ፍልስፍና እውነትን በመፈለግ- ልማዳዊ እምነቶችን በመሞገት እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤ ሀይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።
Информация о канале обновлена 03.10.2025.
ፍልስፍና እውነትን በመፈለግ- ልማዳዊ እምነቶችን በመሞገት እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤ ሀይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።
ንቃት ከፍቅር የበለጠ ዋጋ አለውን?
ምንጭ ፦ የንቃት ጥበብ (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዳዊት መላኩ
የመጨረሻው ከፍታ ላይ መድረስ የሚቻለው ሁሉም ዋጋ የምንሰጣቸው ነገሮች እንደ እውነት፣ ፍቅር፣ ንቃት፣ ምሉዕነት የመሣሠሉት በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ሆነው ፀጥ ሲሉ ነው፡፡ የመጨረሻው ጥግ ላይ ስትደርሱ አንዱ ከአንዱ ሊበላለጡና ሊለያዩ አይችሉም፡፡ የተለያዩ መስለው የሚታዩን ባለመንቃት ውስጥ በሚገኘው የጨለማ ሸለቆ ወስጥ ስንገኝ ብቻ ነው፡፡ ሊለያዩ የሚችሉትም ከሌሎች ነገሮች ጋር ተቀይጠው ሲመረዙ ብቻ ነው፡፡ ያልተመረዙና የጠሩ ከሆኑ ግን አንድ ይሆናሉ፡፡ እጅግ በጣም እየጠሩ በመጡ ቁጥር ደግሞ እርስ በራሣቸው የተጠበቁና የማይነጣጠሉ ይሆናሉ፡፡ ለምሣሌ በርካታ የሆኑ ዋጋ የምንሰጣቸው ነገሮች በየደረጃው ተከፋፍለው ይገኛሉ። እያንዳንዳቸው ማህበረሰቡ ለሚያስቀምጥልን ከፍተኛው ደርጀ እንደመወጣጫ መሠላል በመሆን ያገለግላሉ፡፡ ፍቅር ማለት ሴሰኝነት ብቻ ሲሆን ዝቅተኛውን ዋጋ ይይዝና እስከ ገሃነም የሚለውን ደረጃ ያገኛል፡፡ ነገር ግን ፍቅር ፀሎት ሲሆን ከፍተኛውን የክብር ቦታ ያገኝና እስከ ገነት ጥግ ይደርሣል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ በሁለቱ መካከል በርካታ የሆኑና በቀላሉ ሊታዩ የማይችሉ እርከኖች አሉ፡፡
ፍቅር ሴሰኝነት በሚሆን ጊዜ አንድ መቶኛውን ክፍል ሲይዝ ቀሪውን ዘጠና ዘጠኝ ከመቶውን የሚይዙት ምቀኝ ስጋዊ ፍላጎት ፣የኩራት ስሜት፣ እንደግል ንብረት መቁጠር ፣ ብስጭት የመሣሠሉት ሌሎች ነገሮች ይሆናሉ፡፡ ይህ በይበልጥ አካላዊና ስሜታዊ እንጂ ከዚህ ባለፈ የሚሰማን ነገር የለውም። እንደውም ቆዳን ዘልቆ የማይገባና የታይታ ብቻ ነው ፡፡ ከፍ እያላችሁ ስትሄዱ ግን ነገሮች ጥልቀት እያገኙና አዲስ ገፅታን እያገኙ ይመጣሉ። ቁስአካላዊ ገፅታ የነበራችሁ ስነ-ልቦናዊ ገፅታ ይይዛሉ። ሥነ-ፍጥረታዊ ብቻ የነበሩት ነገሮች ወደ ስነ- ልቦናዊነት ይቀየራሉ፡፡ ስነ-ፍጥረትን ከሌሎች እንስሣት ጋር የምንጋራው ነገር ሲሆን ስነ-ልቦናዊት ግን ለሠዎች ብቻ የተሰጠ
ፀጋ ነው፡፡
