Лента постов канала የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት (@gibigubayat_mirukan_hibret) https://t.me/gibigubayat_mirukan_hibret ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ቻናል የተከፈተው በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት መንፈሳዊ ትምህርት ሲከታተሉ ቆይተው ከግቢ ጉባኤያት ለተመረቁ በመላው ዓለም ለሚገኙ አባላት ሲሆን በዚህ ቻናል የሚተላለፉ መልዕክቶች፣ ትምህርታዊ ጽሑፎች እና ልዩ ልዩ የፕሮጀክት ሐሳቦች በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል አማካኝነት ሲሆን ምሩቃን ወደዚህ ቻናል እንዲቀላቀሉ የበኩልዎትን ድርሻ ይወጡ። ru https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Wed, 13 Aug 2025 19:43:17 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Wed, 13 Aug 2025 10:56:49 +0300
https://t.me/gibigubayat_mirukan_hibret
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Wed, 13 Aug 2025 10:56:37 +0300
፲ ስኬትን ማክበር
በመጨረሻም በእያንዳንዱ የስኬት ምዕራፍ ውስጥ ውጤታማ ሥራዎችን ለማስቀጠል ድሉን ማክበር ለዘላቂነቱ ወሳኝ ነው። በብዙ ፈተና ውስጥ የተገኘውን ውጤት መዘከር ለሌላ አዲስ ስኬት ስለሚያነቃ በመንገዳችን ውስጥ ድርሻ ከነበራቸው ጋር ጊዜን ማሳለፍና ዕውቅና መስጠት ይገባል።
"ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህንን ወይም ያንን ማድረግ አለብን ማለት ይገባችኋል።" (ያዕ ፪፥፬)
መልካም ምንባብ
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Wed, 13 Aug 2025 10:56:23 +0300
ስኬታማ የሥራ ፈጣሪ ለመሆን ምን እናድርግ?
ክፍል ሦስት


፮ ኪሳራን ግምት ውስጥ ማስገባት
ስኬታማ ሥራ ፈጣሪዎች ሊገጥማቸው የሚችለውን ኪሳራ ቀድመው ይገምታሉ፤ የሚገጥም ኪሳራም አስደንግጧቸው ወደ ኋላ ሲያስቀራቸው አልተስተዋለም። ከተለምዷዊው የምቾት ቀጠና አስቀድመው ለመውጣት ስለወሰኑ ከባድ ኪሳራ ቢገጥማቸው እንኳን አይሰበሩም። አንዳንዶቹ እንደውም ከደረሰባቸው ኪሳራ አንጻር ዳግም ይነሳሉ ተብለው ያልተጠበቁ ናቸው። ነገር ግን ሲጀምሩትም ኪሳራውን አስልተው ስለተዘጋጁበት ከግባቸው ደርሰዋል።

፯ ደንበኛ ላይ ማተኮር
ስኬታማ የስራ ፈጣሪ ደንበኞቹንና ፍላጎታቸውን ጠንቅቆ ያውቃል፤ አስተያየታቸውን ያደምጣል። የደንበኞቹን ርካታ መጨመር ይዞት የሚመጣውን ገበያ ይረዳልና ሁሌም ከደንበኞቹ ጋር የቤተሰባዊ ያህል ቅርርብን ይፈጥራል። የተለየና አዳዲስ ፈጠራዎችን በማከል ደንበኞቹን ለማስደሰትም ያለማቋረጥ ይተጋል።

፰ የጊዜና ሀብት አጠቃቀምን ማዘመን
ሥራ ፈጣሪዎች ጊዜ እና ሀብታቸውን በአግባቡ ማስተዳደር የሚችሉበትን ሥርአት ማበጀት አለባቸው። ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን መለየት እና ተጽዕኗቸው ከፍ ያሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮርም ይኖርባቸዋል። ሥራዎችን በፍጥነት እና በዝቅተኛ ወጪ ማጠናቀቅ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀሙ ይገባል።

፱ ለአዳዲስ ፈጠራ ዝግጁ መሆን
የሥራ ፈጠራው አለም በየጊዜው የሚለዋወጥ እንደመሆኑ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ጋር ራስን ማወዳጀት ተገቢ ነው። ሌሎች ስራ ፈጣሪዎች የሚከተሏቸውን አዳዲስ ፈጠራዎች እና ቴክኖሎጂዎች በማጥናትም ከራሳችን የሥራ ፈጠራ ጋር አብሮ የሚሄድ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል። ሁሌም ለአዳዲስ ፈጠራ ዝግጁ መሆን ፉክክር በበዛበት አለም ውስጥ ወሳኝነቱ አያጠያይቅም።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Tue, 12 Aug 2025 10:14:47 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Tue, 12 Aug 2025 10:14:37 +0300
https://forms.gle/NFyiuorafEFe2n5VA

MK x 7Jobs Online Registration is Now Live!

