ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!
Информация о канале обновлена 20.11.2025.
ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!
ወደ ሚዛን አማን ከተማ እየተጓዝን እኔና ሼህ ኤሊያስ አሕመድ የተነሳነውን ፎቶግራፍ አንዳንዶች በደስታ፣ሌሎች በመገረምና እጅግ ጥቂቶች ደግሞ እንዴት በሚል እንድምታ ሲያዘዋዉሩት አየሁ።የነርሱ መገረም እኔንም ገረመኝና እንዲያውም የኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅንም ጨምሬበት ትንሽ ከፋይል ማውጣት ፈለግኩ።
1) ከኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ ጋር በጅማ ከተማ በአንድ ትምህርት ቤት ነበር የተማርነው። በጅማ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት (ቄራ ሰፈር) የ7ኛ ክፍል ተማሪ ሳለን ጀምሮ እስከ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት (Jimma high school) ድረስ የዳዕዋ አሚራችን ነበር። በትምህርት ቤት ዳዕዋም የሚያደርግልን እና በተማሪነት ዘመን ሰላት ተከልክለን ለመብታችን መታገልንም በትምህርት ቤት በሰላማዊ ሰልፍ ጭምር መታገልን የጀመርነው በዑስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ አሚርነት ነበር።
በሰላት ጉዳይም የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ የወጣነውና ጁምዓ ሰግደን ወደ ትምህርት ቤት ልንገባ ስንል አትገቡም ተብለን መሳሪያም የተቀባበለብን በጅማ ከተማ በርሱ መሪነት ነበር።በእረፍት ሰዓትም ዳዕዋ ለምን አደረግክ ተብሎ ሲከሰስም ከበን አብረን ወደ ቢሮ ሄደናል።
2) ሼህ ኤሊያስ አሕመድ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋከልቲ (4ኪሎ ካምፓስ) እኔ የመጀመሪያ ዓመት እርሱ ደግሞ የ2ኛ ዓመት ተማሪ ሆነን በሳባ ህንፃ በዶርም ቁጥር 339 አብረን ነበርን።የአዲስ አበባ ልጅ ሆኖ ዶርም ስለማይሰጠው እኛ ጋር ይሆን ነበር።ያኔ ጊዜ መጠሪያ ስሙ ሁንዳኦል አሕመድ ነበር። «ሁንዳኦል» ማለት በኦሮምኛ ቋንቋ ከሁሉ በላይ የሚል ትርጉም ስላለው ከሁሉ በላይ አላህ ብቻ ነው። በዚህ ስም መጠራት ትክክል አይደለም በማለት ስሙን በፍርድ ቤት ወደ ኤሊያስ አሕመድ አስቀየረ። በኋላም የአዲስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በማቆም ወደ መዲና ዩኒቨርሲቲ አቀና።
ለተገረማችሁ ወገኖች ምክንያታችሁ ባይታየኝም ከሁለቱም ጋር የቆየ ትውውቅ አለን ።
🔥 ዝምድናህን አጥብቀህ ያዝ!
ረሱልﷺ እንዲህ ብለዋል፦
﴿لَيْسَ الْوَاصِلُ بِالْمُكَافِئِ ، وَلَكِنِ الْوَاصِلُ الَّذِي إِذَا قَطَعَتْ رَحِمُهُ وَصَلَهَا﴾
“ውለታን በውለታ የሚመልስ ዝምድና ቀጣይ አይባልም። ነገር ግን ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናውን ሲቆርጡት የሚቀጥል ነው።”
ቡኻሪ ዘግበውታል: 5991
ሸይኽ ሙሀመድ ሁሴን አል አሙዲ የፍልውሀ ተዉፊቅ መስጂድን በእናታቸው ስም መገንባት ጀመሩ።
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ፍልውሀ ተውፊቅ መስጂድን በዘመናዊ መንገድ ለመገንባት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ባደረገው ስምምነት የግንባታው ሂደት ተጀምሯል። የመስጊዱ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተለዋጭ የመስገጃ ቦታ ግንባታ ይጀመራል ተብሏል።
መስጂዱን ሸይኽ መሀመድ ሁሴን አልአምፊ በ እናታቸው ስም የሚያስገነቡት ሲሆን የመስጂዱ ግንባታ ሙሉ ወጩ የሚሸፈነው በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ነው።
የ'ፍፁም ሰው ፍፁም ነቢይ 'መፅሐፍ ምርቃት! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በሚያጋራቸው ኢስላማዊ ፅሁፎች መልካም ተቀባይነትን ያገኘው ኡስማን ሙስጠፋ አሁን ደግሞ 'ፍፁም ሰው ፍፁም ነቢይ' በሚል ርእስ ስለ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የሚያትት አዲስ አቀራረብ እና ይዘት ያለውን መፅሐፍ አበርክቶልናል።
የመፅሐፍ ምረቃውም ፥ ከምርቃትም ባሻገር የተዘነጋውን የ 'ኢቅራእ' (አንብብ) መለኮታዊ ቃል ለኡማው ለማስታውስ እና የሞተውን የንባብ እና የመፃፍ ልምድ ህያው ለማድረግ ያነገበ ነው።
በዚህ ቀጣይነት ይኖረዋል ተብሎ በሚጠበቀው ጥበባዊ የዳእዋ እና የንባብ ማዕድ በመገኘት ከመልካም ምንዳው ይቋደሱ።
መሠል ሰናይ አላማ ያላቸው እቅዶቹ ቀጣይነት ይኖራቸው ዘንድ ፀሀፊውን ማግኘት እና አላማውን መደገፍ እንዲሁም መፅሀፉን ማግኘት የምትፈልጉ በ 0921390122 /0912027023 ኡስማን ሙስጠፋን ያናግሩት።
📆 የፊትችን እሁድ ጥቅምት 23 ከ ጠዋቱ 3:30 ጀምሮ
📍 :- 4 ኪሎ (አብርሆት ላይብረሪ አጠገብ የሚገኘው) ኢኽላስ ህንፃ ዋልያ መፅሐፍት አዳራሽ
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐
﴿البَخيلُ مَنْ ذُكِرْتُ عِندَهُ، فلَمْ يُصَلِّ علَيَّ﴾
“እድለቢስ ማለት እኔ እሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሰለዋት ያላወረደ ነው።”
📚 ሰሂህ አልጃሚ: 2878
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.
Наш сайт использует cookie-файлы, чтобы сделать сервисы быстрее и удобнее.
Продолжая им пользоваться, вы принимаете условия
Пользовательского соглашения
и соглашаетесь со сбором cookie-файлов.
Подробности про обработку данных — в нашей
Политике обработки персональных данных.