Информация о канале обновлена 20.08.2025.
Информация о канале обновлена 20.08.2025.
ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና የወሰዱ የትምህርት ቤት አመራሮች የስልጠና ማጠናቀቂያ ፈተና ተሰጠ፡፡
---------
በእንጅራ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የክረምት የአቅም ማጎልበቻ የወሰዱ የትምህርት ቤት አመራሮች የስልጠና ማጠናቀቂያ ፈተና በበየነ መረብ(Online) አማካኝነት ተሰጥቷል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ሀብታሙ ዘገየ(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ለወሰዱ የትምህርት ቤት አመራሮች የስልጠና ማጠቃለያ ፈተና በበየነ መረብ(online) አማካኝነት መሰጠቱን ገልጸው ሌሎች ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ እየወሰዱ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይ እና ርቀት ትምህርት ዳይሬክተር እና የስልጠናው አስተባበሪ አሸናፊ ምህረት
(ረ/ፕሮፌሰር) በበኩላቸው ከሐምሌ 28 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ሲወስዱ ለነበሩ
የትምህርት ቤት አመራሮች የማጠቃለያ ፈተና መሰጠቱን ጠቅሰው 177 ወንድ 37 ሴት በድምሩ 214 የትምህርት ቤት አመራሮች ፈተናውን በበየነ መረብ መፈተናቸውን ገልጸዋል፡፡ ለዚሁ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ይረዳዘንድ የሞዴል ፈተና ቀደም ሲል መሰጠቱንም ጨምረው ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ባለው የትምህርት ቤት አመራሮች እና መምህራን ልዩ የክረምት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከ3ሺህ 4 መቶ በላይ ሰልጣኞች እየተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው እስከ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ያለህን ዕምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!
ለድኅረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፦
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከታች በተጠቀሱት ቀናት መመዝገብና መማር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ነሐሴ9/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በ Accounting and Finance የ3ኛ ዲግሪ(PhD) ለመክፈት የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ (External validation workshop) ተካሄደ፡፡
ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል የ3ተኛ ዲግሪ (PhD) ለማስጀመር የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ የውጭ ግምገማ በበርችዋል ተካሂዷል፡፡
የእንጅባራ ዪኒቨርሲቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ይልቃል አንዷለም(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በርካታ አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በማስፋፋት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በዛሬው ዕለትም በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የ3ተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ለማስጀመር የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ፕሮግራሙን ለመክፈት የሚያስችሉ ግብዓቶች ከሰው ሀይል ጀምሮ መሟላታቸውን ገልጸዋል፡፡
የውጭ ስርዓተ ግምገማው በዶ/ር ደረሰ መገርሻ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ከሲቪል
ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ ዶ/ር ደርበው ቀኑብህ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ከጎንደር
ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የተገመገመ ሲሆን ፕሮግራሙን ለመክፈት የሚያስችሉ ግብዓቶች ከተሳታፊዎችም የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶች ተጨምረውበት ስርዓተ ትምህርት ግምገማው ተጠናቋል፡፡
የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደቀጠለ ነው፡፡
ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ከአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች እንዲሁም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ለመጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው ልዩ የክረምት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይ እና ርቀት ትምህርት ዳይሬክተር እና የስልጠናው አስተባባሪ አሸናፊ ምህረት (ረ/ፕሮፌሰር) ስልጠናው መሠጠት ከጀመረ አራተኛ ቀን መሆኑን ተናግረው ለስልጠናው ከተመደቡት 88 በመቶ ያክሉ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ስልጠናውን እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አስተባባሪው አክለውም በስልጠናው 212 የትምህርት ቤት አመራሮች፣ 3ሽ376 መምህራን በአጠቃላይ 3ሺ 588 ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ እየወሰዱ መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን ከትምህርት ሚኒስቴር ከተመደቡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በየቀኑ ክትትል እና ድጋፍ እየተረገ እንደሚገኝም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ-ትምህርት ዝግጅት ትግበራ ባለሙያ የሆኑት አቶ ታየ መንግስቱ በበኩላቸው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ሰልጣኞች መመደባቸውን ገልጸው ለስልጠናው በቂ ቅድመ ዝግጅት በመደረጉ ያለምንም ችግር ስልጠናው እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን ስልጠና ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን መምህራን በማሰልጠን ላይ መሆኑም እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡ ስልጠናው ከተጀመረ ዛሬ አራተኛ ቀኑ ሲሆን እስከ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ያለህን ዕምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!
የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ፡፡
ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች እንዲሁም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን
ለመጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና ትምህርት ቤት አመራሮች የሚሰጠው ልዩ የክረምት
የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጀምሯል።
ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡
የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
----
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሥራ መስኮች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ሐምሌ 28/2017፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
Рост подписчиков
Публикации
Просмотры
Средний охват + ERR%
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.