Лента постов канала 4-3-3 World News (@Ethionews433) https://t.me/Ethionews433 ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ለመስጠት @atsbaha12 ይጠቀሙ ru https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 17 Aug 2025 17:25:05 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 17 Aug 2025 15:11:35 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 17 Aug 2025 09:56:33 +0300
Подробнее
10.09 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 16 Aug 2025 14:52:44 +0300
Подробнее
13.11 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 15 Aug 2025 23:19:29 +0300
Подробнее
14.13 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 15 Aug 2025 20:29:27 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 15 Aug 2025 15:18:59 +0300
Подробнее
13.51 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 15 Aug 2025 10:11:50 +0300
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 15 Aug 2025 09:38:32 +0300
Подробнее
13.21 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 15 Aug 2025 07:45:33 +0300
Подробнее
13.72 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 14 Aug 2025 17:21:02 +0300
Подробнее
13.69 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 14 Aug 2025 16:05:32 +0300
Подробнее
13.19 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 14 Aug 2025 12:37:40 +0300
Подробнее
13.64 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 13 Aug 2025 15:52:28 +0300
በደቡብ አውሮፓ በቀጠለዉ የሙቀት ማዕበል ግሪክ ከሰደድ እሳት ጋር እየታገለች ነው፡፡

በመላው ደቡብ አውሮፓ በተከሰተው የሙቀት ማዕበል ምክንያት በግሪክ በርካታ የሰደድ እሳቶችን ለማጥፋት የእሳት አደጋ ተከላካዮች እየታገሉ ነው ተብሏል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በመላው ግሪክ ከ1መቶ52 በላይ አዳዲስ ቃጠሎዎች የተከሰቱ ሲሆን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

ከ4ሺህ 8መቶ በላይ የሚጠጉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች እሳቱን ለመቆጣጠር ከየአቅጣጫው ጥረት እያደረጉ መሆኑን ያስነበበዉ ቢቢሲ ነዉ፡፡

በስፔን፣ በአልባኒያ እና በቱርክ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፤ የእሳት አደጋ ተከላካዮችን ጨምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ ሌሎች ደግሞ በቃጠሎ እና በጭስ ታፍነዉ ሆስፒታል ገብተዋል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በበርካታ አካባቢዎች የሙቀት መጠኑ ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ የነበረ ሲሆን፤ በፈረንሳይ እና በስሎቬንያ ሪከርድ የሆነ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል።

ቢያንስ 13 የእሳት አደጋ ተከላካዮች በቃጠሎ እና በሌሎች ጉዳቶች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ሲገለጽ፤ በቀጣዮቹ ቀናት ሁኔታው ይበልጥ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡

የነፍስ አድን ጀልባዎች በእሳት የተከበቡ የባህር ዳርቻ ጎብኚዎችን ለቀው እንዲወጡ እያደረጉ ሲሆን፤ባለሥልጣናቱ የአውሮፓ ኅብረት አገሮች የእሳት አደጋ መከላከያ አውሮፕላኖችን እንዲልኩ ጠይቀዋል ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

@Ethionews433
Подробнее
14.43 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 13 Aug 2025 15:32:02 +0300
ኢትዮጵያ ያሏት የዝሆኖች ቁጥር ከ2ሺህ 5መቶ አይበልጥም ተባለ

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 2ሺህ 5 መቶ የሚደርሱ ዝሆኖች እንዳሏት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በዓለም ላይ የሚገኙት ዝሆኖች ቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊዮን በታች ደርሷል።

39 የሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት የዝሆን መገኛ ቢሆኑም ከእነዚህ ውስጥ 35ቱ ያላቸው የዝሆን ብዛት አነስተኛ እንደሆነ ገልፀዋል።እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ቦትስዋና፣ናሚቢያ እና ዚምባቡዌ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የዝሆን ቁጥር እንዳላቸው አቶ ዳንኤል ተናግረው ሀገራቱ የተሻለ የአስተዳደር ስርአትን መከተላቸው ለዚህ ጥሩ አበርክቶ ሊኖረው ይችላል ብለዋል፡፡

አያይዘውም እንደ ሀገር አሁን ላይ ከ2ሺህ እስከ 2ሺህ 5 መቶ የሚደርሱ ዝሆኖች ብቻ እንደሚገኙ አስረድተዋል።ዛሬ ነሀሴ 6 ቀን ወይም  August 12 ዓለም ሁሉ ስለ ግዙፎቹ እና እጅግ አስደናቂ በሆነው ተፈጥሯቸው ብዙዎቻችንን ስለሚያስደምሙት የዓለም ዝሆኖች ቀን የሚያወራበት ነው፡፡ኢትዮጵያም በዚሁ እለት እጅግ አሳሳቢ በሆነ የህልውና አደጋ ውስጥ የሚገኙ ዝሆኖቿን እየዘከረች ይህን ድንቅ የተፈጥሮ ሀበት ለትውልድ ማሻገር በሚቻልባቸው ፍሬ ጉዳዮች ዙሪያ ስትመክር ትውላለች፡፡

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣንም  ዓለም በሰፊው ከሚወያይበት መሪ ቃል ባሻገር “የኢትዮጵያን ዝሆኖች ከመጥፋት እንታደግ”  በሚል ሀሳብ ዕለቱን በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብሮች በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱን ስለማጠናቀቁ አስታውቋል።

ቅድስት ደጀኔ

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
13.73 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 13 Aug 2025 13:30:43 +0300
ፑቲን ኩርስክን ነፃ በማውጣት የሰሜን ኮሪያውያንን ጀግንነት አድንቀዋል ስትል ፒዮንግያንግ አስታወቀች

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ባደረጉት ውይይት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የሩስያን የኩርስክን ግዛት ከዩክሬን ጦር ለማስመለስ ያደረጉትን ጀግንነት አድንቀዋል ሲል የሰሜን ኮሪያ መንግስት ሚዲያ ዘግቧል። ፑቲን ለኪም እንደተናገሩት የሰሜን ኮሪያ ድጋፍ እና ራስን መሠዋት የማድረግ መንፈስ ወታደሮቿ በምዕራቡ ዓለም ነፃ በወጡበት ወቅት ያሳዩትን ጀግንነት በጣም አደንቃለሁ ሲል የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት ረቡዕ እለት ዘግቧል።

ኪም "ልባዊ ምስጋናቸውን" ለፑቲን ገልፀው ፒዮንግያንግ ባለፈው አመት በሁለቱ ወገኖች ለተፈረመው የጋራ መከላከያ ውል መንፈስ ሰሜን ኮርያ ሁልጊዜ ታማኝ ትሆናለች እንዲሁም "ወደፊት በሩሲያ አመራር የሚወሰዱ እርምጃዎችን ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ" ተናግረዋል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል ሲል የሰሜን ኮርያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት ዘግቧል። ኪም ጆንግ ኡን እና ፑቲን በቅርብ የጋራ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ይህ መረጃ የተሰማው ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በአላስካ ሊገናኙ ከቀናት በፊት ሲሆን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ላይ ለመወያየት ያለመ ነው።ሞስኮ በአለም መድረክ መገለሏን ተከትሎ በሰሜን ኮሪያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የመጨረሻው ምልክት ተደርጎ ተወስዷል። ባለፈው ወር ኪም ለሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንደተናገሩት ፒዮንግያንግ ሞስኮ በዩክሬን ላይ የምትወስደውን እርምጃ ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ትደግፋለች ማለታቸውን የሰሜን ኮሪያ መንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

በስምኦን ደረጄ

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
14.39 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 12 Aug 2025 17:03:06 +0300
የካናዳ ፍርድ ቤት የዩክሬን አየር መንገድ ለአደጋ ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ መክፈል እንዳለበት ወሰነ

