The voice of Ethiopian football
For business enquiries ONLY
Tell: +251940018801
Email: ads@soccerethiopia.net
Информация о канале обновлена 06.10.2025.
The voice of Ethiopian football
For business enquiries ONLY
Tell: +251940018801
Email: ads@soccerethiopia.net
🏆
@goferesportswear
ቻምፒዮኖቹ ዋንጫውን ተረክበዋል!
ከመስከረም 11 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ከ17 ዓመት በታች የታዳጊ ወጣቶች ማጠቃለያ ቻምፒዮን ውድድር ዛሬ መቋጫውን ሲያገኝ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊ በመሆን የተዘጋጀላቸውን ዋንጫ እና ሜዳሊያ ከክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል።
በውድድሩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውድድሩ ቻምፒዮን በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ፣ ወላይታ ድቻ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስተኛ በመሆን የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን የተዘጋጀላቸውን ሜዳሊያ ተረክበዋል።
የኮከቦች ሽልማትም የተሰጠ ሲሆን ኮከብ ተጫዋች ቸርነት ኡፍይሳ ከወላይታ ዲቻ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሙሉዓለም ዱባለ ከሀዋሳ ቢ፣ ኮከብ ግብ አግቢ ሁዘይፋ ሻፊ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኮከብ አሰልጣኝ ተስፋዬ አድማሱ ከንግድ ባንክ ሆነው በመመረጥ የተዘጋጀላቸውን የዋንጫ ሽልማት ተቀብለዋል። እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ ሲሸለም የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅ ክልል በመሆኑ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።
የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክተር ከበደ ወርቁ ፣የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አንበሴ አበበን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ቻምፒዮን ሆነ!
የ2017 ዓ/ም ከ17 ዓመት በታች ማጠቃለያ ቻምፒዮን ውድድር ዛሬ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የወላይታ ድቻ አቻቸውን በማሸነፍ ቻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ከዋንጫ ጨዋታ አስቀድሞ በተደረገ የደረጃ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 'ሀዋሳ ቢ' ን 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በውድድሩ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
የደረጃ እና የፍጻሜ ጨዋታ ውጤቶች!
ሀዋሳ ቢ 1-3 ቅዱስ ጊዮርጊስ
53' ምስክር ተሾመ | 41' እንየው ስለሺ
70' ትንሳዔ መንግሥቱ
83' ብሩክ ዓለማየሁ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-1 ወላይታ ድቻ
88' ቃለአብ አሥራት | 32' ኤፍሬም አለና
(የመለያ ምት ውጤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 4-2 ወላይታ ድቻ)
* የዋንጫ አሰጣጥ ስነስርዓት እና የውድድሩ ኮከቦችን ዝርዝር ከአፍታ ቆይታ በኋላ ይዘን እንመለሳለን።
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.