ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።
✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante
አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿
Информация о канале обновлена 19.11.2025.
ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።
✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante
አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿
👆
ዓፊያ ላይ ያለ ሰው እንዴት ማስተናገድ እንዳለብን ለማየት ደሞ
👇ከስር ያለው ሊንካይጫኑ👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://t.me/hamdumobile
✍
ጣዕረ ሞት ላይ ያለ ሰው እንዴት ማስተናገድ አለብን??
አቡ ሰዒድ አል_ኹድሪይ እና አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦
«لَقِّنُوا مَوْتَاكُمْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ»
«ሟቻችሁን ላ ኢላሃ ኢለላህ አስብሉት።»
ጣዕረ ሞት ላይ መሆኑ ከገመታችሁ "ላ ኢላሃ ኢለላህ" እንዲል አስታውሱት ማለት ነው። የዚህ ምክንያት በሌላ ሓዲስ ሲገልፁ፦
«من كان آخر كلامه لا إله إلا الله دخل الجنة»
«የመጨረሻው ንግግሩ ላ ኢላሃ ኢለላህ የሆነ ሰው ጀነት ገብቷል።» አሉ
ከዚህ ጋ በተያያዘ.........
🌙ለሟቹ ተልቂን የሚያደርገው ሟቹ ዘንድ የሚወደድ ሰው መሆን አለበት። ከነገሩ አስጨናቂነት በተጨማሪ የማይወደው ሰው አጠገቡ ሁኖ "ላ ኢላሃ ኢለላላህ በል" ቢለው በብስጭት መጥፎ ነገር ሊናገር ይችላል።
🌙ምን አልባት ልጁ ወይም የሚወዳት ባለቤቱ ካልሆኘች በስተቀር ሌላ ወራሽ አጠገቡ መቅረብ የለበትም። ይህም ለመጥፎ ንግግር ሊገፋፋው ይችላል።
🌙ተልቂን ሲደረግ ቀጥታ "ላኢላሃ ኢለላህ በል" በማለት ሳይሆን ለዚህ የሚገፋፋ የጥበብ ንግግር መጠቀም ያስፈልጋል። "በል" ስትለው ጭንቀት ላይ ነውና ያለው በብስጭት "አልልም" ሊልህ ይችላል። ስለሆነም በሚሰማህ መልኩ "የመጨረሻ ንግግሩ ላ ኢላሃ ኢለላህ የሆነ ጀነት ይገባል" ምናምን እያልክ ታጓጓዋለህ።
🌙አንዴ "ላ ኢላሃ ኢለላህ" ብሎ ምንም ሳይናገር ከቆየ ድጋሚ እንዲል አታስጨንቀውም። "ላ ኢላሃ ኢለላህ" ካለ በኋላ ሌላ ንግግር ከተናገረ አሁንም ድጋሚ ላ ኢላሃ ኢለላህ ታስብለዋለህ: የመጨረሻ ንግግሩ እንዲሆን።
🌙አንዳንድ ጊዜ አንተ ላ ኢላሃ ኢለላህ ስታስብለው እሱ ሌላ ንግግር ሊናገር ይችላል፤ ይህ ማለት ሁሌም ሓቲማው ለመበላሸቱ ምልክት አይደለም። ምክንያቱም ጣዕረ ሞት ላይ ያለ ሰው እኛ ማየት የማንችላቸው ብዙ ነገሮች በዛች ቅፅበት ይመለከታል: የዱንያ ውድመት፣ የሚጠብቀው አኼራ፣ ወይ የጀነት መንገድ፣ ወይ የጀሀነም ስቃይ፣ የመላኢካዎች ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች አስጨናቂና አስፈሪ ነገሮች ሊመለከት ይችላል። አንተ እያናገርከው እሱ ግን ስለሚያየው ነገር እየለፈፈ ሊሆን ይችላልና በሚለው ነገር በጣም መረበሽ በጣም መፈንጠዝም አያስፈልግም። ምን እያየ ምን እያናገረ እንደሆነ ስለማናውቅ በመሰለን መፈሰር አንችልም።
🌙ጣዕረ ሞት ላይ በመሆኑ ጌታው ላይ ተስፋ ይዞ እንዲገናኘው መልካም መልካም ስራዎቹ እየዘረዘሩ ማበሰር የተወደደ ነው። "አንተ እኮ ሙስሊም ነህ፣ ሙስሊም የጀነት ነው፣ ሰጋጅ የአላህ ወልይ ነው፣ ጾምህ, ሰደቃህ, ቂርኣትህ ጀነት ውስጥ ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ ናቸው" እያልክ ልቡ በደስታ ተሞልቶ የጀነት ተስፋ ሰንቆ ጌታውን እንዲገናኝ የቻልከውን በጥበብ ታደርጋለህ።
🌙በመጨረሻም ወደ ቂብላ ታስተኛውና ሩሑ መውጣቷ ስታውቅ ዓይኖቹን እየከደንክ የተጣጠፈ ሰውነቱ ካለ እንዳይደርቅ በመዘረጋጋት ወደ ጀናዛ እንክብካቤ ትሸጋገራለህ።
🤲አላህ ወደውትና ወዷቸው ከሚገናኙት ባሮቹ ያድርገን🤲
🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante
👇
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.
Наш сайт использует cookie-файлы, чтобы сделать сервисы быстрее и удобнее.
Продолжая им пользоваться, вы принимаете условия
Пользовательского соглашения
и соглашаетесь со сбором cookie-файлов.
Подробности про обработку данных — в нашей
Политике обработки персональных данных.