ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️
የከረመ ናፍቆት
######
"
"
"
ልክ እንደ ህፃናት
የዋህ ሁን የሚል ቃል ሰመመን ያነቃው
***
የሞተች እናቱን ገበያ እንደ ሄደች
ቆሞ ሚጠብቃት እስክትመጣ ናፍቃው
****
ደጅ ደጁን ሲቃኝ
ልቡ ያላረፈው በምንም ባይተካት
*
የሚያሳሳ ገፁን
በእምባ ዶፍ አጅቦ
ይጠብቃት ነበር ቀሚሷን ለመንካት
****
ደሞ,,,,
ሀዘን ላጠላበት
የዘመናት ፍቅሩን ላልገደበው ወሰን
*
እንዲህ ሲል ጠየቀው
ግድ የለም እማዬን
ህይወት እንዝራባት በጭቃ ለውሰን
**
ለጥያቄው ክብደት
የሚመጥን ቃላት ቢያጣ በቂ መልስም
*
ከእንግዲህ በኃላ
እናትህ ፈፅሞ በቃ አትመለስም
*
ብሎ እንዳያረዳው
መቼም ያባት ነገር የልጅ ገላ አሳሳው
***
እንዳይዋሸው ደሞ
መሸከም ከበደው ጉልበት አቅም ነሳው
*
ታዲያ በዚህ መሀል,,,,,,,
የተነገረውን የማይካድ እውነት
በውስጡ አዳፍኖ ያከረመው ሚስጥር
*
አንድ ነገር ያውቃል
ከአፈር እንደ ሆነ አምላክ ሰው ሲፈጥር
****
ተፈጥሮ ብትቸረው
የመውደድን እውቀት የፍቅርን ጥልቀት
***
ደርሶ እንደሚባለው
ከያዘ እንደማይለቅ ልጅ እና ወረቀት
***
ከመፍጠርህ በፊት
እልፍ ዘመናትን እንደ ተቀዳጀህ
****
ካፈር ብናኝ ዘግነህ
በጭቃ ለውሰህ ፍጥረትን ያበጀህ
***
የሰናፍጭ ታህል
እምነት ባይኖረውም እንዳይጠራጠር
***
ለህፃን ልጅ ስትል ሁለት እናት ፍጠር
****
ሁሉን ቻይ ነህና ስለምታውቅበት
ካንዷ ሽጉጥ ይበል አንዷ ስትሞትበት