ይህ የደራው ነው!!
📌በመጽሔት
📌በማህበራዊ ሚዲያዎች
📌በኢንተርኔት ሬዲዮ
ከናንተ ጋር ነን!!
የደራው ዲጂታልስ "ፀሐይ አትጠልቅም!"
visit | www.yederaw.com
ያግኙን @YederawSupport
Информация о канале обновлена 19.11.2025.
ይህ የደራው ነው!!
📌በመጽሔት
📌በማህበራዊ ሚዲያዎች
📌በኢንተርኔት ሬዲዮ
ከናንተ ጋር ነን!!
የደራው ዲጂታልስ "ፀሐይ አትጠልቅም!"
visit | www.yederaw.com
ያግኙን @YederawSupport
አዳማ : ለአዕምሮ እድገት ውስንነት ተማሪዎች ማዕከል ሊገነባ ነው
#Ethiopia | የራዕይ የህፃናት ድጋፍ ድርጅት በአዳማ ከተማ በሚገኘው ሌተናል ኮሎኔል ደጀኔ ስሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናት የእንክብካቤ ማዕከል ለመገንባት በዛሬው እለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የራዕይ የህፃናት ድርጅት መስራች ዶ/ር ጽጌ ጥበቡ እንደገለጹት "የአዕምሮ እድገት ውስንነት ችግር ያለባቸው ህፃናት ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እና ትምህርት እንዲማሩ እንዲሁም በያዙት ሙያ ራሳቸውን እንዲለውጡ ለማስቻል መሆኑን" ገልጸዋል።
የራዕይ የህፃናት ድርጅት የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር፥ ማዕከሉ ህፃናቱ የመማርና የመለማመድ ዕድል እንዲያገኙ፣ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውም እረፍት እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል።
የአዳማ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መለሰ ጽሕፈት ቤቱ በአምስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለነዚህ ተማሪዎች ትምህርት እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፣ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲኖር ማዕከሉ መስፋፋት እንዳለበት አሳስበዋል።
የአዳማ ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በሪሶ ዶሪ
ሁሉም ሰው ለሚቀጥለው ትውልድ የበጎ ፈቃድ ሥራ እና በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በመሳተፍ ድርሻውን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።
የሌተናል ኮለኔል ደጀኔ ሰሚ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት ወ/ሮ አስናቀች ደኑሳ፥ በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡ መደሰታቸውን ገልጸው፣ መምህራንንና ቤተሰቦችን በማሳተፍ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
በአዳማ ከተማ የሚገኘው የሌተናል ኮለኔል ደጀኔ ሰሚ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ3ሺህ በላይ ተማሪዎችን በሁለት ፈረቃ በማስተማር ላይ ሲገኝ ከ30 በላይ ለሚሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናትን ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ማዕከሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የተማሪዎቹን ቁጥር ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ባለ በጎዋ ልብ ፤ መሲ
"የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህጻናት የመጡ ኮምፒዩተሮች ጉሙሩክ ይዞብናል" ~ ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት
* ለአገርና ለሕዝብ ጥሪ አቀርበዋል
