One of the top ranking first generation Universities in Ethiopia.
Информация о канале обновлена 18.11.2025.
One of the top ranking first generation Universities in Ethiopia.
የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን ከትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር የአፈፃፀም ኮንትራት ውል ተፈራረሙ።
*//*
ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚደንቶች እና በኮሌጅ ዲን መካከል የተፈረመውን ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾችን የያዘ የአፈፃፀም ኮንትራት ውል ስምምነት ከትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር ህዳር 3/2018 ዓ/ም ተፈራርመዋል።
የወ/ገ/ደ/ተ/ሃ/ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ተሻለ ወ/አማኑኤል በመድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የሥራ መመሪያ የተፈረመው ስምምነት እስከ ፈፃሚ ድርስ በየደረጃው በማውረድ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ከመምህራን ጋር እንዲፈራረሙ መመሪያ ሰጥተዋል። ዲኑ የትምህርት ክፍልም ሆነ የግለሰብ የአፈፃፀም ደረጃ በተፈረመው ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾች መሰረት እንደሚለካ በማስገንዘብ ሁሉም አካላት የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ከፍተኛ ኃላፊነት መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ሂደቱን በታዛቢነት ተከታትለዋል።
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!
የራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ኮሚቴ ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራሮች ጋር ውይይት አደረገ::
03/3/2018 ዓ/ም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የራስገዝነት ሽግግር ጉዞ ላይ በየካምፓሱ እየተካሄደ ያለው መሰረታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ ቀጥሎ ሕዳር 2/2018 ዓ/ም የስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ኮሚቴ አመራሮች ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
በመድረኩ የራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ብርሃን መሸሻ የዩኒቨርሲቲውን የሽግግር ጉዞ እና ቀጣይ አቅጣጫ የሚያሳየው ፍኖተ ካርታ ላይ ዝርዝር ገለፃ አድርገዋል:: በገለፃው ከተነሱ ነጥቦች መካከልም ዩኒቨርሲቲው በ2021 ዓ/ም ሙሉ ራስ ገዝ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ የሽግግር ትግበራ ላይ እንደሚገባ ተገልፆ ራስገዝ መሆን ይዞት የሚመጣው የአካዳሚክ፣ የአስተዳደር እና የፋይናንስ ነፃነት ወደ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት እንደሚያሸጋግር ተጠቁሟል::
የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ተስፋዬ አሽኔ እና የኮሚቴው ፀሐፊ ዶ/ር እመቤት በቀለ በለውጥ ሂደቱ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተጠባቂ ተግዳሮቶች፣ የዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች ልየታ መነሻዎች እና ተግዳሮቶቹን ወደ ዕድል ለመቀየር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ እንዲሁም የመንግስት ፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል::
የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስሩ የሚያስተዳድረውን ስፔሻላይዝድ ኮምፕሪሄንስቭ ሪፌራል ሆስፒታል፣ የካንሰር እና የጨቅላ ሕፃናት ህክምና ማዕከላትን ጨምሮ በሀገር ደረጃ ከጥቁር አንበሳ ቀጥሎ ባለው የተማረ ሰው ብዛትና የጤና ዘርፍ ምርምር ስራዎች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ከተመረጡት መስኮች ሁለተኛው መሆኑ ተገልጿል።
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና ተሰጣቸው::
*//*
ሕዳር 3/2018 ዓ/ም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ም/ፕ/ጽ/ቤት ከስራ ፈጠራ ልማት ተቋም (Entrepreneurship Development Institute) ጋር በመተባበር የተመራቂ ተማሪዎችን የስራ እድል ፈጠራ እውቀትና ክህሎት ለማሳደግ ያለመ ስልጠና ህዳር 2/2018 ዓ.ም ለተፈጥሮና ቀመር ሣይንስ ተማሪዎች ሰጥቷል።
የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው የቀለም ትምህርት በራሱ ከሚሰጠው የመመርመር እና የማገናዘብ አቅም በተጨማሪ ችግሮችን የመረዳትና መፍትሔ የማፍለቅ ሙሉ እይታን የሚያላብስ አቅም እንደሚጨምር ገልጸዋል። "ስልጠናው ከተማሪነት ወጥታችሁ ወደ ስራ አለም ለመቀላቀል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በምትገኙበት በዚህ ወቅት መሰጠቱ የነገ የህይወት መስመራችሁን በብልሀት እንድትመርጡና ፍሬያማ እንድትሆኑ ያግዛል" ሲሉ ዶ/ር ዙፋን ተመራቂ ተማሪዎች በትኩረት እንዲያዩት መክረዋል።
በም/ት/ም/ፕ/ጽ/ቤት የኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት የስራ ፈጠራ ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት ኢ/ር ትዕግስት አሰፋ በበኩላቸው ስልጠናው የተዘጋጀው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2008 በአሜሪካን ሀገር የተሳካላቸው የስራ ፈጣሪዎች የሚገናኙበትና ልምዳቸውን የሚከፋፈሉበት "አለምአቀፉ የስራ ፈጠራ ሳምንት"ን በማስመልከት መሆኑን ጠቁመው ዓላማውም የተማሪዎችን የቢዝነስ አመለካከት በማሳደግ የስራ ፈጠራ ተነሳሽነትን መጨመር ስለመሆኑ ተናግረዋል። ለተመረጡና የቢዝነስ ሀሳብ ላላቸው ተማሪዎች ደግሞ ተጨማሪ ከ2-3 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እንደሚኖር ኢ/ር ትዕግስት ጨምረው ገልጸዋል።
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.
Наш сайт использует cookie-файлы, чтобы сделать сервисы быстрее и удобнее.
Продолжая им пользоваться, вы принимаете условия
Пользовательского соглашения
и соглашаетесь со сбором cookie-файлов.
Подробности про обработку данных — в нашей
Политике обработки персональных данных.