የዩክሬን አለም አቀፍ አየር መንገድ በበረራ ፒኤስ 752 ላይ በደረሰበት ጉዳት ለተጎጂ ቤተሰብ መክፈል አለበት ሲል የኦንታሪዮ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አፅድቋል። 55 ካናዳውያን እና 30 ቋሚ ነዋሪዎችን ጨምሮ 176 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላኑ ከቴህራን ከተነሳ በኋላ በሁለት የኢራን ሚሳኤሎች ተመትቶ ወድቋል። የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፖሬሽን ጥቃት ሊደርስብኝ ነዉ ብሎ በማሰብ አውሮፕላኑ ላይ መተኮሱ ይነገራል።

ሌላ የካናዳ ፍርድ ቤት ባለፈው አመት እንዳስታወቀው አየር መንገዱ በግጭት ቀጠና ውስጥ ወይም አካባቢ ሲነሳ ትክክለኛውን የአደጋ ግምገማ ባለማጠናቀቁ ሃላፊነት የጎደለው ነው ብሏል።በአለምአቀፍ የሞንትሪያል ኮንቬንሽን መሰረት አንድ ቤተሰቡ እስከ 180,000 ዶላር የሚደርስ ጉዳት ሊጠይቅም ይችላል፣ እናም መጠኑ ሊጨምር የሚችለው አየር መንገዱ ቸልተኛ ከሆነ ነው።

አየር መንገዱ ለተጎጂ ቤተሰቦች የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን ሊገድብ አይችልም፣ አየር መንገዱ የቀድሞዉን የፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ አድርጎታል።የአንዳንድ ቤተሰቦች ጠበቃ ጆ ፊዮራንቴ ውሳኔውን በደስታ መቀበላቸዉን ተናግረዋል፡፡በካናዳ ፕሬስ በታተመው መግለጫ ላይ ፊዮራንቴ “የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ለቤተሰቦች ትንሽም ቢሆን ፍትህ ያመጣል” ብሏል ።

ነገር ግን ቤተሰቦች ከኢራን ካሳ እየፈለጉ ነው፣ ባለሥልጣናቱ አውሮፕላኑ በስህተት መመታቱን አምነዋል።ከአደጋው ከአምስት ዓመታት በኋላ ኢራን ለአደጋው ሙሉ ህጋዊ ሀላፊነቷን እስካሁን አልወሰደችም።በአለም አቀፍ ህግ በኢራን ላይ ክስ እየቀረበ ሲሆን ካናዳ ግን እልባት ላይ ለመድረስ አመታት እንደሚቀረው ተናግራለች።በአደጋው ከስዊድን፣ ከዩክሬን ፣ከእንግሊዝ፣ ከጀርመን፣ ከአፍጋኒስታን እና ከኢራን የመጡ ዜጎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 12 Aug 2025 00:11:52 +0300
"ቡራ ቡል" በተሰኘ የቲክ ቶክ ስም የሚታወቀውን ግለሰብ ከተሸሸገበት የትግራይ ክልል ለማምጣት እየሰራሁ ነው ሲል ፖሊስ አስታወቀ

በከተማዋ ውስጥ በቡድን እየተደራጁ የውንብድና ስራ ሲሰሩ የቆዩ፣ በቲክቶክ Live ላይ ሳይቀር ራሳቸውን እየቀረፁ የተለያዩ ወንጀሎች ሲፈፅሙና ከተማዋን ሲያውኩ፣ ገጀራ ይዘው ለመገዳደል ሲፈላለጉና ሲዛዛቱና መሰል ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ልጆች ላይ ክትትል ተደርጎ ብዙዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑት በቀን 7/11/2017 ዓ/ም እንወጋጋለን በማለት በማህበራዊ ድህረ ገፅ ሲዛዛቱ የነበሩ በሻሌ ፖሊስ ጣቢያ ተይዘዋል።

ከነዚህ ውስጥ

1ኛ አብዮ ደግ አረገ
2ኛ በረከት ዳንኤል የተባሉት ግለሰቦች በቲክቶክ አካዉንት “live” በመግባትና በተሽከርካሪ በመዘዋወር በስለት ለመወጋጋት እየተፈላለጉ መሆኑን ከህብረተሰቡ ጥቆማ ደርሶ ተይዘዋል።

ሌላኛው ወንጀለኛ “ብሩክ ተስፋዬ አርአያ” የእናቱ ስም ኮረኔል አመለወርቅ፥ በቲክቶክ ስሙ (ቡራ ቡል) የተባለው ልጅ ከዚህ በፊት አደንዛዥ እፅ ይዞ በመገኘት ወንጀል የፌደራሉ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2 ኛ አርቲዲ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 23 ቀን 2017 የአንድ አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት ፍርደኛ ሲሆን ተከሳሹ ከህግ ሸሽቶ በመጥፋቱና በተያያዙ ወንጀሎች እየተፈለገ እንደሚገኝና ባሁኑ ሰአት በትግራይ ክልል ተሸሽጎ እንደሚገኝ ወንጀለኛውን ለማምጣትም ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተገልጿል።


በቀጣይም ከተማዋ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ የታገዘም ሆነ ማንኛውም አይነት የከተማዋን ነዋሪ ሰላም እና ደህንነት የሚያውክ የውንብድና ስራ በሚሰሩ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህግ የማስከበር ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

ምንጭ:- ናትናኤል መኮንን

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
21.58 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 11 Aug 2025 17:10:10 +0300
አንጀሊና ጆሊ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልን ጎበኙ

ዝነኛዋ አሜሪካዊት ተዋናይት ፣ የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ የሆኑት አንጀሊና ጆሊ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።

ተዋናይቷ ያደረጉት ጉብኝት በዋነኝነት ሆስፒታሉ እየሰጠ በሚገኘው መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ፣ የሚታዩ ለውጦችን እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

በጉብኝቱ ላይ አንጀሊና የሆስፒታሉን የቲቢና መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና አገልግሎት መስጫ ዋርድ ፣ ላብራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

አንጀሊና ወደ ሆስፒታሉ ከረጅም ጊዜያት በፊት መጥተው እንደነበር ያስታወሱ ሲሆን በአሁኑ ጉብኝታቸው ላይ ሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦች አምጥቶ በመመልከታቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አክለውም ሆስፒታሉ ድጋፍ ቢደረግለት በቀጣይ የተሻለ
አገልግሎት ለታካሚዎች መስጠት በሚያስችለው አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዳለ በጉብኝቱ ላይ መገንዘባቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በሆስፒታሉ በቲቢ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገኘው እድገት በእጅጉ የሚደነቅ እና የሚያስተማምን ስለሆነ በቀጣይ በጂ.ኤች.ሲ (Global Health Committee (GHC)) በኩል ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ በበኩላቸው ቲቢን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተዋናይቱ ላሳዩት ዘላቂ ቁርጠኝነት ፣ ልግስና እና በቀጣይ ለሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አንጀሊና ጆሊ ከፊልም ስራ ባሻገር በአለምዓቀፍ ደረጃ ለስደተኞች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥብቅና በመቆም በ UNHCR (United Nations High Commissioner for Refugees) የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እንዲሁም ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ከ20 ዓመታት በላይ በማገልገል በሰሩት ሰፊ የሰብዓዊነት ስራ ይታወቃሉ።

/ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል /

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
18.72 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 11 Aug 2025 15:09:02 +0300
እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት አምስት የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ተገደሉ