ፍቅር ከፍ ወደአለ ደረጃ እያደገ ወይም ጥልቅ እየሆነ ሲመጣ መንፈሣዊ ይዘትን እየተላበሰና እየጎመራ ይመጣል፡፡ የእውነት አንዱ አካል ይሆናል ይህን ዓይነቱን እጅግ የጠራ ፍቅር የሚረዱት እንደ ቡድሃ፣ ክርሽና፣ እየሱስ መሆን የቻሉት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ፍቅር መቶ በመቶ የጠራ ሲሆን ብቃትና በፍቅር፣ መካከል ምንም ልዩነት ልታወጡላቸው አትችሉም ሁለት ነገሮች መሆናቸው ያበቃለታል። በፍቅር እና በእግዚአብሔር መካከልም ምንም ልዩነት ልታገኙ አትችሉም ሁለትነት የሚባል ነገርም ስለማይኖራቸው አንድ ይሆናሉ፡፡ ‹እየሱስም እግዘአብሔር ፍቅር ነው› ያለው ለዚህ ነው፡፡ ሁለቱንም እንደ አንድ አድርጎ ነው ያስቀመጣቸው ይህ ንግግሩ ከጥልቅ አመለካከት የመነጨ ነው፡፡ ላይ ላዩን ሲመለከቱት ሁሉም ነገር ከሌላው የተነጠለና ለብቻው ያለ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ወደ መሃል እየገባችሁ ስትሄዱ ይህ ብዙነቱ እየቀለጠ፣ እየሟሸሸ ይመጣና አንድ ብቻ ሆኖ ይመጣል። በዚህ በመሃሉ ላይም ሁሉም ነገር አንድ ብቻ ሆኖ ይወጣል። በዚህ በመሃከሉ ላይም ሁሉም ነገር አንድ ነው፡፡ ስለዚህም ቪራንድራ የጠየከው ጥያቄ ልክ ሊሆን የሚችለው የፍቅርንና የንቃትን ከፍተኛ የጠራ ደረጃ ካልተረዳኸው ብቻ ነው፡፡ እንደ ኤቨረስት ተራራ ጫፍ ከላይ ያለውን የመጨረሻ ጥጉን በከፊል እንኳን ብታየው ኖሮ ይህ ጥያቄህ ፍፁም አላስፈላጊ በሆነብህ ነበር፡፡
ንቃት ከፍቅር የበለጠ ከፍተኛ ዋጋ አለው ወይ? ብለህ ጠይቀሃል ከፍተኛ እንዲሁም ዝቅተኛ የሚባልና የሆነ ነገር ጨርሶ የለም፡፡ እውነቱን ለመናገር ሁለት ዋጋ ያላቸው ነገሮች አብረው አይኖሩም፡፡ ያሉት ሁለት ጫፍ የሚያደርሱ ናቸው፡፡
የመጀመሪያው የንቃትና የተመስጦ መንገድ ሲሆን አሁን የቡድሃ ናየዜን መንገድ እያልን የምንጠራው ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የፍቅር መንገድ ነው፡፡ ይህኛው እራሱንና ጊዜውን ለፍቅር ለሚሰዋ የተሰጠና የክርስቶስናና የሱፊዎች መንገድ ነው። ስትጀምራቸው አካባቢ እነዚህ ሁለት መንገዶች ይለያያሉ። መምረጥ ያለባችሁ እናንተ ናችሁ፡፡ ነገር ግን የትኛውንም መንገድ ይዛችሁ ብትጓዙ የሚያደርሷችሁ ከፍተኛ ቦታ ተመሣሣይ ነው፡፡ ከዚህ የመጨረሻው ከፍተኛ ቦታ ላይ ለመድረስ ስትቃረቡ ደግሞ ሌላውን መንገድ ተከትለው የመጡት ተጓዦች ወደ እናንተ በጣም እየቀረቡ ስለሚመጡ ያስደንቃችኋል፡፡ ቀስ በቀስም እነዚህ ሁለት የነበሩ መንገዶች እርስ በርስ መደራረብ ይጀምራሉ፡፡ ከዚያ በኋላ የመጨረሻው እውነት ላይ አንድ ላይ በመሆን ይደርሳሉ፡፡
የንቃትን መንገድ ተከትሎ የሄደ ሰው በንቃቱ አማካኝነት ፍቅርን ያገኛል። ይህ ከንቃቱ እንደሚገኝ ተረፈ ምርት ይሆናል፡፡ ፍቅር ጥላ ሆኖ ይከተለዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የፍቅርን መንገድ ተከትሎ የተጓዘ ሰው በፍቅር አማካኝነት ንቃት ያገኛል፡፡ ይህኛውም ለእሱ በፍቅር አማካኝነት የሚያገኘው ተጨማሪ ነገር በመሆን ፍቅርን እንደጥላ ተከትሎ የሚመጣ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁለቱ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው፡፡
