We're Here To Help
For any assistance contact us here: @smart_ethio
Информация о канале обновлена 02.10.2025.
We're Here To Help
For any assistance contact us here: @smart_ethio
ለመላው የክርስትና አምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳቹ ፡፡ መልካም በዓል!
@tntethiopia
#ጥቆማ
#SPHMMC
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በህክምና ዲግሪ (Doctor of Medicine) የ2025/26 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች እየተቀበለ ነው።
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ሰኞ መስከረም 19/2018 ዓ.ም ከሰዓት 11:00 ሰዓት
የፅሑፍ ፈተና የሚሰጠው፦
ሐሙስ መስከረም 22/2018 ዓ.ም
አመልካቾች የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ ፈተና (EHEEE) በ2017 ዓ.ም ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ብቻ መሆን ይጠበቅባችኋል።
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ፦
ከአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሶማሌ ክልሎች እንዲሁም ከቦረና ዞን (ኦሮሚያ)፣ ደቡብ ኦሞ ዞን (ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል)፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን (ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል) እና ዋግህምራ ዞን (አማራ ክልል) ለወንድ 475 ፤ ለሴት 450።
ለሌሎች ክልሎች፦
ለወንድ 500 እና በላይ ፤ ለሴት 475 እና በላይ
ማመልከት የሚቻለው በኦንላይን ብቻ ነው 👇
https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement
@tntethiopia
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሲኒማ እና ቴአትር ጥበባት በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛው መርሐግብር በ2018 ዓ.ም ለመማር ፍላጎት ያላቸው የ2ኛ ዓመት ተማሪዎች በማወዳደር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በማኅበራዊ ሳይንስ ወይም በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የ2ኛ ዓመት ተማሪዎች ሆኑ አመልካቾችን እንደሚቀበል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
የመቀበያ መስፈርቶች፡-
➫ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ ወደ ሁለተኛ ዓመት የተዛወራችሁ
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ/በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ጥሩ ውጤት/CGPA ያለው/ያላት
➫ ለጥበባት ዘርፍ ከፍተኛ ፍላጎትና ልዩ ተሰጥኦ ያለው/ያላት
➫ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆናችሁ በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የተመደባችሁ የ2ኛ ዓመት ተማሪዎች ፍላጎታችሁ ታይቶ ወደ ትምህርት ክፍሉ ልትዛወሩ የምትችሉበት ሁኔታ ይመቻቻል።
የማመልከቻ ጊዜ፦
እስከ መስከረም 20/ 2018 ዓ.ም በሥራ ቀናት ብቻ
የምዝገባ ቦታ፡-
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ግቢ፣ የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል
ለበለጠ መረጃ፡-
0910479547 / 0928106018
@tntethiopia
በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርትን በሁለተኛ ዲግሪ መስጠት እንደሚጀምር የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ዲን ዜናማርቆስ ባንቴ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲሱ የትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርት በሁለተኛ ዲግሪ ሊሰጥ ነው።
በሀገሪቷ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን እንደ አንድ አማራጭ የኃይል ምንጭ አድርጎ የመጠቀም ዕቅድ በመኖሩ ፕሮግራሙን መስጠት ማስፈለጉ ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲዉ ትምህርቱን መከታተል የሚፈልጉ ተማሪዎችን እየመዘገበ ሲሆን ለዚህ ትምህርት ብቁ የሚሆኑትም ከዚህ ቀደም በኬሚካል ኢንጅነሪንግ፣ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ በኬሚስትሪ፣ በፊዚክስ እና በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸዉ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
@tntethiopia
በትምህርት ሪፎርሙ የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል የተወሰዱ እርምጃዎች እና ከታች ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና ስራዎች
በሀገራችን የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል ከተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ በትምህርት ፖሊሲው የተቀመጠውን አንድ ተማሪ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ወይም እርከን ለመሸጋገር ቢያን 50 ከመቶና በላይ አማካይ ውጤት ማስመስመዝገብ አለበት በሚል የተደነገገውን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው። በዚህም በሪፎርሙ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችም ይሁኑ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ሲያመጡ ወደ ሚቀጥለው ክፍል/እርከን እንዲሸጋገሩ እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ተማሪዎች 50 ከመቶ በታች አማካይ ውጤት አምጥተው ወደ ሚቀጥለው ክፍል እንዲዛወዱ ወይም በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ይደረግ እንደነበር የሚታወስ ነው። አሁን ባለው አሰራር ይህንን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በየትኛውም የክፍል ደረጃ 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያላመጣ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ወይም እርከን አይዛወርም።
በተጨማሪም በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች በነዚህ ፈተናዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዛወሩ እየተደረገ ይገኛል። ይህም በየደረጃው የትምህርት ጥራቱ ያለበትን ደረጃ እየለኩ ለመሄድ ትልቅ አስተዋጻኦ ይኖረዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤
@tntethiopia
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.