Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
Информация о канале обновлена 17.08.2025.
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
📢 👨⚕️ዓይነት 2 የስኳር ሕመምተኞችን ለ MASLD መመርመር – ዋና ዋና ነጥቦች! 🩺
📢 👨⚕️MASLD in People With Diabetes: The Need for Screening and Early Intervention. A Consensus Report of the American Diabetes Association 2025.
✅Metabolic dysfunction-associated steatotic liver disease (MASLD)፣ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ያለባቸው ታካሚዎች (T2DM) ላይ በስፋት የሚታይ ሲሆን፣ ከእነዚህ ታካሚዎች ውስጥ ~ከ60-75% የሚሆኑት ላይ ይታያል።
ይህ ችግር እንደ metabolic dysfunction-associated steatohepatitis (MASH)፣ ፋይብሮሲስ፣ሲርሆሲስ (cirrhosis)፣ የጉበት ካንሰር (HCC) እና በጉበት ችግር ምክንያት የሚመጣ ሞት መጨመርን ከመሳሰሉ ከባድ የጉበት ችግሮች ጋር የተያያዘ ከመሆኑም በላይ MASLD የልብና የደም ዝውውር በሽታ (CVD)፣ ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ፣ከጉበት ውጪ ያሉ ካንሰሮች እና ሌሎች ችግሮችም ጋር ይያያዛል። በዚህም ምክንያት ቀደም ብሎ ምርመራ ማድረግ እና ህክምና መጀመር ወሳኝ ነው::
✅ ለምን ምርመራው አስፈለገ? (Rationale for Screening)
👉 የችግሩ ስፋት: MASLD ~70% ሚሆኑ የT2DM ታካሚዎች ላይ ይገኛል፤ ከእነዚህ ውስጥ ~50% የሚሆኑት MASH ያለባቸው ሲሆን፣ ~15-38% የሚሆኑት ላይ ደሞ የላቀ የጉበት ፋይብሮሲስ (ደረጃ ≥F2) ይታይባቸዋል።
👉ተያያዥ አደጋዎቹ: በT2DM ታካሚዎች ላይ የሚታየው MASLD የስኳር በሽታ ከሌለባቸው ግለሰቦች ጋር ሲነጻጸር የጉበት ችግር ጋር የተያያዘ ሞትን ከ2-3 እጥፍ ይጨምራል። በተጨማሪም፣ የልብና የደም ዝውውር በሽታ (CVD) ስጋትን ከፍ ያደርጋል።
👉 በቂ ትኩረት አለማግኘቱ: ከፍተኛ ስርጭት እና ከባድ ጠንቆች ቢኖሩትም፣ MASLD አስቀድሞ ምልክት የማያሳይ በመሆኑ እና በታካሚዎችና በጤና ባለሙያዎች ዘንድ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ በመሆኑ ብዙ ጊዜ በወቅቱ ምርመራ አይደረግለትም ።
✅የምርመራ ምክረ ሃሳቦች
👉በ ADA፣ AASLD እና EASL መመሪያዎች መሰረት:
ደረጃ በደረጃ የማጣራት ስትራቴጂ
ደረጃ 1: ስቴአቶሲስን (steatosis) ለመለየት አልትራሳውንድ ይጠቀሙ።
ደረጃ 2: የፋይብሮሲስን (risk of fibrosis) ስጋት ለመገምገም FIB-4 score ያሰሉ::
ደረጃ 3: ከፍተኛ የFIB-4 ውጤት ያላቸውን ታካሚዎች ለ VCTE ምርመራ ወይም ወደ የጉበት ስፔሻሊስት ይላኩ።
ደረጃ 4: አስፈላጊ ከሆነ የጉበት ባዮፕሲ (liver biopsy) በመውሰድ ማረጋገጥ ይቻላል።
✅ልክ እንደ ሬቲኖፓቲ (retinopathy) ወይም ኔፍሮፓቲ (nephropathy) ምርመራዎች ሁሉ፣ ይህንንም ምርመራ ከመደበኛ የስኳር በሽታ እንክብካቤ ጋር ማካተት እንደሚያስፈልግ ይሄ ሪፖርት ይመክራል።
✅ ለተጨማሪ ዝርዝሮች የ ADAን ሪፖርት (Diabetes Care፣ https://doi.org/10.2337/dci24-0094) ይመልከቱ።
#MASLD #T2DM #የጉበትጤና #የጉበትምርመራ
Dr. Abera Etana: Internal Medicine resident R2
@HakimEthio
መልካም ዜና ከመቀሌ
"Congratulations to Dr. Fasika Amdeslasie Gebrekirkos and his team on launching Shalom Substance Rehabilitation Center today in Mekelle. Wishing you success in bringing hope and healing to many lives."
