጣዕሟ ባንደበታችን ይደርብን!!!
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 19 Aug 2025 09:30:00 +0300
#ቡሄ #ጅራፍ_ማስጮህ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው ⁉️


➯ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው።

➯ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡ በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ

➯ቡሄ ማለት:- ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ" አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ

➯ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡ አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ [ማቴ 10፥12] ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት

➯ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት

➯በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡

👉የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣

👉ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

➯በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

@AndEmnet ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 19 Aug 2025 09:29:37 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 19 Aug 2025 09:06:23 +0300
#አባ_ጋልዮን_መስተጋድል (ስንክሳር)

➯በዚችም ቀን ዳግመኛ ተጋዳይ አባ ጋልዩን አረፈ። ይህም በቀንና በሌሊት ለጸሎት የማይታክት ተጋዳይ ሆነ ጐልማሳ ሁኖ ሳለ ከመነኰሰም ጀምሮ እስከ ሸመገለ ድረስ ከበአቱ ቅጽር ውጭ አልወጣም ከማኅበር ጸሎት ጊዜ በቀር ከመነኰሳቱ ማንም አያየውም።

➯ሰይጣናትም ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ መነኰሳትን ተመስለው ወደርሱ በመንፈቀ ሌሊት ገብተው እንዲህ አሉት። እኛ ተሠውረን የምንኖር ገዳማውያን ነን ከእኛ አንዱ በሞት ስለተለየ ከእኛ ጋራ ልንወስድህ ወደን ወዳንተ መጣን ለእርሱም ቃላቸው እውነት መስሎት ልብስና ሲሳይ ወደማይገኝበት ጠፍ ወደ ሆነ ተራራ ላይ እስከ አደረሱት ድረስ አብሮአቸው ሔደ።

➯ሲጠቃቀሱበትም በአየ ጊዜ ሰይጣናት መሆናቸውን አውቆ በላያቸው በመስቀል ምልክት በአማተበ ጊዜ ተበተኑ። በሚመለስም ጊዜ በወዲያም በወዲህም መንገድ አጣ የክብር ባለቤት ወደሆነ ጌታችን ጸለየ ከዚህ በኋላ ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም የሚዘዋወሩ ከአባ ሲኖዳ ገዳም የሆኑ መነኰሳት ተገለጹለት። እነርሱም የዳዊትን መዝሙር ያነቡ ነበር ስለ ሥራው ጠየቁት በእርሱ ላይ የደረሰውን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ ወስደውት በፀሐይ የበሰለ ዓሣ እየተመገበ ከእሳቸው ጋራ አንዲት ዓመት ሙሉ ኖረ።

➯ያመነኰሰው መምህሩ አባ ይስሐቅም ወሬውን በአጣ ጊዜ ፊቱን ያሳየው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አባ ጋልዮንም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ርሱ መጣ አባ ይስሐቅም በአየው ጊዜ በእርሱ ደስ አለው ወዴት ነበርክ አለው እርሱም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገረው።

➯ከዚህም በኃላ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሶ በሰላም አረፈ መነኰሳቱም በክብር ቀበሩት።


➯ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

#ስንክሳር ነሐሴ 13 እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 19 Aug 2025 09:06:22 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 19 Aug 2025 09:06:22 +0300
#ቅዱስ_ሙሴ_ሊቀ_ነቢያት (ስንክሳር)

➯በዚችም ቀን የቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ልደቱ ነው።

➯ዓለም በተፈጠረ በ3,600 ዓመት እሥራኤል በረሃብ ምክንያት ያዕቆብ ወደ ምድረ ግብፅ ወረደ:: በዚያም ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ለ215 ዓመታት ተከብረው ለ215 ዓመታት ደግሞ በባርነት በድምሩ ለ430 ዓመታት በምድረ ግብፅ ኑረዋል። በባርነት ዘመናቸውም 'ራምሴና ጋምሴ' የሚባሉ 2 ከተሞችን (ዛሬ ፒራሚዶች የምንላቸውን) በደም ገንብተዋል። ግፋቸው እየበዛ ሲሔድ ግን ጩኸታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ። ያድናቸውም ዘንድ አንድ ቅዱስ ሰው እንዲወለድ አደረገ። ይኽም ሰው ሙሴ ይባላል።

