#Orthodox_Tewahdo_new
Ethiopian Orthodox Tewahdo Church is a channel that broadcasts current news and teachings to the Christian public.
📢ለማስታወቂያ ሥራዎች 👉 @mane_tekel27
Информация о канале обновлена 20.10.2025.
#Orthodox_Tewahdo_new
Ethiopian Orthodox Tewahdo Church is a channel that broadcasts current news and teachings to the Christian public.
📢ለማስታወቂያ ሥራዎች 👉 @mane_tekel27
💧 💧
የ ግ ፉ ዓ ን መ ጠ ጊ ያ !
✝️ ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን ፤
ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉዓን ፤
እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን ፤
ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን ፤
ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን ፤
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን። ❞
ትርጉም ፦
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሰደዱ የስደተኞች ተስፋ በመገፋቱ የግፉዓን መጠጊያ ኾነ። የዓለማት ፈጣሪ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን በለበሰበት የሕፃንነቱ ወራት እንደ ነዳያን ቤት ስንኳ የሌለው ስደተኛና መጻተኛ ኾኖ በሰዎች ዘንድ እንደምን ተናቀ እያልኹ የእናቱ ድንግል ማርያም ኀዘን ለእኔ የልቅሶ ዜማ ኾነብኝ።
☦️ሰቆቃወ ድንግል☦️
📖ትምህርቱን ለሌሎች እናካፍል
🌐//𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯
#pray🙏#share❤️
አስቸኳይ መልክት ለወንድማችን ብሩኬ እንድረስለት።
ኦቶዶክሳዊያን ለብሩኬ ልብ ከልብ እንድረስለት።
📖ትንሿ ቤተክርስቲያን በኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ☦️
ባለትዳሮች በቤታቸው ውስጥ ማድረግ ያለባቸው ቤተ ክርስቲያን መጥተው ያዩትን ነው፡፡ ለምሳሌ፦
➡️ ቤተክርስቲያን ውስጥ የጠዋትና የሰርክ ጸሎት እንዳለ ኹሉ እነዚህ ባለ ትዳሮችም የጠዋትና የሰርክ ጸሎት በቤታቸው ውስጥ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
➡️ በቤተክርስቲያን ያለው የኅብረትና የአንድነት ጸሎት እንደ ኾነ ኹሉ፥ ባልና ሚስት ልጆችም ሳይለያዩ አብረው መጸለይ አለባቸው፡፡
➡️ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ በኋላ ትምህርተ ወንጌል እንዳለ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም እራት ከበሉ በኋላ ቃለ እግዚአብሔር ሊማማሩ ይገባቸዋል፡፡
➡️ በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሳቸውን ገዝተው የሚኖሩ ትጉሃን መነኰሳት እንዳሉ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ይህን ትግሃትና ምስጋና ወደ ቤታቸው ይዘዉት ሊኼዱ ይገባቸዋል፡፡
➡️ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ላይ ኅብስቱን አበርክቶ ሕዝቡን ከመገባቸው በኋላ ወዲያው ወደ መኝታ እንዲኼዱ እንዳላደረገ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ወደ መኝታቸው ከመኼዳቸው በፊት የቀን ውሎአቸውን መገምገም አለባቸው፡፡
➡️ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሊት ሌሊት ሲጸልይ ያድር እንደ ነበረ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ሌሊት ላይ ነቅተው መጸለይ ይገባቸዋል፡፡ ሕፃናት ካሉም አብረዋቸው እንዲነሡ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
➡️ በቤተክርስቲያን ጾም እንደሚታወጅ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም በቤተ ክርስቲያን ከሚታወጀው ጾም በተጨማሪ ከንስሐ አባቶቻቸው ጋር ተመካክረው በፈቃዳቸው ሊጾሙ ይገባቸዋል፡፡
➡️ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳለው፥ ባልና ሚስትም የቤታቸውን ግድግዳ፣ መስኮትና በር በመስቀል ሊያስጌጡት ይገባቸዋል፡፡ ማማተብ በማይችሉ ልጆቻቸው ግንባርም አድገው ራሳቸው ማማተብ እስኪችሉ ድረስ እነርሱ ያማትቡላቸው፡፡ ቅዱሳት ሥዕላትም በቤታቸው ውስጥ ሊኖሩ ይገባል፡፡
ቤታቸው ትንሿ ቤተ ክርስቲያን የምትኾነው በዚህ መንገድ ነው፡፡
☦️ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 60 - 61📖
📖ትምህርቱን ለሌሎች እናካፍል
🌐//𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯
#pray🙏#share❤️
"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ"
☦️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ📖
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው "
☦️ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ📖
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት"
☦️ቅዱስ አውግስጢኖስ📖
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ"
☦️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ📖
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"
📖ትምህርቱን ለሌሎች እናካፍል
🌐//𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯
#pray🙏#share❤️
ጥቅምት ፭ /5/
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)
ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ::
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ ልብስ ያልለበሱ ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት ናቸው።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስለ ሀገራችን ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።
ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር እና ፍትሃ ነገስት
📖ትምህርቱን ለሌሎች እናካፍል
🌐//𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯
#pray🙏#share❤️
ስጋውን የበሉት አናብስት ልቡን ግን ያልነኩት ቅዱስ አግናጥዮስ በተደጋጋሚ ራሱን ቲኦፎረስ ወይም እግዚአብሔርን በልቡናው የተሸከመ፣ ክሪስቶፎረስ ወይም ክርስቶስን በልቡናው የተሸከመ፣ እያለ ይጠራ ነበር፡፡
ጌታችን በዘመነ ስጋዌው በማቴዎስ 18÷2-5 ስለመንግስተ ሰማያት ሲያስተምር “እውነት እላችኋለሁ ካልተመለሳችሁ እንደዚህም ሕፃን ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም” ባለበት ወቅት ጠርቶ ያቀፈው ሕጻን ይሕ ቅዱስ አግናጥዮስ ነው፡፡
ቅዱስ አግናጥዮስ በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን በ70 ዓ.ም በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ወንጌላዊ ጵጵስናን ተሾሟል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከልቡ ይወዳት ነበርና ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን መተኪያ የሌላት ነፍሱን ሰጥቷል፡፡ እኛስ ካለን ምን ያህል ለመስጠት ዝገጁ ነን?
በሮማ ንጉሥ ትርያዳን ትእዛዝ ለተራቡ አናብስት ተሰጥቶ ሰማዕት እስኪሆን ድረስ ለ40 ዓመታት ያበራ ሐዋርያ ነው፡፡ በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የሚገኙ መነኮሳትም ከሞቀው ቤታቸው ወጥተው በረሃብና በውሃ ጥም ስለ ክርስቶስ ፍቅር ይንገላታሉ፡፡
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ ከ 5፡00 ጀምሮ በተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመሳተፍ ትኬቱን በመቶ ብር ብቻ በመግዛት በልባችን ያለውን የቤተ ክርስቲያን ፍቅር እናሳይ፤ ከበረከቱ እንሳተፍ፡፡
አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.