Лента постов канала Thoughts (@justhoughtsss) https://t.me/justhoughtsss ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም? comment for the writer : @nhymn discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk Tiktok: https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1 Since: Dec-10-2022 ru https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 19 Aug 2025 14:57:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 19 Aug 2025 13:24:17 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 18 Aug 2025 23:32:01 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 18 Aug 2025 23:31:25 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 18 Aug 2025 17:18:34 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 17 Aug 2025 14:58:51 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 17 Aug 2025 10:37:21 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sat, 16 Aug 2025 21:31:03 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sat, 16 Aug 2025 21:30:08 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sat, 16 Aug 2025 21:01:28 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sat, 16 Aug 2025 07:24:11 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sat, 16 Aug 2025 07:23:56 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 15 Aug 2025 23:31:28 +0300
ህይወትን ወደ ሁዋላ ለማሰብ ስሞክር መመለሱ ዳገት ቢሆንብኝም፣

እነዛ የድሮ ትዝታዎች አሁንም ቢሆን ደስ ይሉኛል፣

ልክ ለመሰታቢያ ተብሎ እንደሚበራ ሻማ፣

ሲጠፋ ሀዘኑ እንዳይረሳ ተብሎ እስካሁን እንዳልበራ ሻማ፣

ስንኖር እንደሚሞት ሰው ብንኖር ጥሩ ነው፣
ከዚህም በላይ ሁለት ሞት ባትሞቱ ፀሎቴ ነው፣

ሁሉም ከንቱ መሆኑን ሞት ቤት ገብቶ እስኪያስታውሳቹ አትቆዩ...
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 15 Aug 2025 19:24:45 +0300
📩💌📨 ደብዳቤዎቻችን...📜#


አታውቂም እንዲደርሱሽ እንድታያቸው የምፈልጋቸው ብዙ ደብዳቤዎች የእሳት እራት መሆናቸውን።ጊዜ አልፎ ዛሬ ለማያውቁኝ ለማላውቃቸው ስለአንቺ መጻፌ ግን ለምኑ ምናልባትም ለአልፎ ሂያጅ ራስ ምታት የማስታገሻ እንክብል እንደመዋጥ አይነት ስሜት ነው !!

መሆንና አለመሆን:መኖርና አለመኖር:ትዝታና ናፍቆት:ማለዳና ምሽት:በረዶና እሳት:እኩለ ቀንና እኩለ ሌሊት ብዙ ተቃራኒ ስሜቶች በድንገት ቢዋሃዱ የሚፈጥሩት ክስተት እንደዛ ነን እኔና አንቺ !!


ምን እንደሚገርመኝ ታውቂያለሽ አንቺን እንደ መሻቴ አውርቼሽ ጽፌሽ ተሳክቶልኝ አለማወቁ! እኔ ጋር ግዝፈትሽ እኔንም ያስፈራኛል።

የህይወቴ turning point ያ ይመስለኛል አንቺ ስትሄጂ!! ልዩነቱ እስከማይገባ ድረስ ከራስ አዋህደው የያዙት ሰው ነበር መሆን በቀስታ መሞት አይነት ሕመም ነው ልኩ !!

ማመስገኔም ማማረሬም መሃል አለሽ :መፈለግንም አለመፈለግንም እኩል ነሽ አንቺ !ማወቄንም አለማወቄንም ብቻውን አታስመርጪኝም !!ከሁሉም መብሰልሰሎቼ በኋላ አንድ ቃል ብቻ ይቀርልኛል ማነሽ ??

ከሚያውቀኝ አብዛኛው ሰው ምቾት በማይሰጠው ገጼ በኩል ነበር መምጣትሽ :ከመድረስሽ ለረጅም ጊዜያት ካሰቃየኝ እሳቤዬ ሸሸግሽኝ እንዴት እንደሆነ ሳይገባኝ የምሸሸውን ነገር ውበት አሳየሽኝ።እኔን የያዝሽበት መንገድ ጋር ሰላም ነበረው !!


ቆይ እስኪ ንገሪኝ ስለማውቅሽ እድለኛነቴን ልመን ወይስ ስትሄጂ ስለሰመጥኩበት hell ላጉረምርም? ባላውቅሽ ብዬ ያስተማርሺኝን ሁሉ ልካድ ወይስ ባትመጪ ኖሮ የምኖርበትን ቅሽምና ልምረጥ ??

ለምን ትተሽኝ ሄድሽ ?ብዬ እንኳን እንድወቅስሽ አይደለምና አካሄድሽ የሆነ አየር ላይ እንደ መበተን ጥግ አጥቶ እንደመቅበዝበዝ  ያለ ከለምን የሚሸሽግ ምክንያት አልባ ነው።


እውነታው ግን ዛሬም ካለሽበት ጊዜ ባልተዛነፈ ልክ እወድሻለሁ ነው !!ሃቁ አንቺን ከመጥላት ጋር አብሮ የሚያኖር እኔነት የለኝም ነው።የገባኝ ልረሳሽ ከራሴ ጋር በተስማማሁበት ቅጽበት የበለጠ መድመቅሽን ነው።

ያለ ቃላት ልውውጥ ባለ መግባባት ውስጥ የማምነው አለመኖር ውስጥ ባለ የማይብራራ መኖር ውስጥ መኖርሽን መኖሬን ነው።ያንን ታውቂያለሽ ያንን አውቃለሁ እርሱ በቂ ነው !!

ከሁሉም በላይ ግን መሄድ መተው ማቆም ያልቻሉ ሰዎች ስሜት የሚገባኝ እንዴት አቃታቸው? የማልል ትሁት አድርገሽኛል !!


✍️🖤  [not sad just mysterious £]


https://t.me/yeesua_queen
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 14 Aug 2025 23:32:56 +0300
እያንኳኩ ነው።

ኳኳታቸው ቀለም ቢኖረው ከፈዛዛ ሮዝ ወደ ቀይ ከዛ ከቀይቡኒ ወደ ጥቁር ሲቀየር ይታይ ነበር። መጀመሪያ ትህትና ያለው ኳኳታ "እዚህ ቤት..." የሚል ድምፀት ያለው ከዛ በኋላ ግን "ኧረ እዚህ ቤት" ወደሚል ብስጭት ተቀየረ ሲቆይ "እንዴነችና ምን ስለሆንክ ነው የማትከፍተው ወደሚል ቁጣ ተቀጣጠለ።

ቡኒ ቀለሙ የተላላጠው በሬ በመቀርቀሪያው ግድግዳውን አጥብቆ ይዞ ሰዎቹ እንዳይገቡ እየተከላከለለኝ ነው። ከማጠፊያው የሚወጣው ሲቃ ግን "ብዙ ልንጠብቅህ አንችልም" የሚል የድረሱልኝ ጥሪ ይመስላል።

እስካሁን ያቆየኋቸው የመጀመሪያው ረቂቅ ሊታተም እንደማይችል እና ለእርማት ጊዜ ስጡኝ ብያቸው ነበር። የሰጡኝ ጊዜ ስላለቀ የታረመውን ሊወስዱ ነው አመጣጣቸው እኔ ግን እርማት አልወድም ስለዚህ አላረምኩትም።

ያልታረመ ፅሁፍ ፍፁም አይደለም አይወደድም ይሉኛል ግን ለመወደድ ፍፅምና ካስፈለገ ማንና ምንድነው የሚወደደው? ደግሞስ ፍፁም ከሆነ ተፍጥሯዊነቱን አያጣም?