➯ወላጆቹ መታመናቸውን በፈጣሪያቸው ያደረጉ ዮካብድና እንበረም ሲሆኑ ከሌዊ ነገድ ናቸው፡፡ ከሙሴ ውጪም አሮንና ማርያምን ወልደዋል። ቅዱስ ሙሴ በተወለደበት ወራት ወንድ የእሥራኤል ሕጻናት ይገደሉ ነበር። ጌታ ግን በገዳዮቹ ልቡና ርሕራሔን አምጥቶ አትርፎታል።

➯በተወለደ በ3 ወሩ ወንዝ ላይ ጥለውት ተርሙት (የፈርኦን ልጅ) ወስዳ በቤተ መንግስት አሳድጋዋለች:: ሙሴ ያለችውም እርሷ ናት። 'ዕጓለ ማይ (ከውሃ የተገኘ) ለማለት ነው። ወላጆቹ ያወጡለት ስም ግን 'ምልክአም' ይባላል። ገና ሲወለድ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ ነበርና።

➯ቅዱስ ሙሴ 5 ዓመት በሆነው ጊዜ ፈርኦንን በጥፊ በመማታቱ ለፍርድ ቀርቦ እሳትን በመብላቱ አንደበቱ ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል። እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው 40 ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ። ቅዱስ ዻውሎስ እንደሚለው በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና። (ዕብ. 11÷24)

➯አንድ ቀንም ለዕብራዊ ወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎት ወደ ምድያም ሸሸ። በዚያም ለ40 ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ኖረ። ልጆንም አፈራ። 80 ዓመት በሞላው ጊዜ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው። ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው፡፡ ሙሴም ከወንድሙ ጋር ግብጻውያንን በ9 መቅሰፍት በ10ኛ ሞተ በኩር መታ። እሥራኤልንም ነጻ አወጣ፡፡

➯ሊቀ ነቢያት የሠራቸው ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም፦ እርሱ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ አሻግሯል፣ ግብጻውያንን ከነሠረገሎቻቸው በባሕር ውስጥ አስጥሟል፣ ለሕዝቡ መና ከደመና አውርዷል፣ ውሃን ከጨንጫ (ከዓለት) ላይ አፍልቁዋል፣ በብርሃን ምሰሶ መርቷቸዋል፣ በ7 ደመና ጋርዷቸዋል፣ ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል ነስቶላቸዋል፣ ቅዱስ ሙሴ ለ40 ዓመታት ሕዝቡን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ለ570 ጊዜ ተነጋግሯል።

➯ከጸጋው ብዛትም ፊቱ ብርሃን ስለ ነበር ሰዎች እርሱን ማየት አይችሉም ነበር። ታቦተ ጽዮንንና 10ሩ ቃላትን ተቀብሎ ጽላቱ ቢሰበሩ ራሱ ሠርቶ በጌታ እጅ ቃላቱ ተጽፈውለታል፡፡ ቅዱስ ክቡር ታላቅ ጻድቅ ነቢይና ደግ ሰው ቅዱስ ሙሴ በ120 ዓመቱ ዐርፎ በደብረ ናባው ሊቃነ መላእክት ቅዱሳን ሚካኤል ገብርኤልና ሳቁኤል ቀብረውታል። መቃብሩንም ሠውረዋል። (ይሁዳ 1÷9)
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 19 Aug 2025 09:06:22 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 19 Aug 2025 09:06:22 +0300
#ዝክረ_ቅዱሳን_ነሐሴ_13/፲፫ (ስንክሳር)

እንኳን #ለጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ብርሃነ_መለኮቱን_በደብረ_ታቦር ለገለጠበት ዕለት መታሰቢያ፣ #ለቅዱስ_ሙሴ_ሊቀ_ነቢያት ለልደቱ መታሰቢያ፣ ተጋዳይ ለሆነ #ለአባ_ጋልዩን ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"

#ደብረ_ታቦር

➯ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው።

➯በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ።

➯ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።

➯በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።

➯ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።

➯የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት።

➯ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።

➯ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም።

➯ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ።

➯ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።

➯እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ።

➯ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Mon, 18 Aug 2025 11:44:59 +0300
#ነሐሴ_12_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ

"እግዚኦ ኵነኔከ ሀበ ለንጉሥ። ጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ። ከመ ይኰንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ። መዝ.71÷1-2

#ትርጉም፦ "አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥ ሕዝብህን በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ"። መዝ.71÷1-2


#ነሐሴ_12_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ

ማቴዎስ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ኢየሱስም መለሰ ደግሞም በምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦
² መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች።
³ የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ሊመጡም አልወደዱም።
⁴ ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ፦ የታደሙትን፦ እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፥ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፥ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ በሉአቸው አለ።
⁵ እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥ ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ፤
⁶ የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው ገደሉአቸውም።
⁷ ንጉሡም ተቈጣ፥ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።
⁸ በዚያን ጊዜ ባሮቹን፦ ሰርጉስ ተዘጋጅቶአል፥ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤
⁹ እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ አለ።
¹⁰ እነዚያም ባሮች ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን ሁሉ ክፉዎችንም በጎዎችንም ሰበሰቡ፤ የሰርጉንም ቤት ተቀማጮች ሞሉት።
¹¹ ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው አየና፦ ወዳጄ ሆይ፥
¹² የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ? አለው እርሱም ዝም አለ።
¹³ በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን፦ እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል አለ።
¹⁴ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

የሚቀደሰው ቅዳሴ #የእመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የፆም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ጾሙን የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነት፣ የበረከት፣ የድኅነት....ጾም ያድርግልን።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Mon, 18 Aug 2025 08:58:18 +0300
ነሐሴ ፲፪ / 12


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስከ አሸነፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው።

ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እናደርግ ዘንድ አዘዙን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር

@AndEmnet
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 17 Aug 2025 21:14:07 +0300
🥖#ቡሄ_በሉ🥖

@AndEmnet
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 17 Aug 2025 21:13:36 +0300
ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማው
ብርሃን ከበበው
አሸብርቋል ረጅሙ ተራራ
ክብሩ ሲያበራ

ክብሩ ሲያበራ.....

ጴጥሮስና ያዕቆብ ደግሞ ዮሐንስን
ዩዟቸው ተጓዘ የወረጣቸውን
በፊታቸው ሳለ ድንገት ተለወጠ
ኢየሱስ ሲያበረ ልባቸው ቀለጠ

ክብሩ ሲያበራ....

ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ታዯቸው
ጴጥሮስ በተመስጦ ዳስ እንስራ አላቸው
ፍቅሩን የቀመሰ አይመኝም ሌላ
ክርስቶስ ነውና እውነተኛ ተድላ

ክብሩ ሲያበራ....

በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነውና
ስለመዳናችሁ ስሙት በጽሞና
ብሎ ሲመሰክር የሰማይ ንጉሱ
ከኢየሱስ በቀር አላዩም ሲነሱ
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 17 Aug 2025 21:13:00 +0300
የደብረ ታቦር (ቡሄ) መዝሙራት👇👇👇
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Fri, 15 Aug 2025 11:43:17 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 14 Aug 2025 10:35:57 +0300
#የነሐሴ_8_ምስባክ

ጾመ ፍልሰታ

ንባባት፡ --- ሮሜ. ም፫ ቊ.፱—፳፬ (ወንሕነ እሙንቱ እለ ጸውዐነ ውስተ ክብሩ) ፩ኛ ጴጥ. ም.፬ ቊ. ፲፪—ፍጻሜ ም. (አኃዊነ ኢታንክርዋ ለእንተ ትመጽአክሙ፤) ግብ.ሐዋ. ም.፲፯ ቊ.፴፩—ፍጻሜ ም. (ወጸቢሖ ለእኩ መኳንንት)

ምስባክ
ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ፤
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ፤
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ፡፡

ወንጌል -- ወንጌለ ማቴዎስ ም. ፯ ቊ. ፲፪—፳፮ (ኵሎኬ ዘትፈቅዱ ይገብሩ ለክሙ ሰብእ)
ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ)
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 14 Aug 2025 10:23:45 +0300
ወር በገባ በ8 የቅዱስ አባ (ብሶይ) ብሾይ ወርኀዊ መታሰቢያያ በዓላቸው ነው።

#የገዳም ኮከብ ቅዱስ አባ ብሶይ በግብጽ ሼስና በተባለች ቦታ የተወለደ ሲኾን ሰባት ወንድሞች ነበሩት፤ ከዕለታት ባንዳቸው ለእናቱ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልሟ ተገልጾ “ጌታ ከልጆችሽ መኻከል አንዱን እንዲያገለግለኝ ስጪኝ ይልሻል አላት” ርሷም፤ “ጌታ የወደደውን ይውሰድ” ብላ መለሰችለት፤ መልአኩም ቀጭን የነበረውን ሰውነቱም ደካማ የነበረውን የብሶይን እጁን ይዞ “ዝንቱ ውእቱ ወልድ ለእግዚአብሔር ገባሬ ሠናይ” (ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ የሚሠራ ይኽ ልጅ ነው” አለ፤ ያን ጊዜ እናቱ “የእኔ ጌታዬን እንዲያገለግለው ጠንካራውን ይውሰድ” በማለት ስትመልስ፤ መልአኩም “ጌታስ የመረጠው ይኽነን ነው” ብሎ መልሶላታል፡፡

ከዚያም በ340 ዓ.ም. ቅዱስ አባ ብሶይ ወደ ሲሐት በረሓ በመኼድ ቅዱስ ዮሐንስ.ሐጺርን ባመነኮሱት በአባ ባውማ እጅ ምንኲስናን ተቀበለ፡፡ አባ ባውማ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና አባ ብሶይ በጸለዩ ጊዜ መልአኩ ለአባ ብሶይ ተገልጾለት ወደ ገዳም መርቶ አድርሶታል፤ በዚያም ወደ ርሱ ለተሰበሰቡ ለብዙዎች መነኮሳት አባት ኾኗቸዋል፤ በቅድስና እጅግ የከበረ፤ በፍቅር፣ በደግነት፣ በርኅራኄ የሚታወቁ በተጋድሎም የበረታ ነበረና ዜናው በመታወቁ ቅዱስ ኤፍሬም ወደ አባ ብሶይ መጥቶ አይቶታል፡፡

ጌታችንን በእጅጉ ከመውደዱ የተነሣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በማንበብ በመጻሕፍት ቃል ነፍሱን እያረካ፤ እጅግ ጽኑ የኾነ ተጋድሎን በማድረግ በጾም፣ በጸሎት ይጋደል ነበር፤ ሁሌም ርሱን ለማመስገን ከመሻቱም የተነሣ በምሽት ጸሎት ጊዜ እንቅልፍ እንዳይወስደው ጸጒሩን በገመድ በማሰር ይጸልይ ነበር፤ ዛሬ ድረስ ይኽ ማሰሪያ በዚያው ገዳም አለ፤ በዚኽም ንጽሐ ልቡና መኣርግ ላይ በመድረሱ ጌታችን ደጋግሞ ይገለጽለት ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸውም ጌታ በአምሳለ ነዳይ በእንግድነት ወደ በዓቱ በመጣ ጊዜ በእንግዳ ልማድ ውሃ አቅርቦ ለማጠብ ሲዠምር በምስማር የተወጉ እግሮቹን ዳስሶ በማየቱ ጌታችን እንደኾነ ዐውቋል፡፡ ርሱም በደስታ በመኾን ጌታን ያጠበበትን ውሃ ጠጥቶታል፡፡

ይኽነን ብቃቱን አይተው መነኰሳቱ ጌታችን እንዲገለጽላቸው ይለምንላቸው ዘንድ እጅጉን በዘበዘቡት ጊዜ ወደ ጌታችን አመለከተ፤ ጌታም በተራራው ላይ እንደሚገለጽ ነግሮት ለመነኰሳቱ ኹሉ ነገራቸው፤ እነርሱም በማለዳ ወደ ተራራው ጫፍ ሲገሰግሱ ከተራራው ሥር ጌታን በአምሳለ አረጋዊ ኾኖ በመገለጥ ይዘውት እንዲወጡ ቢጠይቃቸው አንዳቸውም በእንቢተኝነት ጸንተው ወደ ተራራው ይሮጡ ጀመር፡፡ በመጨረሻም አረጋዊዉ አባ ብሶይ ወደ ተራራው ሊወጣ ሲል በአምሳለ አረጋዊ የተገለጸው ጌታችን ዐዝሎት እንዲወጣ ጠየቀው፤ አባ ብሶይም በትሕትና በመኾን ታዝዞ ዐዝሎት ሲወጣ በእጅጉ ከበደው ቀስ እያለ ግን ቀለል ቀለል እያለው መምጣቱን ዐውቆ ጌታችን መኾኑን ተረድቶ ቀና ብሎ ቢያይ ዠርባው ላይ በፍቅር የታዘለው ርሱ ነው፤ ጌታም ስለ ትሕትናው ለርሱ እንደተገጠለት ነግሮት አባ ብሶይን ባርኮታል፤ በመኾኑም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ያዘለበት የአባ ብሶይ ሰውነት ዛሬ ድረስ ሳይፈርስ ሳይበሰብስ ብዙ ተአምራትን እያደረገ በገዳሙ አለ፡፡

ቅዱስ አባ ብሶይ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ክዶ የነበረውን በበረሓ የነበረውን ሰው ስለ ነገረ መንፈስ ቅዱስ ከብሉይ ከሐዲስ በምሳሌ ጭምር በስፋት አስተምሮ እንዲመለስ አድርጓል፤ ቅዱስ አባ ብሶይም ብዙዎች ተጋድሎዎችን ካደረገ በኋላ ሐምሌ 8 በ417 ዓ.ም. በመዐዛ ገነት፣ በይባቤ መላእክት ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጥቷል፡፡

የቅዱሳኑ በረከት ከእኛ ጋር ትሁን፡፡

#መጋቤ_ሐዲስ_ሮዳስ_ታደሰ
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Thu, 14 Aug 2025 10:23:35 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Wed, 13 Aug 2025 11:31:04 +0300
#ነሐሴ_7

የዕለቱ ምስባክ እና ወንጌል


የዕለቱ ምስባክ:- መዝ ፺፫ ፥ ፲፪

ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ::
ወዘመሀርኮ ሕገከ::
ከመይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት::

ትርጉም
አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም
ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው፡፡

የሚነበበው ወንጌል፡- የማቴዎስ ወንጌል፡- ምዕ ፲፮፥ ቁጥ ፲፫

በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ )

@AndEmnet
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 12 Aug 2025 21:24:28 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 12 Aug 2025 21:24:00 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sat, 09 Aug 2025 10:16:17 +0300
#ሳይፀልዩ_ማደር #ይነበብ


የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋ ፀለየች....
"አውጣኝ አውጣኝ" አለች - ለፈጠራት ጌታ ነብሩም ተርቦ
ወደ አምላኩ ቀርቦ
ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ
ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ
.
የሁለቱን ማብላት - የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም -
ሰማቸው
ፈጣሪ
አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት
"እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታ ጠላት"
.
ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት
ምግብህ አርገህ ብላት" ሚዳቆዋ ስትሮጥ
ከነብር ለማምለጥ
ነብሩም ሲከተላት
ሆዱን ሊሞላባት
.
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ ሆዱን ብትረግጠው
የተኛው
ከርከሮ
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር
.
አውጣኝ ያለው ወቶ - አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ

እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይስማን

@AndEmnet
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sat, 09 Aug 2025 09:55:53 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Fri, 08 Aug 2025 08:00:19 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Wed, 06 Aug 2025 21:57:29 +0300
#ፍልሰታ_ምን_ማለት_ነው?



