ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Информация о канале обновлена 21.08.2025.
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
ጋና በውርርድ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ሰዎች የአሻራ እንደዚሁም የፊት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ብላለች።
በጋና ያሉ አቋማሪ ተቋማት ከዚህ በኋላ የፊት እና የአሻራ መረጃዎችን ይጠይቃሉ ተብሏል። ውሳኔው በዘርፉ እየተስተዋለ ያለውን የገንዘብ ማሸሽ፣ ዕድሜ ሳይደርስ መጫወትን እንደዚሁም ሌሎች የማጭበርበር ተግባራትን መከላከልን ያሰበ ነው።
በተጨማሪ ጋና ለኦንላይን የውርርድ አይነቶች የጋና ብሔራዊ መታወቂያ በብቸኝነት የሚያገለግል መታወቂያ መሆኑን ገልጻለች።
የውርርድ ተቋማትም ሥርዓታቸውን ከሃገሪቱ የብሔራዊ መታወቂያ ስርዓት ጋር ማስተሳሰር አለባቸው ተብሏል።
ሰዎች ውርርድ ላይ ከመሳተፋቸው በፊ፤ ውርርዱን ካሸነፉ በኋላ፤ እንዲሁም ገንዘቡን ለማውጣት የፊት እንዲሁም የአሻራ መረጃዎችን መስጠት ይጠበቅባቸዋል።
አቋማሪዎች በ30 ቀናት አዲሱን አሰራር ወደ ስራ ማስገባት አለባቸው ተብሏል።
በጋና ውርርርድ እና ተያያዥ ጨዋታዎችን የሚመራው ተቋም ይህንን አሰራር ወደ ሥርዓታቸው ለማካተት ያልቻሉ ተቋማት ፈቃዳቸው እንደሚነጥቅ አስጠንቅቋል።
ጋና በአፍሪካ በስፖርታዊ ውርርዶች እና ቁማሮች በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ሃገራት መካከል አንዷ ስትሆን በ2025 ከስፖርታዊ ውርርድ የሚገኘው ገቢ ብቻ 120 ሚሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል።
Source: IGB
@Tikvahethmagazine
ሩሲያ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ የሚደረጉ የስልክ ልውውጦች ላይ በከፊል እገዳ ማስቀመጥ ጀመረች።
ሩሲያ ከውሳኔው ላይ የደረሰችው ሁለቱ መተግበሪያዎች ከማጭበርበር እና ከአሸባሪነት ጋር በተያያዘ ለህግ ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ብላለች።
በዚህ የተነሳ ሩሲያ የወንጀል ተግባራትን ለመቀልበስ በመተግበሪያዎቹ የሚደረጉ አንዳንድ የስልክ ልውውጦች ላይ እገዳ ማስቀመጧ ተዘግቧል።
የሩሲያ የዲጂታል ልማት ሚኒስቴር ቴሌግራም እና ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መተግበሪያቸው ላይ የማጭበርበር እና የሽብርተኝነት ተግባራት እንዳይካሄዱ እንዲያደርጉ ተጠይቀው እምቢ ማለታቸውን ገልፀዋል።
የሩሲያ ባለስልጣናት እነዚህ መተግበሪያዎች ሉዓላዊነታችንን የሚጥሱ ስለሆኑ በሃገራችን አግልግሎት አይስጡ ብለው ሲጠይቁ የነበረ ሲሆን ፕሬዚዳንት ፑቲንም በሩሲያ የበለፀገ እና ከደህንነት ተቋሙ ጋር የተሳሰረ የመልዕክት መለዋወጫ እንዲሰራ ማዘዛቸው ይታወሳል።
ሩሲያ ሁለቱ መተግበሪያዎች መረጃ ከሰጡ እና ከህጓ ጋር ከተስማሙ እገዳው እንደሚነሳ ገልፃለች።
Source: Reuters
@TikvahethMagazine
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.