ኳኳታቸው እየጨመረ ነው

ምናልባት ብደብቀው ይሻል ይሆን? የት ብዬ? ምክንያቱም ለኔ መፅሀፍ መፃፍ በጠረጴዛ እና በወንበር የተወሰነ ተግባር አይደለም። ሳሎኔ ውስጥ ያለው ቦርድ ሴራዬን የምጠነስስበት በቀስት ወዲህና ወድያ የተያያዙ ፅሁፎች ያሉበት ነው። እቃ ቤቴ በገፀባህርያቴ የምግብ ምርጫ መሰረት የተዘጋጀ ነው። በየግድግዳው ላይ የሆነ የታሪኩን አካል ማግኘት አዲስ አይደለም። ምክንያቱም ለኔ ገፀባህርያቶቼ የኔ ፍጥረቶች አይደሉም። የኔ ስብዕናዎች ናቸው። ድክመቶቼ ጥንካሬዎቼ የበቀል ጥንስሶቼ ምናምን ምናምን

የምፅፈው ለህዝብ አይደለም ከራሴ ጋር ለማውራት ነው። ደርዘን ልሞላ አንድ መፅሀፍ ሲቀረኝ ነው ያገኙኝ አሳታሚዎቹ በታሪኩ በኩል

ታሪኩ ቡና የሚወድ ገፀባህሪዬን ወክዬ ቡና ልጠጣ ስወጣ ያገኘሁት ወጣት ነው። በእጄ ወረቀት እና እስክርቢቶ ሲያይ "ደራሲ ነህ?" አለኝ "አዎ እፅፋለሁ አልኩት ደረቴን ነፍቼ እባክህ ስራዎችህን አሳየኝ ብሎ መቀመጫ መቆሚያ ሲያሳጣኝ ቤቴ ይዤው ሄድኩ

ትዕንግርት ሆኖበት በወረቀት የተጥለቀለቀ ቤቴን አይቶ ሲጨርስ መፅሀፍ መደርደሪያው ጋር ቆሞ "ለምንድነው ከራስህ መፅሀፍ ውጪ ሌላ መፅሐፍ የሌለህ አለኝ "አንድ ቤት ውስጥ አንድ ፈጣሪ ይበቃል" ስለው ከት ብሎ ሳቀና "እንደዚህም ጉረኛ መሆን ይቻላል" እያለ ሲያበሽቀኝ ቆየ

ከዛ ከመሀል "የአልጋ ስር ኑሮ" የሚለውን መፅሀፌን ወሰዶ "አንብቤ ልመልስልህ" አለ ምቾት ባይሰጠኝም ፈቀድኩለት

አንብቦ ሲመልስ ግን ብቻውን አልመጣም አሳታሚዎች ይዞ መጣ። ታትሞ ይሸጥ ብለው በስንት ሊያሳምኑኝ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቶ ሄዱ።

በስንተኛው ጊዜ በታሪኩ ስም ታትሞ ገበያ ላይ አየሁት። የዛን ቀን ያሳለፍኩትን እኔና እግዜር ብቻ ነን የምናውቀው ተቃጠልኩ። ለመተኛት ስሞክር ገፀባሕርያቶቼ በህልሜ እየመጡ "ስትዝረከረክ ይኸው በሌላ ሰው ስም አደባባይ ወጥተናል አሁን እኮ አትረቡም ይሉናል ይሰድቡናል። አንተን አምነን ብንገጥልህ የሰው መጫወቻ አደረግከን" ብለው ሲያቃዡኝ ነጋ

ከዛ በኋላ ጥበብም አኮረፈቺኝ ባዶ ቤቴ ውስጥ ጭራሽ ብቻዬን አስቀረቺኝ። ቃላቶቹ ቀለም ለብሰው ወረቀት ተንተርሰው ህያው መሆንን ነፈጉኝ።

ከስንት ደጅ ጥናት በኋላ ደግመው ገቀበኙኝ ብዙ ወራት አብሬያቸው ቆየሁ። ስለነሱ ብቻ ደጋግሜ አሰብኩ ፃፍኩ። ከዛ አሳታሚዎቹ ደግመው መጡና ከባለፈው በደንብ ስለተጠቀምን ቀጣዩንም አምጣ አሉኝ የሚያልቀው ካራክተሩ በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ ነው አልኳቸው

በል መጨረሻ ስጠው እና እንወስደዋለን አሉኝ። ለኔ የነገሩኝ ይሄን ያህል ብቻ ከሆነስ ከዛ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ካላወቅኩስ ደግሞስ ሁሉም ነገር መጨረሻ ያገኛል እንዴ?

መቀርቀሪያው በድብደባ ብዛት እየተንሸራተተ ነው

ቆይ ከወሰዱት ምንድነው የማደርገው? ድጋሜ ብቻዬን ልቀር ነው? የብዙ ወራት ደባሎቼን የሆኑ ሰዎች ሊወስዷቸው ነው?

ኳኳታው ቀጥሏል


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 14 Aug 2025 23:31:41 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 13 Aug 2025 22:07:24 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 13 Aug 2025 17:40:30 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 13 Aug 2025 13:35:36 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 13 Aug 2025 13:35:00 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 13 Aug 2025 11:47:03 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 13 Aug 2025 11:44:23 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 12 Aug 2025 18:57:21 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 12 Aug 2025 12:08:22 +0300
የተወሰነ የእድሜ ክልል የሚመለከት ቢሆንም እኔን ይመስላል ካላችሁ እነሆ

አስተውላችሁታል ስንሰበሰብ የምናወራው ከtiktok trend እና tiktoker እንደማይዘል? የሚያግባቡን ነገሮች በmeme ካልተደገፉ ያወራን የማይመስለን

እስኪ እኛን ስናረጅ አስቡን ምን አይነት አያቶች እንደምንሆን ምን አይነት ወሬ ነው ለልጅ ልጆቻችን የምናወራላቸው (ያው ሁላችንም scroll እያደረግን ካልሆነ)

መጋቤ ሀዲስ እሸቱ ምን አሉ "ወደፊት 'አቤት በኛ ጊዜ የነበረ tiktok አቤት ስድብ ፐ' እያላችሁ ልታወሩ ነው?" ብለው ነበር

ያው የተሰበሰው ሰው ስቋል ግን ወይራው ከባድ ነው። ደቂቃ የማይሞላ attention span ይዘን ትንሽ ቁምነገር የሚያንገሸግሸን ከሆነ ከባድ ነው

ትላልቆቹን መፅሀፎችማ ተዉአቸው። ማን ትዕግስት ኖሮት

ስለዚህ ምን ይሻላል?

ከስልካችን መላቀቅ ስልክ ማጥፋት ምናምን ሁላችንም ሞክረን ያቃተን ይመስለኛል። ስለዚህ ዘዴ መጠቀም ነው የሚሻለው

1. youtube

youtube በአግባቡ ለተጠቀመበት ተዝቆ የማያልቅ እውቀት የሚገኝበት ቦታ ነው ስለዚህ shorts ማየት እናቁምና TedTalk እንይ

TedTalk ቢበዛ 18 ደቂቃ ንግግር የሚደረግበት ፕሮግራም ነው። ተጋባዦቹ እንግዶች በተሰማሩበት ስኬታማ የሆኑ እና እንዴት አድማጭን በአግባቡ መያዝ እንዳለባቸው የሚያውቁ ናቸው

ስለዚህ ውስጣችሁ ስለሚፈልገው ነገር tedtalk ላይ የተወራውን ስሙ። 18 ደቂቃ ባልሞላው ጊዜ ብዙ ነገር ትማራላችሁ

2. Substack

ይሄ application እስካሁን ብዙ ሰው በደንብ ያላወቀው ግን ጥሩ ይዘት ያለው ከተለመዱት social media platform የተለየ ነው። substack ላይ በተለያየ ጉዳይ ላይ የተፃፉ articles ታገኛላችሁ። ይሄ አንደኛ እወቀታችሁን ያሰፋል ሁለተኛ ደግሞ focus ይጨምራል።

ስለዚህ ዝም ብላችሁ tiktok ላይ ከምትውሉ እና ደባሪ ሰዎች ከምትሆኑ ትንሽ እውቀት...

✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 12 Aug 2025 12:07:44 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 11 Aug 2025 22:54:13 +0300
  ደወለች!

ግን ስሟ ስልኬ መስታወት ላይ ሲውለበለብ ልቤ እንደድሮ አታሞውን አልሳተም አዕምሮዬም ራሴን ለመግዛት ብዙ መልፋት አላሻውም።

ደስ አለኝ "ረስቻታለሁ" ብሎ ማውራት ሳይሆን በተግባር ሰውነቴ ራሱ ሲያረጋግጥልኝ ደስ ወረረኝ። የጨበጥኩት እጄን ከፍቼ ሳየውም እንደድሮ ላብ አላራሰውም። "እንዲ ነው እንጂ አንበሳ አብርሀም" እያልኩ ፈገግ ብዬ አነሳሁት

"የት ነህ?" አለች "የት ልምጣ?" ነበረ የምላት ለምዳለች "ህይወቴን ለምሳ ቀጥሬያት እየጠበኳት ነው" አልኳት መተካቷን ለማስታወስ እሷንም ህይወቴ ነበረ ስለምላት

ከነከናት መሰል "ህይወቴ?!ደሞ ከመቼ ወዲህ ነው አንተ ቀጠሮ ቀድመህ መድረስ የጀመርከው" አለች ጠበቅ አድርጋ ቃላቶቹን "አብርሽ አመረረክ እንዴ የዛችን ልጅ ነገር?!" አለችኝ "ምነው እውነት አልመሰለሽም ነበር?!" አልኳት

"አዋ!! እንዴ የምር ግን ወደሀት እንዳይሆን?! አብርሽ የምር ትወዳታለህ እንዴ?!" አለች ድምጿ ላይ ጥርጣሬ እየተስተዋለ

"መውደድ ቢሉሽ መውደድ መሰለሽ ህይወቴን ነፍሴን ብትፈልገው እንኪ ብዬ ብሰጣት አይከፋኝም" አልኳት
"ቆይ እንዴት...?" ብላ ዝም አለች በቀላሉ መተካቷ ቆርቁሯት

"እንዴት ልበልሽ...ድሮ እናቴ መማር የምትፈልገው ትምህርት ነበረ እና ምዝገባው ሊያልቅ አንድ ቀን ሲቀረው በአጋጣሚ ባየችው ማስታወቂያ ነው ተመዝግባ መማር የቻለችው እናቴ ያንን አጋጣሚ ከነ ቀኑ አትረሳውም ለኔም እሷን ያገኘሁበት ቀን እንደዛው ነው በአስራ አንደኛው ሰዓት ነፍሴ ስትፈልጋት የነበረችውን ሌላ ነፍስ ከዚ ሁሉ እልፍ ህዝብ መሀል ያገኘሁበትን ቀን ሳስበው ከእድለኛ በላይ እድለኛ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ

እሷን ሳስብ ምን እንደሚሰማኝ ታውቂያለሽ በመንገድ ስታልፊ በህፃንነትሽ የምትወጂው ዘፈን በሬዲዮ ተከፍቶ ስትሰሚ የሚሰማሽ ልብ የሚያሞቅ ደስታ

በቃ እንዴት ልበልሽ ለረጅም ጊዜ ማንበብ የምትፈልጊው መፅሀፍ መግዛት ቸግሮሽ ልትተዪው ስትዪ መፈለግሽን እንኳን የማያውቅ ወዳጅሽ ስጦታ ሲሰጥሽ የሚሰማሽ አይነት ደስታ ነው የምትሰጠኝ

እሷን ማግኘት ማለት ከረጅም አድካሚ የስራ ቀን በኋላ ትኩስ ምግብ እንደመብላት ወይ ደግሞ ሄዶ አልጋ ላይ እንደመዘረር፣ ከረጅም እንቅልፍ እንደመንቃት፣ በልቶ እንደመጥገብ፣ በዝናባማ ጠዋት ስራ የለም ተብሎ እንደመተኛት ብቻ ምን ልበልሽ በደስታ መንሳፈፍ ማለት ናት" አልኳት

"አምኜሀለው... በደንብ ወድቀህላታል... ደግሜ አልደውልም እሺ" ብላ ዘጋቸው የበለጠ ደስ አለኝ ስለሷ ማውራት ራሱ በቂ አይደል እንዴ ቀኔን ለማብራት?!

"አብርሽ..." አለች ህይወቴ ከጀርባዬ ቆማ "ወዬ" ብዬ ስዞር አፏን በእጇ ሸፍና አይኗ አቅርሯል "ምነው? ምን ሆንሽብኝ??" ብዬ ተነስቼ ሳያት "ያልከውን ሁሉ ሰምቻለሁ እኔም እወድሃለሁ እሺ" ብላ አቅፋኝ የደስታ እንባ አነባች

✍ናኒ



https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 11 Aug 2025 22:54:10 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 11 Aug 2025 18:32:17 +0300
@Jaymasangula_bot | info
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 11 Aug 2025 09:51:19 +0300
Realized Reality

Part - One

“Damn! He is fine. If only I was 18 or so, I would’ve the courage to ask for his number.”

Looking at the plumber who came to their house to look at their sink which has been leaking since yesterday making the kitchen a complete mess.
.......

Daisy is an only child for her parents and as lonely as it may seem, the truth was quite far from what someone would expect. Although she has been living with her widowed mother after losing her husband 2 years ago to an illness, she was definitely not lonely. Her cousins near by used to hang out with her all the time, probably out of pity. But she didn’t mind at all because what she needed the most was a person to spend the time with. Her mother was a strong-willed woman henceforth she quickly recovered from her husband’s death and tried her best to fulfill the duties of both being the breadwinner and doing the house chorus. Even though it was hard on her at first she adapted her new situation and became a working supermom.
.......

Mom, the plumber is here.”

“Show him to the kitchen then.” answered her Mom.

“Okay.”


A tall devastatingly handsome figure entered the house. Although stranger to Daisy, a peculiar expression can be read from the plumbers face.

“Hmm...okayyyyy.”

“Please, lead the way.”
He gave her a stern glance and waited for her to take the initial step.
She showed him the kitchen and left him alone to continue the movie she was watching earlier in the living room.

“Daisy, where are you?”

“Here Mom.”


Her mom came to the living room full of snacks she took out from the cabinet which she considered appealing to Daisy taste buds.

“Let’s have a movie night.”

“Perfect.”
Daisy was elated to hear this since her mom was super busy these last weeks so that they weren’t able to spend more time with each other. And today felt like a reunion she craved badly. With pure ecstasy Daisy started searching for a movie, neglecting the previous movie she was already watching before her mom came by. Lastly undecided she asked her mom to join her quest to find the perfect family movie, something witty and clever.

After spending half an hour solely searching for a movie, they’ve decided to go with 27 dresses starring Katherine Heigl.

“The house seems too quiet mom, did the plumber finish his work already?”

“I don’t know.”
Mom got up from the couch heading over to the kitchen finding Mr. Plumber with a knife.

“Sir, what’re you doing?” frightened by the way he was handling the knife she found herself backing away from the kitchen.

“Hello Evelyn, Remember me?”

“Pardon?”

“Oh, come on....How could you forget me?”

“Mom, what the hell is this man talking about?”

“Would you like to tell her or should I?”

“Tell me what?”

“That she was, is a con artist. Her husband isn’t your father, just an accomplice of her and were in a contract marriage with your mother. All this wealth belongs to your real father whom she betrayed. A person who truly loved her and fooled totally by her seemingly incredible acting. And I’m his brother or you could say your biological uncle.”


Daisy couldn’t even believe what she was hearing. Everything turned blurry, she tried to hold on to the table for support but it failed her.

(The alarm starts beeping continuously)
“Shit, I couldn’t get passed this scene every single damn time.”

To be continued

✍Benon/Me
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 10 Aug 2025 22:29:54 +0300
"ቅዳጅ ገፆች" ባልኳት channel ውስጥ የልቤን እውነታ እና በጥቂቷ የአፍላ ወጣትነት ህይወቴ የተነሳውን ታሪክ እፅፋለሁ፤አቀርባለሁ።የህይወታችን ትናንሽ ቅዳጆች ቀላል ይመስላሉ፤ ነገር ግን ከእውነት መነሻ ያላቸው ሕይወታዊ አሳቤዎችን ያሳያሉ።

ልጅነቴ፣ ጥላቻዬ፣ እምነቴ፣ መሰማቴ፣ ትንሽ ሐሳቤን በውስን ቃላቶች፤በቅዳጅ ገፆች ላይ የማሰፍርበትን ይችን ትንሿን ግን ሀሳባዊ እውነታዎችን በትልቁ የያዘችውን channel subscribe አድርጋችሁ ቤተሰባዊ መስተጋብርን እንፍጠር።🫶🏼

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 10 Aug 2025 19:33:49 +0300
✨ሲጋራ እና እሷ✨

ራሷን ፃድቅ አድርጋ አታቀርብልህም፥ "ሞክረኝ ታስተካክለኝ ይሆናል" አትልህም... በቃ የሲጋራ ማሸጊያ ላይ እንዳለው ፅሁፍ ማለት ናት "ገዳይህ ነኝ... ስገድልህ ደግሞ በሱስ አናውዤህ ነው" ትልሀለች

እንደሲጋራው ናት... አትከለከልም... ታገኛታለህ መጥፊያህ እንደሆነች እያወቅክ ትጥምሀለች ከዛ አሁንም እንደሲጋራው አብረሀት ውለህ እንኳ አልበቃ ትልሀለች፥ ያላየሀት ቀን የሰው ዘር ያስጠላሀል፥ ሀያ ምናምን አመት የኖረው ዛፍ መገተሩ ግልፍ ያስብልሀል።

ደምህ ውስጥ እንደገባች የምታውቀው.... እንዴት እንደከረረብህ የሚገባህ ትንሽ ድምጿ ሲጠፋ ነው። በቀን...በደቂቃ አርባ ጊዜ ልብህ በእሷ ስም ስልተ ምት ሲደልቅ ያኔ ነው እንዳለቀልህ የሚገባህ...

ከራስህ ጋር ስትሟገት "ናፍቃኝማ አይደለም" እያልክ ብቻህን "እናቷንና" ብለህ ስትዝት ያኔ አክትሞልሀል



         ✍nani



https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 10 Aug 2025 19:33:29 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 10 Aug 2025 15:40:39 +0300
https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 10 Aug 2025 15:02:49 +0300
https://youtu.be/DCh3N2ulmJY?si=eADeFLc45QtXeU0b
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 10 Aug 2025 11:48:00 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 10 Aug 2025 11:47:51 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sat, 09 Aug 2025 17:12:11 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 08 Aug 2025 18:47:00 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 08 Aug 2025 18:46:27 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 08 Aug 2025 18:46:26 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 08 Aug 2025 17:44:04 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 08 Aug 2025 12:27:38 +0300
ስራ ቦታ ስወጣ ስገባ ሁሌ ነው የማየው አይኔን ጥዬበታለሁኝ አለችኝ በጣም ነበር የደነገጥኩት ....


እናቴ እንዲህ ታወራኛለች ብዬ ስላላሰብኩ ይሁን በሰአቱ ስላልጠበኩት ምን እንደምላት ግራ ገብቶኝ ዝም አልኩ ምን ልበላት ማን ነው? ጭራሽ አንቺም ደርሰሽ እኔን መቆጣጠር ጀመርሽ ብትለኝስ የሚከተለኝን አሰብኩት 🥶 ፈራሁ ቢቀርብኝስ ብዬ ትውኩት.....

ኧረ ናኒ ወዴት ሄድሽ እየሰማሽኝ ነው አለች..አለሁ እየሰማሁሽ ነው አልኳት ከሃሳቤ እየተመለስኩ ንግግሯን ቀጠለች

የስራ ቦታ ሁኔታዬን አይቼ እቤት አመጣዋለሁ አለችኝ አሁን አልቻልኩም እንዴ ማን ነው እሱ????አልኳት ይህንን በማሰብ ብቻ ማለፍ ስላልቻልኩ😤

ጠራችው ስሙን ጠራችው እፎይይይ አልኩ ለካ አይኔን ጣልኩበት ብላ የምትነግረኝ ስራ ቦታዋ ውስጥ ስለማይጠቀሙበት የተዉትን የኤሌክትሪክ ገመድ ነው አዘንኩ በራሴ....

..እናቴ የኤሌክትሪክ ገመድ ካየች አታልፍም ለክፉ ቀን ይሆናል ብላ የማምጣት ልምድ አላት እቤት እራሱ ኤሌክትሪክ ሲበላሽ በእሷ በኩል ታይቶ ነው ከአቅሟ በላይ ሲሆን ባለሙያ እንዲያየው የሚደረገው

እንዴት ይህን እያወቅኩ በዚህ ልክ እንደተሸወድኩ ገረመኝ ወይ አገላለጿ ይሆን እንዴ??????



