እንደመደበርም እንደመሰልቸትም አድርጎኝ ነበረ። ለመኖር ምክንያት አጣሁ ማለት ጀምሬ ነበረ።
እነዚህ ትናንሽ ሀሳቦች ቀኔን መረበሽ ጀመሩ ። ጠዋት መነሳትና ድጋሜ ሌላ ተመሳሳይ አድካሚ ቀን መዋል ትርጉሙ አልታይሽ ብሎኝ ነበረ።
ከዛ ግን ቀልቤን ገዛሁ የእናቴን እጅ አየሁት። ቆዳዋ ተሸብሽቦ ደምስሮቿ በጉልህ ይታዩ ነበረ። ደነገጥኩ ያ እንደዛ የሚያሳሱ ቀያይ እጆቿ አሁን መዳፎቿ ሳይቀሩ ጠቋቁረዋል።
ውሎዋን አየሁት እንደነገሩ ነው የምትለብሰው ያ ሁሉ መሸቀርቀር የት እንደ ሄደ ግራ ገባኝ። ፈጥና ያረጀችም መሰለኝ።
ከዛ ድግስ ተጠርተን ዘመድ ቤት ስንሄድ በእያንዳንዱ ነገር ላይ የምትሰጠውን የሰላ ሂስ ሰማሁ።
እቤት ስንገባ ጠየኳት "ለምን ስራሽን ተውሽው እስካሁን በጣም ምርጥ ጭንቅላት አለሽ እኮ" አልኳት በቁጭት
"ኤድያ ተይው ባክሽ ሁሉም ነገር ከቤተሰቤ አይበልጥብኝም" አለች
"እስኪ ተመልከቺ እንዴት ትናንሽ እንደነበራችሁ" በእጇ ህፃን ሆነን እኔና እህቴ የተነሳነውን ፎቶ ይዛ
"አሁን ያላችሁበት ደረጃ ለኔ ከምንም ነገር በላይ ነው" አለቺኝ በፈገግታ።
እንዴት እንደሆነ ባላውቅም መሰልቸቱ መደበሩ ቀርቶ ጭራሽ አዲስ ጉልበት ይሰማኝ ጀመረ።
ስለእሷ ማሰብ ከአልጋዬ ተስፈንጥሮ ለመነሳት በቂ ነበረ። እሷ መኖር ያቆመችው ለኔ ስትል አልነበር ስለዚህ እኔም የምልፈሰፈስበት ምክንያት አልነበረኝም።
ለኔ ማማር የሷ መጎሳቆል ይበልጥ አጠነከረኝ። በደንብ በኔ እስክትኮራ ድረስ...
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss