Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.
Call 0116635757 for more details.
Информация о канале обновлена 19.11.2025.
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.
Call 0116635757 for more details.
የቀድሞው የማራቶን የዓለም ሬኮርድ ባለቤት እና የሺካጎ ማራቶን የአራት ጊዜ አሸናፊው አሜሪካዊ ካሊድ ካኑቺ እንዲሁም የወቅቱ የማራቶን የዓለም ሻምፒዮን ኬኒያዊቷ ፔሬስ ጄፕቺርቺር ፤ እሁድ ህዳር 14 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ውድድር ላይ በእንግድነት እንደሚገኙ አረጋግጠዋል፡፡
ካኑቺም እንደ ኃይሌ ገብረስላሴ ሁለቴ የዓለም ሬኮርድን ሰብሯል - በመጀመሪያ እ.ኤ.አ. በ1999 በሺካጎ በ2፡05፡42 ሰዓት እና ከሶስት ዓመታት በኋላ በለንደን የራሱን ሰዓት በአራት ሴኮንዶች ወደ 2፡05፡38 በማሻሻል፡፡ ካኑቺ በለንደኑ ውድድር ፖል ቴርጋትን እና ኃይሌ ገብረስላሴን ቀድሞ ሲያሸንፍ ሁለቱ በቅደም-ተከተል 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
ካኑቺ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚያደርገው ጉዞ ሲናገር ‹‹በተወዳዳሪነቴ ወቅት ከብዙ ኢትዮጵያዊያን ጋር የመለማመድ እና የመወዳደር እድል ነበረኝ፡፡ ጠንካራ ሰራተኝነታቸው እና ለሩጫ ያላቸው ፍቅር ለስኬታቸው ዋነኛ ምክንያት ነበሩ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ መገኘት እና በዚያ ያሉ ጓደኞቼን ማግኘት አጓጉቶኛል›› ብሏል፡፡
ለ2025 የሴቶች ከስታዲየም ውጪ የዓመቱ ምርጥ አትሌትነት የታጨችው ኬኒያዊቷ የማራቶን ኮከብ ፔሬስ ጄፕቺርቺርም ከ8 ዓመት ሴት ልጇ ናታሊያ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትመጣለች፡፡ በቶኪዮ የኦሊምፒክ ማራቶንን ካሸነፈች አንድ ዓመት በኋላ በ2015 በታላቁ ሩጫ ላይ ተገኝታ የነበረችው ጄፕቺርቺር፣ በእዚያው በቶኪዮ ኢትዮጵያዊቷ ተፎካካሪዋ ትዕግስት አሰፋን በጥቂት ሰኮንዶች ቀድማ በማራቶን የዓለም ሻምፒዮንነትን ከተቀዳጀች ሁለት ወራት ብቻ ተቆጥረዋል።
‹‹ያ ውድድር ከእጄ እንዲያመልጥ በጭራሽ አልፈለኩም፡፡ ድሉን እጅግ ፈልጌው ነበር›› ስትል ጄፕቺርቺር ከሁለት ወራት በፊት በቶኪዮ ስላገኘችው ድል ታስታውሳለች፡፡ ከመንፈቅ በፊት ትዕግስት ድል ባደረገችበት እና የጄፕቺርቺርን የ2024 ክብር በወሰደችበት የለንደን ማራቶን፣ ኬኒያዊቷ ውድድሩን አቋርጣ ነበር፡፡
በሶስት የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮናዎች ሶስት የግል የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያሸነፈችው ጄፕቺርቺር አሁን የአራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን ስትሆን ፤ በቦስተን፣ ኒው ዮርክ እና ለንደን በማሸነፍ የሶስት-ጊዜ የዓለም ሜጀር ማራቶን ባለድል ነች፡፡
የካኑቺ እና ጄፕቺርቺር ስሞች ከዚህ ቀደም ይፋ በተደረጉት ሶስቱ ኬንያውያን አትሌቶች ፖል ቴርጋት ፣ ዳንኤል ኮመን እና ሞሰስ ታኑይ’ን በያዘው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ላይ የሚታደሙ እንግዶች አስደናቂ ስብስብ ላይ ተጨምረዋል።
ለሚድያ ባለሞያዎች - የመጨረሻ ጥሪ!
ሀዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. ለሚካሔደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር ላይ በቦታው ተገኝተው መዘገብ ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሚድያዎች የይለፍ መታወቂያ ለማዘጋጀት ፤ ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም እንድትመዘገቡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የመጨረሻ ጥሪውን ያቀርባል!
የሚድያ ምዝገባ የምናከናውነው እሰከ 08 ህዳር 2018ዓ.ም. ነው!
👉 https://ethiopianrun.org/accreditation
2 ሳምንት ብቻ ቀርቶናል - እየተዘጋጃችሁ ነው?
የ9ኛ ሳምንት ልምምዳችንን ፤ ከህያት ሬጀንሲ እና ከብላቴና ጤና ቡድን ጋር ሆነን እንቀጥላለን ✨
እሁድ ማለዳ ወሎሰፈር አደባባይ እንገናኝ!
2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.!
#GreatEthiopianRun #10k #25thEdition #ANationIn10km #RaceInNumbers #10WeeksChallenge
ከኬንያ አንጋፋ የረጅም ርቀት ሩጫ አትሌቶች መካከል ሦስቱ - ፖል ቴርጋት፣ ዳንኤል ኮመን እና ሞሰስ ታኑይ – እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018 በሚካሄደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር ላይ ለመገኘት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተገለፀ።
ሦስቱም አትሌቶች በዓለም አቀፍ የሩጫ ሕይወታቸው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በ1994ዓ.ም. ከመሠረተውና የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ሩጫ ምልክት ከሆነው ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር ከፍተኛ ተፎካካሪነት ነበራቸው።
ቴርጋት ቀደም ሲል እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2003 በበርሊን የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ከሰበረ በኋላ በውድድሩ ላይ በእንግድነት ተገኝቶ ነበር። በ1990ዎቹ ከኢትዮጵያዊው ጓደኛው ኃይሌ ጋር ከፍተኛ ፉክክር የነበረው ሲሆን ፤ በ1996 እና በ2000 ኦሎምፒክ ኃይሌን በመከተል የብር ሜዳሊያውዎችን አግኝቷል። ሁለቱም ወደ ማራቶን ሲያድጉም ፉክክሩ የቀጠለ ሲሆን፣ ኃይሌ በሴፕቴምበር 2007 በመጀመሪያው የማራቶን ክብረ ወሰን የዓለም ሪከርዱን ከቴርጋት በ29 ሰከንድ ልዩነት ወስዷል።
ዳንኤል ኮመንም ከ1996 እስከ 1998 ባሉት ሦስት ዓመታት በትራክ ላይ ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር ከባድ ፉክክር ነበረው።
እ.ኤ.አ. 1996 በተካሔደው የአትላንታ ኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ ያልተካተተው ኮመን በሴፕቴምበር 1 ቀን 1996 በጣሊያኗ ሪየቲ የ3000 ሜትርን 7፡20.67 በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰንን ይዞ ነበር ፤ ይህም ጃኮብ ኢንገብሪግስተን በኦገስት 2024 እስኪሰብረው ድረስ ለ28 ዓመታት ያህል ዘልቋል። በ1997 ኮመን የ5000ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን 12፡39.74 በመሮጥ ከኃይሌ ወስዶ የነበረ ቢሆንም ኃይሌ በ12፡39.36 በመሮጥ በአንድ ዓመት ውስጥ መልሶ ወስዶታል።
ሞሰስ ታኑይ በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜው ነው። ታኑይ የሁለት የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊ (በ1991 በትራክ እና በ1995 በጎዳና ላይ) ሲሆን ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአጋርነት የሚሰራው የኤልዶሬት ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ነው። ታኑይ በ1993 የዓለም ሻምፒዮና የ10,000ሜትር ውድድር ላይ ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር አይረሴ ፉክክር ቢያደርግም በመጨረሻው ዙር ጫማው በመውለቁ ኃይሌ አሸንፎት እንደነበር ይታወሳል።
ሶስቱም የኬንያ ታላላቅ አትሌቶች ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ በእንግድነት ታድመውበት በነበረው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መድረክ ላይ በድጋሚ ከኃይሌ እና ከሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ጋር መገኘት የ25ኛውን ዓመት ክብረ በዓል በሚያደምቁት 55,000 ተሳታፊዎች ላይ ተጨማሪ ደስታን ይፈጥራል።
የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር መነሻዎቹን መስቀል አደባባይ እና ግዮን ሆቴል በማድረግ ፤ እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. ይካሔዳል።
አያይዞ በየዓመቱ በሚያካሂደው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከ4 ሚሊዮን ብር የበለጠ ለመሰብሰብ አልሟል።
ይህም በውድድሩ አማካይነት በተሰበሰበ ገንዘብ መጠን ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ይሆናል፡፡ ዘመቻው ባለፈው ዓመት ከ3 ሚሊዮን ብር የበለጠ አሰባስቧል፡፡ ከ25 ቀናት በኋላ ፤ ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. የሚካሄደው የዚህ ዓመቱ ውድድር 25ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት በመሆኑ በተለየ ስሜት እየተዘጋጀም ይገኛል፡፡
‹ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ› በሚል የሚጠራው ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ የተጀመረው በ1998 ዓ.ም. ፤ በ5ኛው የውድድር ዓመት ነበር፡፡ ባለፉት 20ዓመታት በዘመቻው ከ43 ሚሊዮን ብር የበለጠ ተሰባስቦ ከ60 ለበለጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተከፋፍሏል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዚህ ዘመቻ አስተባባሪ አብድራዛቅ አለዊ፣ ከታለመው የገንዘብ መጠን 75በመቶውን መደበኛው የምዝገባ ጊዜ ከተዘጋ በኋላ በተከናወነው የመጨረሻው የምዝገባ ጊዜ ከፍ ባለ ዋጋ ከተከናወነው ምዝገባ ለማሰባሰብ እንዳቀዱ ገልጿል። ለዘመቻው ድጋፋቸውን ሲሰጡ የቆዩ በርካታ ድርጅቶች ለጋስነትንም ጠቅሶ አመስግኗል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአምስት ዓመታት በፊት ጀምሮ GivenGain በተሰኘው ድረ-ገፅ አማካይነት ከሀገር ውጪ የሚገኙ ተሳታፊዎችም ለዘመቻው ድጋፍ እንዲያደርጉ ማመቻቸቱ ይታወቃል።
በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ተመርጠው በዚህ ዓመት ተጠቃሚ የሚሆኑት ሶስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ቼሻየር ኢትዮጵያ ፣ ተስፋ ማህበራዊ እና ልማት ማህበር እንዲሁም የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ናቸው፡፡
💫ሰባተኛ ዙር ልምምዳችንን ከአህመድ የጤና ቡድን አባላት ጋር✨
እሁድ ወሎሰፈር እንገናኝ ✨
የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ✨
#GreatEthiopianrun #25thEdition #10k #ANationIn10km
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.
Наш сайт использует cookie-файлы, чтобы сделать сервисы быстрее и удобнее.
Продолжая им пользоваться, вы принимаете условия
Пользовательского соглашения
и соглашаетесь со сбором cookie-файлов.
Подробности про обработку данных — в нашей
Политике обработки персональных данных.