#Yederaw | በዛሬው ዕለት የድርጅቱ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ( Goodwill Ambassador )የሆነችው አትሌት መሰረት ደፋር እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አርቲስቶች፣ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት በትንቢተ ኤርምያስ እና ስብስቴ ነጋሲ ትምሕርት ቤቶች ጉበኝት አካሂደዋል።
የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ጽጌ ጥበቡ፣ "እነዚህ ልጆች ከቀለም ትምሕርቱ ይልቅ ይበልጥ የሚጠቅማቸው የሞያ ትምሕርት ቢማሩ ነው። ውጤታማም ይሆናሉ" በሚል መነሻ ሃሳብ የትምሕርት ቤት የደንብ ልብስ፣ ሥዕል የሚስሉባቸውን ቀለማትና መሰል ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
አያይዘውም ለሕጻናቱ የልዩ ፍላጎት ባለሞያዎችን በመመደብ እና በመምሕራኑ ትብብር ጥናት በማስጠናት፣ እነዚሁ ሕጻናት የሽመና ማሽን ተገዝቶላቸው ውብ የሸማ ውጤቶችን ሰርተው እስከማቅረብ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
ድርጅቱ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የእእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ወጣቶች በሸማ ሙያ፣ በኮምፒውተር (ኮዲንግ)፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ሥዕል፣ በስፖርት እና በሌሎችም ዘርፎች እያሰለጠነ ይገኛል።
ዶ/ር ጽጌ እንዳወሱት በዚህም የት/ቤት የደንብ ልብስ፣ ሥዕል የሚስሉባቸውን ቀለማትና መሰል ነገሮችን በማቅረብ የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎችና በመምህራኑ ትብብር ጥናት በማስጠናት የሽመና ማሽን ተገዝቶላቸው የሚያማምር ሸማ ሰርተው እስከ ማቅረብ ደርሰዋል ብለዋል።
የአእምሮ እድገት ውስንነትና ሌሎች የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናትና ወጣቶች በመንፈሳዊ፣ ስሜታዊ፣ ትምህርታዊና ሙያዊ ፕሮግራሞች በመደገፍ ላይ ናቸው።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት አትሌት መሰረት ደፋርን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ( Goodwill Ambassador ) አድርጎ መሾሙንም በአሜሪካን ሀገር በተደረገ ሥነ ስርዓት ተከናውኗል።
ድርጅቱ ከአትሌት መሰረት ደፋር ጋር የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ስምምነት ያደረገው ድርጅቱ ህዝቡ ጋር የነበረውን ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበት የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት እንደሆነ ተነግሯል።
ጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋር እንደተናገረችው የእነዚህ ህጻናት ጉዳይ የሁሉም ሀላፊነት ነው ብላለች። በህጻናት ህይወት ላይ መስራት ሀገር ከመስራት እኩል ነው ስትልም አጽንኦት ሰጥታ ተናግራለች።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት እ.ኤ.አ በ 2007 ዓ.ም ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ አገር ኑሮ ባደረጉት በዶ/ር ጽጌ ጥበቡ ተመሰረተ፡፡
ከየካቲት 09 ቀን 2014 ዓ/ም በበጎ አድራጎት
በአዋጅ ቁጥር 11/03/2011 መሠረት በመዝገብ ቁጥር 6067 በኢ.ፊ.ዲ.ሪ. የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት ተሰጥቶት የሰሜን አሜሪካውን ተሞክሮ ለማስፋፋት እየሰራ ያለ ( በጎ ሥራው ያልተነገረለት) ተቋም ነው፡፡
ራዕይ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ያስመጣኋቸው የኮምፒዩተር መሳሪያዎች ጉምሩክ ላይ ተይዘውብናል ሲሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ራዕይ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ከአገር ውጭ ያስመጣቸው የኮምፒዩተር መሳሪያዎች ጉምሩክ ይዞብናል ብሏል።