ማስታወስ ያለባችሁ ንቃታችሁ ፍቅር አልባ ከሆነ አሁንም ገና ያልጠራ መሆኑን ነው 100% የጥራት ደረጃው ላይ ገና አልደረሰም ማለት ነው፡፡ እውነት ለመናገር ይህ ንቃት ሊባል አይችልም፡፡ ምናልባትም በውስጡ ያለመንቃት ሣይቀየጥበት አይቀርም፡፡የጠራ ብርሃን ስለሌለው በውስጣችሁ የተወሠኑ የጨለማ ኪሶች ይፈጥራል። እነዚህም አሁንም ድረስ እየተንቀሳቀሱ፣ ተፅዕኖ እያደረጉባችሁ እየጨቆኗችሁ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ይህ ፍቅር እንደ ፀሎት ከፍ ያለ ሣይሆን እጅግ የዘቀጠና ለሥጋዊ ስሜት ያደላ ነው፡፡
ስለዚህ መሥፈርት የምታስቀምጡ ከሆነ የንቃትን መንገድ በምትከተሉ ጊዜ መስፈርታችሁ ፍቅር ይሁን ይህ ንቃታችሁ በድንገት ፍቅር በመሆን ሲጎመራና ሲያብብ በትክክልም ንቃትን የተላበሳችሁ ትሆናላችሁ፡፡
በተመሣሣይ መንገድ የፍቅርን መንገድ ተከትላችሁ ስትጓዙ መሥፈርታችሁን ንቃትን በማግኘት ላይ አድርጉት ሰረ መሰረታችሁ አድርጋችሁ ያዙት፡፡ እናም በድንገት ከየት እንደመጣ የማታውቁት የመንቃት፣ የማወቅ ነበልባል ፍቅራችሁን ማዕከል አድርጎ ሲንቀለቀል ትሰሙታላችሁ፡፡ ይህን በደንብ እወቁት፣ ተረዱት....ተደሰቱበት። ምክንያቱም ቤታችሁ ደርሳችኋልና።
@Zephilosophy
@Zephilosophy
የእስረኞቹ እንቆቅልሽ
አንተ እና ጓደኛህ በአንድ ወንጀል ተጠርጥራችሁ ታሰራችሁ፡፡ ሆኖም መርማሪ ፖሊሶቹ ምንም አይነት ማስረጃ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ እናም ሁለታችሁም በተለያየ ክፍል እንድትሆኑ ተደረገ። መርማሪዎቹም ለየብቻችሁ ያሉትን አማራጮች አቀረቡላችሁ።
አማራጭ አንድ - አንተ ከተባበርክ እና ወንጀላችሁን ከተናዘዝክ ነገር ግን ጓደኛህ ዝም ካለ አንተን በነጻ እንለቅሃለን እርሱ ግን
አስራ አምስት አመታት ይታሰራል፡፡
አማራጭ ሁለት - ጓደኛህ ወንጀላችሁን ከተናዘዘ ነገር ግን አንተ ዝም ካልክ፣ እርሱ በነጻ ይለቀቃል... አንተ አስራ አምስት አመታትን ትታሰራለህ።
አማራጭ ሶስት- ጓደኛህም አንተም ከተባበራችሁን ሁለታችሁም አምስት አመታትን ትታሰራላችሁ፡፡
አማራጭ አራት- አንተም ጓደኛህም ካልተናዘዛችሁ፤ ሁለታችሁም ቀላል የሆነ የአንድ አመት እስራት ትታሰራላችሁ።
በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆን ምን ታደርጋለህ?
መናዘዝህ የተሻለ ውጤትን የሚያስገኝ ይመስላል፤ ጓደኛህን ብትከዳውና ብትናዘዝ የሚገጥምህ በነጻ የመለቀቅ ዕድል ነው᎓᎓በተቃራኒው ዝም ብትልና ባትናዘዝ፣ የአንድ አመት ወይም የአስራ አምስት አመት እስራት ይጠብቅሃል።
ሆኖም አንተ ነጻ ሁነህ ጓደኛህ አስራ አምስት አመታትን በእስር ቤት ሲማቅቅ ማየት ምን አይነት ስሜት ይፈጥርብሃል?