📲 We’ve made it easier — this is the same registration form as before, now in Google Form format for quick and easy online access.

✅ Simple and accessible
✅ No need to download or email files
✅ Each person gets a login email to activate their account

🎯 Maekel and Gibi Gubae coordinators: Use this form to register students, staff, and affiliates under your coordination. Help them access job opportunities, CV support, and tailored career tools.

Let’s make opportunity reachable for all!
#7Jobs #MahibereKidusan #DigitalAccess #JobOpportunity #ForEveryone
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Tue, 12 Aug 2025 09:25:41 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Mon, 11 Aug 2025 10:03:12 +0300
ስኬታማ የሥራ ፈጣሪ ለመሆን ምን እናድርግ?
ክፍል ሁለት

፪ ራስን በዕውቀት ማሳደግ፤ ሁሌም መማር

በየዕለቱ ለዕውቀት እና አዳዲስ ፈጠራዎች መጠማት የስኬታማ የሥራ ፈጣሪነት ሌላኛው ወሳኝ መንገድ ነው። “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል።" (ትንቢተ ሆሴዕ ፬፥፮) እንዳለን ነብዩ ሆሴዕ ሁሌም የዕውቀት ክህሎታችንን ማዳበርና መፈተሽ እንዲሁም ሁልጊዜ ተማሪ መሆን ይጠበቅብናል። መጻሕፍትን ማንበብ፣ ከሙያችን ጋር የተያያዙ ሥልጠናዎችን መውሰድ፣ የሥራ ፈጠራ አማካሪዎችን ማነጋገር እና አዳዲስ እውቀት እየገበዩ ከፈጣኑ አለም ጋር ራስን ማጣጣም ያስፈልጋል።

፫ ከፈተናዎች መማርና መጽናት
በሥራ ፈጠራ ውስጥ ለችግሮች እጅ የማይሰጥ ጠንካራ ጽናትን መገንባት ወሳኝ ነው።
የአብዛኞቻችን መሠረታዊ ችግር ስናገኝ እንጅ ስናጣ አንደሰትም፤ከብርታታችን እንጅ ከድክመታችን መማር አንችልም። ፈተና በራሱ ትልቅ ት/ቤት ነው፤ስለሆነም ከሚደርስብን መከራና ልዩ ልዩ የዓለም ፈተና ራሳችንን በማጽናት ከቅዱስ እግዚአብሔር ጋር በጸሎት መነጋገር ያስፈልጋል። በእያንዳንዱ ጉዞ ውስጥ መውጣት መውረድ እንዳለ ማመንና ችግሮችን ለተሻለ ነገ መማሪያ እንጂ ተስፋ መቁረጫ አድርጎ አለመውሰድ ይገባል። የዘመናችን እጅግ ውጤታማ ሥራ ፈጣሪዎች በርካታ ፈተናዎችን በጽናት ተፋልመው ከስኬት ጫፍ የደረሱ መሆኑን በማጤንና ተሞክሯቸውን በመውሰድ ራስን መቀየር ይቻላል።

፬ የተጠና የቢዝነስ ዕቅድ ማውጣት
የገበያ ጥናት ማድረግ፣ ዋና ዋና የቢዝነሳችን መዳረሻዎች መለየት፣ ተፎካካሪዎቻችን ያላቸውን የተለየ አገልግሎትና ብቃት ማጥናትና የኛን የተለየ ውጤታማ መንገድ መዘርዘር ለቢዝነስ ዕቅዳችን ዋነኛ ግብአቶች ናቸው። የምናከውናቸውን ተግባራት በጊዜ ገደብ ለይቶ ማስፈር፣ ወጪና ገቢያችን ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ እንዲሁም የገበያ ስትራቴጂ መንደፍም ወሳኝ ነው። ከላይ የጠቀስናቸውን ነጥቦች ያካተተ የቢዝነስ ዕቅድ ሌሎች ሰዎች አብረውን እንዲሠሩ ከመጋበዙም በላይ ከግባችን ለመድረስ እንደመሰላል ያገለግለናል።