እነዚህ ልጆች የኮምፒዩተር ስልጠና እንዲወስዱ የኮምፒዩተር መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ለማስገባት እየተሰራ ቢሆንም መሳሪያዎቹ ጉምሩክ ላይ በመያዛቸው ልጆቹ እስካሁን የኮምፒዩተር ስልጠና ሊወስዱ አልቻሉም ለዚህም የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲቀርፍ ለአገርና ለሕዝብ ጥሪ አቀርበዋል።
ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሌሎች ህጻናቶች ለመደገፍና ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንዲሁም ተጨማሪ ስራዎቹን ለማከናወን የቦታ እጥረት እንዳለበት የገለጸ ሲሆን የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቋል።
በዛሬው የመስክ ዝግጅት ላይ የተገኙት ወላጆችም ሲቃ በተሞላበት ስሜት ሆነው ተቋሙን ያመሰገኑ ሲሆን እንደስምሽ መሰረት ለልጆቻችን መሰረት ሁኚልን ብለዋል።
ራዕይ ልጆቻችንን ቢቻ አይደለም የሚደግፈው እኛንም በየወሩ ገንዘብ እየሰጠን ኑሮአችንን እንዲሻሻል አግዞናል ብለዋል።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት በ7 ት/ቤት ከ300 በላይ ለሚሆኑ ልጆች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን በዛሬው እለትም ድጋፍ ከሚያደርግባቸው ት/ት ቤቶች ውስጥ በትንቢተ ኤርሚያስና በስብስቴ ነጋሲ ት/ቤቶች የሚማሩ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች የሚሰሯቸውን የሙያ ስራዎች ጉብኝት ተካሄዷል።
በተጨማሪም ሌሎች ልጆችንም በሙያ ለመደገፍ የቦታ እጥረት ስላለ የሚመለከተው አካል ይህንንም ችግር እንዲመለከት ጥሪ አቀርበዋል።
በመላው አገሪቱ ባሉ ሁለም ት/ቤቶች ልዩ ፍላጎቶች ያላቸው ልጆች ትኩረት ተሰጥቷቸው፣ የሙያና የህይወት ክህሎት ስልጠና አግኝተው ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ አላማው ያደረገው ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት በዶክተር ፅጌ አማካኝነት በኢትዮጵያ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት ተልዕኮ የአእምሮ እድገት ውስንነትና የእድገት መዘግየት ላለባቸው ልጆች የስነልቦና እና የሙያ ክህሎቶችን በማቅረብ እራሳቸውን እንዲችሉ መርዳት ነው።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ስብስቴ ነጋሲ ት/ቤት፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትንቢተ ኤርምያስ ት/ቤት፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወይራ ት/ቤት፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የማነ ብርሃን ት/ቤት እንዲሁም ት/ቤት መምጣት የማይችሉ በየቤታቸው ድጋፍ የሚያገኙ ልዩ ፍላጐት ያለባቸው ልጆች፤ ተቋሙ የሚረዳቸው ከ300 በላይ ልጆችን በሙያ በማሰልጠን እንዲሁም የሕክምናና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡ ተገልጿል።
ኮኬት ኢንቨስትመንት ኢንተርናሸናል ሞዴል ሌንሳ ጥላሁንን ከአሜሪካን ሃገር በማስመጣት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።
#Yederaw | ኮኬት ኢንቨስትመንት ኢንተርናሸናል ሞዴል ሌንሳ ጥላሁንን ከአሜሪካን ሃገር በማስመጣት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።
