Информация о канале обновлена 20.08.2025.
Информация о канале обновлена 20.08.2025.
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ የዕረፍት መታሰቢያ ሥርዓተ ጸሎት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ ።
ሪፖርተር ሙሉቀን ሀሰን
(#EOTCTV ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም)
የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ነሐሴ ፲ ቀን በጸሎት ይታሰባል ።
በዘንድሮም የቅዱስነታቸው የዕረፍት መታሰቢያ የጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ጽባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ; ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት፣ ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ; ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሐዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ; ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ; የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጆችና የመምሪያና የድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ; ሊቀ ትጉሀን ታጋይ ታደለ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ልጆቻቸዉ በተገኙበት ተከናውኗል ።
ቅዱስነታቸው በክህነት ዘመናቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዓለምአቀፍ ተሰሚነት እንዲኖራት በማድረግ እና አስተዳደሯ እንዲቀና በማድረግ ረገድ ጉልሕ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል ።
እንዲሁም በመርሐ ግብሩ ላይ አባታዊ መልዕክት ያስተላልፉት ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የነበራቸው ጠንካራ የአገልግሎት ዘመን ልንከተለው ይገባናል ሲሉ የገለጡ ሲሆን ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያንን በቀናነት አገልግለው አልፈዋል ለዚህም ቤተክርስቲያን ሁሌም ተዘክራችዋልች ሲሉ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ያሬዳዊ ዜማ እና ቅኔ ቀርቧል።
Рост подписчиков
Публикации
Просмотры
Средний охват + ERR%
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.