✍በእኔ

https://t.me/kineenote
https://t.me/kineenote
https://t.me/kineenote
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 08 Aug 2025 07:47:58 +0300
"ኢየሱስም አለ:- እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ" ማቴ. 28:19
#share
@diyakonhenokhaile
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 07 Aug 2025 12:23:18 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 07 Aug 2025 00:47:32 +0300
ቢሮዋ

"ሰው የሚፈልገውን ነገር ሲያጣ ያለውን ነገር ከልክ በላይ በማድረግ ለማካካስ ይሞክራል" ቢሮዋ ስንገባ በትልቁ ተለጥፏል። እንዳነበብኩት ፈገግ ስል አይታ ፀሀፊዋ "የቢሮው መርህ ነው እንግዲህ ያው አንቺ ብቻ አይደለሽም የተገረምሽው የመጣ ሰው በሙሉ ነው ለተወሰነ ደቂቃ ቆም ብሎ እንዲያስብ የሚያረገው" አለቺኝ።

የመጣነው ሀያ ተማሪዎች ያህል እንሆናለን "የዘንድሮ ተመራቂ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪዎችን ማነጋገር እፈልጋለሁ" ብላለች ተብለን ነው-ወ/ሮ ሳባ።

ሳባ ደግሞ ማናት? ትሉ ይሆናል ሳባ ማለት ሳድግ እሷን ነው መሆን የምፈልገው የምልላት ታዋቂ የስነልቦና አማካሪ ነች። በየመድረኩ ያደረገቻቸውን ንግግሮች እያሳደድኩ ያዳመጥኩላት ትምህርት ሲያማርረኝ እንደሷ መሆንን እያሰብኩ ሳታውቀኝ ያበረታችኝ ሴት ነች ሳባ!" ስሟ ራሱ ታላቅነትን አያንፀባርቅም?! ሳባ ሲባል ከንግስቷ ጋር ማመሳሰል አይቀር

እና እንደዚህ የማከበራት የማደንቃት ሳባ የኔን ባች ማየት እፈልጋለሁ ስትል ሁላችንም ደስ ብሎናል እኔ ግን እንደ ህፃን እየቦረቅኩ ነው።

ገና ወደ ቢሮዋ ከመግባታችን በፊት እንግዳ መቀበያ ቦታው ጋር ስንቀመጥ አይኔን ከግድግዳዎቹ ላይ መንቀል አቅቶኝ አንገቴ እስኪሰበር እየተዟዟርኩ አየሁት። ከግድግዳው ቀለም ጀምሮ(ፈዛዛ ሮዝ ሁለቱ ግድግዳ ቀሪው ሁለቱ ፈዛዛ ወይንጠጅ ነው የተቀባው) በነጫጭ እቃዎች ያሉት አርንጓዴ ተክሎች መረጋጋትን ይፈጥራሉ በዛ ላይ በቀጭኑ የተዘረጉት ሀረጎች ቦታውን ታመው ሳይሆን ለመዝናናት የሄዱበት ቦታ ያስመስለዋል።

እነደዚህ ስመሳሰጥ ከቢሮዋ ወጥታ "ኑ ግቡ" አለች እና ወደ ቢሮዋ ተመለሰች።ሰፊ ቢሮዋ ተቀበለን ሶፋው ጋር የለችም ዞር ስንል እግሯን አጣጥፋ ምንጣፍ ላይ ተቀምጣለች እንደ ሁልጊዜዋ ነች አለባበሷ እንከን የለውም ሙሉ ጥቁር ቱታ ለብሳለች ፀጉሯ ወደ ኋላ ፅደት ተደርጎ ተይዟል ስስ ሜክአፕ አድርጋለች።

ምንጣፍ ላይ መቀመጧ ትንግርት ሆኖብን ቆመን ስናያት ኑ እንጂ ተቀመጡ ብላ ወደቀሪው ቡኒው ምንጣፏ ጋበዘችን "ማን ወንበር ላይ ይጨናነቃል" ስትለን ያካበድናትን ያህል እንደጓደኛ ቀለለችን። በየተራ ፊቷ ሄደን ተደረደርን።

"ራሴን ማስተዋወቅ ያለብኝ አይመስለኝም ታውቁኛላችሁ አይደለ" አለችን በሙሉ ፈገግታ በራስ መተማመኗ ከሆነችው በላይ ቆንጆ እንድትሆን አድርጓታል "በሚገባ" አልኳት እኔ ፈጠን ብዬ "እና ቢሮዬን እንዴት አያችሁት አለችን ሁላችንም ደግመን አየነው ከግድግዳው ቀለም ውጭ ተክሎቹ እዚህም አሉ ግድግዳው ግን ከላይ ፈዛዛ ግራጫ ከግማሽ በታች ደግሞ ፈዛዛ ጎመኔ ቀለም ነው የተቀባው በአንድ በኩል ሙሉ በሙሉ መስታወት መሆኑ የበለጠ ቅልል የሚል ስሜት ይፈጥራል ሶፋዎቹ ብርቱካናማ ቀለም ኗሯቸው ለመቀመጥ ሳይሆን ለመተኛት ይጋብዛሉ። ችግር የሚወራበት ሳይሆን ደስታ የሚከበርበት ቦታ ነው የሚመስለው።

" ዛሬ የፈለግኳችሁ ዋና አላማ ምን መሰላችሁ" ስትል ከምሰጣዬ አባነነቺኝ "መመረቂያችሁ ከደረሰ አይቀር ስለስራ ህይወታችሁ ለመነጋገር ነው"አለችና ትንፋሿን ሰብስባ

"እንደሌሎች ከዚህ ዲፓርትመንት ተመርቀው ወጥተው ስራ አጣን ብለው እንደሚያማርሩ ሰዎች እንድትሆኑ ስለማልፈልግ ነው ምክንያቱም እናንተ ለመስራት ፈቃደኛ እስከሆናችሁ ድረስ ስራ አለ። እኔ እንዴት ስኬታማ የሆንኩ ይመስላችኋል?" አለች

ሁልጊዜ የሚገርመኝ ነገር ስለሆነ ጆሮዬን የበለጠ አቁሜ ማዳመጥ ጀመርኩ "ተመርቄ ወጣሁ ይሄንን ቢሮ ከፈትኩ ያው እንደዚህ ባያምርበትም ማለት ነው ግን እዚህ ዝር የሚል ሰው አልነበረም ስለዚህ ይሄንን ለመለወጥ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ መጀመሪያ የእውቀት ማነስ ነው ብዬ ስላሰብኩ በየትምህርት ቤቱ በመሄድ ለማስተማር ሞከርኩ ግን የማህበረሰብን አስተሳሰብ መቀየር ብቻዬን የምችለው ነገር አይደለም ስለዚህ ታማሚ ወደዚህ የማይመጣ ከሆነ እኔ መሄድ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ

ይህንን እያሰላሰልኩ በታክሲ የሆነ ቦታ ስሄድ በጣም ግንን ያለ ሽቶ የተቀባች ሴት አብራኝ ተቀመጠች "ሰው ለምን እንደዚህ የተጋነነ ሽቶ ይገዛል?" የሚለው ሀሳብ ሲያብሰለስለኝ ስልክ ተደውሎላት አነሳችና "በቃ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሀሙስ ነው ተፋተን ይለይናል" አለች ያኛው ጫፍ ላይ ያለችው ሴትዮ ምን እንዳለቻት መስማት ባልችልም ያፅናናቻት ይመስለኛል "ኧረ ደህና ነኝ አሁን ራሱ እውነት shopping ወጥቻለሁ" አለቻት ስልኩ ሲዘጋ አይኗን በሶፍት ሸፍና አለቀሰች ያ ሁሉ የሽቶ መርከፍከፍ ታድያ ሀዘኗን ለመደበቅ ነበረ ማለት ነው?!