ሞዴል ሌንሳ ጥላሁን ነዋሪነቷን በአሜሪካን ሃገር ያደረገች ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሞዴል ስትሆን ከዚህ ቀደም በሚስ ኢትዮጵያ ውድድር ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን የሚስ ኦሮሚያ የቁንጂና ውድድርን ደግሞ በአንደኝነት በማሸነፍ ሃገሯን በአለም አደባባይ ያስጠራች ኢንተርናሽናል ሞዴል ናት ።
ኮኬት ኢንቨስትመንት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 የተቋቋመ ሲሆን በዋነኛነት በሶፍት ዌር ኢንጂነሪንግ ፣ በሶፍት ዌር ማበልፀግና ለተቋማት ማቅረብ ፣ በኮንስትራክሽን እና በኢንቴሪየር ዲዛይ ስራ ላይ የተሰማራ ሃገር በቀል ድርጂት ነው ።
ኮኬት ኢንቨስትመንት ኢንተርናሽናል ሞዴል ሌንሳ ጥላሁንን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ የሾማት ድርጂቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ተደራሽ ለማድረግ ሞዴል ሌንሳ አሜሪካንን ጨምሮ በተለያዮ የአለም ሃገራት ካካበተችው አለም አቀፍ እውቅናና የስራ ተነሳሽነት እንደዚሁም ኮኬት በቀጣይ አለማቀፍ የቢዝነስ ሰዎች ጋር ለሚያደርገው ግንኙነት ራዕዮን እውን ከማድረግ አኳያ ስኬታማ ተግባራትን እንደምታከናውን በማመን መሆኑን የኮኬት ኢንቨስትመንት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዋሲሁን ተፈራ ገልፀዋል ።
ኢንተርናሽናል ሞዴል ሌንሳ ጥላሁን የኮኬት ብራንድ አምባሳደር ለመሆን 15 ሚሊየን ብር የተከፈላት ሲሆን ኮኬት ኢንቨስትመንት ከሃገር አልፎ በተለያዮ የአለም ሃገራት ለሚያደርገው የንግድ እና የተለያዮ አገልግሎቶች እንቅስቃሴ የተቋሙን ርዕይ እውን ለማድረግ እንደምትሰራ ቃል ገብታለች ።
ሁለቱ መላዎች ብራንድ አምባሳደር ሾሙ
#Ethiopia | መላ ጆብስ ኢትዮጵያውያን ሥራ የሚፈልጉበትን እና የሚያመለክቱበትን መንገድ እየቀየረ ነው። ተጠቃሚዎች ለሀገር ውስጥ የሥራ ማመልከቻ የኢትዮጵያ 12 ብር ብቻ፣ ለዓለም አቀፍ የሥራ ማመልከቻ ደግሞ በ30 ብር፣ በመላ ጆብስ መድረክ በቀላሉ ማመልከት ይችላሉ።
ይህም ለሙያ ዕድገት ተመጣጣኝ እና ቀልጣፋ መግቢያ በር ነው።መላ ጆብስ ከመሠረታዊ የሥራ ማስታወቂያዎች የዘለለ ነው። ተጠቃሚዎች ለቀጣሪዎች ጎልተው እንዲታዩ የሚያስችላቸውን፣ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለዓለም አቀፍ መስፈርቶች የሚስማማ ሙያዊ የሥራ ልምድ (CV) በራስ-ሰር የሚያዘጋጅ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተደገፈ የሲቪ ማዘጋጃ አለው።
መድረኩ በተጨማሪም ተጠቃሚዎች የሥራ ጉዟቸውን በእያንዳንዱ ደረጃ— ከመገለጫ መፍጠር ጀምሮ እስከ ለቃለ መጠይቅ መዘጋጀት ድረስ — የሚመራ AI ቻትቦት ያካትታል።የገንዘብ ልውውጦችን ለማቃለል፣ መላ ጆብስ ተጠቃሚዎች ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ሂሳብ ማስተዳደር እና ለሥራ ማመልከቻዎች ወደሚያገለግል "Connects" የሚለውጥ ዲጂታል የኪስ ቦርሳ (Wallet) አስተዋውቋል።በእነዚህ ፈጠራ ባህሪያት፣ መላ ጆብስ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሥራ ፈላጊ የሙያ የወደፊት ሕይወቱን በፍጥነት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በብልሃት እንዲቆጣጠር ኃይል ይሰጣል።ዛሬውኑ ንቅናቄውን ይቀላቀሉ።
www.melajobs.com
መላ ገበያ (MELA GEBEYA) – ጋዜጣዊ መግለጫ
መላ ገበያን በማስተዋወቅ ላይ፡ የኢትዮጵያ የመስመር ላይ ግብይት የወደፊት ዕጣ
መላ ገበያ ቀላልነትን፣ መተማመንን እና ቴክኖሎጂን በአንድ ዲጂታል የገበያ ቦታ በማጣመር ኢትዮጵያውያን ምርቶችን በመስመር ላይ የሚገዙበትን እና የሚሸጡበትን መንገድ እየገለጸ ነው።በመላ ገበያ፣ ተጠቃሚዎች ሰፊ ዓይነት ምርቶችን — ከሀገር ውስጥ የእጅ ሥራዎች እና የፋሽን ዕቃዎች እስከ ኤሌክትሮኒክስ ከተረጋገጡ ሻጮች ማግኘት ይችላሉ።
