"ከባባድ ጥያቄዎች በቀላል መልሶች ይረታሉ"
ሀሳብ ለማስፈንጠር.... @kalu30
Facebook - https://www.facebook.com/profile.php?id=100007449047737
Информация о канале обновлена 28.09.2025.
"ከባባድ ጥያቄዎች በቀላል መልሶች ይረታሉ"
ሀሳብ ለማስፈንጠር.... @kalu30
Facebook - https://www.facebook.com/profile.php?id=100007449047737
የመዳን ጅማሮ
(ካሊድ አቅሉ)
ዝናብ መሀል ሙሉ ማፍቀር
እያራሰኝ
ገነት ደጃፍ ፃድቃን መንደር
በከንፈርሽ አደረሰኝ !
አቤት ለዛ
አቤት መኖር
ዘመንን በሰአት የተካ
ስሩ እረጅም ዉሉ ጠጣር
ያስጠለለን ትልቅ ዋርካ ፤
ሳቁ ሚታይ የደስታዎች
ማሰሪያ ዉል
መዳፎችሽ ሲዳብሱኝ
ነፍሴ በሀሴት ሲንከባለል ፤
እላለሁኝ ምድር ለቀኩ
ከመላዕክት ተመካከርኩ
ተስፍዬ ላይ ህይወት ደረብኩ !
ቀለስኩኝ መዉደድ በቅኝት
እንደ ዋሽንት እየባባዉ
ሳልፈተሽ እንደ ዘመድ
አይንሽ ሀገር በአይኔ ገባዉ !
ልብሽ የጥጥ ፍልቂቅ መንጣት
በቀር ያልጎበኘዉ
ነፍስን ፍቅር ሚመግብ ማፍቀር
ስሙን ያናኘዉ
የረጋ ፀጥ ያለ ቦታ አማኞች
ሚፀልዩበት
ከአምላክ ጋር ንግግር ያለዉ
በቃሉ ሚገናኝበት
ሰላም አየር ፀዳል ዉበት
ሳይቆጠብ የሚፈስበት !
እሱ ነዉ ያንቺ አድባር
ልብ የሚሉት ልብ ያላቸዉ
የመዳን ጅማሮ መንገድ
ፈውስ አርጎ ሚሰጣቸዉ ።
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.