መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Информация о канале обновлена 20.11.2025.
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰራተኛ ምዘናና ምደባ ሊያካሄድ ነው
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰራተኛ ምዘና እና ምደባ ሊያካሂድ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሰራተኛ ቅነሳ ሊያደርግ እንደሆነ የተሰራጨው መረጃም ትርጉም የማይሰጥ መሆኑንም አመላክተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የ75ኛ ዓመት አልማዝ ኢዮቤልዩ አከባበር እና የራስገዝነት ሪፎርም አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በዚህም ወደ ራስገዝነት የሚያደርገው ሽግግር የእስካሁን ጉዞ፤ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ እና ቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ሳሙኤል (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የሠራተኞች ምደባና ሥምሪት ማስፈፀሚያ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ፣ ውይይት ተደርጎበት ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
በዚህም የሰራተኛ መልሶ ሥምሪትና ምደባ የሚከናወንበት የጊዜ ሰሌዳ ፀድቆ ለሚመለከታቸው አካላት ተልኳል ያሉት ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ፤ ለሰራተኞች መመዝገቢያና የመረጃ ማጥሪያ ኦንላይን ፎርም ተዘጋጅቶ ምዝገባ ተከናውኗል ብለዋል፡፡
እንደ ሳሙኤል (ዶ/ር) ገለጻ፤ ከደረጃ 08 በላይ ላሉት አንድ ሺህ 500 ለሚደርሱ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ፈተና በመስጠት ብቃትና ውጤታማነትን ማዕከል በማድረግ ምደባ ይሰጣል፡፡
ሌሎች ከደረጃ 08 በታች ላሉ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች በሰነድና በነበራቸው የግምገማ ውጤት በውድድር ምደባ እንደሚሰጥ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ አመላክተዋል፡፡
እንዲሁም የአካዳሚክ ሰራተኞች፣ ተመራማሪዎች፣ የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች እና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ሙያተኞች በውድድር ላይ የተመሰረተ ልየታ በማድረግ ስምሪት እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ የሰው ኃይል በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ የተዘጋጀውን የመውጫ ስትራቴጂ በመመርኮዝ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር እንደሚከናወንም ጨምረው ገልጸዋል።
ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ጋዜጠኞች ዩኒቨርሲቲው ሰራተኞቹን ሊቀንስ ነው ተብሎ የተሰራጨውን መረጃ በሚመለከት ላቀረቡላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡም፤ የተሰራጨው መረጃም “ትርጉም የማይሰጥ” ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በዩኒቨርሲቲው 4 ሺህ የአስተዳደር ሰራተኞች ያሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ እነሱም በተዘጋጀው የሰራተኛ ስምሪት ማዕቀፍ መሰረት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አንስተዋል።
በዩኒቨርሲቲው በሁሉም መዋቅሮች “በቂ ሰራተኛ አለ ማለት ሁሉም ይቀጥላሉ ማለት አይደለም፤ በቅድሚያ ብቃት ያላቸው ሰራተኞች ቦታውን መያዝ አለባቸው” ብለዋል፡፡
Via ጋዜጣ ፕላስ
@Yenetube @Fikerassefa
!
