አወድሰኝ ኤፍሬም
አወድሰኝ ኤፍሬም ብላ ጠየቀችው ድንግል እናታችን
ባርክኒ ብሎ ወገቡን ታጠቀ ኤፍሬም አባታችን
የልጄ በረከት ይደርብህ ብላው ጀመረ ምስጋና
ወደ ብርሃን ድንኳን ወደ ተከበረው ደራሲው ገባና
አዝ
ልቡ ያዘነ አዳምን ሊያድን ጌታ ወደደ
ዳግሚት ሰማይ ማደሪያው ልትሆን እሱ ፈቀደ
የሰማይ ምስጢር በማህጸንሽ ተከናወነ
ከዘሩ ቀርተሽ በንጽሕናሽ የሰው ዘር ዳነ
ሰዐሊ ለነ /2/
አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
አዝ
በሔዋን ምክንያት በለስዋን በልተን ገነት ቢዘጋ
በአንቺ እናትነት ዳግም ተዛመድን ከአምላካችንጋ
ትውልድ ሁሉ ስምሽን በክብር አመሰገነ
የሲዖል ቀንበር በላያችን ላይ ስላልተጫነ
ሰዐሊ ለነ/2/
አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
አዝ
የእዳ ደብዳቤ ተቀዳደደ የባርነቱ
አዳም ሔዋንም ከእስራታቸው ወጡ ተፈቱ
የሲዖል ጽልመት በልጅሽ ጠፍቶ ብርሃን ሆነ
እረፍት አገኘን የምሕረት ዓመት ባንቺ ዘመነ
ሰዐሊ ለነ /2/
አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
አዝ
ሙሴ በሲና ሳትቃጠይ ያየሽ ሐመልማል
እግዚአብሔር መርጦሽ በማህጸንሽ ዙፋኑን ተክሏል
የዲያብሎስን ጥበብ እንዲያፈርስ አምላክ ሰው ሆነ
በልጅሽ መሞት መዳናችንም ተከናወነ
ሰዐሊ ለነ
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️