➥ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

➥ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

➥ ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

➥ ‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

➥ ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡››

➥ ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

➥ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

➥ ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

➥ እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

➥ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

➥ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡

➥ ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡

መልካም ፆም
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Wed, 06 Aug 2025 21:37:43 +0300
እንኳን ለፍልሰታ ጾም አደረሳችሁ!


@AndEmnet
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 03 Aug 2025 00:42:59 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 03 Aug 2025 00:42:59 +0300
#ቅዱስ_ሴት_ነቢይ (ስንክሳር)

➯ዳግመኛም በዚህች ቀን የአዳም ልጅ ሴት ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፡፡ ሔኖስንም ወለደው፡፡ ሔኖስንም ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፡፡ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፡፡ መላ ዕድሜውም ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት በሆነ ጊዜ በሰላም ዐረፈ፡፡


➯ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#ስንክሳር ሐምሌ 27 እና #ከገድላት_አንደበት
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 03 Aug 2025 00:42:59 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 03 Aug 2025 00:42:59 +0300
#ቅድስት_መስቀል_ክብራ (ስንክሳር)

➯በዚህችም ቀን ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት መስቀል ክብራ ዕረፍቷ ነው፡፡ ይኽችም ቅድስት የቅዱስ ላሊበላ ባለቤት ስትሆን የትውልድ ሀገሯ ወሎ ላስታ ቡግና ነው፡፡ የታላቁ ጻድቅ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ ሚስት ናት፡፡ ከእርሱም ደገኛውን ይትባረክን ወልዳለች፡፡ ቅዱስ ላሊበላን እና ቅድስት መስቀል ክብራን ሁለቱ እንዲጋቡ ያዘዛቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ዲዛኖችና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር ከመለሰው በኃላ ድጋሚ ተገልጦለት "እንዳንተ የተመረጠች ናት እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል፡፡

➯ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል፡፡

➯ቅድስት መስቀል ክብራን ወደ ትግራይ እየመራ የወሰዳት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እርሷን በትግራይ ቅዱስ ሚካኤል እንዲጠብቃት ከተዋት በኃላ ቅዱስ ላሊበላን ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ መንግሥተ ሰማያት አውጥቶታል፡፡

➯ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ሆና መልአኩ እየጠበቃት ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል፡፡

➯ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች፡፡ ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዱጠመቁ አድርጋለች፡፡
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 03 Aug 2025 00:42:59 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Sun, 03 Aug 2025 00:42:59 +0300
#ዝክረ_ቅዱስ_ሐምሌ_27/፳፯ (ስንክሳር)

እንኳን #ለቅዱስ_አሞን በሰማዕትነት ላረፈበት መታሰቢያ፣ ለኢትዮጵያዊቷ #ለቅድስት_መስቀል_ክብራ ለዕረፍቷ መታሰቢያ፣ ለአዳም ልጅ #ለቅዱስ_ሴት ዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡

"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"

#ሰማዕቱ_ቅዱስ_አሞን

➯ሐምሌ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን ቅዱስ አሞን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኸውም ቅዱስ ተርኑጥ ከሚባል አገር የተገኘ ሰማዕት ነው፡፡ ወደ ላይኛው ግብጽ በሄደ ጊዜ የእንዴናው ገዥ ሰማዕታትን ይዞ በጽኑ ሲያሠቃያቸው ተመለከተ፡፡ እርሱም በመኮንኑ ፊት ቀርቦ የጌታችንን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው፡፡ ሥጋውን ሁሉ ሰነጣጥቆ ከጣለው በኋላ ዳግመኛ በትላልቅ ችንካሮች ቸነከረው፡፡ ነገር ግን ጌታችን አጽናንቶ ከቁስሉ ፈውሶ ጤነኛ አደርጎ አስነሣው፡፡