በጋዛ ከተማ አልሺፋ ሆስፒታል አቅራቢያ በእስራኤል ባደረሰችው ጥቃት አምስት የአልጀዚራ ጋዜጠኞች መገደላቸውን ተቋሙ ገልጿል። ዘጋቢዎቹ አናስ አል ሻሪፍ እና መሀመድ ቂቀህ ከካሜራማን ኢብራሂም ዛህር፣ መሀመድ ኑፋል እና ሞአመን አሊዋ ጋር በሆስፒታሉ ዋና በር ላይ በሚገኝ ድንኳን ውስጥ ነበሩ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል። እሁድ እለት የተፈፀመው “የታቀደው ግድያ” በፕሬስ ነፃነት ላይ የተደረገ ሌላ ግልጽ እና ሆን ተብሎ የተደረገ ጥቃት ነው ሲል በመግለጫው ገልጿል።

ከጥቃቱ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የእስራኤል መከላከያቅ ሃይሉ አናስ አል ሻሪፍ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መሆኑን አረጋግጦ በቴሌግራም ፖስት ላይ ባጋራው መረጃ ጋዜጠኛው "በሃማስ የአሸባሪ ቡድን መሪ ሆኖ አገልግሏል" ሲል የእስራኤል መከላከያ ጽፏል። የመከላከያ ሃይሉ ስለተገደሉት ሌሎች ጋዜጠኞች ምንም አልተናገረም። በአጠቃላይ በጥቃቱ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

አልጃዚራ መጀመሪያ ላይ አራት ሰራተኞቻቸው መገደላቸውን ተናግሯል፣ነገር ግን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የሟቾቹን ቁጥር ወደ አምስት ከፍ ኡድርጎታል። አል ሻሪፍ በጋዛ ሰርጥ ምን እየተከሰተ እንዳለ አለም እንዲያውቅ ብቸኛው ድምጽ እና እውቅና ያለው ጋዜጠኛ ነበረ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።በጦርነቱ ጊዜ እስራኤል ወደ ጋዛ የሚገቡ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች በነፃነት እንዲዘግቡ አልፈቀደችም። ስለዚህ፣ በርካታ መገናኛ ብዙሄን የመረጃ ሽፋን ለማግኘት በግዛቱ ውስጥ ባሉ የሀገር ውስጥ ዘጋቢዎች ላይ ጥገኛ ሆነዋል።

በስምኦን ደረጄ

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
16.21 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 11 Aug 2025 12:43:18 +0300
ከትግራይ ክልል 189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደረገ
+++++++++++++++++

በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከትግራይ ክልል 189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን የትግራይ ክልል ማዕድን ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ማዕድን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዓለም ሀድጉ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንከ ማስገባት ተችሏል። በዚህም ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።

በባህላዊ መንገድ በተለያየ የማዕድን ሥራ ለተሰማሩ 50 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

የማዕድን ቦታዎችን የመለየት ሥራ በርካታ ወጪ እና ማሽኖችን የሚጠይቅ ነው ያሉት አቶ ተስፋዓለም፤ ክልሎችም በራሳቸው አቅም አጥንተው እንዲለዩ የሚያደርግ አካሄድ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
++++++++++++++++++++++++

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
17.02 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 11 Aug 2025 11:36:02 +0300
ቤት አልባ ሰዎች ከዋሽንግተን "በፍጥነት" መውጣት አለባቸው አሉ ትራምፕ


የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሺንግተን ዲሲ የሚታዩ ወንጀሎችን ለመከላከል ቃል ገብተው በከተማዋ የሚገኙ ቤት የሌላቸው ሰዎች "መውጣት አለባቸው" አሉ።


የከተማዋ ከንቲባው ግን ዋይት ሐውስ ዋና ከተማዋን ከባግዳድ ጋር በማነጻጸሩ ተችተዋል።


እሁድ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ "የምትቆዩበት ቦታ እንሰጣችኋለን፤ ነገር ግን ከዋና ከተማው የራቀ ነው" በማለት ለጥፈዋል።


የሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ከተማዋን "ከዚህ በፊት ከነበረችው የበለጠ አስተማማኝ እና የበለጠ ውብ" ለማድረግ ስለወጠኑት ዕቅድ ሰኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።


የከተማዋ ከንቲባ ዲሞክራቷ ሙሪየል ቦውሰር "የወንጀል መጨመር እያጋጠመን አይደለም" ሲሉ አስተባብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።
 

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
16.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 11 Aug 2025 09:38:04 +0300
አውስትራሊያ በመስከረም ወር ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ልትሰጥ ነው

አውስትራሊያ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ የወሰዱትን ተመሳሳይ እርምጃ በመከተል በመስከረም ወር ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት ማቀዷን አስታውቃለች።

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ፤ይህ ዉሳኔ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይፋ የሚደረግ ሲሆን፤ይህም አገራቸዉ ከፍልስጤም ባለስልጣን ጋር ከተነጋገረች በኋላ መሆኑን ተናግረዋል።

ባደረጉት ንግግር በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የጥቃት አዙሪት ለመስበር እና በጋዛ ያለውን ግጭት፣ ስቃይ እና ረሃብ ለማስቆም የሁለት-መንግስት መፍትሄ ለሰብአዊነት የተሻለው ተስፋ ነው ብለዋል።

በጋዛ ያለውን ጦርነት እንድታቆም ከፍተኛ ጫና እየደረሰባት ያለችው እስራኤል በበኩሏ የፍልስጤምን መንግስት እውቅና መስጠት ሽብርተኝነትን መሸለም ነዉ ስትል መናገሯን ያስታወሰው ቢቢሲ ነው።


እስከዳር ግርማ

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
17.78 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 10 Aug 2025 14:06:53 +0300
በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ያቄር ቀበሌ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ከግንቦት ወር በኋላ 22 ሰዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳቶች መሞታቸው ተገለጸ።

በቀጣይ ሳምንታት እርዳታ የማይደርስ ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊያልቁ እንደሚችሉ የቆላ ተምቤን ወረዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎይቶም ገብረ ሐዋርያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
18.24 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 09 Aug 2025 21:26:33 +0300
600 ሚልየን ብር የወጣበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አርማ እንዳይተዋወቅ በባለስልጣናት ተከለከለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  አዲስ የማንነት አርማ ከከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት በተሰነዘረ ተቃውሞ ሳቢያ እንዲቆም መደረጉን ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ።

ባለስልጣናቱ የቀረበውን አዲስ የአርማ ንድፍ አልወደዱትም ተብሏል።

እንደ ምንጮቹ ገለፃ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይህ አርማ ባለፈው ሳምንት ይፋ ለማድረግ ታቅዶ ነበር። ሆኖም የባንኩ ከፍተኛ ኃላፊዎች በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ ዕቅዳቸውን እንዲያቆሙ ተደርጓል።

የባንኩ ኃላፊዎች ከአምሳ ዓመታት በላይ ባልተለወጠው እና የባንኩ መለያ በሆነው ወርቃማ ሽክርክር ቅርጽ ያለው አርማ ምትክ ዘመናዊና ነጠላ ቀለም ያለው አርማ ለማስቀመጥ አስበው ነበር።

ጥቁሩ አርማ ‘CBE’ የሚሉትን ፊደላት፣ ዘመናዊና የተዘበራረቁ በሚመስሉ ፊደላት ተጽፎ፣ ከስር ደግሞ ‘ሁልጊዜ አስተማማኝ’ የሚል መፈክር ይዟል።