እኔም የት መሄድ እንዳለብኝ ተረዳሁ ሴቶች ያሉበት የበዛ ዊግ የሚሰሩ የበዛ ሜክአፕ የሚቀቡ እንዲሁም በሳምንት በሳምንት የሚለበስ ካልገዙ የሚጨንቃቸው ሴቶች ብዙ ማግኘት ፈልገው ያላገኙት ማግኘት የሚችሉትን ደግሞ ከልክ በላይ እያደረጉት እንዳሉ ተረዳሁ እነሱን ለመርዳት ብዙ አይፈጅም ነበረ የተወሰነ ቀርቦ ማውራት ነው መፍትሄ እንደሚያገኙ ሲረዱ ራሳቸው መምጣት ጀመሩ።

ከዛ ደግሞ አንድ ሰሞን የበዛው የቢራ ማስታወቂያ ይገርመኝ ነበረ "ሰው እንዴት መጠጥ ይወዳል?" እያልኩ እኔ መጠጥ አልወድም ሆዴን አሞኝ እናቴ በግድ አረቄ ያስጠጣቺኝ ቀን ግን ስቃጠል ዋልኩ ግን ሰዉ በሊትር እየገዛ ሲጋት ሳይ ግራ ገባኝ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መጠጥ ቤት ሆነ ማለት ነው" ስትል ሁላችንም ሳቅን

"ስለዚህ ስራ የለም ማለት አይቻልም አካባቢያችሁን ካሰተዋላችሁ ሁሉም እርዳታ ፈላጊ አዳማጭ ፈላጊ ነው ሌላውን ተዉት የዘንድሮ አስራ እድሜዎች ላይ ያሉትን ልጆች ብታዩ ሁሉም ነገር ነው ድብርት ውስጥ ጭንቀት ውስጥ የሚጥላቸው አላማችሁ ሰውን መርዳት ከሆነ ብዙ እናንተን የሚጠብቅ አለ" አለችን "እሺ" አልናት እንደእኔ ሁላችንም በልባችን ቃል የገባንላት ይመስለኛል

"የምትሉኝ ነገር ከሌለ ስራ የምጀምርበት ሰዓት ነው" አለችን "በተግባር ነው የምናሳይሽ" አላት ከመሀላችን አንዱ ልጅ ሁላችንንም አቅፋ ተሰናበተችን



✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 07 Aug 2025 00:47:08 +0300
Подробнее
10.27 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 06 Aug 2025 20:17:15 +0300
...አንተዋወቅም ከጓደኞቻችን ጋር ለምሳ የምናዘወትረው ቤት አለ ስንገናኝ ከሰላምታ ውጪ ንግግር የለንም አለማወቄ መስለኝ ይሆናል ብዬ ለራሴ በሰጠሁት ማንነት ውስጥ ነው እሱን ማየው😊



ለኔ ይህ ድርጊቴ ትስማምቶኛል ምክንያቱም አለማወቅ ዉስጥ ሰላም ነው መጣላት የለ መጨቃጨቅ የለ መለያየት የለም ከሰው ጋር አብሮ በመኖር ውስጥ ከባዱ ነገር መተዋወቁ ማውራቱ ሳይሆን አብሮ ትዋውቆ መኖሩ መዝለቁ ላይ ነው ቁም ነገሩ!!

እኛ ብዙ ጊዜ የማናውቀውን ለማወቅ እንጓጓለን ካወቅን በኃላ ካገኘው ማንነት ጋር አብሮ ተቻችሎ መቀጠል ሲያቅተን የምን መጨነቅ ነው ብተወውስ ብለን መለያየትን እንደ መፍትሄ እንወስዳለን ባናወራም አብረን ባንቀጥልም እንዴት በሰላም መለያየት እንዳለብን አናውቅም ( not knowing how to leave for peac




.......በእርግጥ በህይወታችን መጥተው የሚያልፉ ሰዎች ያስተምሩናል ዳግም እንዳንሳሳት ይባላል ግን ሁሌ  አንዱን አወቅነው ዳግም አንጎዳም ስንል መልኩን ቀይሮ ይመጣል .
                     .
                     .
                     .
                     .
ቆየንብሻ ( የጓደኞቼ መምጣት ከሃሳቤ አወጣኝ ያለ ወትሮ ቆይተዋል ዳይይ ወደ ምሳ

https://t.me/kineenote
https://t.me/kineenote
https://t.me/kineenote
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 05 Aug 2025 16:52:17 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 05 Aug 2025 13:07:46 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 05 Aug 2025 13:07:14 +0300
Подробнее
10.22 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 04 Aug 2025 18:44:11 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 04 Aug 2025 16:34:58 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 04 Aug 2025 16:34:41 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 04 Aug 2025 14:24:31 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 04 Aug 2025 14:17:33 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 04 Aug 2025 08:46:12 +0300
በዚህ መሰረት ሰሞኑን የሚጀመር ተከታታይ ፅሁፍ ይኖረናል።

ከጓደኞቻችሁ ጋር እያወራችሁ እንድታነቡ ቻናሉን share አድርጉላቸው😁
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 03 Aug 2025 20:34:55 +0300
ተከታታይ ፅሁፍ ይጀመር ላላችሁ የምን ዘውግ እንዲኖረው እንደምትፈልጉ comment እያደረጋችሁ
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 03 Aug 2025 17:23:46 +0300
thanks for voting

ያላነበባችሁ ሰዎች search አድርጋችሁ እንድታነቡ በአክብሮት ትጠየቃላችሁ

ያነበባችሁ ሰዎች ደግሞ ምን እንደተሰማችሁ comment ላይ አስቀምጡልኝ
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sat, 02 Aug 2025 16:02:08 +0300
እስረኞች ነን። መንፈሳችን በድብርት አዚም ታስሯል። በድንቁርና ማጥ ተሸብበናል። በተስፋ መቁረጥ ፍርግርግ ተከርችሞብናል።

ነፍሳችን ከእስራት ሳይወጣ፣ መንፈሳችን ከእንቅልፉ ሳይነቃ ስጋችን ብቻ ቢያመልጥ የጎላ ትርጉም የለውም።

ህሊና መንቃት አለበት። ማንበብ፣ በጥልቅ ማሰላሰል፣ በአርምሞ መመሰጥ አለበት።

ቦብም

Emancipated yourself from slavery
None but ourselves can free our minds ብሏል።

ማንም መጥቶ ነፃ አያወጣችሁም። አሳሪውም፣ ታሳሪውም፣ ነፃ አውጪውም ራሳችሁ ናችሁ።

እጃችን ላይ ከጠለቀው የብረት ሰንሰለት ይልቅ አእምሯችንን የቀፈደደወ የማይታየው ካቴና ይበረታል። ታዲያ ይሄ ካቴና የሚሰበረው በጉልበት ሳይሆን በፍቅር፣ በተስፋ፣ በጥበብ፣ በብልሃት፣ በትጋት፣ በፅኑ መንፈስ ነው። ድንቁርናን የምናመልጠው በእውቀት ነው።

