This is the official Telegram Channel of the Ethiopian Ministry of Health.
Информация о канале обновлена 23.08.2025.
This is the official Telegram Channel of the Ethiopian Ministry of Health.
የሩሲያ ቀይ መስቀል ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር አንድሬ ጎንቻሮቭ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በህክምና ትብብር ዙሪያ መክረዋል
_________
ሩሲያ የህክምና በጎ ፈቃደኞች ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደምትልክ እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ድጋፍ ለማድረግ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ተወያይተዋል።
ውጥኑ የታካሚ እንክብካቤን ለማሻሻል፣ የህክምና ስልጠናን ለማሳደግ እና የላቀ መሳሪያዎችን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ትብብሩን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዉ ለኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ያለውን ጠቀሜታ አመልክተዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
በ2017 ዓ.ም የተሻለ የቁጥጥር ስራ መሠራቱን የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ
________
የኢትዮጵያ የምግብነኣ መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት መልካም አፈጻጸም እንደነበረውና የተሻለ የቁጥጥር ስራ መሠራቱን አስታውቋል።
በምግብ፣ በመድሀኒት፣ በህክምና መሣሪያዎች፣ በመዋቢያ፣ በትንባሆና በአልኮል ምጠጦች ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ ላይ መሆኑንም የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ገልጸዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሪፎርም ስራዎች በመሠራቱ የተያዘው የልማት እቅድ ለማሳካት የጤና ቁጥጥር ዘርፍ የህግ ማሻሻያዎች፣ የዲጃታል ስርአት፣ መሠረተ ልማት እና የአደረጃጀት ማሻሻል እንዲሁም በማእከልና በቅርንጫፍ ጽ /ቤት፣ በመግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ የቁጥጥር ስራዎች በበጀት አመቱ ሲሰሩ መቆየታቸው ዋና ዳይሬክተሯ ሄራን ገርባ አስረድተዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
የጤና ሚኒስቴር 4.2 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የህክምና መሣሪያዎች ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ድጋፍ አደረገ
___________
የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ስርአትን ለማጠናከር የሚያስችል የህክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ጤና ሚኒስቴር ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች በዛሬው ዕለት አድርጓል።
የህክምና መሣሪያዎች የህክምና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ያሉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ የተደረገው ድጋፍ የጤና ተቋማት የህክምና መሣሪያዎች የረጅም ጊዜ ፍላጎትን የሚያሟላ መሆኑን ገልፀዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ በመቀጠልም የጤናው ዘርፍ ትልቁ ወጪ የህክምና መሣሪያዎች ግዢ መሆኑን በመግለፅ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካላት የህክምና መገልገያ መሳሪያዎቹን በተገቢዉ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲያዉሉ አሳስበዋል...More
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
በአገር በአቀፍ ደረጃ የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና እየተሰጠ ነው
_________
የብቃት ምዘና ፈተናው ከሁሉም የመንግሥትና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች እየተሰጠ ነዉ፡፡
ጤና ሚኒስቴር በተለያዩ የጤና ሙያ መስኮች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ በ17 የጤና ዘርፍ ት/ታቸውን ተከታትለው በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ 14,353 ባለሙያዎች በ31 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች (ማዕከካት) የብቃት ምዘና ፈተና እየወሰዱ ነው።
ከነሃሴ 7 - 9/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተናው ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል እና ከተለያዩ ዩኒቪርሲቲዎች የተውጣጡ ከ900 በላይ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች የክትባት ተደራሽነትን የሚያሰፋው "ድራይቭ" ኢንሼቲቭ በሶማሌ ክልል ተጀመረ
_______
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ክትባትና ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን ተደራሽነት ለማስፋት የተጀመረው DRIVE_ direct delivery of routine immunization and other PHC commodities for equity ኢንሼቲቭ በሶማሌ ክልል ተጀምሯል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የክትባት ተደራሽነት ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል ከመንገድ መራቃቸውና በመኪና ለመድረስ አስቸጋሪ መሆናቸው ነው ያሉት በጤና ሚኒስቴር የክትባት አገልግሎት አስተባባሪ አቶ መልካሙ አያሌው ድራይቭ ኢንሼቲቭ ይህንን ችግር በመቅረፍ የክትባት ተደራሽነቱን እንደሚያሰፋ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።
70 በመቶ የክልሉ ነዋሪዎች አርብቶ አደሮች መሆናቸውን የጠቀሱት የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ መሀሙድ መሀመድ በበኩላቸው ሞተር ሳይክሎቹ ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ የዳዋ፣ ሊበን፣ ኤረርና አፍደር ዞኖች ክትባት ለማድረስ ይጠቅማሉ ብለዋል። ጤና ሚኒስቴር፣ ዩኒሴፍና የስራ ፈጠራና ክህሎት ሚኒስቴር ላደረጉት የተቀናጀ ጥረትም አመስግነዋል በመድረኩ ወደ ስራ ለገቡት የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የምረቃ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Владелец канала не предоставил расширенную статистику, но Вы можете сделать ему запрос на ее получение.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Также Вы можете воспользоваться расширенным поиском и отфильтровать результаты по каналам, которые предоставили расширенную статистику.
Подтвердите, что вы не робот
Вы выполнили несколько запросов, и прежде чем продолжить, мы ходим убелиться в том, что они не автоматизированные.