- Daniel Gebrehiwet, Clinical Psychologist
@HakimEthio
ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ | Professor Malede Maru
ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ ትውልድና እድገታቸው ጎንደር ነው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል፡፡ በመቀጠልም በቤሩት (ሊባኖስ) የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ በልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል ጠቅላላ ሐኪም በመሆን አገልግለዋል፡፡
የፕሮፌሰር ማለደ ማሩና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንኙነት የሚጀምረው በ1962 ዓ.ም. ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ከተማ ሄደው በጎንደር ሕዝብ ጤና አጠባበቅ ኮሌጅና ማሰልጠኛ ማእከል ማገልገል ጀመሩ፡ ለሦስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ ተጕዘው የውስጥ ደዌና የልብ ሕክምና ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡
በመቀጠልም ወደ ጎንደር ተመልሰው በ1970/71 ዓ.ም. የጎንደር ሕዝብ ጤና አጠባበቅ ኮሌጅና ማሰልጠኛ ማእከል ወደ ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሸጋገር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። የኮሌጁም መሥራች ዲን በመሆን አስቸጋሪ በነበሩት የተቋሙ የመጀመሪያ ዓመታት በከፍተኛ ቁርጠኝነት በመምራት የተቋም ግንባታ ታሪክ ላይ ጉልህ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
ላቅ ያሉ የሕክምና ጠበብትን በማፍራት የታወቀው ይህ ኮሌጅ ለዚህ ልህቀት ዐቢይ ሚና የተጫወቱትን የካርል ማርክስ/ላይብዚሽ የሕክምና ምሁራንን ከምሥራቅ ጀርመን በማስመጣት ረገድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዱሪ መሐመድ ጋር በመሆን ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ ከአመራርነት ሚናቸው በተጨማሪ መምህር፣ ተመራማሪ፣ እውቅ ካሪዲዮሎጂስት፣ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያ እና ገምጋሚ በመሆን ኮሌጁን አገልግለዋል። የጎንደር ሕክምና ሣይንስ ኮሌጅ አባት በመባልም ይታወቃሉ።
ለልብ ሕሙማን ያሳዩት በነበረው ርህራሄ፣ በባለሙያዎች አያያዝና ለሕክምና ትምህርትና ሙያ ያደረጉት አስተዋፅኦ በብዙዎች ዘንድ ሁሌም ሲታወስ የሚኖር ሆኖ ይገኛል።
ስለሆነም ይህንን ዘርፈ ብዙ ውለታቸውን በመገንዘብ፣ ላበረከቱት ላቅ ያለ አገልግሎት እና ትሩፋት እውቅና ለመስጠት የጎንደር ዩንቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአስተዳደር ሕንጻ በእርሳቸው ስም እንዲሰየም ወስኗል።
ማሳሰቢያ፦
ፎቶው በ1970ዎቹ ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም ከጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ተፈራ ወንዴ እና ከኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ ጓድ ኢንጂነር ካሳ ገብሬ ጋር ጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ሲጎበኙ የወቅቱ የኮሌጁ ዲን ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ እያስጎበኙ ነው።
የፕሮፌሰር ማለደ ማሩ ታሪክ: https://youtu.be/pP-FtnxE28E?si=jt9AhyefjMsat90_
Professor Malede Maru was born and raised in Gondar. He earned his first degree from Addis Ababa University, then pursued his medical education at the American University of Beirut (AUB) in Lebanon.
After returning to Ethiopia, he served as the General Medical Director at Princess Tsehay Hospital.
His connection with the University of Gondar began in 1962 E.C., when he moved from Addis Ababa to Gondar to serve at the Gondar Public Health College and Training Center. After three years of service, he traveled to the United States to specialize in Internal Medicine and Cardiology.
Upon his return to Gondar in 1970/71 E.C., he played a major role in upgrading the Gondar Public Health College and Training Center into the College of Medical Sciences. As the founding Dean, he led the institution with great dedication during its challenging formative years, leaving a lasting mark on its history.
Renowned for producing highly skilled medical professionals, the college greatly benefited from his key role in bringing bringing University of Leipzig (then Karl Marx university) medical experts from East Germany in collaboration with Dr. Duri Mohammed, then President of Addis Ababa University.
In addition to his leadership roles, Professor Malede served the college as a teacher, researcher, distinguished cardiologist, curriculum designer, and evaluator. He is also remembered as the “Father of the Gondar College of Medical Sciences.”
His compassion for cardiac patients, his mentorship of professionals, and his contributions to medical education and practice remain a lasting legacy in the minds of many.
In recognition of his outstanding service and remarkable contributions, the Senate of the University of Gondar, in its meeting on August 31, 2025, decided to name the College of Medicine and Health Sciences Administrative Building in his honor.
Note:
The photo shows Professor Malede Maru in the 1970s, as Dean of the College, guiding then Head of State Mengistu Hailemariam, together with Minister of Health Dr. Tefera Wondé and Minister of Construction Eng. Kassa Gebre, during their visit to the Gondar College of Medical Sciences.
Watch Prof. Mallede's life journey on: https://youtu.be/pP-FtnxE28E?si=jt9AhyefjMsat90_
Prepared by: Asrat Atsedeweyn
@HakimEthio
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.