መድረኩ ትኩረቱ የኢትዮጵያ ሻጮች ምርቶቻቸውን ለሰፊው ሕዝብ እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸውን መሣሪያዎችን በመስጠት ማብቃት ላይ ነው። በቀላል የክፍያ አማራጮች፣ ብልህ የዕቃ መመዝገቢያ መሣሪያዎች እና በAI የታገዘ የሽያጭ ዝርዝር ሥርዓቶች አማካኝነት መላ ገበያ ንግዶች ያለ ከባድ የማስታወቂያ ወጪ እንዲያድጉ ያግዛል።
በኢትዮጵያ የኢ-ኮሜርስ ትልቁ ችግሮች አንዱ ያልተስተካከለ የዕቃ ክምችት (inventory) እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ ጥሬ ዕቃዎች ናቸው። መላ ገበያ ይህንን ችግር የሚፈታው ትንታኔዎችን (analytics) እና ብልህ የዕቃ ክምችት አስተዳደርን በማቅረብ ነው።
ይህም ሻጮች ብክነትን እንዲያስወግዱ እና ሥራቸውን ቀልጣፋ እንዲያደርጉ ያግዛል።የመድረኩ ዓላማ በመስመር ላይ መገበያየትን ቀላል ማድረግ ብቻ ሳይሆን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን (SMEs) በመደገፍ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ማጠናከር ጭምር ነው።ኢትዮጵያውያን አምራቾች እና ሻጮች ጥሬ ዕቃዎቻቸውን እና የዕቃ ክምችታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲጠቀሙ ቴክኖሎጂ ተጨማሪ እንዴት ሊረዳቸው ይችላል ብለው ያስባሉ?ውይይቱን ይቀላቀሉ።
www.melagebeya.com
ስለ Marvels Creative Technology
በሦስት ሥራ ፈጣሪዎች የተመሰረተው Marvels Creative Technology በኢትዮጵያ ተደራሽነትን እና ዲጂታል ዕድገትን የሚያሻሽሉ ፈጠራ ያላቸው መድረኮችን ያዘጋጃል። መላ ገበያ (Mela Market) እና መላ ጆብስ (Mela Jobs) ይበልጥ ብልህ እና የተሳሰረች
ሀገርን ለመገንባት ኩባንያው እያደረገ ያለውን ቀጣይ ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ዋና ምሳሌዎች ናቸው።
የመገኛ አድራሻ Marvels Creative Technology
📞 0977667575
📧 contact@marvelscreative.com
🌐 www.marvelscreative.com
አሸቅሉኝ !
መድኃኔዓለምን ከመቼም ጊዜ በላይ ብር ያስፈልገኛል
አሁን የተለያዩ ስራዎችን በክፍያ (ልብ በሉ) በክፍያ መስራት እፈልጋለሁ። አሪፍ ስራ አሰሩኝ ክፈሉኝ ።
1. ለሬድዮ፣ ለቴሌቪዥን፣ ለሶሻል ሚዲያ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ድምፅ ከነስክሪፕቱ አሪፍ አድርጌ መስራት እችላለሁ።
2. የሬድዮና ድራማ እና ዶክመንተሪዎች ላይ Voiceover የሚሰራ ባለሞያ ከፈለጋችሁም አለሁ።
3.ለኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ምርቃቶች፣ለአደባባይ በዓላት እና ለተለያዩ የማስጀመሪያ (የመክፈቻ) ሥነ ሥርዓቶች፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎች አስተባባሪና መድረክ መሪ ከፈለጋችሁ አለሁ።
4.ይህን ጽሑፍ የምታነቡበት የፌስቡክ ገፄ በ28 ቀናት ከ3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ዘንድ ይደርሳል። በፌስቡክ ገፄ ማስታወቂያ ማስነገረ የምትፈልጉ ገፁ ለክፍያ ማስታወቂያ ክፍት ነው። ተጠቀሙበት።
ልብ በሉ: ከዚህ ቀደም የተለያዩ ስራዎችን ሰርቻለሁ የሰራሁትን ሳምፕል ማቅረብ እችላለሁ።
እናማ እኔን ናቲ ማናዬን ማሸቀል የምትፈልጉ
ሀብታም እናደርገው የምትሉ :-
Contact Telegram:- @Tmanaye
ስራ ሲኖራችሁ ስልኬን በውስጥ መስመር አስቀምጥላችሁ!!
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.
Наш сайт использует cookie-файлы, чтобы сделать сервисы быстрее и удобнее.
Продолжая им пользоваться, вы принимаете условия
Пользовательского соглашения
и соглашаетесь со сбором cookie-файлов.
Подробности про обработку данных — в нашей
Политике обработки персональных данных.