➯መኮንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ቅዱስ አሞንን ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው፡፡ በዚያም ሳለ ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራና ገድሉን ለሚጽፍ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍ ቃልከዳን ከገባለት በኋላ ሰማዕትነቱን በድል እንዲፈጽም ነገረው፡፡

➯ወዲያውም ይዘው ጽኑ በሆኑ ልዩ ልዩ ሥቃዮች አሠቃዩት፡፡ ጌታችንም ከመከራው እያዳነው ልዩ ልዩ ተአምራትን ስላደረገለት ይህንን ያዩ ብዙዎች ‹‹በቅዱስ አሞን አምላክ አምነናል›› እያሉ በመመስከር ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡ እነርሱም ውስጥ ቲዮጲላ የምትባል ድንግል ነበረች፡፡ እርሷም ወደ መኮንኑ ዘንድ በመሄድ በጌታችን ታመነች፡፡ መኮንኑም እቶን እሳት ውስጥ ከተታት ነገር ግን እሳቱ አላቃጠላትም፡፡ በመጨረሻም ራሷን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች፡፡

➯ከዚህም በኋላ አባለ ዘሩንና አካሉን ሁሉ በሰይፍ እየቆረጡ ቅዱስ አሞንን እጅግ ካሠቃዩት በኋላ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Wed, 30 Jul 2025 20:47:46 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 29 Jul 2025 17:59:57 +0300
እውቀታቸው፣ ለሃይማኖታቸው ያላቸው ቀናዒነት እና ከንጉሣዊው ቤተሰብ ጋር የነበራቸው ቅርበት፣ በ1920 ለጵጵስና ከተመረጡት የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን አንዱ ሆነው ለመመረጥ አስችሏቸዋል፡፡ “ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ሞአ” በሚል ማዕረግ፣ በሀገረ ግብጽ፣ እስክንድሪያ በሚገኘው የቅዱስ ማርቆስ ገዳም ማዕረገ ጵጵስና ተቀበሉ፡፡ ከዚህ በኋላ፣ አቡነ ጴጥሮስ የሀገረ ስብከታቸውን ዋና ጽሕፈት ቤት ደሴ ላይ በማድረግ፣ የመንዝ አውራጃ እና የወሎ ክፍለ ሀገር ጳጳስ ኾነው ተሾሙ፡፡

በ1927 ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስትወርር፣ በዘመኑ እንደነበሩት አብዛኞቹ የቤተ ክህነት ሰዎች፣ አቡነ ጴጥሮስም ከአጼ ኃይለሥላሤ ጋር ወራሪውን ለመመከት ወደ ማይጨው ዘመቱ፡፡ ሆኖም የወራሪው ጠላት ኃይል አይሎ፣ ንጉሡ ሀገር ጥለው ሲወጡ፣ አቡነ ጴጥሮስ ከአርበኞች ጋር ለመቆየት ወሰኑ፡፡

መቀመጫቸውን በደብረ ሊባኖስ ገዳም በማድረግ፣ አርበኞች ለሀገራቸው ነጻነት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ያደፋፍሩ ነበር፡፡

ሐምሌ 20 ቀን 1928 አቡነ ጴጥሮስ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የፋሺስት ጦር ከመዲናዋ በአራት አቅጣጫ ለማጥቃት ሲወጠን አቡነ ጴጥሮስ የዕቅዱ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በዕቅዱ ከመሳተፍ ባሻገር ራሳቸውም ጠብመንጃ ታጥቀው ከበስተ ሰሜን በኩል ጥቃት ከሚሰነዝረው የሰላሌው የአርበኞች ቡድን ጋር ተቀላቀሉ፡፡