፭ ከሚመስሉን ጋር መወዳጀትን ማጠናከር
በሥራችን የሞራልና የዕውቀት ድጋፍ የሚሰጡን ባለሙያዎች፣ አማካሪዎች እና ጓደኞች ማብዛት ወደ ስኬት ለመቅረብ ሌላኛው መንገድ ነው። እግዚአብሔርን በማያሳጣን መልኩ ከሥራ ፈጠራ ጋር በተያያዙ ሁነቶች መሳተፍና የሥራ ማኅበራትን መቀላቀል፣ ከሙያችን ጋር ተቀራራቢ የሆኑና ድጋፍ ሊሰጡን የሚችሉ ሰዎችን ማግኘትና ትስስር መፍጠር ይጠበቅብናል። ይህ ትስስርም በጋራ ተቋም የመገንባት እና ሀብት የማፍራትን በር ይከፍታል።
ይቆየን!
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Sat, 09 Aug 2025 12:04:22 +0300
፩ የምንወደውን ሙያ እና ራእያችን መለየት
የእያንዳንዱ ስኬታማ ሥራ ፈጣሪ ታሪክን ብንመረምር የመጀምሪያ የስኬት መንገዱ የሚወደውን ነገር የመለየት እና በዚያ ዘርፍ መዳረሻ ራእዩን የማወቁን ጉዳይ ከፊት እናገኘዋለን። “እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን።” (ሮሜ ፲፪፥፮) እንዳለ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተሰጦአችንን ወይም ደግሞ ጸጋችንን መለየት ተቀዳሚ ተግባር ነው። የአይናችን ተግባር ማየት እንጅ መስማት ወይም ደግሞ መሔድ እንዳይደለ ሁሉ ሁሉም ሰው በአንድ አይነት ብቻ የንግድ ሴክተር ሊሰማራ አይችልም። ስለሆነም የራስን የተለየ ፍላጎት፣ ልዩ ችሎታ እና ልምድ ለይቶ ከስኬት የሚያደርስ ግልጽ ዕቅድ መንደፍ ይገባል። በሚገባ የተጻፈ ራእይ የስኬት አመላካች ኮምፓስ ሆኖ ያገለግላል።
ይቆየን!
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Sat, 09 Aug 2025 12:04:07 +0300
ስኬታማ የሥራ ፈጣሪ ለመሆን ምን እናድርግ?
ክፍል አንድ


የሰው ልጅ የተሳካለት ሥራ ፈጣሪ ለመሆን የያዘውና ተግባራዊ የሚያደርግበት ገንዘብ ወሳኝ ቢሆን በቅድሚያ ሁሉን ማድረግ የሚቻለውን ልዑል እግዚአብሔርን መያዝ ቀዳሚ ሥራው ማድረግ አለበት ። ሥራ ፈጣሪው ሁሉን ነገር አስቦ ከመጀመሩ በፊት በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጠንክሮ ፈጣሪውን አስቀድሞ መሄድ ሲችል ስኬትን መቀዳጀት እንዲችል ያስችለዋል።

“በዐሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና፦ ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ? አላቸው።” (ማቴዎስ ፳፥፮)
ሥራ ፈጣሪነት በበርካታ ፈተናዎች የተሞላና የማይቋረጥ ትጋትን ይጠይቃል፤ ስኬታማ የሥራ ፈጣሪ ለመሆን ጸጋን ማወቅና አብዝተን የምንወደውን ሙያ ለይቶ ግልጽ ዕቅድ ማውጣት ቀዳሚው ተግባር ነው። ”የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው። መንፈስ ግን አንድ ነው። ” (፩ቆሮ. ፲፪፥፭)
በዚህ ነገሮች በፍጥነት በሚለዋወጡበት ዓለም የሥራ ፈጣሪነት ጉዳይ ከፍተኛ ትጋትን ይጠይቃል። ሥራ ፈጣሪ ለመሆን የሚተጉ ሰዎች የፈጠራ ነጻነትን እና ፈጠራቸው ይዞላቸው የሚመጣውን ጥቅም አስቀድመው ቢያስቡም የሚያልፉበት መንገድ ግን ፈታኝ ነው።
ስኬታማ ሥራ ፈጣሪ ለመሆን በርካታ ፈተናዎችን ማለፍ፤ መውደቅ እና መነሳት እንዲሁም የማይቋረጥ ትጋት ማድረግን ይጠይቃል። “ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ።” እንዲል (ሮሜ ፲፪፥፲፩)
ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ነጥቦች ስኬታማ የሥራ ፈጣሪ ለመሆን የሚያግዙ ወሳኝ መንገዶች ናቸው።
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Fri, 08 Aug 2025 10:37:47 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Thu, 07 Aug 2025 10:00:38 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Thu, 07 Aug 2025 10:00:22 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Wed, 06 Aug 2025 15:03:08 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Tue, 05 Aug 2025 10:13:59 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Mon, 04 Aug 2025 11:10:03 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Mon, 04 Aug 2025 11:02:30 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Mon, 28 Jul 2025 12:05:23 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Fri, 25 Jul 2025 10:52:39 +0300
The Angel of God saved the mother and son saints