የአማርኛ ጽሁፍ ያላካተተው አዲሱ አርማ አንዳንዶች አርማውን “አሰልቺ” ነው በማለት የተቹት ሲሆን  ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በአዲሱ አርማ  አልተስማሙም።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አዲሱ አርማ የተረዱት በይፋ ሊተዋወቅ  ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ነው። ከዚህ በፊት አያውቁም ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ አርማው ሊተዋወቅ አንድ ቀን ቀደም ብሎ እንዲቆም አዘዙ” ሲሉ አንድ ከፍተኛ ምንጭ ለሪፖርተር ተናግረዋል።

@Ethionews433 @Ethionews433
Подробнее
24.06 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 09 Aug 2025 01:43:10 +0300
Подробнее
23.49 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 09 Aug 2025 01:34:40 +0300
Подробнее
14.88 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 08 Aug 2025 14:26:40 +0300
Подробнее
22.77 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 08 Aug 2025 10:50:07 +0300
Подробнее
18.77 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 08 Aug 2025 09:02:47 +0300
Подробнее
21.18 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 07 Aug 2025 22:08:04 +0300
Подробнее
18.55 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 07 Aug 2025 14:15:20 +0300
Подробнее
19.27 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 07 Aug 2025 13:14:45 +0300
Подробнее
16.28 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 07 Aug 2025 12:10:26 +0300
Подробнее
17.02 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 07 Aug 2025 09:31:47 +0300
Подробнее
16.84 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 06 Aug 2025 14:46:24 +0300
Подробнее
18.61 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 06 Aug 2025 09:39:39 +0300
Подробнее
14.56 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 05 Aug 2025 19:08:36 +0300
Подробнее
18.78 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 05 Aug 2025 14:21:53 +0300
Подробнее
16.75 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 05 Aug 2025 12:20:37 +0300
Подробнее
16.61 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 04 Aug 2025 21:59:57 +0300
Подробнее
10.82 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 04 Aug 2025 21:44:38 +0300
Подробнее
18.51 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 04 Aug 2025 13:51:34 +0300
"በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው " - ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM)

68 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

በየመን አብያን ግዛት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስጠሟ ቢያንስ 68 ስደተኞች መሞታቸውንና 74 ስደተኞች ደግሞ የደረሱበት እንደማይታወቅ ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

በየመን የድርጅቱ ተወካይ አቤዱሳቶር ኢሶቭ ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል " በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ #ኢትዮጵያውያን ናቸው " ብለዋል።

ኢሶቭ በሰጡት ቃል፤ ' ካንፋር ' በተባለ አካባቢ የ54 ስደተኞች አስክሬን በውቅያኖስ ዳር የተለያየ ቦታ ወድቆ መገኘቱን በሌላ ቦታ የተገኘ 14 አስክሬን ወደሆስፒታል መላኩን ተናግረዋል።

12 ሰዎች ደግሞ በህይወት መትረፋቸው ተመላክቷል።

እንደ ተወካዩ ገለፃ ኢትዮጵያውያኑ አደጋው የደረሰባቸው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።[ቲክቫህ]

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
18.46 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 04 Aug 2025 12:39:34 +0300
አንዲት የኒውዝላድ ሴት በአውቶቢስ ውሰጥ የ2 አመት ልጅ በሻንጣ አድርጋ በመገኘቷ በቁጥጥር ስር ዋለች ፡፡

የ2 አመቷን ህፃን ልጅ በተሸከርካሪው የሻንጣ ክፍል ውስጥ ከተከማቹ ሻንጣዎች መካከል የአውቶቢስ ሹፌር በህይወት እንዳገኛት ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የአውቶቢሱ ሹፌር ከኦክላንድ በስተሰሜን በሚገኘው ካይዋካ ሰፈር መኪናውን በሚያቆምበት ግዜ በሻንጣ ውስጥ እንቅስቃሴ ማስተዋሉን ተናግሯል፡፡

ተሳፋሪዋ ወደ ሻንጣው ክፍል እንድትገባ እና እንድትከፍተው ከተጠየቀች በኋላ ነው የ2 አመት ህፃን ልጅ በህይወት የተገኘችው፡፡

በሰአቱ ህፃኗ ከፍተኛ ሙቀት ቢኖራትም በአካሏ ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳደርስባት በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መወሰዷን ተጠቅሷል፡፡

ባለስልጣናቱ ይህች ህፃን ለምን ያህል ሰአት በሻንጣ ውስጥ እንደቆየች አልገለፁም ፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለችው ኒውዝላንዳዊት ሴት፤ ልጅን በማንገላታት ክስ እንደቀረበባት ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬው

@ethionews433
Подробнее
17.44 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 03 Aug 2025 08:27:14 +0300
በሶሪያ ጦር ላይ ጥቃት

የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በኩርድ መራሹ ሀይል ጥቃት ተሰንዝሮብኛል አለ።

ኩርዶች የሚመሩት የሶሪያውያን ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች (SDF) አራት የጦሩን ዓባላት እና ሶስት ንጹሃን ዜጎችን አቁስለውብኛል የሚል መረጃ አጋርቷል ጦሩ።

ሚኒስቴሩ ጥቃቱን "ሀላፊነት የጎደለው እና ምክንያት አልባ ነው" ሲል ገልጾታል።

ጥቃቱን ኩርድ መራሹ እና አሜሪካ አይዞህ የምትለው SDF የተሰኘው ቡድን አድርሶታል ሲል አህመድ አል-ሻ’ርዓ የሚመሩት የደማስቆ መንግስት በመከላከያው በኩል አሳውቋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው “ማንቢጅ” በተሰኘች የገጠር ከተማ እንደሆነም ዘገባው ይጠቁማል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከሶሪያ ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች (SDF) በኩል የተባለ ነገር የለም።

ሶሪያ የበሽር አል-አሳድ መንግስት ከተገረሰሰ በኋላ ፖለቲካዊ መረጋጋት በአህመድ አል ሻ’ርዓ (አል ጁላኒ) አማካኝነት ታመጣለች የሚል ተስፋ ቢጣልባትም ዛሬም በውጭ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት እየታመሰች ትገኛለች።

ዘገባው የጀሩሳሌም ፖስት ነው።

በ-ቢኒያም ካሴ

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
15.12 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 02 Aug 2025 21:19:43 +0300
የሩሲያን ምድር በድሮን እያደባየሁት ነዉ ! /ዩክሬን /

‎ዩክሬን የሩሲያን ቁልፍ ስፍራዎች ላይ መብረቃዊ ጥቃት መድረሷን ተናገረች ።

‎የዩክሬን ጦር ዛሬ ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ በሩሲያ ውስጥ የነዳጅ ማምረቻዎችን ዋና ዋና ማጣሪያ ፋብሪካን እንዲሁም የድሮኖችን እና የኤሌክትሮኒክስ ፋብሪካን ወታደራዊ አየር ማረፊያን ጨምሮ መምታቱን ተናግሯል።

‎በቴሌግራም ላይ በሰጠው መግለጫ የዩክሬን ሰው አልባ ሲስተም ሃይሎች ከሞስኮ በስተደቡብ ምስራቅ 180 ኪሜ (110 ማይል) ርቀት ላይ በምትገኘው ሪያዛን የሚገኘውን የነዳጅ ማጣሪያ በመምታቱ በግቢው ላይ የእሳት ቃጠሎ ዳርገዋል ብሏል።

‎መግለጫው በሰሜን ምስራቅ ዩክሬን በሚያዋስነው በቮሮኔዝ ክልል የሚገኘው የአናኔፍቴፕሮዶክት ዘይት ማከማቻ ቦታ መመታቱን ቢገልፅም ተቋማቱ እንዴት እንደተመቱ ባይገልፅም ከዚህ በተጨማሪ የዩክሬን ኤስቢዩ የስለላ ድርጅት ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ በዩክሬን ዒላማዎች ላይ የረዥም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለማጥቃት ያገለገለውን የሩሲያ ፕሪሞርስኮ-አክታርስክ ወታደራዊ አየር መንገድን መምታቱን አስታውቋል።