እናም ይህ እንቆቅልሽ የሚያስነሳው መሰረታዊ ጥያቄ “እንደ ማህበረሰብ ማሰብ” ወይስ “እንደ ግለሰብ ማሰብ” የሚል ይሆናል። ለሁላችንም የተሻለ አማራጭ የሚሆነው እንደ ማህበረሰብ ማሰብ ነው፤ ሆኖም ሌላኛው ሰው ምን እንደሚያስብ አናውቅምና ለራሳችን
መልካም የሚሆነውን ለማድረግ ስንል ራስ ወዳድ እንሆናለን፡፡ እኔ እንኳ ባልስርቅ ሌላው ይሰርቃል የሚል ሃሳብ ይፈጠራል። ይህ አስተሳሰብም በድሃ አገራት ላለው የሙስና እና ስርዓት አልበኝነት አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል፣ አንድ አሳ የሚሰገርበት ሃይቅ አለ ብለን እናስብ። አሳ አስጋሪዎች በዚህ ሃይቅ ውስጥ ያሉት አሳዎች በራስ ወዳድነት ያለ ልክ የሚያጠምዱ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር ተመናምኖ በአንድ አመት ውስጥ ሃይቁ አሳ አልባ ይሆናል። ሆኖም ግን አግባብ ባለው ሁኔታ በልክ እና በመጠን የሚያሰግሩ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር አይመናመንም፤ እንዲያውም ከአመት ወደ አመት የሚያገኙት የአሳ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል።
እዚህ ላይ ዋነኛ ጥያቄው መተማመን የሚለው ነው፡፡ አሳ አስጋሪዎቹ በመጠን ሊያሰግሩ ቢስማሙም አንዳቸው ሌላኛውን እስካላመኑ ድረስ ስምምነታቸው ዋጋ አይኖረውም፡፡ ልክ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ለብቻቸው ተቀምጠው እንዳሉ እስረኞችም ይሆናሉ፡፡
ፍሉይ አለም
@Zephilosophy
@Zephilosophy
አዲሱ ሰው
ኦሾ
እኔ የማስተምረው አዲሱን ሰው፣ አዲሱን ሠብዓዊነት፣አዲሱን ዓለም ላይ የመሆን ፅንሰ-ሃሳብን ነው፡፡ አሮጌው ሰው እየሞተ ነው፤ በህይወት እንዲቆይ መርዳቱ አስፈላጊ አይደለም፡፡ አሮጌው ሰው በመሞቻው አልጋው ላይ ነው፡፡ ከማዘን ይልቅ እንዲሞት እርዱት፡፡ ምክንያቱም የአሮጌው ሞት ነው የአዲሱን ውልደት እንዲቻል የሚያደርገው፤ የአሮጌው መቆም ነው ለአዲሱ ጅማሬ የሚሆነው፡፡
እኔ ለሰው ልጅ ያለኝ መልዕክት አዲሱ ሰው ነው፡፡ አንድ ከባለፈው ጊዜ የተሻለ አልያም ከባለፈው ጊዜ የሚቀጥል ሳይሆን ከባለፈው ጊዜ ጋር ፍፁም የተቆራረጠ የሰው ልጅ ነው መልዕክቴ ::
ሰው እስካሁን ባለው ህይወቱ እውነተኛ እና ትክክለኛ ሀይወትን አልኖረም፡፡ሰው የኖረው አስመሳይ ህይወትን ነው፡፡ የሰው ልጅ በታላቅ በሽታ ውስጥ ነው የኖረው፡፡ እናም በዚህ መሰሉ በሽታ ውስጥ ደግሞ መኖር አያስፈልግም፡፡ ከዚህ እስር ቤት ውጭ መውጣት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም እስር ቤቶቹ በራሳችን እጆች ነው የተሰሩት፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ያለነዉ እስር ቤት ውስጥ ለመሆን ስለወሰንን ነው፡፡ እስር ቤት ቤታችን እንጅ እስር ቤት እንደሆነ ስላላመንን ነው፡፡