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በ ኢትዮጵያ ውስጥ መጠነ-ሰፊ የአሉሚኒየም ማቅለጫ ፋብሪካ ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትን በዓለምአቀፍ ደረጃ ግዙፍ የአልሙኒየም አምራቾች መካከል አንዱ ከሆነው የሩሲያው ሩሳል ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።
ፋብሪካው በየዓመቱ 500,000 ሜትሪክ ቶን የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን በቀጠናዊና በዓለምአቀፍ የአሉሚኒየም ገበያዎች ተወዳዳሪ አቅራቢ እንድትሆን እንደሚያደርጋት ተጠቁሟል።
ፕሮጀክቱ እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ለማሟላት፣ የኢንዱስትሪ ልማትን ለመደገፍ፣ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ አሉሚኒየምን ወደ ሀገር ማስገባት ሂደት ወቅት የሚያስወጣውን የውጭ ምንዛሪ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል።
ይህ የተገለፀው ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዩሮኤዥያ ቀዳሚ የዲጂታል መድረክ በሆነው ዋይልድ ቤሪስ መካከል የኢትዮጵያን የኢ-ኮሜርስ እና የዲጂታል መሠረተ ልማት ልማት ለማፋጠን ከተፈረመው የአጋርነት ስምምነት በኋላ ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ መረጃ መሠረት፣ የአሉሚኒየም ፋብሪካ ግንባታው ከሦስት እስከ አራት ዓመታት ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን፣ ለ50 ዓመታት ያህል አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዩክሬይን ጦር መሳሪያ ማምረቻ ተቋም አማካሪ ሆኑ፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ማይክ ፖምፒዮ ለበርካታ አመታት በዲፕሎማሲ ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል የአሜሪካ የስለላ ተቋም (ሲአይኤ) ሀላፊ የነበሩት ፖምፒዮ 70ኛው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የትምህርት ዝግጅታቸውም በህግ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ዛሬ እንደተሰማው ግን እኚህ የ61 አመቱ አንጋፋ የቀድሞ ባለስልጣን ‹‹ከዲፕሎማሲ ወደሚሳኤል›› ተሸጋግረዋል፡፡ ማይክ ፖምፒዮ የዩክሬይን ረጅም ርቀት ሚሳኤል ማምረቻ የሆነው ፋየር ፖይንት ፋብሪካ አማካሪ ቦርድ አባል መሆናቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ፋየር ፖይንት ማለት ሩሲያ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ጥቃት መፈፀም የሚችሉ ሚሳኤሎችን የሚያመርት ሲሆን በዚህ ፋብሪካ ከተመረቱት ውስጥ ፍላሚንጎ የተሰኘው ሚሳኤል አንዱ ነው፡፡
ፍላሚንጎ እስከ 3 ሺ ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት መጓዝ የሚችል እንደሆነ የተገለፀለት ሲሆን ባለፈው ሳምንት ይህንን ሚሳኤል ሩሲያ ላይ መሞከራቸውን ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
የሶማሌ ክልል በሥሩ ከ18 በላይ ሆስፒታሎች ፣ 40 በላይ ጤና ጣቢያዎች እና በርካታ ጤና ኬላዎች አሉት። በእነዚህ የጤና ተቋማት የሚሠሩ በርከት ያሉ የጤና ባለሙያዎች አሉ። በክልሉ የሚሠሩ የጤና ሙያተኞች እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመንግሥት ሠራተኛ በተለይ ደግሞ እንደ ጤና ባለሙያ የሚያነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች አሏቸው።
የሶማሌ ክልል ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በልዩነት የአየር ንብረቱ እንዲሁም የመሠረተ ልማት ዝርጋታው አስቸጋሪ እና ኋላቀር የሚባል ነው።
በክልሉ ያሉ የጤና ሙያተኞች ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ታግሰው እየሠሩ ቢገኙም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የክልሉ ጤና ቢሮ እና በተዋረድ ያሉ የጤናው ዘርፍ አመራሮች በሠራተኛው ላይ ኅልቆመሳፍርት ግፎችን በመፈፀም ላይ ይገኛሉ። ከበደሎቹ በጥቂቱ ከደሞዝ እና ከሙያ እድገት ጋር የተገናኙትን እንጥቀስ፡-
