ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ለመስጠት @atsbaha12 ይጠቀሙ
Информация о канале обновлена 16.11.2025.
ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ለመስጠት @atsbaha12 ይጠቀሙ
ኑሮ ከበደኝ በማለት ከመንትያ ልጆቿ መካከል አንደኛዋን የአንድ አመት ከ6 ወር ልጅ በድንጋይ ደብድባ የገደለችው እናት በእስራት ተቀጣች
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ሜራ ቀበሌ ውስጥ የወንጀል ድርጊቱ ተፈጽሟል።ተከሳሽ ገነት መንግስቱ በሜራ ቀበሌ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት የ1 ዓመት ከ6 ወራት ልጇን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የግድያ ወንጀል መፈፀሟን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
የአዲዮ ወረዳ ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር በማድረግ በምርመራው እንዳረጋገጠው ግለሰቧ ከምትኖርበት ሜራ ቀበሌ ወደ አዲስ አበባ ለስራ ሄዳ ባለችበት በማርገዟ ምክንያት ተመልሳ በመምጣት መንታ ሴት ልጆችን በሰላም እንደወለደችና በፍቅርና በእንክብካቤ ለአንድ አመት ከስድስት ወር ስታሳድግ መቆየቷን ፖሊስ አረጋግጧል።ይሁንና የኑሮ ሁኔታ እየከበዳት ሲሄድ ከሁለቱ አንደኛዋን ለማስወገድ በማሰብ ልጇን ከተኛችበት አንስታ አቅፋ አቅራቢያዋ ወደ ጫካ በመዉሰድ ጭንቅላቷን ላይ በድንጋይ ሁለት ጊዜ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን ግለሰቧ ለፖሊስ በሰጠችው የእምነት ቃል አረጋግጧል።
የወረዳው ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በማደራጀት ክስ እንዲመሰረትባት መዝገቡን ለዓቃቤ ህግ ያስተላልፉል።የካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ከአዲዮ ወረዳ ፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ ግለሰቧን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ 540 ላይ የተደነገገውን ተላልፋ በመገኘቷ በፈፀመችው ሰዉ የመግደል ወንጀል ክስ መስርቶባት ካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ ፍረድ ቤቱ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ካደመጠ በኋላ ተከሳሿን ጥፋተኛ በማለት የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።
በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ገነት መንግስቱ በ10 አመት እስራት እንድትቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፉን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
ሳምራዊት ስዩም
@ETHIONEWS433 @ETHIONEWS433
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.
Наш сайт использует cookie-файлы, чтобы сделать сервисы быстрее и удобнее.
Продолжая им пользоваться, вы принимаете условия
Пользовательского соглашения
и соглашаетесь со сбором cookie-файлов.
Подробности про обработку данных — в нашей
Политике обработки персональных данных.