ለሰው ልጆች ያለኝ መልዕክት፦ ይህ ሁሉ ነገር መቆም ይኖርበታል የሚል ነው፡፡ ንቁ! የሰው ልጅ በሌላው የሰው ልጅ ላይ ያደረገውን ነገር እዩ፡፡ በሶስት ሺህ አመታት ውስጥ የሰው ልጅ አምስት ሺህ ጦርነቶችን ተዋግቷል፡፡ ይህንን የሰው ልጅ "ጤነኛ ብላችሁ ልትጠሩት አትችሉም፡፡ እናም አልፎ አልፎ ብርሃነ-ህሊና የተገለጠለት ሰው ይከሰታል፤ በአትክልት ቦታው ላይ አልፎ አልፎ አንድ ዕጽዋት፣ አንድ አበባ ቢያብብ እና ሌላው የአትክልት ቦታው ከአበባዎች ውጭ ቢሆን ይህንን ቦታ የአትክልት ቦታ ብላችሁ ትጠሩታላችሁን? አንድ መሰረታዊ ነገር ተሣስቷል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ቡድሃን /ብርሃነ-ህሊና የተገለጠለት ሰው ለመሆን ነው የሚወለደው፡፡ ከዚያ ያነሰ ማንኛውም ነገር ምሉዕ አያደርጋችሁም፤አያረካችሁም፡፡
እኔ ብርሃነ-ህሊናዊነትን /መገለጥን/አውጅላችኋለሁ::
ግን ምን የተሳሳተ ነገር ቢኖር ይሆን የሰው ልጅ ለሺህ ዓመታቶች ይህንን በመሰለ ገሀነብ ውስጥ የኖረው? በሺህ ለሚቆጠሩ አመታት "ይህንኛውን" አልያም ያኛውን በሚለው “የበላይ" እና "የበታች"፡ "የመንፈሳዊና ቁሣዊ፡ ዓለማዊ እና 'ውስጠ-ዓለማዊ ፣ በጐ እና ክፉ ፡ በሚሉ የሰው ልጅ ፅንሰ ሀሳቦች ፣ የጦርነት አውድማዎች መካካል ኖረናል፡፡ይህን በመሳሰሉ ጽንሰ ሀሳቦች ውጤት ሳቢያ የሰው ልጅ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ታቅቧል፡፡
የሰው ልጅ እና ኃይሉን ለማውደም ታላቅ እስትራቴጂ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ እናም ያ... እስትራቴጂ ሰውን ለሁለት ከፍሎታል፡ የሰው ልጅ "ይህኛውን አልያም ያኛውን በሚለው ፅንሰ ሀሳብ ኖሯል የሰው ልጅ አንድም ቁሳዊ አልያም ደግሞ መንፈሳዊ ይሆናል፡፡ ሁለቱንም መሆን እንደማትችሉ ተነግሯችኋል ወይ ስጋ አልያም ነፍስ መሆን፡ ሁለቱንም መሆን እንደማትችሉ ተምራችኋል፡፡
ይህ ነው የሰው መከራ መሰረታዊ ምክንያት፡፡ከራሱ በተቃራኒ የተከፋፈለ ሰው ገሀነብ ውስጥ እንደሆነ ነው የሚቀረው፤ ገነት የምትወለደው ሰው ከራሱ በተቃርኖ ካልተከፋፈለ ብቻ ነው፡፡ የተከፋፈለ ሰው ማለት መከረኛ ማለት ሲሆን ውህድ የሆነ ሰው ማለት የተባረከ ሰው ማለት ነው፡፡ እስካሁን የሰው ልጅ ብትንትኑ የወጣ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ተፈጥሯዊ ሰብዓችሁን እንድትኮንኑ፣ እንድታስወግዱ፣ እንድትክዱ ተነግሯችኋል፡፡ እናም እነዚሀ ተፈጥሯዊ ነገሮችን ለማስወገድ፣ ለመካድ በመሞከር ልታጠፏቸው አይቻላችሁም:: እነዚህ ተፈጥሯዊ ነገሮች ከስር ብቻ ነው የሚጓዙት፣ ከያልነቃው አዕምሯችሁ ውስጥ ነው የሚሰሩት፤ እናም የእውነት በጣም አደገኞች ናቸው፡፡
ሰው ተፈጥሯዊ እና ምሉዕ ነው፡፡ እናም እግዝሀብሄር ለሰው የሰጠው ሁሉም ነገር ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡፡ አንዳች ነገር ሊካድ አይገባም፡፡ የሰው ልጅ ኦርኬስትራ መሆን ይችላል፤ የሚፈለገው ብቸኛ ነገር በራሳችሁ ውስጥ ሰላማዊ ህብራዊነት የመፍጠር ጥበብን መለማመድ ብቻ ነው፡፡
@Zephilosophy
@Zephilosophy
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.