‎የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በየእለቱ በሚያወጣዉ ዘገባ እንዳስታወቀው የመከላከያ ክፍሎቹ በአንድ ጀምበር 338 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መውደቃቸውን አስታውቋል።

‎ከዚህም በተጨማሪ በዩክሬን ምስራቃዊ ጦር ግንባር ላይ ቅዳሜ ዕለት የሩስያ ጦር እየገሰገሰ መሆኑን የገለፀዉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዶኔትስክ ክልል የሚገኘውን ኦሌክሳንድሮ-ካሊኖቭን መንደር መያዙን አስታውቋል። ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነዉ ።

(‎የኔታ ቲዩብ)

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
19.54 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 02 Aug 2025 12:23:01 +0300
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራተኛውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ዛሬ ተረከበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞችን ረጅም ርቀት መጓጓዝ የሚያስችለውን አራተኛውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ዛሬ ተረክቧል፡፡

አየር መንግዱ የተረከበው አዲሱ A350-1000 አውሮፕላን የኢትዮጵያን ገፅታ በአዲስ ዕይታ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

አየር መንገዱ አሁን ላይ እጅግ ዘመናዊ 4 ኤርባስ A350-1000 እና 20 ኤርባስ A350-900XWB አውሮፕላኖች ባለቤት መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
16.02 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 02 Aug 2025 11:08:47 +0300
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ27 ኪሎ ግራም በላይ ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአዲስ አበባ ከተማ በቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ቱሉ ዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 27 ነጥብ 75 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ጥፍጥፍ ወርቅ ከአንድ ወር በላይ ክትትል ሲደረግበት መቆየቱን የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዥነት ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ጥፍጥፍ ወርቁን በህገወጥ መንገድ በተሽከርከሪ አካል ውስጥ ደብቀው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎችና ሁለት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

የኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

(ኤፍ ኤም ሲ)

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
17.51 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 01 Aug 2025 23:20:25 +0300
ትራምፕ የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከቦች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ አዘዙ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ 2 የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከቦች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ አዘዙ።

ዶናልድ ትራምፕ እና የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቨ አሜሪካ ለሩሲያ በሰጠችው የታሪፍ ቀነ ገደብ ዙሪያ ባለፉት ቀናት ቃላት ሲወራወሩ ነበር።

ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት ሳምንት በፊት ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የምታደርገው ጦርነት ላይ የተኩስ አቁም እንድታደርግ የ50 ቀናት ገደብ በመስጠት ይህ የማይሆን ከሆነ ታሪፍ እንደሚጥሉባት ዝተው ነበር።

ትራምፕ ይህንን ካሉ በኃላ በተያዘው ሳምንት ቀነገደቡን ከ 10 እስከ 12 ቀን ማውረዳቸውን ተከትሎ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ትራምፕ "የዛቻ ጨዋታ" ጀምረዋል ሲሉ ነቅፈዋል።

ከዛ ባለፈም አሜሪካ እያደረች በምትገኘው ነገር እራሷን ወደ ጦርነት እየጋበዘች ነው ያሉት ሜድቬዴቭ ይህ የሚሆን ከሆነ ሩሲያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም እንደምትችል የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል።

ትራምፕ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ የሰጡት አስተያየት ግጭት ቀስቃሽ እንደሆነ በመግለጽ ከሚሰጧቸው መሰል ያልተገቡ አስተያየቶች እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

ይህንን መሰል ንግግሮች ወዳልተፈለገ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ ያሉት ትራምፕ፤ ይህ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለው ሲሉ በትሩዝ የማህበራዊ ትስስር ገጻችው ላይ ገልፀዋል።

በዚህም ሁለት የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከቦች በተገቢው ቦታ እንዲቀመጡ ማዘዛቸውን ተናግረዋል። የባህር ሰርጓጅ መርከቦቹ የት ቦታ እንደተቀመጡ አለመገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
16.84 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 01 Aug 2025 19:31:42 +0300
ታግተናል በማለት ወላጆቻቸውን 500ሺህ ብር የጠየቁ ታዳጊዎቸ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

አጋችና ታጋች በመምሰል የማታለል ወንጀሉን የፈፀሙት አራቱ ተጠርጣሪዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ሲሆኑ ለሁለት ቀናት ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሲዝናኑ ቆይተው ገንዘብ ሲያጥራቸው በመመካከር ለቤተሰብ ስልክ ደውለዋል፡፡

ወንዶቹ አጋች ሴቶቹ ደግሞ ታጋቾች በመሆን ለሴቶቹ ቤተሰቦች በደወሉት ስልክ 5 መቶ ሺ ብር የጠየቁ ሲሆን የሴት ወላጆች አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ጥቆማ ሠጥተዋል።

ፖሊስም ለቀረበው ጥቆማ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት መረጃዎችን በማሰባሰብ አራቱንም ተጠርጣሪዎች ካሉበት ቦታ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ችሏል፡፡

የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በወቅቱ ሴት ልጆቻቸው መታገታቸውን ሲሰሙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተው እንደነበር ተናግረው ፖሊስ ላከናወነው ተግባርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በልጆች አስተዳደግ ዙርያ የቤተሰብ ኃላፊነት ከፍተኛ ሲሆን በአንዳንድ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚስተዋለው ባህሪ የነገ ተስፋቸውን ሊያጨልም የሚችል በመሆኑ ሊታረምና በወላጆች ዘንድም ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያቀርባል ።

(አዲስ ፖሊስ)

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
18.16 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 01 Aug 2025 18:14:45 +0300
ጣናነሽ ፪ ባሕዳር ከተማ ገባች

ጣናነሽ-፪ ጀልባ ወደ መዳረሻዋ ባሕር ዳር ከተማ ገብታለች፡፡

ከጅቡቲ ዶላሬ ወደብ የተነሳችው ጣናነሽ ጣናነሽ ፪ ጀልባ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የየብስ ጉዞዋን በማድረግ ዛሬ ባሕር ዳር ከተማ ገብታለች፡፡

‎38 ሜትር ርዝመት እንዲሁም በአንድ ጊዜ 188 ሰዎችን የማጫን አቅም ያላት ጣናነሽ ቁጥር ፪ ጀልባ መዳረሻዋ በሆነችዉ ባሕርዳር ከተማ ስትደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
14.58 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 01 Aug 2025 13:48:44 +0300
በ2018 ዓ.ም ተበላሽተው የቆሙ አውቶቢሶች እና ባቡሮች ወደ ስራ ይገባሉ ተባለ

በዛሬው እለት በትራንስፖርት ዘርፉ የሚሰሩ ተቋማት በጋራ በመሆን አመታዊ አፈፃፀማቸውን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም የህዝብ ቁጥር መጨመር ተከትሎ አገልግሎቱን አሁንም ተመጣጣኝ እየሆነ እንደማይገኝም ነው የተገለፀው። በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ መሰማራት የቻሉ ተቋማት አፈፃፀማቸውን ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑ ተነስቷል።

ሆኖም ለዚህም ሲባል አሁንም ድረስ ስራ ያቆሙ የአውቶቢስ እና ባቡሮች ወደ አገልግሎቶቻቸው እንዲመለሱ ሌሎች አማራጮችን መዘርጋት አስፈላጊ ስለመሆኑም ተገልጿል።