እያነበብን ጎበዝ . . .
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 01 Aug 2025 23:54:04 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 01 Aug 2025 23:53:10 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 01 Aug 2025 22:58:33 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 01 Aug 2025 21:16:09 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 01 Aug 2025 00:32:03 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 01 Aug 2025 00:22:44 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 31 Jul 2025 22:36:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 31 Jul 2025 22:20:58 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 31 Jul 2025 22:20:50 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 31 Jul 2025 18:06:33 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 31 Jul 2025 09:06:40 +0300
"ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ፡ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል" ምሳ.18:13
#share
@diyakonhenokhaile
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 31 Jul 2025 09:01:48 +0300
እንዴት ሰነበታችሁ?

ተናፋቂው " ንባብ ለሕይወት" ከዓመታት በኃላ ተመልሶልናል።


የእኔን አምስቱም መፅሐፍትና የደራሲ አበረ ሽፈራውን "የበርበሬ ዐውሎ ነፋስ" ጃፋር ብቻ ባስለመዳችሁ ቅናሽ ለመሸመት ከዛሬ ሐሙስ ከሰዓት ጀምሮ እስከ እሁድ በኤግዚቢሽን ማእከል ተገኙ።


እኔና አቢን ማግኘትና ማስፈረም ከፈለጋችሁ ደግሞ ቅዳሜ ከስምንት ሰዓት ጀምሮ ብቅ ብትሉ አለን።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Thu, 31 Jul 2025 09:01:16 +0300
📌"ንባብ ለሕይወት" ግዙፉ አውደርዕይ ሊካሄድ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ግዙፉ የመጽሐፍ አውደርዕይ "ንባብ ለሕይወት " የመጽሐፍና ንባብ አውደርዕይ ከቀናት በኃላ ሊካሄድ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"ንባብ ለሕይወት" የመጻሕፍት አውደርዕይ ዘንድሮ ከሐምሌ 24 እስከ ሐምሌ 27 2017 ዓ.ም ድረስ ለቀናት መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ውስጥ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል።

የንባብ ከሕይወት ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በመተባባር ባዘጋጀው በዚህ አውደርዕይ ላይ በርካታ ደራሲያን በመገኘት መጻሕፋቸውን ያስተዋውቃሉ ተብሏል።

የመጻሕፍት አሳታሚዎችና አከፋፋዮች መጻሕፍትን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ።

በአውደርዕዩ ላይ የመጽሐፍ ምርቃትና ሀሳብ ማንሸራሸሪያ ልዩ ልዩ መድረኮች ተዘጋጅቷል።

የአውደርዕዩ መግቢያ በነፃ ሲሆን ሐሙስ ሐምሌ 24 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ይከፈታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 30 Jul 2025 12:07:55 +0300
መልእክቱ✍

ለወትሮው ያለምክንያት ሳንቲም የማያወጣው ሰውዬ አሁን አዲስ የእርዳታ ተቋም ተከፈተ በተባለ ቁጥር እየሄደ እጁ ላይ ያለውን ብር በሙሉ ይሰጣቸዋል። መለገሱ ደግ መሆኑ አልበረም የከነከነኝ በአንድ ግዜ ለጋስ መሆኑ እኮ ነው ያጠራጠረኝ።

"የተፈጠረ ነገር አለ አይደል?" አልኩት ሌላ የእርዳታ ድርጅት እየሄድን "ሰውን ለመርዳት የሆነ ነገር መፈጠር?" አለበት አለ አይኔን እየሸሸ።ይሄኔ የደበቀኝ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ሆንኩ። "ንገረኝ ችግር የለውም" አልኩት ምናልባት የሚያናድድኝ ነገር ከሆነ ብዬ "አይ ጥፋት እንኳን አይደለም" አለ ወደ መስኮት ዞሮ አይኖቹ እንባ አቅርረዋል ይሄኔ ልቤ መሸበር ጀመረ።

"ምንድንው ቢኒዬ? እያስጨነከኝ ነው" አልኩት "ሳልነግርሽ ቀኑ ተሸርሽሮ ቢያልቅ ደስ ይለኝ ነበረ... ግን አልቻልኩም... አይኖችሽን እያየሁ በየቀኑ መደበቅ አቃተኝ"
"እንዴ የምን ቀን ነው የሚሸረሸረው?? ምንድነው ያልነገርከኝ?" አልኩት እንባውን ከፊቱ ላይ እየጠረግኩ።

"ግፋ ቢል አምስት ወር ነው የቀረህ ብለውኛል..."
"ለምኑ? ፕሮሰሱ ተሳካ እንዴ?" አልኩት ሰፍ ብዬ
"የጉበት እጢ ነበረህ... እና አሁን ወደ ካንሰር ተቀይሯል ያለህ ጊዜ ከ አምስት እና ስድስት ወር አይበልጥም አሉኝ።" ሰውነቴ ቅዝቅዝ ሲል ተሰማኝ።

እነዛ ፊልም ላይ እንዳሉት፤ ወይ ታሪካቸው እንደሚወራላቸው ሰዎች ጠንካራ አልነበርኩም። ላስታምመው እና የመጨረሻዎቹን ወራቶች በጥሩ ሁኔታ እንዲያሳልፍ አላደረግኩም። ወይ ማድረግ አልሞከርኩም ራሱ።

የዛን ለታ ከተለያየን በኋላ፤ መጀመርያ ቤቴ ገብቼ ማሰብ ጀመርኩ 'እሱስ መሞቱ አይቀርም እኔ ግን እንዴት ነው ሀዘኑን የምችለው ከወዲሁ መለማመድ አለብኝ' አልኩና እሱ የሚያውቀውን ሲም ካርድ አውጥቼ በሌላ ቀየርኩት ከዛ በሳምንቱ ሌላ ሰፈር ሄጄ ተከራየሁ ደብዛዬን አጠፋሁበት። ያው እየፈለገኝ መሆኑ አይቀርም ብዬ ነው።

ህይወት ከቀጠለ፤ ያለሱ መኖርን ከለመድኩት ከብዙ ወራት በኋላ፤ ለስራ ጉዳይ አንድ ፋይል በድሮ ስልክ ቁጥሬ ላኩልኝ እና እሱን ለማየት ሲም ካርዴን መልሼ ስከተው ከሰባት ወራት በፊት የእሱን አርባ ምናምን መልክት ከሀምሳ ሶስት ሚስድ ኮል ጋር አየሁ። አልገረመኝም ይሄንኑ ሽሽት አይደል እንዴ የጠፋሁት። 'ይሄኔ እኮ ሞቶ ይሆናል' አለኝ ጭንቅላቴ። "ነፍስህን በገነት ያኑረው" ብዬ አንሾካሸኩ።