1 . መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ያደረጋቸውን የደሞዝ ማሻሻዎች ተከትሎ ሊስተካከሉ የሚገባቸው የዲዩቲ እና የውሎ አበል ክፍያዎች አለመስተካከላቸው።
ሀ . ጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማስተካከያ ሲደረግ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይከፈል የነበረው በአሮጌው ደሞዝ ነበር። ሠራተኛው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ከሚመለከታቸው አካላት አጥጋቢ ምላሽ አልተሰጠውም። ከዚህ በላይም ሠራተኛው ላይ ፍረጃ እና ለያይቶ ማጥቃትን ሲተገብሩ በተደጋጋሚ ታዝበናል። ጥያቄ የሚያነሱ ሙያተኞችን በማናለብኝነት ከቃል ማስጠንቀቂያ እስከ ማባረር የደረሱ እርምጃዎችን ሲወስዱ ታዝበናል።
ለ . በዚህ ዓመት ከመስከረም ወር ጀምሮ የተተገበረውን አዲሱን የደሞዝ ማሻሻያ ክልሉ መተግበር አልቻለም። እንደተለመደው የዲዩቲ ክፍያውን 2ቱንም ማሻሻዎች በመተው ሁለት እርከን ወደ ኋላ በመመለስ በድሮው እየከፈለ ይገኛል። በአዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ መሠረትም የመስከረም ወር ተጨምሮ መከፈል ያለበት ክፍያ (Backpayment) ሳይጨመር ተከፍሏል። የክልሉ መንግሥት በተለይ የጤና ጥበቃ ቢሮው እና በሥሩ ያሉ ተቋማት ለሠራተኛው ክብር የሌላቸው (Disrespect) ፣ የሠራተኛውን የሥራ ወኔ የሚያጠፉ (Discourage) እንዲሁም ሠራተኛውን እንደ ባሪያ የሚያዩ እና ራስ ወዳድ (Slavery ideation and Selfish) ) - DDS ናቸው። እኛ የጤና ሙያተኞች የሚከፈለን ክፍያ በቂ አይደለም በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ ባለንበት ሁኔታ የሶማሌ ክልል በዚህ ልክ አግላይ እና ጨቋኝ ባይሆን መልካም ነበር።
2 . ሠራተኛው ለሥልጠና እና ለሌሎች ሙያዊ ጉዳዮች ሲወጣ የውሎ አበል አይታሰብም፣ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም። የውሎ አበሉ በደሞዝ ደረጃ እና ሙያተኛው እንደተጓዘበት ከተማ እንደሚለያይ የፌደራል መንግሥቱ መመሪያ ይገልፃል። ሆኖም ግን በሶማሌ ክልል ውስጥ የሚሠሩ የጤና ሙያተኞች ለተደጋጋሚ እንግልት ሲዳረጉ ከአመራሮች ዘንድ አጥጋቢ ምላሽ አይሰጥም። የሠራተኛውን ቅሬታ ለማድመጥም ፈቃደኛ አይደሉም።
3 . ለጤና ሙያተኞች የሥራ ልምድ ደብዳቤ በሁሉም የክልሉ የጤና ተቋማት ማለት በሚያስችል ሁኔታ አይሰጥም። የጤና ሙያተኛው የሥራ ልምድ ደብዳቤ የማግኘት ሕጋዊ መብት እያለው በክልሉ ያሉ የጤና ዘርፍ አመራሮች ግን ለየትኛውም ሙያተኛ የሥራ ልምድ ደብዳብዴ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም።
ሀ . ሠራተኛው ሕጋዊ ዝውውር እንዲያደርግ አይፈቅዱም።
ለ . ሠራተኛው በሕጋዊ መንገድ ከሚሠራበት የጤና ተቋም መልቀቅ አይችልም።
ሐ . የጤና ሙያተኛው የደረጃ እድገት በጊዜ እንዳያገኝ እና የሙያ እድገቱን ተከትሎ የደሞዝ ማሻሻያ ባለማድረግ።
መ . በየጤና ተቋሙ በልዩ ልዩ ዘርፍ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሙያተኞች የተመደበላቸውን ክፍያ ከመቀነስ እስከ መንፈግ የደረሰ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ መኖሩ።
ክልሉ በማናለብኝነት ሠራተኛው ላይ እየፈፀመ ያለውን በደል የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ ገብቶ እንዲያስተካክልልን ስንል እንጠይቃለን።
የሶማሌ ክልል ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.
Наш сайт использует cookie-файлы, чтобы сделать сервисы быстрее и удобнее.
Продолжая им пользоваться, вы принимаете условия
Пользовательского соглашения
и соглашаетесь со сбором cookie-файлов.
Подробности про обработку данных — в нашей
Политике обработки персональных данных.