https://youtube.com/c/MusseSolomon
https://www.facebook.com/mussesolomonsisay/
https://www.tiktok.com/@mussesolomonsisay?_t=ZM-8uOFfWUbCM9&_r=1
Информация о канале обновлена 05.10.2025.
https://youtube.com/c/MusseSolomon
https://www.facebook.com/mussesolomonsisay/
https://www.tiktok.com/@mussesolomonsisay?_t=ZM-8uOFfWUbCM9&_r=1
ነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን ነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። በዚህም መሠረት፦
• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣
• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣
• ከሐራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት፣
• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣
• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ፣ እንዲሁም
• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ የሚዘጋ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳይዋቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያቀርባል።
Via @mussesolomon
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ለመማር ያለፋችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
Via @mussesolomon
የ2017 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሚከተሉት አማራጮች ከአሁን ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ትችላላችሁ።
ውጤታችሁን
➫ በድረ-ገጽ፦ https://result.eaes.et
➫ በቴሌግራም ቦት፦ https://t.me/EAESbot
➫ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት፦ 6284
Via @mussesolomon
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ የተወሰኑ መንገዶች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
***
አዲስ አበባ፤ መስከረም 3 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በትውልድ ቅብብሎሽ ዕውን የሆነው የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጳግሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት መመረቁ የሚታወቅ ነው ።
ከምረቃው ዕለት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተካሄዱ ሲሆን ዕሁድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ/ም በመዲናችን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ የተዘጋጀ ሲሆን መርሀ ግብሩን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት በከተማው የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ፡፡
***
በዚህም መሠረት ከመስከረም 3 ቀን 2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ የድጋፍ ሰልፉ እስከሚያልቅ ድረስ የሚከተሉት መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ማቆም እንዲሁም ዝግ ይደረጋሉ፡-
👇
- ከልደታ ፍርድ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
- ከአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ፒኮክ መብራት ላይ
- ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ ላይ
- ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ )
-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
- ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)
- ከሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቲያትር ጎማ ቁጠባ መብራት ላይ
- ከተክለ ኃይማኖት አደባባይ በኢምግሬሽን ጥቁር አንበሳ ላይ
- ከንግድ ማተሚያ ወደ ፍልውሃ ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ ላይ
- ከቸርችል ወደ ጥቁር አንበሳ መብራት ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ፓርላማ መብራት
- ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት ሀራምቤ መብራት ላይ
- ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሀር መብራት
- ከሰንጋ ተራ 40/60 ወደ ለገሃር ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ ላይ
- ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
- ከአረቄ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ ላይ
- ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ባልቻ ሆስፒታል መታጠፊያ ላይ
- ከቫቲካን ኤምባሲ ወደ ሳር ቤት አደባባይ ሳር ቤት አደባባይ ላይ
- ከቅዱስ ዮሴፍ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ
- ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት ላይ መንገዶቹ የሚዘጉ ሲሆን በተጠቀሱት መስመሮች ላይ ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽት 12፡00 ሠዓት ጀምሮ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡
*
Via @mussesolomon
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.