ከዛ ግን አንድ መልእክት ቀልቤን ያዘችው። የተላከው ከሌሎቹ አንፃር በቅርብ ነው። ከሶስት ሳምንት በፊት ይላል መልዕክቱም፦

"አየሽ እንዳንዴ የሰውን እውነተኛ ማንነት ለማወቅ የትንሸ ደቂቃ ትወና በቂ ነበረ። ይገርምሻል ካንሰር አልያዘኝም ። ገና ለገና ሊሞት ነው ብለሽ ግን በአንድ ቀን ትተይኛለሽ ብዬ አላሰብኩም ነበረ። ምናልባት ደንግጣ ይሆናል፤ ራሷን እስክታረጋጋ ነው እያልኩ እስክትደውዪ እስክትመጪ ስጠብቅ ነበረ። አንቺ ግን የራስወዳድነትን ጥግ አሳየሺኝ።

ይሄ ሁሉ ትወና ለምን ካልሺኝ ቀለበት ገዝቼልሽ ነበረ። በኔ ቤት propose ላደርግ እኮ ነው። ከዛ ግን ምን ሹክ እንዳለኝ አላውቅም ያደረኩትን አድርጌ ማንነትሽን አየሁበት። ደግሞ ግምትሽ ትክክል ነበረ ፕሮሰሱ አልቋል ይህን ስፅፍ ሻንጣዬን እያስፈተሽኩ ነው። በይ ደህና ሁኚ" ይላል

ከዛ ብቻ ብዥዥ ሲልብኝ ይታወቀኛል...ስልኬ ከእጄ ላይ ሲወድቅ... የቤቴ ጣራ ሰያፍ ሲንሻፍፍ... የቆሞኩበት ሲከዳኝ ይታወቀኛል... ብቻ ከስብርባሪ ሰከንዶች በኋላ ጉልበቴ ሲከዳኝ.... ተንሸራትቼ ስወድቅ አጠገቤ የነበረው ጠረጴዛ ማጅራቴን ሲመታኝ አንድ ሆነ....እያየሁት ደሜ ፈሰሰ።

✍አበቃ



✍ናኒ



https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Wed, 30 Jul 2025 12:07:20 +0300
Подробнее
10.24 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 29 Jul 2025 21:20:29 +0300
ይገናኛሉ፤ ከዛ እንደጉድ ይጠጣሉ። ሲሰክሩ ሌላ ሰው አይፈልጉም ተደጋግፈው ይሄዳሉ። አንዳንዴ አንደኛው አፅናኝ ሆኖ ሌላኛው እያለቀሰ ይጠጣል።

ሌላ ጊዜ ደግሞ በውስኪ ውስጥ አለማቸውን ከትተው ብርጭቋቸውን እያሽከረከሩ ከሩቅ ላያቸው የፈላስፋ መዝናናት የሚዝናኑ ይመስላሉ።

"ግንቦት ላይ ነበረ ልደቷ ይላል" አንደኛው  "የኔዋ ደግሞ ታህሳስ ነበረ። ግንቦት ስንት ነበረ ቆይ?" መልሶ ይጠይቃል። "ግንቦት 30 ያንተስ?" "እኔ አላምንም ታህሳስ 30 ነበረ የሷም" "ቺርስ!" ብለው ይስቃሉ ወዲያው አይናቸው እንባ ይሞላዋል

" አውርታ አትጠግብም ነበረ ።እሷ ስታወራ ራሱ ማየት ደስታ ይሰጠኛል ይላል"አንደኛው "አይ የኔዋ እንኳን ዝምተኛ ነበረች። ዘላለም ብለፈለፍባት አይሰለቻትም ነበረ ።የምታወራው ማውራቷ ግድ ሲሆን ብቻ ነው" ያወሩት ባይመሳሰልም "ቺርስ" ይላሉ ።

"በነገራችን ላይ ሙት አመቷ የፊታችን ቅዳሜ ነው እንዳትቀር" ይለዋል። እንዲመጣ የሚፈልገው እሱ ብቻ በሚመስል ልምምጥ ባለው ድምፅ "ኧረ እንዴት እቀራለሁ የኔዋም ሁለተኛ አመቷ ከሶስት ወር በኋላ ነው።"

አንዳንዴ እኩል ያወራሉ። አንዳንዴ ደግሞ አንዱ ሲያወራ ሌላኛው ስለራሱ የተወራለት ይመስል አፉን ከፍቶ ያዳምጠዋል።

ይጠጣሉ ፤ያወራሉ ፤ ደጋግመው ያወራሉ።
አንደኛው ለመርሳት አንደኛው ላለመርሳት ያወራሉ።


✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 29 Jul 2025 21:19:49 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 29 Jul 2025 18:25:41 +0300
https://youtu.be/1UnvywH1sFQ?si=5cRrZqjaxrXpQ5Ow
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 29 Jul 2025 14:51:01 +0300
አምና እንደተባበርነው አሁንም ትንሽም ብትሆን ያለንን በማዋጣት ወንድማችንን እንታደገው 🙏
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 29 Jul 2025 14:18:28 +0300
https://t.me/SimaEsubooks
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Tue, 29 Jul 2025 14:16:05 +0300
🔔Urgent and Important Notice ‼️

📢 Let’s Come Together for Abel 💛

Our beloved book club friend needs us now.

You all know Abel? The one who always brought thoughtful insights, honest reflections, and pure kindness to every book discussion and made this club feel vibrant?

What many of us didn’t know is that for the past 3 years, Abel has been silently fighting a battle, going through dialysis 3 times a week, every week.
Now, he needs a kidney transplant to survive.
The total cost is 3 million birr, and he can’t do it alone.

💸 HOW YOU CAN HELP

We’re launching the #BookForLife Challenge, where each of us contributes whatever we can because no one should face this alone.

Choose your tier:
• 📚 Bookmark Tier – 100 birr
• 📖 Chapter Tier – 300 birr
• 📘 Book Lover Tier – 500 birr
• 💎 Author’s Circle – 1000+ birr

Join the Chain of Hope
1. Donate to Abel’s account
2. Tag 3 friends in the club and challenge them to do the same
3. (Optional) Post a screenshot of your donation to inspire others

Let’s turn our love of books into love in action.
Let’s remind Abel that this club isn’t just for reading.

💳 Donation Info

Bank Name: Commercial Bank of Ethiopia (CBE)
Account Holder: Abel Tewodros
Account Number: 1000309265231

Abel gave so much to this community without ever asking for anything. Now it’s our turn.
Let’s help him write the next chapter with hope, healing, and life. 💛

#BookForLife
#HelpAbelHeal
#BookClubFamily
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 28 Jul 2025 21:01:02 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 28 Jul 2025 16:57:41 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Mon, 28 Jul 2025 16:57:14 +0300
Подробнее
11.22 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 27 Jul 2025 19:05:01 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 27 Jul 2025 19:04:22 +0300
Подробнее
12.95 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Sun, 27 Jul 2025 19:04:22 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001662932240 Fri, 25 Jul 2025 19:46:50 +0300
@Jaymasangula_bot | info
Подробнее
]]>