This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Информация о канале обновлена 03.10.2025.
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
በትምህርት ሪፎርሙ የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል የተወሰዱ እርምጃዎች እና ከታች ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና ስራዎች
በሀገራችን የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል ከተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ በትምህርት ፖሊሲው የተቀመጠውን አንድ ተማሪ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ወይም እርከን ለመሸጋገር ቢያን 50 ከመቶና በላይ አማካይ ውጤት ማስመስመዝገብ አለበት በሚል የተደነገገውን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው። በዚህም በሪፎርሙ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችም ይሁኑ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ሲያመጡ ወደ ሚቀጥለው ክፍል/እርከን እንዲሸጋገሩ እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ተማሪዎች 50 ከመቶ በታች አማካይ ውጤት አምጥተው ወደ ሚቀጥለው ክፍል እንዲዛወዱ ወይም በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ይደረግ እንደነበር የሚታወስ ነው። አሁን ባለው አሰራር ይህንን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በየትኛውም የክፍል ደረጃ 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያላመጣ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ወይም እርከን አይዛወርም።
በተጨማሪም በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች በነዚህ ፈተናዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዛወሩ እየተደረገ ይገኛል። ይህም በየደረጃው የትምህርት ጥራቱ ያለበትን ደረጃ እየለኩ ለመሄድ ትልቅ አስተዋጻኦ ይኖረዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/17CF2bPKAt/
ማስታወቂያ
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ለመማር ያለፋችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተበረከተ።
በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ በ2017 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች እውቅናና ሽልማት አበርክቷል።
-------------------- // ----------------------
(መስከረም 09/2018 ዓ.ም) በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተመዘገበው 22 በመቶ ውጤት አበረታች መሆኑን ጠቁመው ክልሉ ለትምህርቱ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።
እንደ ሀገር በትምህርት ዘርፉ የሰራና የለፋ ብቻ ውጤት የሚያገኝበት ሥርዓት እየተዘረጋ መጥቷል ያሉት ሚኒስትሩ ዛሬ የተሸለማችሁ በአቋራጭ ሳይሆን በስራና በድካም ያገኛችሁት ውጤት በመሆኑ ልትኮሩ ይገባችኋል ብለዋል።
በቀጣዩ የ2018 የትምህርት ዘመንም የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በክልሉ ሙሉ በመሉ ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ በኦላይን ለመስጠት ከክልሉ አመራር ጋር መግባባት መደረሱንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
በመሆኑም በክልሉ አሁን በተገኘው ውጤት መዘናጋት ሳይኖር የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም ይሄ ትውልድ የሥራ ትውልድ፣ በራሱ የሚኮራ ትውልድ እንዲሆን እንደ ሀገር የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
በዕውቅናና ሽልማት መርሀ-ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የቅጥር ማስታዎቂያ
የትምህርት ሚኒስቴር ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ት/ቤቶች የአሰተዳደርና ፋይናንስ ቡድን መሪ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ከላይ በቴምፕሌቱ የተጠቀሱ መስፈርቶችን የምታሟሉ በ https://sbs.moe.gov.et/career በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
እየተቀየረ ያለውን የአለም ሁኔታ ሊሸከሙ የሚችሉ በሁሉም ዘርፍ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ተወዳዳሪ ልጆችን ማፍራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
ትምህርት ሚኒስቴር በሀረሪ ክልል የሚያስገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የሚኒስቴሩና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።
------------------ // ------------------------
(መስከረም 09/2017 ዓ.ም) በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ሥርዓቱ መጪውን ዓለም መሸከም የሚችሉ እውቀትና ክህሎት ያላቸው በራሳቸው የሚተማመኑ ተወዳዳሪ የሆኑ ልጆችን ማፍራት ይገባል፤ ለዚህም የተጀመረው ሪፎርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በተለይም በትምህርት ያለው ኢፍትሃዊነትን በማስቀረት ዜጎች እኩል ትምህርት በማገኘት እኩል ተወዳድረው የሚማሩበትን ሥርዓት መፍጠር አለብን ብለዋል።
ለዚህም 50 ሞዴል እንዲሁም 13 ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለመገንባት ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
ይህም ሁሉም ዜጎች እኩል ተወዳድረው ውጤት የሚያገኙበትን ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ ይህ ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1777uVaWXV/
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተማሪዎችን የማንበብ ክህሎትና ፍላጎትን ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቆመ።
አለም አቀፍ የንባብ ቀን "በቴክኖሎጂ ዘመን ንባብን ማዳበር" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ተከብሯል።
----------------------------// -----------------------------
(መስከረም 09/2018 ዓ.ም) በመድረኩ ላይ የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ ለመሄድ የተማሪዎችን የንባብ ክህሎትን በየጊዜ ማሳደግ እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ይጠበቃል፤ ለዚህም ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ትምህርትን በፍትሃዊነት ለሁሉም ዜጎች በጥራት ለማድረስ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆ እየተተገበረ ሲሆን በተለይም አዲስ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ፀድቆ ወደ ተግባር ገብቷል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የነገው ትውልድ እጣፈንታ የሚወሰነው ዛሬ መሠረቱ ላይ በሚሰራው ሥራ በመሆኑ የልጆችን የንባብ ክህሎት ማሳደግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ የልጆች የማንበብ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቶ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል የተባለ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት መሥራት ይጠበቃል።
በተለይም ቴክኖሎጂ የዚህ ዘመን ስጦታ ቢሆንም አጠቃቀሙን መግራትና እኛ በምንፈልገው መልኩ በመጠቀም የንባብ ባህላችን መመለስ የሁላችን ጉዳይ ሊሆን ይገባል ተብሏል።
በመድረኩም የኢትዮጵያ ቤተመፅሃፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት እና ኢትዮጵያ ታንብብ የተባለ ድርጅት የተማሪዎችን የንባብ ባህል ሊያዳብሩ የሚችሉ የተለያዩ መጽሐፍትን ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።
ይህ ባለፈው ሳምንት በአለም ለ58 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ የተከበረው የአለም የንባብ ቀን ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጋር በትብብር የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.