በመግለጫውም ደረጃቸውን የጠበቁ ተርሚናሎች መገንባት የተቻለበት ሁኔታ እንዳለ እና የትራንስፖርት መጫኛ እና መውረጃ ቦታዎችን ላይ የተሰሩ ስራዎች አሉም ተብሏል።

(መናኸሪያ ሬዲዮ)

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
16.32 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 31 Jul 2025 22:42:04 +0300
በ2017 ዓመት በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ካስፈተኑ 24 ትምህርት ቤቶች 50 ከመቶ በላይ ያመጣ ተማሪ የለም

በ2017 ዓ.ም በተሰጠው ክልል አቀፍ 8ኛ ክፍል ፈተና  ውጤት ይፋ የሆነ ሲሆን  በተገለጸው ውጤት መሰረት  የውቅር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  ፈተና ላይ የተቀመጡ 13 ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ  50 በመቶና በላይ  በማስመዝገብ  በወረዳው ከሚገኙ 41 ትምህርት ቤቶች መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ መያዙ ተገልጿል ።

የሌሎችን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ውጤት በተመለከተ   6 ትምህርት ቤቶች  ካስፈተኗቸው  ተማሪዎች  መካከል 90 በመቶ   በላይ የሚሆኑት  ከግማሽ በላይ  ወይም 50  ውጤት  አስመዝግበዋል ፡፡ እነዚህም  ውቅር ፤አምባፈሪት ፤አጅባር ፤አሽንጋ ፤ኢሎግና ዋሮ  ትምህርት ቤቶች ናቸው ፡፡

በሌላ በኩል ከ24 ትምህርት ቤቶች የተፈተኑ 254 ተማሪዎች  መካከል  50 በመቶና በላይ ያመጣ ተማሪ አለመኖሩን ብስራት ሬዲዮ ከአማራ ሳይንት ኮሙኒኬሽን  መረጃ ያመላክታል።በአንጻራዊነት በርካታ ተማሪዎችን ያስፈተኑ  6 ትምህርት ቤቶች  ማለትም   አዋ ፤ጓሜዳ ፤መለስሳንቃ፤መሃል ሜዳ  ሸንጎ ደፈር፤ተድባበ ማርያም   እና ገብሮ  ትምህርት ቤቶች  ከሌሎቹ ትምህርት ቤቶች አንጻር በርካታ ተማሪዎችን ያስፈተኑ ቢሆኑም  50 በመቶና በላይ ያመጡት ተማሪዎች ቁጥር ዝቅተኛ ነው፡፡

በወረዳው የተከሰተው የሰላም እጦት  በትምህርት ተቋማት  አፈፃፀም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ  ተገልጿል ።

በኤደን ሽመልስ

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
16.68 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 31 Jul 2025 11:42:02 +0300
Подробнее
16.38 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 31 Jul 2025 10:36:20 +0300
Подробнее
15.49 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 31 Jul 2025 09:55:19 +0300
Подробнее
16.36 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 30 Jul 2025 23:17:02 +0300
Подробнее
15.75 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 30 Jul 2025 13:01:19 +0300
Подробнее
16.37 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 30 Jul 2025 09:27:02 +0300
Подробнее
15.32 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 30 Jul 2025 07:25:37 +0300
Подробнее
12.75 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 29 Jul 2025 21:47:30 +0300
Подробнее
16.03 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 29 Jul 2025 19:07:06 +0300
Подробнее
15.76 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 29 Jul 2025 16:23:21 +0300
Подробнее
15.14 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 29 Jul 2025 10:04:19 +0300
Подробнее
16.72 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 27 Jul 2025 20:32:51 +0300
“ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጥልቅ መሠረት ያለው ታሪካዊ፣ ባሕላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትስስርን ይጋራሉ” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በምታስተናግደው 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡትን የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ በማሕበራዊ ገጻቸው ባጋሩት ፅሁፍ የተናገሩት ነው።

“ይኽን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር መሥራታቻንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

@ethionews433
Подробнее
19.89 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 27 Jul 2025 13:53:21 +0300
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባለፈው የበጀት ዓመት ከአየር ጉዞ አገልግሎት 3.3 ቢሊየን ብር ማግኘቱን አስታወቀ

የአቪዬሽን ዘርፉን ለማሳደግ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የአየር ማረፊያዎችን እና አነስተኛ የሄሌኮፕተር ማረፊያዎችን እየገነባሁ ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ፣ 20 የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዳሏትና 4 ተጨማሪ አውሮፕላን ማረፊያዎች ግንባታ ላይ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
17.85 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 27 Jul 2025 11:55:43 +0300
ለጋዛ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከከፍተኛ አለምአቀፍ ጫናዎች በኋላ እንድገቡ ተፈቀደላቸው...

እርዳታው በእስራኤል መከላከያ ኃይል ወደ ጋዛ እንዳይገባ ዕቀባ ተጥሎበት የቆየ ሲሆን ሁለት ሚሊዮን የጋዛን ህዝብ ለ90 ቀናት ይመግባል ተበሏል።

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
15.28 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sun, 27 Jul 2025 09:47:44 +0300
የኢራን ጥቃት

በኢራን በደረሰ የሽብር ጥቃት ቢያንስ ስድስት ሰዎች  ህይወታቸውን አጡ።

በፓኪስታን መቀመጫውን ያደርውገው ጃኢሽ  አል ኤድል ጥቃቱን መፈጸሙን ይፋ አድርጓል።


በደቡባዊ ኢራን በተፈጸመው ጥቃት 22 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም የአር ቲ ዘገባ ያሳያል።

የእስላማዊት ኢራን አብዮታዊ ዘብ ሀይል አንዲት እናት ከአንድ ዓመት ልጅዋ ጋር በደቡብ ምስራቅ ኢራን እንደተቀጠፈች አሳውቋል።

ሶስት ታጣቂዎች አንድ ፍርድ ቤት ላይ ተኩስ በመክፈት የህንጻውን ሰራተኞች እና ተገልጋዮችን መግደደላቸውን የቴህራን ጦር ይፋ አድርጓል።

በሲስታን  ባሉቼ'ስታን ግዛት ላይ የደረሰ ጥቃት ነው።
በተለይም አንደኛው ከመገደሉ በፊት የእጅ ቦምብ ህንጻው ላይ በመወርወር ከባድ ጉዳት እንዲመዘገብ አድርጓል።

አይ አር ጂ ሲ እንዳስታወቀው ሁሉም አጥቂዎች በተወሰደባቸው እርምጃ ተገድለዋል።

በሞርታር የታጀበ አደጋ ታጣቂዎቹ መፍጠራቸውንም የኢራን መገናኛ ብዙሃን አስነብበዋል።

በ-ቢኒያም ካሴ


@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
14.48 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 26 Jul 2025 18:59:12 +0300
አቢሲኒያ ባንክ በኢትዮጵያ በሚገኙ በሁሉም  ቅርንጫፎቹ ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ይህ የወረቀት አልባ ልዩ የባንክ አገልግሎት ዘመናዊ የባንክ አሠራሮችን እንዲይዝ ተደርጎ በአዲስ መልክ በተዋቀረው ራስ ልዩ ቅርንጫፍ  ነው በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራ የጀመረው ።

የአቢሲኒያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ፤በዚህ አዲስ አሠራር ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ገንዘብ ለማስተላለፍ፣ ለማስገባትና ለማውጣት፣ ሒሳብ ለመክፈት ያስችላል ብለዋል።

አገልግሎቱ የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀም በመሆኑ፣ ጊዜ የሚወስዱ የአሠራር ሂደቶችን በማስወገድ የባንኩን አገልግሎት ለማሳደግ እንደ ሚያገለግልም ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