Archangel Saint Gabriel performed miracle for Saint Cyriacus (Qirkos) and Julitta (Iyalota) his mother on Hamele 19. When this saint was a child, and his days were three years, his mother took him and fled from the country of Rome to another country. And she found there the brother of the governor from whom she had fled, and certain men laid information against her before him, and he had her brought and questioned her about the worship of idols.https://eotcmk.org/e/
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Fri, 25 Jul 2025 10:51:13 +0300
ጽኑ እምነት

ዲያቆን ተስፋዬ ቻይ
ሐምሌ ፲፰፤፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት


የእምነት ጽናታቸው የተጋድሎ ሕይወታቸው እጅግ ድንቅ የሆነው፣ ለሌላው ማስተማሪያ ይሆን ዘንድ ገድላቸው ከተጻፈላቸውና የመታሰቢያ በዓል ከሚከበርላቸው ሰማዕታቱ መካከል ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ አብነት የሚሆኑ ናቸው፡፡ እለእስክንድሮስ የተባለው መፍቀሬ ጣዖት፣ ጸላዬ እግዚአብሔር፣ የዲያቢሎስ ምርኮኛ የሆነው በሰው እጅ ከድንጋይ ተጠርቦ ለተሠራው ጣዖት ሕዝቡን እንዲሰግዱ ሲያስገድድ፣ ስቶ ሲያስት፣ ሲያስፈራራ ኖሯል፡፡ አብዛኛው ለሥጋው ሳስቶ፣ መከራውን ተሰቆ ለጣዖት ሲሰግድ ሕፃን ቂርቆስ ግን እምቢ አለ፤ የቀደሙ አባቶቹን የተጋድሎ ታሪክ ያውቃልና ልቡን አጸና፤ ለመከራው ተዘጋጀ፤ እናቱ ለልጇ ሳስታ፣ ለጣዖት ልትንበረከክ፣ ልትክድ ሲዳዳት ሕፃኑ ግን ጸና፤ መከራውን ሳይሰቀቅ እለ እስከንድሮስ ላቆመው ጣዖት አልሰግድም አለ፡፡https://eotcmk.org/a/
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Tue, 22 Jul 2025 11:37:12 +0300
ወገንተኝነት
መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ክፍል አምስት
አቤቶ ፋሲል

በዐሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንጉሥ ዓፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ዓፄ ሱስንዮስ በሮም ካቶሊካውያን በእነ አልፎንሱ ሜንዴዝ ተንኮልና ሤራ ተጠልፈው ‹‹ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ ሃይማኖት ይርከስ፤ የሮም ካቶሊካዊ ሃይማኖት ይንገሥ›› የሚል ዐዋጅ ዐወጁ፡፡ ‹‹አልቀበልም የአባቶቼን ሃይማኖት አልተውም!›› ያለውንም እስከ ስምንት ሺህ የሚጠጋ የመናገሻ ከተማቸውን የጎንደርን ገበሬ በግፍ አስፈጁ፡፡ ይህን የንጉሡን ዕብሪትና ዐውቅልሃለሁ ከአብራካቸው የተከፈሉት ልጃቸው አቤቶ ፋሲል አልተቀበሏቸውም፡፡ አቤቶ ፋሲል የአባትነት ወገንተኝነትና ዝምድና ሳይዛቸው የአባታቸውን የግፍ ሥራ ተቃወሙ፡፡ አባታቸውም ከዚህ ክፉ ሥራቸው እንዲመለሱ በሕዝቡም ላይ ከሚያደርጉት የግፍ ሥራ እጃቸውን እንዲሰበስቡ አሳሰቡ፡፡ በዚህም ሊመጣ ያለን አያሌ ጥፋት መልሰዋል፡፡ የምትሠራበት ተቋም፣ ወንድምህ፣ እኅትህ፣ ልጅህ፣ ዘመድ አዝማዶችህ የተገፋሁ የተበደልኩ ክስና አቤቱታ ይዘው ሲመጡ ወገንተኛ ሳይሆን ፍትሐዊ ሆነህ ጉዳዩን ተመልከት፡፡
ፍትሐዊ ስትሆን ዐይነ ልቡናህ የንሥር ዓይን ይሆናል፡፡ አላግባብ አጥፍተው ተበደልን የሚሉ ወገኖችህንም ከስሕተትና ከጥፋት ትታደጋለህ፡፡ ወገንተኝነታችን ለእውነት ሲሆን ፍትሐዊነት ይነግሣል፤ እግዚአብሔርንም እንመስለዋለን፡፡ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ፍትሐዊ አምላክ ነው፡፡ ከሰማያት የወረደው ከእመቤታችን ተወልዶ ያዳነው የተወሰነ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ሳይሆን ሰውን ሁሉ ነው፡፡ ፀሐይ የሚያወጣው፣ ዝናብ የሚያዘንበውም ላመኑት ብቻ ሳይሆን ላላመኑትም ጭምር ነው፡፡ ንስሓን የሰጠው፣ መንግሥተ ሰማያትን ያዘጋጀው፣ ሥጋውን የቆረሰው ደሙንም ያፈሰሰው፣ በዚህም ወገኖቼ ያለው ጥቂቶችን ሳይሆን ዓለምን በሙሉ ነው፡፡ ሲፈርድም ሚዛኑ ማነህ? ሳይሆን ‹‹አይቴ ነበርከ፤ የት ነበርክ፤ ምንተ ገበርከ፤ ምን ሠራህ?›› በሚለው ነው፡፡ (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ አባ ጎርጎርዮስ፣ ገጽ ፶፯)
መልካም ከሠራን ይፈርድልናል፤ ክፉ ከሠራን ይፈርድብናል፡፡ ሰው ከፍ ሲልም ክርስቲያን ከሆንን ለእውነት እንጂ ወገኔ ለምንለው አካል አንቆምም፡፡ በዓለም በሚደረጉ የእርስ በእርስ መጠፋፋቶችና ጦርነቶች ላይ የራሳችንን ጥናት አድርገን ፍትሐዊ ዘገባ እናቀርባለን የሚሉና ገለልተኞች ነን የሚሉ አያሌ ዓለም አቀፍ ተቋማት ‹‹ከወገንተኝነት የጸዳ ዘገባችን ይኸው›› ይበሉ እንጂ ወገንተኝነታቸው ለእውነት ሳይሆን ለገዛ ራሳቸው ጥቅም ነው፡፡
አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ጭፍን ከሆነና እውነትና ፍትሐዊነት ከጎደሉት ወገንተኝነት በቸርነቱ ይሰውረን፤ አሜን!
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Tue, 22 Jul 2025 11:02:45 +0300
በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አገልግሎቱን በማጠናከር በግቢ ጉባኤያት ላይ ውጤታማ ሥራ ለመሥራትና ብቁ አገልጋዮችን ለማፍራት ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቶቹን ለማስፈጸም ይረዳውም ዘንድ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ትኬት ሽያጭ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በማሠራጨት ላይ ይገኛል፡፡ እርስዎም ትኬቱን በመግዛት ትውልድን ለመቅረጽ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አሻራዎን ያኑሩ፡፡
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1001718832800 Mon, 21 Jul 2025 22:54:57 +0300
የቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ካርታ

ክፍል ሁለት
ዲያቆን ይትባረክ መለሰ
ሐምሌ ፲፬፤ ፳፻፲፯ ዓ.ም.

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! እንደምን ሰነበታችሁ? የጊዜ ባለቤት አምላካችን ክብር ምስጋና ይድረሰውና ዳግም አገናኝቶናል! በመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የመጭው ዐሥር ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግቦችን ማስተዋወቅን ዓላማ አድርገን ስለ ዕቅድ በጥቅሉ አቅርበንላችሁ ነበር፡፡

በዚህ ክፍለ ጽሑፍ ደግሞ ስለ መሪ ዕቅዱ ይዘቶች በጥቂቱ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡https://eotcmk.org/a/
Подробнее
]]>