በዕቅዱ መሠረት ጥቃቱ ሲፈፀም በተካሄደው ከባድ ውጊያ በጠላት ላይ ትልቅ ጉዳት ማድረስ ቢችሉም፣ በደጃዝማች አበራ ካሳ የሚመሩት የሰላሌ አርበኞች እና ሌሎችም ቡድኖች ማፈግፈግ ግድ ሆነባቸው፡፡ በማፈግፈግ ላይ ሳሉ ግን፣ አቡነ ጴጥሮስ በጣሊያኖቹ እጅ ላይ ወደቁ፡፡

ሐምሌ 22 ቀን 1928 በመሃል አዲስ አበባ፣ ዛሬ የስማቸው መጠሪያ በኾነው አካባቢ፣ በስምንት የኢጣሊያ ወታደሮች የእሩምታ ተኩስ በአደባባይ ተረሸኑ፡፡ 

በረከታቸው ይደርብን
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 29 Jul 2025 17:59:38 +0300
#አቡነ_ጴጥሮስ


በ1880 በሸዋ ክፍለ ሀገር፣ #ፍቼ የተወለዱት አቡነ ጴጥሮስ፣ ከአርበኞች ጋር ለነጻነት ትግል ሲያካሂዱ ተይዘው፣ በስምንት የጣሊያን ወታደሮች በአዲስ አበባ ከተማ በአደባባይ በግፍ የተረሸኑት፣ የዛሬ 89 ዓመት ነበር፡፡

በ1920 ከእስክንድሪያ ቤተ ክርስቲያን በይፋ ማዕረገ ጵጵስናን ከተቀበሉት የመጀመሪያዎቹ አራት ኢትዮጵያውያን አንዱ የኾኑት አቡነ ጴጥሮስ ከ1928 እስከ 1933 ለአምስት ዓመታት በዘለቀው የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ለጠላት አንበገርም በማለት ሕይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር የሰጡ ሰማዕት ናቸው፡፡

ቀዳሚው የመጠሪያ ስማቸው ኃይለ ማርያም ሲኾን፣ ከገበሬ ቤተሰብ ነው የተወለዱት፡፡ ሀገራዊውን የቤተ ክህነት ትምህርት በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተማሩት አቡነ ጴጥሮስ በ1908 ገደማ ነበር ሥርዓተ ምንኩስና የፈፀሙት፡፡

አቡነ ጴጥሮስ በጎጃም (ዋሸራ)፣ በጎንደር እና በቦሩ ሜዳ በሚገኙ ገዳማት ውስጥ ኖረዋል፡፡
የመምህርነት ሕይወታቸውን ወሎ፣ ሳይንት በሚገኘው ምስካበ ቅዱሳን ገዳም ቅኔ እና መጻሕፍት በማስተማር የጀመሩት አቡነ ጴጥሮስ፣ ኋላ በቤተ ክህነት የማስተማር ብቃታቸው ተመስክሮላቸው ወላይታ ወደሚገኘው የደብረ መንክራት ገዳም ተዛውረዋል፡፡

… በ1916 በዝዋይ ሐይቅ ደሴት ላይ ለሚገኘው የደብረ ማርያም ገዳም በዋና መምህርነት ተመደቡ፡፡ በ1919 ደግሞ በገነተ ልዑል ግቢ በሚገኘው የመንበረ ልዑል ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን መምህር ኾነው የተመደቡ ሲኾን፣ በዚያም የደጃዝማች ተፈሪ (ኋላ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሤ) የነፍስ አባት ኾኑ፡፡
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001627214774 Tue, 29 Jul 2025 17:58:44 +0300
22🕯"ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ መፅሐፈ እዝራ 2:122"


የመልአኩ በረከቱ ፣ ፍቅሩ ፣ ጸሎት ልመናው፣ አምላጅነቱ አይለየን ክፉውን ሁሉ በክንፎቹ ይጋርድልን
Подробнее
]]>