Информация о канале обновлена 06.10.2025.
Информация о канале обновлена 06.10.2025.
#AASTU
በ2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ
በተጨማሪ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል።
@tikvahuniversity
በክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተከታትለው የመቁረጫ ነጥብ ላስመዘገቡ ሰልጣኞች ሰርትፍኬት በፖርታል መለቀቁ ይታወቃል፡፡
ውጤታችሁ ላይ Incomplete የሚያሳያችሁ ሰልጣኞች፥ ከአሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች ከ30% ውጤት ያልተሞላላቸው እንደሆነ ተገልጿል።
ከውጤት፣ ከስም ስህተት እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር ቅሬታ ያላችሁ ሰለልጣኞች ቅሬታቸውን በኦንላይን ማቅረብ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ቅሬታ ያላችሁ ሰልጣኞች https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት በምታገኙት የማመልከቻ ቅጽ ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ።
ማንኛውም በአካል የሚቀርብ ቅሬታን የማይቀበል መሆኑን ሚኒስቴር ገልጿል።
@tikvahuniversity
#ASTU
በ2018 ዓ.ም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ እና #አዳማ_ሳይንስና_ቴክኖሎጂ_ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 28 እና 29/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
አጠቃላይ ገለጻ (Orientation) መስከረም 30/2018 ዓ.ም ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይሰጣል።
በቅጣት መመዝገቢያ እና ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ ፓስፖርት መጠን የሆነ 4 ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።
@tikvahuniversity
#AASTU #ASTU
በ2018 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ በአፕላይድ ሳይንስ ወይም በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ለመማር የተመዘገባችሁና የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ማለፋችሁን ለማረጋጋጥ በ http://stuexam.astu.edu.et/
ላይ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።
@tikvahuniversity
Рост подписчиков
Публикации
Просмотры
Средний охват + ERR%
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.