ለአጠቃቀም እንዲመች እንግሊዝኛን ጨምሮ በተለያዩ አገራዊ ቋንቋ  እንደ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማሌኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛ እና ሲዳምኛ አቅርበናል ብለዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ግለሰቦች በቅርንጫፍ ውስጥ ወረፋ መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው፤ እንዲሁም ቴክኖሎጂው ላይ በተገጠሙ ዘመናዊ መሳሪያዎች ያለ መብራትና  ኢንተርኔት አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ(ዶ/ር) ፤ባለፉት 30 ዓመታት በባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ  አዳዲስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ረገድ አቢሲኒያ ባንኩ ትልቅ አበርክቶ እያደረገ ነው ብለዋል።

የፋይናንስ ዘርፍን በተቻለ መጠን ተወዳዳሪና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የማህበረሰቡን ጊዜ፣ድካምና ጉልበት ሊቆጥቡ የሚችሉ አሰራር ማስተዋወቅና ተግባራ ማድረግ ግድ ይላልም ሲሉ  የብሔራዊ ባንክ ገዢው ተናግረዋል።

ከውጭ ከሚገቡት ባንኮች ጋር በእኩልነት ለመስራት የአሰራር ደረጃን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አሁን የብሔራዊ ባንክ ገዢው  ማሞ(ዶ/ር)፤ባንኮች እያደረጉት ባለው ጥረት የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ አገልግሎቱ በቅርቡ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ይሆናሉም ብለዋለ።


ልኡል ወልዴ

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
14.63 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 26 Jul 2025 13:46:21 +0300
የጋዛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲያቆም ሶስት የአውሮፓ ሀገራት ጠየቁ።ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ትናንት አርብ በጋራ ባወጡት መግለጫ ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ እስራኤል ፈቃድ እንድትሰጥ አሳስበዋል።የሶስቱ ሀገራት መሪዎች ሁኔታውን "ሰብአዊ ጥፋት" በማለት አፋጣኝ የተኩስ አቁም ጠይቀዋል።መሪዎቹ የዘላቂ ሰላም ጥረቶችን ለመደገፍ "ተጨማሪ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን" ብለዋል። መሪዎቹ ሰላም ለማስፈን ተጨማሪ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ቢገልጹም፤ ምን አይነት እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ግን አልገለጹም።የጋራ መግለጫው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት ቃል ከገቡ እና ማክሮን፣ ለብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር እና ለጀርመኑ መራሄ መንግስት ፍሪድሪክ ሜርስ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ ነው።ሶስቱም ሀገራት የፍልስጤምን መንግስት በመርህ ደረጃ ቢደግፉም፤ ጀርመን የፈረንሳይን መሪነት ለመከተል የቅርብ ጊዜ እቅድ እንደሌላት ገልፃለች።ብሪታንያም የፓሪስን እርምጃ አልተከተለችም። ማክሮን በመጭው መስከረም ወር በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እውቅናውን መደበኛ ለማድረግ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
17.28 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Sat, 26 Jul 2025 12:38:36 +0300
በጋዛ ከሦስት ሰዎች አንዱ ለቀናት ምግብ አይመገብም - ተመድ

ከጋዛ ነዋሪዎች ውስጥ ከሦስቱ አንደኛው ለቀናት ምግብ ሳይመገብ እንደሚቆይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

በመግለጫው አሁን ላይ በጋዛ “የተመጣጠነ ምግብ እጥረት” በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲልም አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም 90 ሺህ ሴቶች እና ህፃናት “አስቸኳይ ክብካቤና ህክምና” እንደሚያስፈልጋቸው አስገንዝቧል።

በጋዛ ባለፉት ሳምንታት በተለይም የእስራዔል ጦር የሚያካሂደው ወታደራዊ ዘመቻ መጨመሩን ተከትሎ የረሃብ ማስጠንቀቂያዎች የተጠናከሩ ሲሆን፥ ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድርጅቶችም እስራዔል በቂ እርዳታ እንዲገባ ትፍቀድ እያሉ ነው።

እስራዔል በበኩሏ ከዚህ ቀደም ተሞክሮ ለተረጂዎች ህልፈት ምክንያት የሆነውን የአየር ላይ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በቀጣዮቹ ቀናት ሀገራት ማቅረብ ይችላሉ ማለቷን ቢቢሲ አስነብቧል።

ከዚህ ባለፈ ለተፈጠረው የምግብ እጥረትም ሆነ ረሃብ ሐማስ እንጅ እኔ ተጠያቂ አይደለሁም ማለቷንም ነው ዘገባው ያመላከተው።

ዓለም አቀፍ ረድኤት ድርጅቶች ደግሞ “እስራዔል ለመፍትሄ ተባባሪ ከመሆን ይልቅ አሁንም ሌሎች አካላትን በመውቀስ ለህጻናት እና እናቶች ህልፈት ምክንያት መሆኗን ቀጥላለች” ሲሉ ለአስቸኳይ መፍትሄ ተባባሪ እንድትሆን እየጠየቁ ነው።

በጋዛ የእስራዔል ሃማስ ግጭት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 122 ሰዎች በረሃብ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።


@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
16.96 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 25 Jul 2025 22:17:45 +0300
ሀሰተኛ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት በማዘጋጀት ሲሸጥ የነበረ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

ያፌት አለማየው የተባለው ተጠርጣሪ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ትኬት ቆራጭ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው 7ኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ የቲኬት መሽጫ ቢሮ ነው፡፡

ተጠርጣሪው ከድርጅቱ ህጋዊ ቲኬት ጋር የሚመሳሰል ሀሰተኛ ትኬቶችን በማዘጋጀት ለደንበኞች ሲሸጥ በቲኬት ተቆጣጣሪዎች ጥቆማ ሰጪነት ከ553 ሀሰተኛ ትኬቶች ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየጣራበት መሆኑን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቡ የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በማለት የመንግስትና የህዝብ ሀብትን በህገ-ወጥ መንገድ ለግል ጥቅሙ ለማዋል በፈፀመው ወንጀል በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም በአቋራጭ ሀብት ለማፍራት የሚጥሩ ግለሰቦችን በማጋለጥ ረገድ ሁሉም ዜጋ የኃላፊነት ድርሻውን እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያቀርባል።

ዘገባው የአዲስ አበባ ፖሊስ ነው



@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
18.49 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Fri, 25 Jul 2025 14:34:09 +0300
ፈረንሳይ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና እንደምትሰጥ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ገለፁ፡፡

ፈረንሳይ በመስከረም ወር ለፍልስጤም መንግስት በይፋ እውቅና እንደምትሰጥ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚያደርጉ ከሆነም ፈረንሳይ ይህን በማድረግ የመጀመሪያዋ የG7 ሀገር ትሆናለች ።

ማክሮን በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ በትክክለኛ መንገድ  በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሚያስፈልገው የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ማድረግ እና ነዋሪዎችን መታደግ ነውም ብለዋል።

እንዲሁም አስቸኳይ የተኩስ አቁም፣ ሁሉንም ታጋቾች መልቀቅ እና ለጋዛ ህዝብ ትልቅ ሰብአዊ እርዳታ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ  ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል።

የፍልስጤም ባለስልጣናት የማክሮንን ውሳኔ የተቀበሉ ሲሆን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ  ግን እርምጃው "ሽብርን ያበረታታል" ሲሉ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬው

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
17.99 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 24 Jul 2025 18:13:02 +0300
ኢትዮ ቴሌኮም ከከብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ከ2.9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የምዝገባና የህትመት ሂደትን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋፋት እና ለማፋጠን በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስታዉቋል ።ለዚህ የሚሆን 2ሺህ የባዮሜትሪክ መመዝገቢያ ማሽኖች በመግዛት እና ተጨማሪ 1ሺህ 500 ማሽኖችን ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፅህፈት ቤት በውሰት በማግኘት አስፈላጊውን ሀብት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል በማሟላት ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል ።

በ12 ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በ575 የሽያጭ ማዕከሎች ፣በ769 ከተሞች ፣ በ104 ዞኖች እና በ67ዐ ወረዳዎች ላይ ስራዉ እየተከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

እስካሁን የ11 ሚሊዮን ደንበኞች ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን ለ9.7 ሚሊዮን ደንበኞች የፋይዳ ቁጥራቸውን እንዲያውቁ ተደርጎ በበጀት ዓመቱ 1ዐ.4 ሚሊዮን ዜጎችን በመመዝገብ ከብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ 2.94 ቢሊዮን ብር ማግኘት መቻሉን ወይዘሪት ፍሬህይወት አክለዉ ገልጸዋል ። በአሁኑ ወቅት ዕለታዊ የምዝገባ ምጣኔን በአማካይ 70 ሺ ማድረስ ተችሏል ።

በመባ ወርቅነህ

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
17.75 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 24 Jul 2025 15:30:33 +0300
ከባድ ዝናብ ካስከተለው ጎርፍ ጋር ተያይዙ ያልተገባ አስተያየት ተሰቷል አለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

በትላንትናው ዕለት የተከሰተው ጎርፉ ወቅቱን ጠብቆ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታ ላይ በነበረው ጊዮን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመሙላቱ እና የተሰራለትን ጊዜናዊ ግድብ ጥሶ በመውጣቱ ሆኖ ሳለ አንድንድ ግለሰቦች ግን ወቅቱን ያላገናዘበና ከእውነት የራቀ አስተያየት ሲሰጡት ተሰምቷል ሲል አዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በማህራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ የነበራትን አስቸጋሪ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት እንደ አዲስ በመገንባት የተሰራውን ስራ ወደ ጎን በመተው አንዳንዶች ያልተገባ ስያሜ መስጠታቸው አግባብ እንዳልሆነም ገልጧል በመግለጫው፡፡

የከተማዋ ነዋሪ እና ህብረተሰብም ትክክለኛውን እና ሚዛናዊ የሆነውን መረጃ እንዲመረምር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ወቅቱን በማስመልከት የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት እራሱን ከጎርፍ አደጋ እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡

በከተማዋ እየተሰራ ያለውን ግንባታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጎርፍ የመከላከል ስራው ህብረተሰቡ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከተማው በሚያደርገው የመከላከል ሥራ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል፡፡

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
18.29 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 24 Jul 2025 12:13:06 +0300
49 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ የሩሲያ አዉሮፕላን ተከሰከሰ

43 መንገደኞችንና 6 ሠራተኞችን አሳፍሮ ይበር የነበረ አንድ የሩሲያ የመንገደኞች አዉሮፕላን ሩሲያን ከቻይና ጋር በሚያውስነዉ ድንበር አካባቢ ተከሰከሰ።

አንቶኖቭ 24 (A-24) የተባለዉ አዉሮፕላን ዛሬ ጧት ሩሲያን ከቻይና ጋር ከሚያዋስነዉ ድንበር ላይ ከምትገኘዉ ብላጎቬሽሼንስክ ከተባለችዉ ከተማ ትይንዳ ወደተባለች ሌላ ከተማ መብረር ላይ ነበር።

አዉሮፕላኑ አሳፍሯቸዉ ከነበሩት ሰዎች በሕይወት የተረፈ መኖሩ ብዙ አጠራጥሯል።

አዉሮፕላኑ በወደቀበት አካባቢ ቀድመዉ የደረሱ የአደጋ ሠራተኞች በእሳት የተቃጠለ የአዉሮፕላኑን ሥብርባሪ ማግኘታቸዉን አስታዉቀዋል።

አዉሮፕላኑ ይበር በነበረበት አካባቢ «አስቸጋሪ» የዓየር ሁኔታ ነበር ከመባሉ በስተቀር የአደጋዉ ትክክለኛ መንስኤ አልታወቀም።

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
15.55 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Thu, 24 Jul 2025 09:29:02 +0300
በቻይና ያጋጠመው የሙቀት መጨመር የአየር ማቀዝቀዣዎች ሽያጭ እንዲጨምር ማድረጉ ተሰማ

አንድ አንድ ቻይናውያን ከፍተኛ ሙቀቱን ለመቋቋም አነስተኛ የአየር ማቀዝቀዣዎችን ይዘው በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል።

ቻይና ከመጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ ያሳለፈቻቸው ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበባቸው ቀናት ብዛት በጣም በርካታ መሆናቸውን የቻይና ሚቲዎሮሎጂ አስተዳደር ባለስልጣን ገልፆል። አስተዳደሩ ረቡዕ ዕለት እንደገለፀው ከሆነ በቻይና ውስጥ ያሉ 152 ብሄራዊ የአየር ሁኔታ ታዛቢዎች ከሀምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ ከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ የሙቀት መጠን መዝግበዋል።

እንዲሁም ሰዎች ወደ አየር ማቀዝቀዣ እና የአየር ሙቀት መጨመርን ለመቋቋም የሚያስችሉ መሳሪያዎች ግዢ ፊታቻን ያዞሩ ሲሆን በዚህም የኃይል ፍጆታን ለመቆጣጠር ወቅታዊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ለሀገሪቱ የኃይል ኢንዱስትሪ ማስጠንቀቂያ ልኳል። ባለፈው ሳምንት ከ200 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባትን አካባቢ ሸፍኖ፣ በደቡብ ምዕራብ ከምትገኘው ቾንግቺንግ ከተማ አንስቶ እስከ ጓንግዙ የባህር ዳርቻ ድረስ ከፍተኛ ሙቀት ተመዝግቧል።

በሃቤይ እና ሁናን ማእከላዊ አውራጃዎችም የሙቀት መጠኑ እስከ 50 ዲግሪ ሴንትግራድ እንደሚደርስ ተንብዮ ነበር። በደቡባዊ ጂያንግዚ እና ጓንግዶንግ ግዛቶችም ተመሳሳይ የሙቀት መጠን ይጠበቃል።በቻይና ውስጥ የተከተሰተው ከፍተኛ መቀት የህይወትን ምቾት ከማሳጣት፣ የእርሻ መሬቶችን ከማቃጠል እና የእርሻ ገቢን ከመሸርሸር በተጨማሪ ከፍተኛ የአየር ሙቀት መጨመሩ የማምረቻ ማዕከላትን ሊጎዳ እና በቁልፍ ወደቦች ላይ ስራዎችን ሊያስተጓጉል ይችላል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችንም ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።

በሚሊዮን ሙሴ

@ethionews433 @ethionews433
Подробнее
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 23 Jul 2025 14:34:13 +0300
Подробнее
18.56 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Wed, 23 Jul 2025 11:44:58 +0300
Подробнее
17.72 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 22 Jul 2025 18:05:24 +0300
Подробнее
18.66 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 22 Jul 2025 12:36:46 +0300
Подробнее
16.71 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 22 Jul 2025 09:12:02 +0300
Подробнее
13.52 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Tue, 22 Jul 2025 08:05:47 +0300
Подробнее
19.84 k
]]>
https://linkbaza.com/catalog/-1002264268428 Mon, 21 Jul 2025 23:14:10 +0300
Подробнее
13.75 k
]]>